🌸የተውሂድ ጎዳና 🌸


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


➜ ውድ እና የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ በአላህ ፍቃድ እዚህ ቻናል ላይ ወንዱንም ሆነ ሴቷን አማኝ የሚመለከቱ ዲናዊ ትምህርቶች+ፅሁፎች+ዳዕዋዎች+ምክሮች የሚቀርቡበት ይሆናል ኢንሻአላህ ።
➟ ሀሳብ +አስተያየት +ምክር ካለዎት
👇👇👇👇👇👇👇
➖➖➖➖➖➖➖
@Hafsu97
@BintMama_Bot
➖➖➖➖➖➖➖
ላይ ያድርሱኝ ኢንሻአላህ እቀበላለሁ ባረከላሁ ፊኩም።

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


💎ጉዞ ወደ ኒቃብ💎
ክፍል 6 ...

የዘንድሮው የ2ተኛ ዓመት ፕሮግራም አሪፍ እየሄደ ወደ 4……5 ወራቶችን እያስቆጠረ ነው። ግን በዚህ ዓመት ኒቃቢስትና ጂልባቢስቶች መኖራቸው ለኮሌጁ እረፍት የሠጠው አይመስለም። ለነገሩ ምኑ ይገርማል ስንት ትምህርት ቤቶች ላይ ነው ሰላት ሰግደሀል/ሻል፤ሂጃብ ለብሰሻል፤ሡሪ አሳጥረሀል እየተባለ ከትምህርታቸው ሚስተጓጎሉት ስንቶቹ ናቸው!? በዚህም ኮሌጅ የምሠማው ጥሩ አነበረም። በባለፈው ክፍል የኮሌጁ ምክትል ዲን ሙስሊም እንደሆነ ገልጬ ነበር እናም ለምን እንደሚከለክል እንደ ምክንያት የሚያስቀምጠው "እኔ ሙስሊም ስለሆንኩ ስፈቅድ ሲያዩ ለራስህ እምነት አደላህ ይሉኛል" ነበር። ግን ይሄ አሳማኝ ምክንያት አይደለም ሙስሊሞች በተለያዩ ተቋማት ላይ ቦታዎችን ይዘው ሳለ ዲኑን ባላቸው አቅም ካነሰሩ ማን ሊሰራ ነው ታድያ?

በዚህ ዓመት ብዙውን የት/ት ጊዜያችን የምናሳልፈው በተግባር(practis) ነበር። አምና እኔ የገባሁበት ፊልድ ለትምህርት ቤቱ የመጀመሪያ እንደመሆኑ እንዲሁም በነበረው ሁኔታ የራሡ የተግባር ማሠልጠኛ ቦታ አነበረውም ለዚያም ለተግባር ወደ ሌላ ቦታ እየሄድን ነበር የምንማረው ይህም ነበር በብዛት ከኮሌጁ አስተዳደሮች ጋ እንዳልገናኝ የረዳኝ ። አሁን ግን በአዲሡ አመት ቦታውን ከፍቶ አስመርቋል አዲስም ስለሆነ የኮሌጁ መምህራንና ዲን እየመጡ ይጎበኙታል። በዚህ መሀልም በአንዱ ቀን ዋናው ዲን ወደዚህ ቦታ ሲመጣ ያየኛል ከዚያ ከአስተማሪዬ ጋር ያስጠራኝና

"ተማሪ ነሽ?"
"አዎን"አልኩት
ስሜንም ጠየቀኝ ነገርኩት።
ወደ አስተማሪዬ በመዞር
"ስንተኛ አመት ተማሪ ናት?"
እሡም 2 አለው።
እንዴት ይህን ለብሳ ትማራለች አምና እኮ ለዲኑ (ለሙስሊሙ) ነገሬው ነበር ለምን ዝም አላት ለማንኛውም ይህን ለብሰሽ እንዳትመጪ ከፈለክሽ ( አጠገቤ ታዝባ የምታየውን ሙስሊም እህቴን እየጠቆመ) ሻርፕ አድርገሽ ነይ ብሎ ሄደ።
በነገራችን ላይ አስተማሪዎቼ እግሬ እዛ ከረገጠበት ቀን አንስቶ ምንድነው የለበሽው ለምን ይህን ለብሠሽ ተማርሽ ወላሂ አንድም ቀን ጠይቀውኝ አያውቁም አሁንም ቢሆን ምንም እነሡ አይመስላቸውም።

እኔን ግን ያልገባኝ የአስተዳደሮቹ እንዲህ መሆን ነው ዛቻቸውም በዚህ አልበቃም ጨርሠን ስወጣ ደግሞ በተራው ጥበቃው ጠራኝና"የዚህ ት/ቤት ተማሪ ነሽ አለኝ አው ስለው ከዚህ በኋላ ግን በዚህ ከመጣሽ አትገቢም አለኝ።
"ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ" አለ ያገሬ ሠው።

ዝም ብዬው ወጣው በሠዐቱ ራሡ አጠገቤ ሙስሊም ያልሆነች ልጅ ነበረች እንዴት ልታደርጊ ነው ስትል ጠየቀችኝ " ትምህርቱ እንደሆነ ጥንቅር ብሎ ይቀራታል ማውለቄ ሲያምራቸው አይታሠብም " ብያት ጉዟችንን ቀጠልን።

ይቺ ቀን እዛ ኮሌጅ ከተማርኩባቸው ቀናቶች ሁሉ የተለየች ናት እንግዲህ ዲኑ ለጥበቃው አታስገባት ብሎት መሆኑ ነው ሥል አሰብኩኝ………


ኢንሻ አላህ ይቀጥላል…


﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ۝﴾

قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً»
በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል
اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمدﷺ 🍃


የጁመዓ ተወዳጅ ሱናዎች

#መልካም_ጁመዓ


#ውዷ__እህቴ ሆይ!
👉ንፅህናን + ፅዳትን ህይወትሽ አድርጊ!
ማለቴ ከትዳር በፊትም + በኋላም የፀዳሽ ሁኝ!
ነብዩ ( عليه الصلاة والسلام) እንዲህ ብለዋል:-
👉#ንፅህና የዒማን ግማሽ ነው!
እናማ
👉ንፁህናን ልምድሽ አድርጊ!
በተለይም + በተለይም ከትዳር በኋላ እጂግ አስፈላጊ ነውና!
👉አስተውይ + አገናዝቢ እህቴ!
አንዴ አግብቻለሁ + አንዴ ወልጃለሁ ብለሽ ራስሽን አትጣይ!
👉አው አትጣይ!
↪ዓማኝ ሴት ሁሌም ንፁህ ናት
↪ዓማኝ ሴት ለማን ምን አይነት አለባበስን ትለብሳለች የሚባለውን!
☞በፅሁፍና በአፍ /በንግግር ብቻ አታድርጊው!


👉አንዴ አግብቻለሁ + ወልጃለሁ ብለሽ ራስሽን አትጣይ!
♂የምትለብሽው ልብስ ንፅህናው ከማንሰሻ ልብስ የማይሻል ንፅህና የጎደለው አይሁን!




☞ሽታው/ጠረኑ ሽንኩርት ሽንኩርት (በሳል በሳል) + በርበሬ በርበሬ + ወጥ ወጥ እየሸተተ!
↪ፀጉርሽን አንጨባረሽ (ማበጠርያ ማስነካት እንኳን እየከበደሽ + ለራስሽ ጊዜ የሌለሽ እስኪመስል መሰብሰብ ተስኖሽ!

↪ ቤትሽ ንፅህና ጎድሎት!
☞የተኛሽበት + የበላሽበት + የጠጣሽበት………ዕቃ የለበሽው/ የለበሳችሁት ( የአንች + የልጆችሽ + የባለቤትሽ) ልብሶች በየቦታው ተዝረክርከው


↪የትዳር አጋርሽ/ባለቤትሽ ሌላ ሴቶችን ቢፈልግ እንዲሁም በሚድያ ወጥቶ የሚድያ ሴቶችን(እህቶችሽን) ቢጀነጂን ምን ይገርማል!¡ ኣ?¿

↪ ባለቤቴ ሊያገባብኝ ነው!
↪ባለቤቴ ቺት እያረገብኝ ነው!
↪ባለቤቴ አይወደኝም… …………………………… እያለሽ ከምታወሪ / ከምታለቅሽ!

☞ራስሽን ተመልከች!
ጉድለትሽን ፈትሽ!

አው እህቴ!
☞ፈትሽ ባለቤትሽ ካንች ጉድለት ከሌለ ሌላ ፍለጋ አይሄድም!
👉ከሀራም ለመጠበቅ ብሎ ነው ጌታው(አላህ) የፈቀደለትን ሀላል የመሰረተው!
👉ከባለቤቱ/ ከሚስቱ የሚፈልገውን ሁሉ በአላህ ፈቃድ ለማግኘት
♂መሳቅ + መጫወት + ማውራት + መቃለድ + መደሰት+መተሳሰብ+መተጋገዝ ………………ለማግኘት!
↪በፅዳት ደረጃ ሁሌም ንፁህ ልትሆኚለት + ባላሽ ልብስ ልትዋቢለት ይፈልጋል!

ሀታ ☞የጂስምሽ ሁኔታ ከእድሜና ከመውለድ በኋላ እንኳ ቢቀየር ማለት ነው!!
👉ገባሽ አይደል እህቴ!

So ንፅህና ልምድሽ + ባህሪሽ አድርጊው👂!!!

ሴት ማለት ደግሞ ሁሌም የራሷን + የቤቷን እንዲሁም የልጆቿንም ንፅህና የጠበቀች የሆነች ነች!!!


ሰምተሻል + ተሀል /ሰምታችኋል!!!

@YeTewhidGodana
@YeTewhidGodana


ሙስሊም ያልሆነ ወጣት አንድ ሸይኽ ጋር ይመጣና
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
"እናንተ ሙስሊሞች ሴቶቻችሁን ለምንድን ነው ሒጃብና ኒቃብ የምታስለብሷቸው ? ፣ ለምንድነው ነፃ እንዳይሆኑ እየሸፋፈናችሁ የምትጨቁኗቸው?"
ብሎ ይጠይቃል።
ሸይኹም የዋዛ አልነበሩምና "ጥያቄህን ከመመለሴ በፊት ሁለት ከረሜላ ገዝተህ ይዘህልኝ ና!" ብለው ከኪሳቸው አንድ ብር አውጥተው ይሰጡታል።
ልጁም በፍጥነት ሁለት በላስቲክ የታሸጉ ጣፋጭ ከረሜላዎችን ይዞ ይመጣል።
ሸይኹ ከረሜላውን ተቀብለው አንዱን ሽፋኑን አንስተው ፣ ሌላኛውን ደግሞ ከነሽፋኑ አቧራ ላይ ጣሉት።
ወደ ልጁም ዘወር አሉና ከሁለቱ መርጠህ ውሰድ ብትባል የትኛውን ትወስድ ነበር?" ሲሉ ይጠይቁታል።
ልጁም "ይህማ ምን ጥርጥር አለው፣ ሽፋን ያለውን ነዋ የምመርጠው " ሲል ቆፍጠን ብሎ ይመልስላቸዋል።
ሸይኹም ፈገግ ብለው:- " አየህ የኛም ሴቶች እንደ ታሸገው ከረሜላ ናቸው። ራሳቸውን ስለሚጠብቁ ንፁህና ተፈላጊም ናቸው። " ሲሉ በጥበብ የተሞላ መልስ ሰጥተው አሰናበቱት።
*
ብዙ ሰዎች የሒጃብን ጥቅም ስለማይገነዘቡ መጨቆን ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ውድ ነገር ተሸፍኖ መገኘቱ ነው፣ መአድን በቀላሉ እንደማይገኘው ሁሉ የኛም ሴቶች በጣም ውድ ዋጋ ነው ያላቸው!
አንዳንድ የሙስሊም ጠላቶች ሒጃባችን ላይ ዘመቻ ከፍተውብናል። እኛም የሂጃብነ ክብር ማሳየትና ማስተማር አለብን እርሶም ሼር በማድረግ የበኩሎን ሃላፊነት ይወጡ!






እህቴ ለማን ነው የምትዋቢው ?
በጣም የሚያሳዝነው ብዙ እህቶቻችን መቆነጃጀት እራስን ማስዋብ ጥሩ ልብስ መልበስ የሚቀናቸው
ወደ ሰርግ ሊሄዱ ሲሉ
ወይም ጓደኛቸው ጋር ሲቀጣጠሩ
አንዳንዶች ደግሞ ወደ ሥራ ሲወጡ
ሌሎቹ ደግሞ የአላህ ባሮችን አሳስተው ወደ ሐራም ለመጥራት ያለ ምክንያት ሲወጡ
እና ለመሳሰሉት ነው
የባሎቻቸውን ሐቅ አሽቀንጥሮ ይጥላሉ
ከወጡበት ወደ ቤት ሲመለሱ ያ ሁሉ ያጌጡበት ነገር አውጥተው ይወረውራሉ
ባል ሲመጣ በማድ ቤት ልብስ በላብ ሽታ
በሊጥ እጅ በሽንኩርት ባለቀሰ ዐይን
በተንጨባረረ ፀጉር
በተዝረከረከ ገፅታ ከሷ እንዲርቅ በሚያደርግ ሁኔታ ትቀበለዋለች ተመልከቺ እህቴ ባለቤትሽ ላንቺ ምን አይነት ፍላጎት ይኖረዋል በዚህ ሁኔታሽ ምን አይነት የፍቅር ስሜትስ ያገኛል
እንዴትስ ያንቺ ታደርጊዋለሽ
በተለይ ከቤት ወጥቶ አስከ ሚመለስ አላህን በማይፈሩ የለበሱ መስለው ራቁታቸውን ሆነው ወደ ጀሃነም በሚጣሩ ተከቦ ከሸይጣንና ነፍስያ ጋር ታግሎ ወዳንቺ ሲመጣ ያን በሚያብስ ገፅታና ሐላል ፍቅር ተቀብለሽ ማስተናገድ ካልቻልሽ በሌባ ላለመዘረፍሽ ምን ዋስትና አለሽ
አው የቤት እመቤት ስትኾኚ እናት ነሽ
ይህ ማለት መዝረክረክ ማለት አይደለም
ይህ ማለት እቤት ውስጥ እራስን መጣል ማለት አይደለም
አንቺ ለልጅሽም እናት ነሽ
ለፍቅርሽም እናት ነሽ
ለቤትሽም እናት ነሽ እናት በሁሉም የእናትነት ድርሻዋ የተዋጣላት ናት
እቤት ውስጥ ያለብሽን ሃላፊነት ከመወጣትሽ ዋናውና ትልቁ የትዳር አጋርሽን የፍቅር ቱኩሳት ሳይበርድ ጠብቀሽ ማቆየትሽ ነው
ይህ ደግሞ ውስጥሽን አላህን በመፍራት ላይሽን ባለሽ ልብስና ጌጥ በማስዋብ ነው ይህን ካላደረግሽ ስትወጪ የምትዋቢው ለማን ነው ?


📐:::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::::📐

https://t.me/HijabNewWebta


#ያ_አላህ_እህቶቻችንን_ከዚህ_መጥፎ_ነገር_ጠብቅልን

እህቴ ሆይ! ጀነት አይገቡም ከተባሉት ውስጥ ነሽ ወይስ...???

ይህንን ፁሁፍ አንብበሽ ያለሽበትን ተመልከቺ!

አብዛኛው ቤት ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተነበዩት ትንቢት እየታየ ነው አላህ ካዘነላቸው ሲቀር!

ጉርድ ቀሚስ ለብሰናል ይላሉ ከጉልበታቸው በታች እራቁታቸውን ናቸው፣ ሙሉ ቀሚስ ለብሰናል ይላሉ ነገር ግን ከመወጣጠሩ የተነሳ የሰውነታቸውን ቅርፅ ሙሉ ለሙሉ ያሳያል፣ ሲላቸውም ደረታቸውና የወገባቸው ክፍል የማይሸፍንም ይለብሳሉ፣ ሻርፕ ለብሰናል ይላሉ ነገር ግን አስሬ የምትወርድ ወይም ለሳንፕል እዩልኝ በሚል መልኩ ይለብሳሉ። ሌላም ሌላም ጉድ የሚሳኝ አይነት ምናልባትም ሙስሊም ያልሆኑት ከሚለብሱትና ከሚያስከፈ መልኩ ለብሰው እያየን ነው።

እኔ እምልሽ እህቴ! ምን ፍለጋ ነው ቅጥ ያጣ አለባበስ የምትለብሺው?

☞ “#ደስታ ” እንዳትይኝ ሸሪዐዊ አለባበሳቸውን ጠብቀው ካንቺ በተሻለ ደስታን የሚጎናፀፉት ስንትና ስንት ናቸው!!

☞ “#ውበት” እንዳትይኝ ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ውበት ያለው ስርኣት ባለው ሸሪዓዊ አለባበስ ነው፡፡ እመኚኝ ይሄ ቅጥ ያጣ አለባበስሽ አያምርብሽም!!

“አይኔን ግንባር ያርገው” ካልሽ አትጠራጠሪ የውስጥሽን መታወር ነው ገሀድ ያወጣሽው፡፡ ምናልባት “ውበት እንደተመልካቹ ነው” እያልሽ እራስሽን ትሸውጂ ይሆናል፡፡ አልተሳሳትሽም! ውበት እንደተመልካቹ ስለሆነ ብልግናም ለባለጌዎች ያምራል!! አዎን ውበት እንደተመልካቹ ስለሆነ ጋጠ ወጥነትም ለጋጠ ወጦች ያምራል፡፡ ልክ ነሽ ውበት እንደተመልካቹ ስለሆነ ርካሽነትም ለርካሾች ያምራል!! ህሊናችን ሲገለበጥ አስተሳሰባችንም ምርጫችንም ይገለበጣል፡፡

☞ “#የህይወት_አጋር_ፍለጋ” ነው እንዳትይኝ፤ በዚህ አለባበስሽ አይናቸውን የሚጥሉብሽ ያለጥርጥር ርካሽ ወንዶች ናቸው፡፡ የህይወትሽ አጋር፣ ውሃ አጣጪሽ እንዲሆን የምትፈልጊው ርካሽ ወንድ ነውን?አላሁልሙስተዓን!!

እስኪ ውስጥሽን አዳምጪው፡፡ የወረደ አለባበስ የምትለብሽው የነቁ በሚመስሉሽ፣ “ስም” ያላቸው ዘፋኞች፣ ነጮች፣ ከሃዲዎች፣ ጋጠ ወጦችን ለመመሳሰል ነው ወይስ አይደለም? ከሆነ ነገ አላህ ፊት ያለምንም አስተርጓሚ እርቃንሽን ለምርመራ ትቆሚያለሽ!! ያኔ ምን ይውጥሻል???

በተለይ ደግሞ ጋጠ ወጦችን ተከትለሽ ከፈፀምሺው ጉዳዩ ምን ያክል አሳፋሪ ምን ያክል አሸማቃቂ እንደሚሆን ለአፍታም ቢሆን ከዚያ አስፈሪ ቦታ ላይ እራስሽን አቁሚና ታዘቢው፡፡ ነው ወይስ አንቺ ጀነትን አትፈልጊም? ታማኙና እውነተኛው፣ ከስሜታቸው የማይናገሩት ነብይ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አይነት ቅጥ ያጣ አለባበስ ላይ የወደቁ ሴቶችን ጀነትን ቀርቶ ሽታዋንም አያገኙም እያሉ ነው፡፡

ለዓለም እዝነት የታላኩት የነብያት መደምደሚያ የሆኑት መላክተኛ ምን አሉ መሰለሽ

"ሁለት ክፍሎች የእሳት ናቸው። እነሱንም አላየኃቸውም። አንዶቹ የከብት ጅራት የመሰለ አለንጋ ይዘው በዚያ የአላህን ባሮች የሚገርፉ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የለባሽ እርዘኛ(ለብሳ ያለበሰች)፣ ተዝንባዩች እና አዘንባዩች እራሳቸው እንደ ከሳ ግመል ሻኛ የሆኑ በፍፁም ጀነት አይገቡም፤ አረ እንዳውም ሽታውንም አያገኙም። የጀነት ሽታ ከዚያ ወደዚያ(ከረጅም ርቀት) የሚገኝ ሆኖ ሳለ።" (ሙስሊም 2128፣ አህመድ 440/2)

እኔ እምልሽ የኔ እህት! እጣ ፈንታሽ ይሄ እንዲሆን ትፈልጊያለሽን?!
አልፈልግም እንደምትይኝ አልጠራጠርም ስለዚህ ውድ እህቴ ለዲንሽ ዋጋ ስጪ!!

#አንተስ_ባል_የሆንከው_ወንድሜ! ባለቤትህ ወርዳና ተዋርዳ ስትወጣ ዝም ማለት ያንተ ባልነት ምኑ ጋር ነው?

