ያሲራጀል አለም


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ﺑﺄﺑﻲ ﻭﺃﻣﻲ ﺃﻧﺖ ﻳﺎ ﺧﻴﺮ ﺍﻟﻮﺭﻯ
ﻭﺻﻼﺓُ ﺭﺑﻲ ﻭﺍﻟﺴﻼﻡُ ﻣﻌﻄﺮﺍ ⚘
ﻳﺎ ﺧﺎﺗﻢَ ﺍﻟﺮﺳﻞ ﺍﻟﻜﺮﺍﻡ ﻣﺤﻤﺪٌ
ﺑﺎﻟﻮﺣﻲ ﻭﺍﻟﻘﺮﺁﻥ ﻛﻨﺖَ ﻣﻄﻬﺮﺍ ⚘
ﻟﻚ ﻳﺎ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﺪﻕُ ﻣﺤﺒﺔٍ
ﻭﺑﻔﻴﻀﻬﺎ ﺷﻬِﺪ ﺍﻟﻠﺴﺎﻥُ ﻭﻋﺒّﺮﺍ ⚘
ለበለጠ መረጃ
@ABDU_RESHID

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


⇒አሏህ ለአንድ ሰው ከሚሰጠው ፀጋዎች መካከል ራሱን ማወቁ አንዱ ነው። ራሱን ያወቀ ሰው ልኩን ያውቃል፣ ድክመትና ጥንካሬዉን ያውቃል፣ የሚችለዉንና የማይችለዉን ያውቃል፣ የሚያውቀዉንና የማያውቀዉን ያውቃል፣ መቆም ያለበትንና መቆም የሌለበትን ቦታ ያውቃል። ይህን በማድረጉ ራሱንም ሆነ ሌሎችን አይጎዳም።

ራሱን አውቆ መቆም ባለበት ቦታ ላይ ለቆመ ሰው አሏህ ይዘንለት።
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


#አውጅ_ቢን_ኡኑክ

አውጅ የነብዩላህ አደም የልጅ ልጅ ነበር። በጣም ረጅም እና ግዙፍ ቁመቱም 3300 ክንድ ይረዝም ነበር። አውጅ ቢን ኡኑክ እስከ 4,500 አመት እድሜ ያለው ሰው ነው። በነብዩላህ ኑህ عليه سلم ዘመን አላህ መርከብ እንዲሰሩ አዘዛቸው። መርከቡ ለመስራት ግን እንጨት ያስፈልጋቸው ስለነበር እንጨቱ የሚገኘው ኩፋ ውስጥ ነበር እናም ኑህ ካሉበት በጣም ስለሚርቅ ተጨነቁ በዚህ ጊዜ አላህ ራእይ አወረደላቸው አውጅ ቢን ኡኑክን ጠይቅ አላቸው። እሳቸውም አውጅን ጠየቁ እሱም ቅድመ ሁኔታ ጠየቀ ሆዴ መሙላት ስላለበት ምግብ አቅርብልኝ አላቸው። ኑህም ምግብ ሰጡት ሊያጠግበው ግን አልቻለም በመጨረሻ ቢስሚላህ ብሎ እንዲበላ ነገሩት በዚህ ጊዜ ቢስሚላህ ብሎ ሲመገብ ጠገበ። እንጨቱን አመጥቷላቸው መርከቡን ሰሩ። የጥፋቱ ውሀ በመጣና አለምን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ ለአውጅ ግን የውሃው ከፍታ ከጉልበቱ መብለጥ አልቻለም ነበር።
   አንዳንዶች በተራሮች ላይ እንደሚኖር ይናገራሉ ረሃብ ሲሰማው አሳ ከባህሩ ስር አውጥቶ በፀሐይ ሙቀት ይጠበስ ነበር። ሰዎችን እንደቆሎ ያፍስ ነበር።
      በነብዩላህ ሙሳ ዘመን ዐውጅ ሙሳንና ህዝቦቹን ሊያጠፋ አሰበ። ከዚያም አውጅ የነብዩላህ ሙሳን ወታደሮች መኖሪያ ቤት ለማየት መጣና ከቦታው ብዙም ሳይርቅ የነብዩ ሙሳ ወታደሮችን መኖሪያ አገኘ። ከዚያም በዙሪያው ያሉትን ተራሮች ነቅሎ በነብዩላህ ሙሳ ወታደሮች ላይ ሊወረውር ተራሮቹን ከጭንቅላቱ አኖራቸው። አውጅ ከጭንቅላቱ በላይ የተያዙትን ተራሮች በነቢዩ ሙሳ ወታደሮች ሊወረውር ጊዜ ከማግኘቱ በፊት አላህ ሁድ(የጀነት) አእዋፍ አማካኝት የአልማዝ ድንጋይ ልኮ አውጅ በያዘው ተራራ ላይ አስቀመጣቸው። አልማዝ በአላህ ሃይል በአውጅ የተያዘውን ተራራ አንገቱ እስኪደርስ ድረስ ዘልቆ ገባው መቋቋም አቃተው። 'አውጅ አልማዙን ለማስወገድ ፈቃደኛ አልነበረም፣ በመጨረሻ ሙሳ መጡ። 
የነብዩላህ ሙሳ ቁመት አርባ ክንድ ሲሆን የበትራቸውም ርዝመት አርባ ክንድ ነበር እና ከቁመታቸው በላይ አርባ ክንድ ዘለው (80 ክንድ) አውጅን በበትራቸው ቁርጭምጭሚቱ ላይ መቱት። በዚያን ጊዜ አውጅ ሙሳ ሆይ ወደ ቀኝ ልውደቅ ወደ ግራ አላቸው ሙሳ ተንኳሉን ስለሚያቁ ወደ ቀኝ አሉት የዚህን ጊዜ ወደ ግራ ወደቀ ግራ ቢሉት ኖሮ ወደ ቀኝ ይወድቅና ሰዎች ላይ ጉዳት ያደርስ ነበር ወደ ቀኝ ሲወድቅ ቀይ ባህርን ለሁለት ከፈለው ለዘመናትም መተላለፊያ ድልድይ ሆነ ሰውነቱንም ጅብ በልቷ እንደጨረሰው ይነገራል። አውጅ በአላህ ሱ.ወ ፈቃድ ወደቀ በመጨረሻ ምንም እንኳን ረጅም እና ከፍተኛ ጥንካሬ ቢኖረውም ከሞት ማምለጥ አልቻለም።

ኢብኑ ከሲር እንዲህ ይላሉ "ስለ አውጅ ዘገባዎች ለመዘገብ ያሳፍራሉ ምክንያቱም 'የአደም ዝርያዎች ተክለ ሰውነት ከዘመን ፍሰት እያነሰ እንደሚመጣ ከሚናገረው ሶሂህ ሀዲስ ጋር ይጋጫል። ምክንያቱም አባታችን አደም ርዝመታቸው 60 ክንድ ነበር" ብለዋል።

*የአደም ልጅ ከሁሉ ፍጥረት የላቀው በግዝፈቱ አይደለም እንደዛ ቢሆንማ ዝሆን ከሰው ይልቅ በከበረች። ሁሌም ይህን በልብህ አኑር: ጥበበኛውን አላህ ማወቅ የልዕቅና ሁሉ ሚስጥር ነው።

https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ዑመር ዛሬ በኒ(ኑር) መስጅድ ላይ ከኹጥባ በፊት ካደረጉት ንግግር ከፊሉ እና ጥቂቱ ..

.......የተከበራቹ  አዳማጮች  ኡለማዎች ይናገራሉ አድማጮችም ያዳምጣሉ አላህ ይፈለገውን ይሰራል ይወስናል ።

የሁሉም መለያው መጨረሻው ከሞት ቡኋላ ነው

ከፊሉ የገንዘብ ባሪያ ይሆናል
ከፊሉ በስልጣን ይታለላል
ከፊሉ ይዋሻል
ከፊሉ ያለቅሳል
አላህ ያሻውን ይሰራል

.......
የሰው ልጅ ዛሬ መሪው ገንዘብ ነው ስልጣንም ሚፈልገው ለገንዘብ ነው ።
አሊሙ ለገንዘብ ሲል ፋሲቅ ይሆናል
  አሊሙ እንዲህ ከሆነ ጃሂሉ በምን ይታማል ?

....
መማር ማለት ወረቀት ላይ መፃፍ ብቻ አይደለም ማወቅ ነው ።

ለምክር ሞት በቂ ነው ።
........

ወንዱ ሴት መሆን እየፈለገ ነው ሴቱ ወንድ መሆን እየፈለገ ነው ለመናገርም ተጠይፈነው ቆይተናል አሁን ግን እየገፋ እየባሰ ህጋዊ እየሆነ መጥቷል 😥

ወንጀል እየበረከተ ነው ወጣቶች እንዳትታለሉ እንዳትሞኙ ሞት አለ ሞት አለ ........

የሞትን ቀን የወደቅንለት ስልጣን አይጠቅምም

https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


እንኳን ለ1444 አመተ ሂጅሪያ በሰላም አደረጋችሁ
# በነገ ቀን ችግርተኛን እንዳንረሳ
ሁላችንም በየጎረቤታችን በየ ሰፈራችን በየ መንደራችን ስንት የቲሞች አቅመ ደካሞች መከርተኞች ይኖራሉ እና በደግነታችን እንዳንረሳቸው
# ድግነት ውጤቱ ለራስ ነው
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


ለኡስታዝ ሀሰን ታጁ

👉 ለሀበሻ ሙስሊሞች የሀይማኖታዊ እውቀት መስፋት የእርስዎ ሚና አይተኬ ነው ፥ በቅርብ አመታት ደግሞ በአማርኛ ፀሀፊዎች በኩል የቲም የሆነውን የአህለሱናን መስመር ለህዝብ ግልፅ የሚያደርጉ የተወሰኑ መፅሀፍቶችን አበርክተዋል ።

🔰በትክክል ባላወቅናቸው ምክንያቶች እነዚያን ድንቅ መፅሀፎች ለህዝብ ከማድረስ ትንሽ ተቀዛቅዘዋል ፥ በቅርቡ ደግሞ ወደ ሚዲያ ተመልሰው ጥሩ ጥሩ ፅሁፎችን እያካፈሉን ነው ሆኖም ግን እነዚህ ፅሁፎች በሌሎችም የአህለሱና ወንድምና እህቶች  ሊፃፋ የሚችሉና የሀበሻ አህለሱና በዐቂዳዊና በፊቅሀዊ ፅሁፎች  ዙሪያ  የሚታይበትን ክፍተት ሊሸፍኑ አልቻሉም ።

🛑 በተለይ በአህለሱናው የዐቂዳ መንሀጅ ዙሪያ ከምናስበው በላይ በሰፊው ውዥንብሮች እየተሰራጩ ነው ፥ ሰፋ ያሉና ለመረዳት ቀላል የሆኑ ምላሾች ያስፈልጋሉ ፥ ይህን ለማድረግ ደግሞ ከእርሶ የበለጠ ቀለሙ የሰላ ወንድም የሚገኝ አይመስለንም ፥ ብዙ ወንድሞች ጋር ምላሽ የመስጠት አቅሙ አለ ነገር ግን አቂዳ ላይ ያሉ ብዙ ቃላትን ወደ አማርኛ መተርጎም ሲከብዳቸው ተመልክተናል ስለዚህ ሀላፊነቱ እርስዎ ላይ የወደቀ ይመስላልና ከወዲሁ እንድታስቡበት በአሏህ ስም እንጠይቅዎታለን 🙏🙏።
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


የተባረከ የተባረከ ጁምአ ይሁንልን
ሱረቱል ካህፍን መቅራት እና ሰለዋት እናብዛ አንርሳ
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


إنا لله وإنا إليه راجعون
انتقل إلى رحمة ربه العلامة الجزائري الطاهر ايت علجت رحمات الله عليه
الفاتحة

https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


🍂 የአሏህ { ሱ.ወ } ፍቅር ያንተ ድርሻ
እሱን በምታወሳው ልክ ነውና
አሏህን በብዙ አውሳው 📿📿📿።

   🍂 ያግራልን!!!


ምሁራን ተብዬዎቹ ሲሰክሱን “ የሀይማኖት ተቋማት ህግን ካላከበሩ ማን ሊያከብር ነው “ ??? አሉ ፥ ካርታ ሳይኖራችሁ እንዴት መስጂድ ትሰራላችሁ ማለታቸው ነው ።

# አዲስ አበባና ዙሪያዋ ላይ የትኛው መስጂድ ነው ከጅምሩ ህጋዊ የሆነው ?? ደም ያልፈሰሰበት ፣ ህይወት ያልጠፋበት መስጂድ የታለ ?? ይህ ሚያሳየን በህጋዊ መንገድ ለመስጂድ ቦታ ስንጠይቅ ተገቢ ምላሽ ስለማይሰጠን ወደ ሌላ አማራጮች ተገደን ገብተናል ማለት ፥ ወደፊትም ይቀጥላል እንጂ አይቆምም አለበለዚያ እቅዳቸው ተሳክቶ መስጂድ አልባ መሆናችን ነው ።
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


ተከታዩን የኢማሙ ሻፊዒ ግጥም ባነበብኩ ቁጥር እንደአዲስ እገረማለሁ፡-

أُحــبُّ الصَّــالحينَ ولسْــتُ مِنهــمْ  لعلِّـي أن أنـــالَ بهــم شـــفاعَةْ
وأَكــرهُ مَنْ بِضــاعتُــــه المـعاصي  ولو كنَّا ســواءً في البِــضاعة

ከደጋጎች ባልሆንም ምልጃቸዉን ከጅየ እነርሱን እወዳለሁ፣
ከሀጢአተኞች ብሆንም ሀጢአተኛን አጥብቄ እጠላለሁ፤

የምጥቀትን ጣሪያ የደረሱ ሰዉ ‹‹ከደጋጎች አይደለሁም፤ ምድቤ ከሀጢአተኞች ነዉ›› ሲሉ እንደመስማት ምን የሚደንቅ ነገር አለ? ዉስጥ እየጸዳና እየነጣ፣ስብዕና እየገዘፈና እየመጠቀ በሄደ ቁጥር ራስን ዝቅ የማድረግን ባህሪ፣መተናነስንና ትህትናን እያወረሰ መሄዱ ዕሙን ነዉ፡፡

ራሱን የሚቆልል ሰዉ ከገጠመህ የዕዉቀትም ሆነ የበጎ ሥራ ስንቁ ጭብጦ እንደማትሞላ እየነገረህ ነዉ፡፡

የደጋጎችን ‹‹ሸፋዐ›› መከጀላቸዉም ለኛ ትልቅ ትምህርት ነዉ፡፡

ምልጃቸዉ በሙሀባ እንደሚገኝም ሚስጥር አካፍለዉናል፤ ሙሀባ የማይሠራዉ ትንግርት የለም፡፡

https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


ቁም ነገር አዘል ቀልዶች
===================
የመጅሊሱን እና የጀንፈሉን ይቅርታ የአህመዲን ጀበልን ጉድ በዝርዝር እንመጣበታለን።

አንዱ ፕሮቴስታንት አንድን ሙስሊም ለማሳመን ሙስሊሙን መንገድ ላይ እያስቸገረ ይከተለዋል ከዛም ለሙስሊሙ እንደዚህ አለው"እየሱስ ይወድሃል እየሱስ ተሰቅሎ አንተንም እኔንም አድኖናል" አለው
ሙስሊሙ ምን ቢል ጥሩ ነው"ተሰቅሎ የሚያድን ግሉኮስ ብቻ ነው"😂😂😂😂

