2.ስለ ሁሉም ነገር ተሳስታችኋል (እኔም)
በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ሳለሁ ለሁሉም ሰው፣ ለምንም ነገር ግድ እንደሌለኝ እናገር ነበር፡፡ እውነቱ ግን በጣም ለብዙ ነገር ግድ ያለኝ መሆኔ ነበር፡፡ ሌሎች ሰዎች እኔ ሳላውቅ የእኔን አለም ያዙበት ነበር፡፡ ደስታ እጣ ፈንታ እንጂ ምርጫ እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ ፍቅር ዝም ብሎ የሚከስት እንጂ የምትሰራው እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ አሪፍነት ራሳችን የምንፈጥረው ሳይሆን ከሌሎች ሰዎች የምንማረው እንደሆነ አስብ ነበር፡፡
ከመጀመሪያ የሴት ጓደኛዬ ጋር ሳለሁ እስከ ዘላለም አብረን እንደምንሆን አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ግንኙነታችን ሲያበቃ፣ ስለ ሴቶች በፍፁም በድጋሚ በተመሳሳይ መንገድ እንደማይሰማኝ አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ለሴት እንደገና ያን አይነት ስሜት ሲሰማኝ ደግሞ ፍቅር ብቻ በቂ እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ግን እያንዳንዱ ግለሰብ “በቂ” የሚለውን መወሰን እንዳለበትና ፍቅር ደግሞ እንዲሆን የፈቀድንለትን ሊሆን እንደሚችል ተረዳሁ፡፡
በመንገዴ በየትኛውም ደረጃ ተሳስቼ ነበር፡፡ ስለሁሉም ነገር ተሳስቼ ነበር፡፡ ህይወቴን ሙሉ ስለ ራሴ፣ ስለ ሌሎች፣ ስለ ማህበረሰቡ፣ ስለ ባህል፣ ስለ አለምና ስለ ሁሉም ተሳስቼ ነበር፡፡
እና በቀሪው ህይወቴም ሁኔታው ያው መሆኑ እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ፡፡ የአሁኑ እርማት የባለፈው እርማት የነበረውን እያንዳንዱን ግድፈትና ስህተት ወደ ኋላ ተመልሶ ሊመለከት እንደሚችል ሁሉ፣ የወደፊቱ እርማትም አንድ ቀን የአሁኑን ግምቶችና ተመሳሳይ ግድፈቶችን ወደኋላ የሚመለከት ይሆናል፡፡ እና ያ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም አድጌያለሁ ማለት ነው፡፡
ደጋግሞ ስለመውደቅ የሚገልፅ የማይክል ጆርዳን ጥቅስ አለ፡፡ እና ስኬታማ የሆነውም ለዚያ ነው፡፡ ጥቅሱ “ስለ ሁሉም ነገሮች ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ተሳስቻለሁ ህይወቴ የተሻሻለውም ፤ለዚያ ነው” ይላል፡፡
ትክክል ህግ ወይም ፍፁም የሆነ የፖለቲካ ዘይቤ የለም፡፡ ያለው ነገር የአንተ ተሞክሮ ለአንተ ትክክል የሚሆነው የቱ እንደሆነ ያሳየህ ብቻ ነው፡፡ እና በዚህም ላይ ያ ልምምድ ራሱ ምናልባት በሆነ ሁኔታ ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ እና እኔ፣ አንተና ሁሉም ሰው የተለያዩ የግል ፍላጎቶች፣ የግል ታሪኮችና የህይወት ሁኔታዎች ያሉን በመሆኑ ሁላችንም ስለ ህይወታችን ትርጉምና እንዴት መኖር እንደሚገባን ወደተለያዩ “ትክክል” ወደምንላቸው መልሶች መምጣታችን የማይቀር ነው፡፡የእኔ ትክክለኛ መልስ አመቱን ሙሉ ብቻዬን ወደተለያዩ ቦታዎች መጓዝ፣ የተረሱ ቦታዎች ውስጥ መኖርና በራሴ ቀልዶች መሳቅ ያጠቃለለ ሊሆን ይችላል ወይም ቢያንስ እስከቅርብ ጊዜ የነበረኝ ትክክለኛ መልስ ይህ ነው፡፡ ያ መልስ ይለወጣል፣ ያድጋል፤ ምክንያቱም እኔም እያደግኩና ብዙ ልምዶች እያዳበርኩ ስመጣ እለወጣለሁ፣ አድጋለሁ፡፡ ምን ያህል የተሳሳትኩ መሆኔን እየሸራረፍኩ በየቀኑ ስህተቶቼን እያሳነስኩ እያሳነስኩ እመጣለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ሙሉ “ትክክል(ፍፁም)” ስለመሆን አጥብቀው ይጨነቃሉ፡፡ ግን በመጨረሻ አይሆኑም፡፡
አንዲት ሴት ያላገባችና ብቸኛ ናት፡፡ እናም አጋር ትፈልጋለች፡፡ ነገር ግን ከቤት አትወጣም፣ ግንኙነት ለመመስረት ምንም ነገር አታደርግም፡፡ አንድ ሰው ደግሞ በጣም ጠንክሮ እየሰራ በመሆኑ የደረጃ እድገት እንደሚገባው ያምናል፤ ግን ያንን በፍፁም ለአለቃው ተናግሮ አያውቅም፡፡
እነዚህ ሰዎች ሽንፈትን፣ አይሆንም መባልን እንዲፈሩ ተነግሯቸዋል ማለት ነው፡፡
ነገር ግን ያ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው አለመፈለግ ይጎዳል፡፡ ሽንፈት ያስጠላል፡፡ ግን ለአመታት ለህይወታችን ትርጉም የሰጡ እሴቶች አድርገን የያዝናቸው ለመጠየቅ የመፍራት ወይም ነገሮችን የመተው እርግጠኝነቶች አሉ፡፡ ያቺ ሴት ከቤት ወጥታ ከወንዶች ጋር መገናኘት ስለ ራሷ ተፈላጊነት ያላትን እምነት ለመጋፈጥ እንድትገደድ ያደርጋታል፡፡ ያ ሰውም እድገት መጠየቅ ይፈራል፤ ምክንያቱም ባለው ክህሎት ራሱን በእርግጥም ዋጋ ያለው አድርጎ ከማመኑ ጋር መጋፈጥ ይጠበቅበታል፡፡
ስለዚህ እነዚያን እምነቶች ፈትኖ እውነቱን ከማወቅ ይልቅ ሰዎች ማራኪ ሆነህ ከማያገኙህ እና ተሰጥኦህን ሳያደንቁልህ ቢቀሩ ከሚሰማህ የሚያሳምም እርግጠኝነት ይልቅ መቀመጥ ቀላል ይሆናል፡፡እንደዚህ አይነት እምነቶች በኋላ ላይ ደስታችንንና ስኬታችንን በመያዣነት ይዘው አሁን መካከለኛ የሆነ ምቾት እንዲሰጡን የተነደፉ ወይም የተሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ አስቸጋሪ የረጅም ጊዜ ስልቶች ናቸው፡፡ ሆኖም እነርሱ ላይ ተጣብቀናል፡፡ ምክንያቱም ትክክል እንደሆንን እንገምታለን፡፡ ምክንያቱም ምን ሊከሰት እንደሆነ አስቀድመን እንደምናውቅ እንገምታለን፡፡ በሌላ አነጋገር ታሪኩ በምን አይነት ሁኔታ እንደሚያልቅ አስቀድመን እንገምታለን ማለት ነው፡፡
እርግጠኝነት የእድገት ጠላት ነው፡፡ ምንም ነገር ሆኖ እስኪገኝ ድረስ እርግጥ አይደለም፡፡ የዚያን ጊዜም እንኳን አከራካሪ ነው፡፡ የእሴቶቻችንን ፍፁም ያለመሆን በሚያጠራጥር አይነት መቀበል እየሆነ ላለው የትኛውም እድገት አስፈላጊ የሚሆነው ለዚያ ነው፡፡
ለእርግጠኝነት ጥረት ከማድረግ ይልቅ፣ ስለራሳችን እምነቶች፣ ስለራሳችን ስሜቶች እዚያ ደርሰን ራሳችን እስክንፈጥረው ድረስ የወደፊቱ ህይወታችን ለእኛ ስለያዘው ነገር ምንነት ሁሉ የማያቋርጥ ጥርጣሬ ሊኖረን ይገባናል።ሁልጊዜ ትክክል መሆናችንን ከማየት ይልቅ፣ ሁልጊዜ እንዴት የተሳሳትን እንደሆንን (ያለ ጥፋተኝነት ስሜት) መፈለግ አለብን።ምክንያቱም መሳሳትን ማወቅ ወደ መለወጥ ወደ መቻል ይወስደናልና።
📚The subtle art of giving a f*ck
Mark Manson
@zephilosophy