“ እንዳንማር ነው እንዴ የተፈለገው? ውጤቱ የማይያዝልን ከሆነ ለምን ሪሚዲያል ተፈተንን ?” - የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
“ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣ መመሪያ ነው” - የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኅብረት
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ጀማሪ የሕግ ተማሪዎች ፊልድ ለመምረጥ የሪሚዲያል ውጤታቸው ብቻ አለመያዙን፣ ሪሚዲያል ከተፈተኑ ከ90 በላይ ተማሪዎች 40 የሚሆኑት ውጤታቸውን ባለማወቃቸው ቅሬታ አሰሙ።
የኢንትራንስ ውጤታቸው ከሪሚዲያል ጋር ተደምሮ ፊልድ ለመምረጥ እንደ መስፈርት መያዙን፣ የሪሚዲል ፈተና ውጤታቸው ከፍተኛ ቢሆንም የኢንትራንሱ በመያዙ ዝቅ ስለሚያደርገው የሚፈልጉትን ፊልድ መምረጥ እንዳልቻሉ ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ ሪሚዲያል ከተፈተኑት 96 የሕግ ተማሪዎች መካከል ውጤት የተለቀቀላቸው የ40ዎቹ ብቻ እንደሆነ፣ ቀሪዎቹ ውጤታቸውን እንዳላወቁ ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ አክለው ምን አሉ?
“ለፊልድ መረጣ በ12ኛ ክፍል ውጤት ወይም በሪዛልቱ ሳይሆን መያዝ የነበረበት በሪሚድያሉ ብቻ ነበረበት። በተጨማሪ ውጤቱ የሁላችንም ተማሪዎች ሙሉ መለቀቅ ነበረበት። 96 ተማሪዎች ተፈትነዋል የተለቀቀው የ40ዎቹ ነው። ለምን የሁሉም አልተለቀቀም?።
ማለፍ ወይም መውደቃችንን ለማወቅ ግዴታ የሁሉም ተማሪዎች ውጤት መለቀቅ ይኖርበታል። ባለመለቀቁ ብዙ ተማሪ ችግር ሊያጋጥመው ይችላል። ውጤታችን ሳይለቀቅ ፈተናውን ራሱ በትክክል እንዳረሙትና እንዳላረሙት በምን ልናቀው እችላለን?
እንዳንማር ነው እንዴ የተፈለገው? ውጤቱ የማይያዝልን ከሆነ ለምን ሪሚዲያል ተፈተንን?” ሲሉ ጠይቀዋል።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ኀብረት ምን አለ?
ለተማሪዎቹ ቅሬታ የጠየቅነው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ኀብረት፣ “ጥያቄው አግባብነት ያለው ጥያቄ ነው ብለንም አናስብም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
“ምክንያቱም መመሪያ ላይ የነበረ ነገርን ነው እየተገበረ ያለው ሪጅስትራር ስናወራ ያገኘነው ነው። 20% የኢንትራስ ውጤትን 30% ትምርት ክፍል ያዘጋጀው ሲኦሲና 50% ኮምሌቲቭ ጂፒያቸው መሰረት ነው የተወዳደሩት።
ያ ደግሞ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣ መመሪያ ነው በዛ መመሪያ መሰረት ነው ሪጅስትራሉ እየሰራ ያለው” ብሏል።
የ40ዎቹ ውጤት ተለቆ የሌሎቹ ያልተለቀቀውስ ለምንድን ነው? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠን ምላሽ፣ “ያለፉት ተማሪዎች ውጤት ነው የሚለቀቀው። እነዚህን ተማሪዎች ተቀብለናል እነዚህ ተማሪዎች አልፈዋል፣ ተብሎ ነው የሚለቀቀው” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
የተፈተኑ ተማሪዎች ወጤቱ ተለቆ ማለፍ/አለማለፋቸው መነገር አልነበረባቸውም? የሚለውን ጥያቄም፣ “ውጤቱን ማየት የሚፈልግ ሪጅስትራል መጥቶ ማየት ይችላል። ያለፉት ተማሪዎች ስማቸው ወደ ኮሌጅ ስለሚተላለፍ ወደምዝገባው ነው የሚቀጥሉት” ሲል መልሷል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia