ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ dan repost
#ደመራ፦ ደመረ ከሚለው መነሻ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መሰብሰብ ማከማቸት እንደማለት ነው፡፡
የመስቀል በዓል የሚከበርበት ምክንያት እንዲህ ነው፦ ክብር ይግባውና የምስጋና ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ አርብ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ለ5500 ዘመን በጥፋቱ ምክንያት ሞት ተፈርዶበት በመከራ፣ በጭንቅ፣ በሀዘን
እና በስቃይ ይኖር የነበረውን የአዳምን ዘር በሙሉ ከሞት ወደ ሕይወት አሸጋገረው። ጌታ በመስቀል ላይ ሞቶ ከተነሣ በኋላ ሕሙማን መስቀሉን እየዳሰሱ በመስቀሉ እየታሹ ይፈወሱ ነበር። በዚህም ተአምራት እየተሳቡ ብዙዎች ክርስቲያን ሆኑ፤ ይህን ያዩ አይሁድ በቅናት ተነሡ፤ ተማክረውም ለምን ይህን መስቀል አንደብቀውም አሉ፤ ከዚያም መስቀሉን በአንድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ ጣሉት። በየቀኑ የአካባቢው ኗሪ ሁሉ ቆሻሻ ስለሚጥልበት ያ
ቦታ አንድ ትልቅ ጉብታ ሆነ። የከተማዋ መልክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ስለተለወጠ ጌታችን የተሰቀለበት መስቀል ወዴት እንዳለ ጠፋ። በዚህም ምክንያት ከ300ዓመታት በላይ መስቀሉ የት እንዳለ ተዳፍኖ ቀርቷል።
እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር ጊዜ አለውና በዐራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የንጉሥ ቆስጤንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ ይህን ታሪክ ትሰማ ነበርና መስቀሉን አስቆፍራ ለማውጣት
ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘች። ነገር ግን በቀላሉ ማግኘት ተሣናት፤ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃዱ ነበርና አንድ ኪሪያኮስ የሚባል
አረጋዊ በጠቆማት መሠረት መስከረም 16 ቀን ደመራ አስደምራ ዕጣን አስጭሳ በእግዚአብሔር አመልካችነት የተቀበረበትን ቦታ አገኘች። በዚህም መሠረት
መስከረም 17 ቀን ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን ተገኝቶ ወጣ። ኋላም ለመስቀሉ መታሰቢያ አሠርታ ቅዳሴ ቤቱ መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን አከበረች።
እንኳን አደረሳቹ 🙏