ይገርማችኋል
አንዱ አፋኝ ሰውየ እንዲህ አለ" አገሬን ሙቼም ቢሆን ከአሽባሪ ነጻ አድርጌ አገሬን አድናለሁ" ሲለው

ታፋኙ ሰው ምን ቢለው ጥሩ ነው"ሙቶ አገር የሚያድነው ፈንጂ አምካኝ ብቻ ነው"
😂😂😂😂😂😂

በቅርቡ ደግሞ መጅሊሱ ውስጥ ያሉት ውስጣዞች ካሉ ዲኑ በትክክል ይቀጥላል ሲል አንዱ ሙስሊም ምን ቢለው ጥሩ ነው "እዚህ አገር ሙቶ ዲን ያስቀጠለው ሱፊዩ ብቻ ነው"
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አቡበክር አህመድ ስለእቅዳቸው ሲለፈልፍ በተለይ አሁን ሰላለው ወቅታዊ ጉዳይ ሰለነ ዶክተር ጀይላን ሁሉ ከ8 -መጨረሻው ያዳመጡ


ይህ ሁሉ ዘመቻ ይህ ሁሉ ግፍ በአማኞች ልብ ውስጥ ፍርሃትን ለማንገስ ነው።

የትኛውንም ምድራዊ ሀይል ብታሰማሩ ምኞቱ ጀንት የሆነን አማኝ ልታስፈራሩት አትችሉም። አማኝ ወዳጆቹ የቆሰለውን ወንድማቸውን ተሸክመው የሚያስታውሱት ነገር ቢኖር ፍፃሜውን እንዲያሳምር የጀነት ቁልፍ የሆነውን የምስክርነት ቃል ላኢላሃ ኢለሏህ የሚለውን እንዲተነፍስ ነው።

እሱም የሸሃዳ ጣቱን ቀስሮ በሸሃዳ ፅናት ላይ ነው ። አትድከሙ ግፉን አብዝታችሁ ውድቀታችሁን ታፋጥናላችሁንጅ አማኞችን አታሸንፉም።


#ማሳሰብያ፦ ለአማኞች ሁሉ‼ በተለይ በዚህ ሰአት የሙስሊሙን ትግል በ #ዉሃብያና #አህባሽ ፤ #አማራና #ኦሮሞ…  እንዲሁም የተለያዩ ማደናቀፍያ ርእሶች ላይ ተጠምዳቹሁ የምታንጫጩ፣ የምታሰድቡን ሁሉ በጊዜ አደብን ያዙ።

አላህ የምትፈሩ ከሆነ፣ ወይም ክብራቹሁን ለማስጠበቅ የምትፈልጉ ከሆነ እንደ አሻቹሁ አትቀባጥሩ። በዚህ ሰአት ሲለ ፊርቃ እና መጠላለፍ አታንሱብን። ኡማውን ወደ ጥንቃቄ እንጂ ወደ ጥርጣሬ አትጋብዙ።
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


#Update

ኡስታዝ ሐሰን ታጁ (አምባሳደር) ፤ " የኃይል እርምጃ  በየትኛዉም መመዘኛ ተቀባይነት የለዉም " አሉ።

ኡስታዝ ሐሰን " በዛሬዉ ዕለት በታላቁ አንዋር መስጂድና በሌሎች  መስጂዶች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የወሰዱት የንጹሀን ዜጎችን ህይወት የቀጠፈና ያቆሰለ የሀይል እርምጃ  በየትኛዉም መመዘኛ ተቀባይነት የለዉም " ብለዋል።

" እንዲህ ዓይነት ያልተገቡ እርምጃዎች ቀዉስን በማባባስና የማህበረሰቡን ምሬት በመጨመር በሀገር ላይ አደጋ የሚደቅኑ አላስፈላጊ ዉጤቶችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚመለከተው አካል ሊረዳ በተገባ ነበር፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።


