Ustaz Kedir Ahmed Al—Kemisse (Abu Juweyriya)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የተለያዩ ሙሀደራ እና የኪታብ ደርሶች የሚለቀቅበት ቻናል ነው
መረጃዎችን ለማግኘት በፌስቡክ like ይበሉ 👇
fb.me/AbuZekeriya8
YouTube subscribe ያድርጉ ፣ የተለያየ ፈትዋ ፣ አጫጭር ምክር ፣ እና ወቅታዊ ጉዳዮች የሚላክበት) 👇
http://www.youtube.com/c/AbuZekeriya

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ለሰዎች ቃል መግባት ማለት በምላስ ጫፍ ብቻ የሚቀላጠፍ ቃል አይደለም
ይልቁንስ ነገ አላህ ዘንድ ተጠያቂ የሚያደርግ ከማውራት በፊት ሰለ ጉዳዩ ማስተዋልና መወሠንን የሚሻ በልቦና የሚሰርፅ የእምነት ቃል ነዉ::
https://t.me/UstazKedirAhmed




ደስተኛ ህይወትን ለመኖር :-
1,ወደ አላህ ቅርብ መሆን
2,ስለሰማነዉ ነገር ከማውራት ይልቅ ለማረጋገጥ ጥረት ማድረግ
3,ከሠዎች ጋር ያለንን ጥላቻም ሆነ ውደታ በልክ መያዝ
4,ቀለል ያለ ህይወትን መኖር
5,አቅመ ደካሞች ና ሚስኪኖችን ማገዝ ወዘተ የመሣሠሉት መልካም ነገራቶች ለደስታ ምንጭ ሁነኛ ሰበብ ናቸው::
https://t.me/UstazKedirAhmed https://t.me/UstazKedirAhmed


እዉቀት :ምሰሶ ቤትን ከፍ እንደ ሚያደርገው ሁሉ የእውቀት ባለ ቤትም ደረጃው ከፍ ያለ ይሆናል :እውቀት ተቅዋን ያላብሳል::መተናነስን ዝቅ ማለትን ያስገነዝባል::
መሀይምነት ግን ድፍረትን ያጐፅፋል የተገነባን ያፈርሳል::/UstazKedirAhmed


አባ-ጨጓሬም አባ ነው አትታለል እሽ

👉በኮፍያቸው ስር‼️
--------------------------

ማንም እየመጣ፤
ሁሌም አይዝገንህ እንደ ሰፌድ ቆሎ፡
እንደ አህያ አይጫንህ፤
አትሁን በፍፁም መካን እንደ በቅሎ፡
አትቅር በአየር ላይ፤
አጨብጫቢ ሆነህ ሐሳብህ ተሰቅሎ፡
ራስህን አፅዳ፤
ዘላለም አትኑር ዘውግህ ተመሳቅሎ፡

ሁሉንም አትመን ግን በጣም ተጠንቀቅ፡
ሰማይ ቤት ለሚልህ ምድርህን አትልቀቅ፡
ለአፍህ ልጓም አብጅ ለስሜትህም ልክ፡
ተዓሱብ አስክሮህ ዑስታዝክን አታምልክ፡

ይልቅስ ነብስ እወቅ፤
ሁሉም ሸህ አይደለም እየፈታ እሚያስር፡
ቅዱስ ነኝ እያለ፤
ፊትና እሚያነፈንፍ ፊርቃ የሚያበስር፡
ስንቶች በዑስታዝ ለምድ፤
እባብ ተቀምጧል በኮፍያቸው ስር፡

.....ኑረዲን አል-ዓረብ

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi


ቤታችን ውስጥ ጨለማ ከሆነ ብርሃን የሚሠጠንን ነገር መፈለጋችን ግድ ነው::
@ቀብርም እንድሁ ጨለማ ነውና ከመግባታችን በፊት ዛሬ ነገ ሳንል ብርሀን የሚሆነን እናዘጋጅ ምክንያቱም አመቱ እንደ ወራት:ወራት እንደ ቀናት:ቀናት እንደ ሠዓት:ሠዓቱ እንደ ደቂቃ በጣም እየፈጠነ ነው ::የእኛም እድሜ በዚህ ልክ ይፈጥናል መሞቻችን በዚሁ ልክ ይቀረባልና ሁል ጊዜ ዝግጁ መሆን ይኖርብናል::
"ከምን ጊዜም በላይ ድንገተኛ ሞት በጣም ተበራክቷል "
አንተ ሁሉን ቻይ የሆንክ አምላክ ሆይ መጨረሻችንን አሳምርል
https://t.me/UstazKedirAhmed


ጠያቂ፡- ምን አዘዝኩሽ ?
መላሽ፡- ጫት
ጫት ከአፈር ጋር ሲቀላቀል ልጅ መሆን ይችላልን ?
ልጅ አባቱን በእድሜ ሊበልጥ ይችላልን ?
ጅብ ይጋለባልን ?
በእናታችን ማህፀን መውጣት በቆሻሻ ቦታ መውጣት ነውን ?
አክታ እና ምራቅ መቀባት ?
አላህ ስልጣኑን የሰጠው ተጋሪ አለውን ?
ለሩሃኒያ ደም ማስጠጣት ?
አላህ አንተን መቼ ነው መርሃባ ያለህ ?
ከድምፅ ማሰረጃ ጋር
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem




ዓላማችን ሰውን ለመብለጥ ሳይሆን እራሳችንን ለመለወጥ በእውቀት ለመብስል እንድሁም ከማውራት ይልቅ መተግበርንና የሰውን ጥፋት ከማውገዝ በፊት ነፍሳችን ላይ ማውገዝ ማስተካከል ስንጀምር ነው ስኬታማ የምንሆነው::
https://t.me/UstazKedirAhmed


የዋህነት መልካም ነዉ ነገር ግን የዋህነትህን ሞኝነት አድርገዉ ለሚያስቡ ግለሰቦች እኩይ አላማ ግብአት አታመቻቸዉ ምክንያቱም የዛኔ በእዉነት ሞኝ ሆነሃልና


ውሎህ መልካም ይሆን ዘንድ ጉዞህን ከነዚህ አካላት ጋር አድርግ:-
-አላህን የሚፈራና አመስጋኝ ከሆነ አካል ጋር
-ንቁና አዋቂ ከሆነ አካል
-ከስህተቱ ተመላሽ ከሆነ አካል
-ቅን አመለካከት ካለው አካል
https://t.me/UstazKedirAhmed








ዛሬ ላይ ለወደደንም ሆነ ለምንወደው አካል ለምናወራቸው ወሬዎች ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ምክንያቱም ፀብ ሊከሰት ይችላል እና::
መቼም በዘመናችን ፀብ ሲክሰት የተወራ ቀርቶ ያልተወራ ነገር ይባላል እና::ለማንኛውም መጠንቀቁ አይከፋም ለማለት ያክል ነው!!
https://t.me/UstazKedirAhmed




ችግርህን ለሠው ስታማክር መዘርዘር :ማስረዳት ይጠበቅብሀል ሲቀጥል መፍትሄ ላታገኝ ትችላለህ እናማ ችግርህን ለሀያሉ አምላክ አውራው ምክንያቱም ችግርህን ሊቀርፍልህ የሚችለው እርሱ ብቻ ስለሆነ::
https://t.me/UstazKedirAhmed


ወቅታዊ የሆነ ጥያቄና መልስ የኦን ላይን ግብይትን በተመለከተ

أبو حاتم





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.