"የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንኳንስ ውለታን መክፈል፣ ራሱን ውለታንም አታውቅም።"
ልደቱ አያሌው
የእኛዋ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የ1960ዎቹ የእነ ጥላሁን ግዛው ኢትዮጵያ፣ ወይም የ1960ዎቹ የእነ ኒኖይ አኲዪኖ ፊሊፒንስ፣ወይም የ2010ቹ የእነ መሐሙድ ቡዓዚዝ ቱኒዚያ እንዳልሆነች ብዥታ የለኝም። የእኛዋ ኢትዮጵያ የታጋይ መስዋዕትነት ተራ እና “ደመ ከልብ” ሆኖ የሚቀርባት ኢትዮጵያ ናት። በተቃራኒው የሚሊየን ሕዝብ ደም በእጃቸው ላይ ያለ ፖለቲከኞች ከተጠያቂነት ነፃ ሆነው በድሎትና በክብር እንቅልፍ እየተኙ የሚኖሩባት አገር ነች ኢትዮጵያ።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንኳንስ ውለታን መክፈል፣ ራሱን ውለታንም አታውቅም። አገዛዝን በፀጋ አንቀበልም ብለው የሚታሰሩና የሚገደሉ ዜጐች አርዓያ፣ አርበኛና ባለውለታ ተደርገው ከመታየት ይልቅ ሰላማዊ ትግልን ለማጣጣል ማስፈራሪያና መፈራረጃ ተደርገው የሚቀርቡባት አገር ነች። በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙ እና በትግሉ ሒደት ተገለው ሜዳ ላይ የተጣሉት “ሰማዕታት” እኛን ለማጀገን የሚወሱ አርዓያዎች መሆን ሲገባቸው፣ በተቃራኒው እኛን በሰላማዊ ትግል ተስፋ ለማስቆረጥ የሚቀርቡ ማስፈራሪያዎች ሆነዋል። የእኔም የነገ ዕጣ-ፈንታ ከዚህ የተለየ የሚሆን አይመስለኝም። “ስንመክረው አልሰማ ብሎ ነው፣ ይገባዋል!” ብባል ብዙም አይደንቀኝም።
በአጠቃላይ በራሳችን የህይወት ዘመን ደጋግመን እንዳየነው አገራችን አስመሳዮች፣ ጥቅመኞች፣አላዋቂዎች፣ ክፉዎችና ከፋፋዮች ባለ ክብርና ባለ ዝና ሆነው እየተሞካሹ የሚኖሩባት ነች።
ዛሬ ላይ የሕዝቡን አይንና ጀሮ የተቆጣጠሩትና ድጋፍ የሚጐርፍላቸው ሰዎች የሕዝብን ጊዜያዊ ስሜት በመኰርኰር የተካኑ ብልጣ-ብልጥ ብሔርተኞችና ጥቅመኞች ናቸው። በአንፃሩ አዋቂዎችና ሀቀኞች፣ አገርና ሕዝብ ወዳዶች፣ ጨዋዎችና ሰላማዊ ዜጐች ተንቀውና አንገታቸውን ደፍተው የሚኖሩባት የጉድ አገር ነች- ኢትዮጵያ።
@zephilosophy