#የሸሂዶች ሃገር ኢትዮጲያ

ሸሂድነት ከ ሚነላህ መታደልን ይጠይቃል
ወንድማችን አላህ በሰፊው ጀነቱ ያብስርህ
አል ፋቲሃ


https://www.facebook.com/940301656169619/posts/pfbid02oM3Gi1fRL2waH6j1auR5YnVSwkeHQAa12GT2zRFmkPWtFQdFRsr6dpDLYh6T7nyyl/
ሰበር ዜና

በአንዋር መስጅድ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቀጥታ ወደ ህዝቡ አየተኮሱ ብዙ ሰው መሞቱና መጎዳቱ ተገለጸ

በታላቁ አንዋር መስጅድ ህዝበ ሙስሊሙ የጁምአ ሶላቱን ሰግዶ ለመውጣት በሚሞክርበት ጊዜ ቁጥራቸው አዳጋች የሆኑ የብልጽግና የጸጥታ ሀይሎች መስጅዱን የወንዱንም የሴቱንም ከበው ይዘው ምንም ያልያዘን ህዝብ በቀጣታ ወደ ህዝቡ እየተኮሱ ቁጥሩ የሚያዳግት ህዝበ ሙስሊም ሲት ወንድ፣አዋቂ ህጻን ሳይሉ በቀጥታ በመምታት ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።

ይህ የለየለት አምባገነናዊ የብልጽግና ወንጀል በየትኛውም ጊዜ ተደርጎ የማይታወቅ፣በዘመነ-ኢህአዴግ ጊዜም ያልነበረ አረመኔያዊ አምባገነንነት በሀገራችን ለመንሰራፋቱ ማሳያ ነው።በየ ጁምአው ለምን መስጅድ አፍርሼ ተቃዋሚ ይኖረኛል በሚል ዱላ እንኳ ያልያዘን ህዝብ በጥይት አረር የሚገድል የህዝብ ጠላት የሆነ አስተዳደር ስር ሀገሪቱ መውደቋን ማሳያ መሆኑን ሁሉም መስክሯል።

SHARE  SHARE  SHARE ያድርጉ
LIKE LIKE LIKE LIKE በማድረግ የእርስወን ድርሻ ለሌሎች በማዳረስ ይወጡ
#የፌስቡክ #ገጻችንን #የዲን #ወታደር #የሚለዉን #ይህንን👇🏿
https://m.facebook.com/yedinwetader
በመንካት ገብተዉ  #LIKE #ያድርጉ

በቴሌግራም ይከታተሉን
https://t.me/joinchat/AAAAAFlZ0HCkBTtYs5KqDA
#እኔ_ኡለሞቸን_ተቋሜን_መስጅዴን_የምጠብቀው_ጀግናው_የሙፍቲ_ትውልድ_ነኝ


«ንቀውናል» ነው ያሉት?😉
   °°°°°°°°°°°°°°°°°
ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ጫና ሲበዛባቸው ትላንት ባደረጉት የይምሰል ስብሰባ ላይ .. «የሙስሊሙን ብቸኛ መሪ በመናቅ በማን አለብኝነት ሄደው መስጂዶችን አፈረሱ» .. ብለው ሲናገሩ ሰምቼ እንደ ሁሌው ሁሉ የሰውየው የዋህነት አስገረመኝ።

ሲጀመር የሙስሊሙን ተቋም በዘ^ር፣ በጎጥ፣ በወሃ^ቢያዊ ቡድ^ንተኝነት በመቀራመት፣ ሰፊውን ሙስሊም በማግለል፣ ቡድ^ንን መሠረት አድርጎ መስጂዶችን በመቀማት ተቋሙን ያጠነ^ባውና ያዋ^ረደው ማን ሆነና?!