#ውዱ_አባቴ_ሆይ! ልጅህ የአደባባይ መነጋገሪያ እስክትሆን ያንተ ሚና ምን እንደሆነ ረሰሀውን?

#አንተስ_ወንድሜ! እህትን መቆጣጠር ምንተሳነህ? ስህተት/ጥፋት እያየን ዝም ካልን አላህ እንዴት ነስሩን ይስጠን? የእስካዛሬው ይብቃ! ዛሬውኑ ቤታችንን በዲን እንፅዳ! አላህ ያግራልን!


@niqabisto
@niqabisto


የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ እውቀቶች
https://telegram.me/yenebiyattaric




💎ጉዞ ወደ ኒቃብ💎
ክፍል 5 ...

ምንም ያህል ነገሮች መጀመሪያ ቢከብዱም ግን በትዕግስት ካበቡ ቀላል እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም። ያኔ ኒቃብ ስለብስ የተቆጣችኝና የከለከለችኝ እናቴ ዛሬ ግን አጅ ነቢ ወንድ ሲመጣ ካየች ተሸፈኚ ምትለኝ እሷ ሆናለች። ድንገት እንኳ ሣያውቁ ሊገቡ ሲሞክሩ የምታስታውሰኝ እናቴው ሆናለች።አዎ ! ህይወት እንዲህ ናት ትላንት ሰዎች የጠሉብህን ማንነት ከጊዚያት በኋላ አምነው ተቀብለው ታያለህ ለነገሩ የሚባለውስ ከአላህ ጋር ሁን ሁሉም ነገር ካንተ ጋር ይሆናል አይደል!!

ክረምት በጋን አሮጌው አመት አዲሡን ሊተኩ ቀርበዋል። የሁለተኛ አመት የትምህርት ፕሮግራም ተጀመረ። ልክ እንዳለፈው አመት በሂጃቤ ትምህርቴ ቀጥሏል። ዘንድሮ ለየት በሚል ሁኔታ ኮሌጁ ውሥጥ አዳዲስ ሙተነቂቦችን እያስተዋልኩ ነው። ደግሞ ምን ይሏቸው ይሆን !?
ብዙ ኮሌጆች ላይ በጣም የሚአጅበኝ አንድ ነገር አለ ካፊር ሴቶች እርቃናቸውን እያዩ ሊማሩ ሳይሆን ሊያማሉ መስለው እየመጡ እየተመለከቱ ግን ጂልባቢስትና ኒቃቢስት ሴቶችን ሲያዩ የሚያንገሸግሻቸው ነገር ነው ። ሀታ ጠርተው ይሄ ምንድነው ብለው እስከመጠየቅም የሚደርሡበት ጊዜ አለ። እኔ የምማርበት ክፍል ውስጥ የኮሌጁ ካውንስል የሆነች ሙሥሊም እህቴ አለች ብዙ ጊዜ መረጃዎችን ከሷ እቀበልም ነበር አንድ አስተማሪ ሙተነቂብ ተማሪ አሥተምር ሲባልም አላስተምርም ብሎ እምቢታውን መግለፁንም ነግራኝ እንደነበር አስታውሳለው።
ይህ ሁሉ ጋጋታ ምንድነው?? የኒቃብን ምንነትና ትርጉም አለማወቅ ይሆን ወይስ እኛ ይህን ግንዛቤ ከመስጠት ወደኋላ ማለታችን?? …………

ኢንሻ አላህ በሁለት ተከታታይ ክፍሎች ታሪኩ ይጠናቀቃል።
ሀሳብና አስታየቶን @BintMama_Bot ላይ ያጋሩን


የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ ትምህርቶች dan repost
ኒ ካ ህ ፣ሰ ር ግ፣ኹ ሉ እ እና ፍቺን የተመለከቱ ሸሪአዊ ድንጋጌ ዎች

ክፍል 5️⃣
ከባለፈው የቀጠለ……

15 | P a g e

6. ዝሙተኛ ሴትን ከዝሙቷ እስክትቶብት ድረስ ማግባት አይፈቀድም ዝሙተኛ ወንድንም እንደዚሁ
ከዝሙቱ እስኪቶብት ድረስ ልታገባው አይፈቀድላትም። አላህ (سبحانه وتعالى (እንዲህ ይላል

