"ከመከራችሁ የሚበዛው ራሳችሁ የመረጣችሁት ነው።"
ደራሲ- ካህሊል ጂብራን
አንዲትም ሴት ተናገረች እንዲህም አለችው። " ስለ ስቃይ ንገርን?"
እሱም አለ ፦
"ስቃያችሁ የማስተዋላችሁ ማቀፊያ ሽፋን (ቅርፊት) መሰበር ነው...
"በፍራፍሬዎች ውስጥ ያለው እንደ ድንጋይ የጠጠረ ፍሬ ልቡ ተከፍቶ በፀሀይ ውስጥ ይቆም ዘንድ የግድ መሰበር እንዳለበት ሁሉ እናንተም ስቃይን ማወቅ ይገባችኋል...
"ልባችሁንስ በህይወታችሁ የእለት ተዕለት ተዐምራት ውስጥ በአስደሳች ሁኔታ ልታቆዩት ይቻለችኋልን? ስቃያችሁስ ከደስታችሁ ያነሰ አስደናቂ ይመስላችኋልን?
"በእርሻ ማሳዎቻችሁ ላይ የሚፈራረቁትን ወቅቶች ሁልጊዜ በፀጋ እንደምትቀበሉዋቸው ሁሉ የልቦቻችሁን ወቅቶችም ወቅቶች በፀጋ መቀበል ይኖርባችኋል። የሀዘናችሁን የክረምት ወራትም በፀጥታ ትጠብቃላችሁ...
"ከመከራችሁ የሚበዛው ራሳችሁ የመረጣችሁት ነው። በውስጣችሁ ያለው ሀኪምም የራሳችሁን ህመም የሚፈውስበት መድሀኒት አለው። ስለዚህ ሃኪሙን እመኑት እና መራራ መድሃኒቱንም በፀጥታ ተረጋግታችሁ ተጎንጩት...
@zephilosophy