ሰሞኑ መስጂዶች እየፈረሱ ጭምር እነ መሀመድ አባተና አቶ ሱልጣን አማን ግን መስጂዶችን በፖሊስ ኃይል በመቀማትና በማስበጥበጥ፣ ሙስሊሞችን በማሳሰር፣ በማስደብደብ፣ ኢማሞቹን አባረው በምትካቸው ቡድናቸውን በመሾም ተጠምደውና እረፍት አጥተው እንደሰነበቱ እያወቃችሁ?! በዚህ ጥበ^ታችሁ ፈፅሞ ሰፊውን የሙስሊሙን ኡማ አትመጥኑም፤ ጭራሹኑ አዋረዳችሁት።

ደሞ መንግስት እራሱ ዑለሞቻችንን አዋ^ርዶ ከመጅሊሱ እንዲያባርር ከተመሳጠራችሁ በኃላ፤ መንግስት በአፈሙዝ ኃይል የመጅሉሱን በሩን ገንጥሎ አዝሎ አስገብቷችሁ ምን ዓይነት ክብር ነው ከሱ ምትጠብቁት?! እራስን አዋ^ርዶ መከበር ከየት ይመጣል?!

መሳጂዶችን ሚያፈርሰውና ቁርአንን ሚያዋ^ርደው መንግስት እናንተን መጅሊስ ወንበር ላይ ለማስቀመጥ ይህን ሁሉ ዋጋ የከፈለው «ለኢስላም አዝኖ ነው» እንደማትሉን መቸም ተስፋ አደርጋለሁ። የመንግስትን ፖለቲካ እንድታስፈፅሙና የሱ አሽ^ከርና ተላ^ላኪ እንድትሆኑ በሚል አዝሎ እንዳስገባችሁ ከማንም በላይ እናንተው ታውቁታላችሁ። ታዲያ አሽ^ከሩን የሚያከብር ማን አለና ነው መንግስት ንቆ^ናል ምትሉት?! መጅሊሱንም ሆነ ሙስሊሙን ከእናንተ በላይ ማን ያዋ^ረደ አለና?!

መንግስት ምን ያህል እንደና^ቃችሁና እንዳቀ^ለላችሁ ምታውቁት ለመከላከያ የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ በሚል ስም በተዘዋዋሪ ሰልፈኞቹ መንግስትን እንዲደግፉ ለማድረግ ለዛሬ እሁድ ግንቦት 20/2015 በሸገር ሲቲ ሰልፍ ሲጠራ ነው። መንግስት እናንተ በሰልፉ ላይ ኖራችሁም ቀራችሁም ምንም አታመጡም እያላችሁ ነው። ሰልፉን ሚደግፍና ሚያደምቅ በቂ የፕሮቴስታንት ኃይል እንዳለው ሊያሳያችሁ ነው።

እናንተ ነባሩን ሙስሊም ለማግ^ለልና ከገዛ ተቋሙ ለማፈ^ናቀል በጠ^ባብነት ሩጫ ተጠምዳችሁ ሳላችሁ መንግስት ግን ሚፈልገውን ሁሉ አድርጎ ጨረሰ። እናንተ ዑለሞቻችንን በየጊዜው በማሳሰር፣ በማዋ^ረድና በማንገላታት ስትጠመዱ፤ መንግስት ግን ሙስሊሙንም መስጂዱንም ከሸገር ሲቲ ጠርጎ በማስወጣት በምትኩ የኔ ሚላቸውን ጴንጤዎች አደላደለ። የእናንተ ጦሳችሁ ለእኛም ተረፈ።

እኩሎቻችሁ በዘ^ርና በጥቅም ተጠልፋችሁ ጭራሽ የመንግስት አጋር ሆናችሁ አረፋችሁት። ንቀ^ትንም አተረፋችሁ። ሲጀመር መንግስት እራሱ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ መጅሊሱ አምጥቷችሁ እንዴት አይና^ቃችሁ?! ዑለሞቻችንን ያዋረ^ዳችሁ ጊዜ እናንተም በመንግስት ሚዛን ላይ ይበልጥ ረከ^ሳችሁ።