الزَّانِي لَا يَنكِحُ إِلَّا زَانِيَةً أَوْ مُشْرِكَةً وَالزَّانِيَةُ لَا يَنكِحُهَا إِلَّا زَانٍ أَوْ مُشْرِكٌ ۚ وَحُرِّمَ ذَٰلِكَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ

[ ሱረት አል-ኑር፣ - 3 ]

{ዝሙተኛው ዝሙተኛይቱን ወይም አጋሪይቱን እንጂ አያገባም፡፡ ዝሙተኛይቱንም ዝሙተኛ ወይም አጋሪ
እንጂ አያገባትም፡፡ ይህም በምእምናን ላይ ተከልክሏል፡፡}
36
በዚህ አንቀጽ ላይ በግልጽ እንደምንመለከተው ይህ (ዝሙተኛን ማግባት) በምእመናኖች ላይ እርም
እንደተደረገ ተነግሯል
ባሪያን ስለማግባት ያለን ብይን ያላመጣሁት በዚህ ዘመን ላይ እምብዛም ባሪያዎች ስለሌሉ ጽሁፎች
እንዳይበዙ በማሰብ ነው።
 እነዚህ የተዘረዘሩት ሰባቱ ደግሞ የተከለከባቸው ሰበቦች እስካልተወገዱ ድረስ ሊያገባቸው ማይችላቸው አካላት
ናቸው። እነዚህ ግን አጅነብይ ይሆናሉ ምክንያቱም የተከለከለበት ሰበብ ሲወገድ ሊያገባቸው ይፈቀዱለታልና ነው።
ለአንድ ወንድ አጅነብይ ማይሆኑት መቼም ቢሆን ሊያገባቸው ማይችላቸው ሴቶች ናቸው።በመሆኑም የሚስት እህት
አጅነብይ ናት ለእህቷ ባል ሂጃቧን መገለጥም ይሁን እሱን መጨበጥ አይፈቀድላትም። ልክ ለባሏ ወንድም
መገለጥም ይሁን እሱን መጨበጥ እንደማይፈቀድላት ሁሉ።

1.6 ክርስቲያን ና አይሁድ ሴቶችን ስለማግባት

ቁርአን አህለል ኪታብ(መጽሀፍ የተሰጡት) የሆኑ ሴቶችን ስለማግባት በሱረተል ማኢዳ ላይ ሲናገር እንዲህ ይላል

الْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ الطَّيِّبَاتُ ۖ وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَّهُمْ ۖ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الْمُؤْمِنَاتِ وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَا آتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِي أَخْدَانٍ ۗ
{ ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፡፡ የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ
ነው፡፡ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች
ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን
በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡}
37
አህለል ኪታብ (መጸሀፍ የተሰጡት) የሚባሉት ደግሞ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ናቸው።
ከቁርአን አንቀጹ ጉልህ መልእክት የምንረዳው ቁም ነገር ከመኖሩ ጋር በጉዳዩ ላይ አንዳንድ መብራራት አለባቸው ብዬ
ማስባቸው ነጥቦች ስላሉ የተወሰነ ላብራራው ወደድኩ። በመሆኑም ኡለሞች በሚጠቅሷቸው ዝርዝር ነጥቦች ላይ
ተንተርሼ ለማብራራት እንዲቀለኝ በማሰብ ርእሱን ለሁለት ከፈልኩት እነሱም
1. በሙስሊም ሀገር እየኖረ አህለል ኪታብን ማግባት
2. በካፊር ሀገር እየኖረ አህለል ኪታብን ማማግባት

ከዚህ በታች ማብራሪያ ነው ከላይ ለተፃፉት ቁጥሮች👇🏻__________________
36 አኑር 3

37 ማኢዳ 5
____
.@yenebiyattaric
@yenebiyattaric






NESIHA TV ነሲሓ ቲቪ dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ሰደቃ ገንዘብን አያጎድልም
@nesihatv


‏قال العلامة صالح الفوزان -حفظه الله-:

"ليس عندنا انتماء إلا لأهل السنة والتوحيد"

📚الأجوبة المفيدة - س103




ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
~~~~~~~~~~~~
↩️‏سنن يوم_الجمعة

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መውጣት
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

255

obunachilar
Kanal statistikasi