መንግስት በሸገር ሲቲ በሙስሊሞች ሂሳብ የኔ ሚለውን የፕሮቴስታንት ኃይል ካደላደለና ዲሞግራፊውን ከቀየረ በኋላ፤ እናንተ ማለት በብዛትም ሆነ በክብደት ምንም እንደሆናችሁ ሊያሳያችሁ የወሰነ ይመስላል። ወደ መጅሊስ አዝሏችሁ እንድትገቡ ያደረገበት ፖለቲካዊ ሚሽናችሁም ሊያልቅና expire ሊያደርግ እየተቃረበ መሆኑን ሊያረጋግጥላችሁ መንግስት ለዛሬ የድጋፍ ሰልፍ ቀጠሮ ይዟል።

የሸሂዶቹ ደም ይፋረዳችሁ!

Hamsa Hamsa
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


«..ራስህን ሷሊሆቹን (ደጋጎቹን) ዝቅ አድርጎ ሲመለከት ካየኸው እና ወደነርሱ መቅረብ የሚከብድህ ሆኖ ከተሰማህ ..... አንተ ከነርሱ የተጋረድክ አይደለህም..... ይልቁን አንተ ከአላህ የተጋረድክ መሆንህን ልታውቅ ይገባል...»

        ኢማም ሸሂድ ሙሀመድ ሰዒድ ረመዳን አልቡጢይ (ቀሰሏሁ ሲርረሁ) 💙🌿 https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


«...ትልልቅ ሐሳቦች ሁሌም ከትልልቆች ነው ሚፈልቁት ..»

(ሀ)....ሀሳብ ያልኩት ነገር አእምሮ ውስጥ ተዋጅቶ የሚፈልቀውን ነገር ብቻ ለመግለፅ እንዳልፈለኩ ልትረዳኝ ይገባል .... ማለትም 'ምልከታ' እና 'የሩቅ እይታ ' የሚለውን ተክቶ ሊገባ እንደሚችልልኝ ተረዳኝ

በ.... የትልቅነት ምልከታህን አላውቅም .... መለኪያህ ግን ለጌታው ባለው አፍቅሮት ካልሆነ መጀመሪያ ለመዛኝነተትህ ራስህን እንድተትመዝን እመክራለሁ  .... እናም "የሩቅ ተመልካች" ካልነው ዘንዳ ትልቅነቱን በምን እንደመጣ እንደምተትረዳኝ አስባለሁ ....

ገ....ትንሽ ሰው ነው ብለህ ያሰብኸው ሰው ትልቅ ሐሳብ ሲያፈልቅ ካየኸው ...በርግጥም ምልከታህ ተሳስቷል እና አርመው ....እሱ ልበ አይናማ ሰው ነውና ሸማህን ከትከሻህ ጥለህ ተቀበለው  ....

(ፀ) ..... ይህ ከላይ ያለው ፅሁፍ በምን ተነሳሽነት ...በማን በምን ለምን እንፃፍኩት አልገባኝም ...notebook ኤ ላይ  አጊንቼው ነው ....የማዎራው ግን ቀሪኔን ነው ብዬ ሸክካለሁ .... ዋናው ነገር ግን ደግሜ ሳነበው ብዙ ያልገባኝ ነገር መኖሩ ነው ....የገባችሁን የተረዳችሁትን 🤲

"...ትልቅነትን ትንሽ በመሰለህ ቦታ ፈልገው"  የሚል የግርጌ ማስታወሻም ነበረው 🙄

#ነሲም_ሚራዥ https://t.me/YASIRAJEL_ALEM


በሲኤምሲ አል ዒምራን መድረሳ ስር የሚተዳደረውን የጎሮ አንቢያእ ሂፍዝ ማእከል ለመቀማት አዲሱ መጅሊስ የሾመው ኮሚቴ የመጨረሻ ያለውን እርምጃ በመጓዝ ላይ ነው ።

# ከመድረሳዎቻችን እጃችሁን አንሱ
         ሼር ሼር

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

512

obunachilar
Kanal statistikasi