የሰው ልጅ በተፈጥሮው ስግብግብና ራስ ወዳድ በመሆኑ ቆፍጠን ያለ መሪ ያስፈልገዋል
ምንጭ ፦ ፍልስፍናና ዘላለማዊ ጥያቄዎቹ
ፀሀፊ፦ ቤተልሔም ለገሰ
ፍልስፍና ከሚያነሳቸው አበይት ጉዳዮች አንዱ ፖለቲካ ነው፡፡ ፖለቲካን ስናነሳ ደግሞ አስቀድመን ከምንጠይቃቸው ጥያቄዎች መካከል ‹‹አንድ ሀገር ብሎም መንግስት እንዴት ተመሰረተ? መንግስት ከመኖሩ በፊት ሰዎች እንዴት ይኖሩ ነበር? አኗኗራቸውስ ፍትሀዊ ነበርን? የመንግስት መቋቋም ለማህበረሰቡ ምን ፋይዳ አስው? የሚሉና የመሳሰሉት ይገኙበታሉ፡፡ እኛም የአንደ ሀገር መገለጫ ከሆኑት ውስጥ ዋነኛ ሚና ስለሚጫወተው መንግስት (goverment) የዚህንም ተቋም ምንነትና ስለ አጀማመሩ የተሰነዘሩ ፍልስፍናዊ መከራከሪያ ሀሳቦችን እያየን እንዘልቃለን ...
አንዲት ሀገር በመንግስት እንድትተዳደር መነሻ ሀሳብ የሆነው የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር (social contract theory) ሲሆን ይህም ውል 'መንግስት ከመፈጠሩ በፊት ሰዎች ይኖሩበት የነበረው የተፈጥሮ ስርዓት አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ ሰላምና መረጋጋትን ማረጋገጥ ስለማይቻል የበላይ አካል መፈጠር አለበት› ከሚል ሀሳብ የመነጨ እንደሆነ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ታዲያ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ፍልስፍናዊ መከራከሪያ ሀሳቦች ሲያቀርቡ ከነበሩት መካከል ዋነኞቹ ቶማስ ሆብስ (Thomas Hobbes) ጆን ሎክ (john locke) እና ሩሶ (Rousseau) ይገኙበታል። እስኪ የነዚህን ፈላስፎች ሀሳብ በዝርዝር እንመልከት. ..
ቶማስ ሆብስ እ.አ.አ ከ1599-1679 ይኖር የነበረ እንግሊዛዊ ፈላስፋ ሲሆን በእርሱ ዘመን ተከስቶ የነበረው የእንግሊዝ እርስ በርስ ጦርነት በስራዎቹ ላይ ተጽእኖ እንዳሳደረ ይታመናል፡፡ እናም ይህ ጦርነት የቱን ያህል ስጋት ላይ እንደጣለው ለመግለጽ በአንድ ወቅት ‹‹እኔና ፍርሀት መንታ ሆነን ተፈጠርን›› ( I and fear were born twins) ሲል ተናግሯል፡፡
ሆብስ የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ያደረገው 'የሰው ተፈጥሮዊ ባህሪይ' እንደሆነ ይናገራል፡፡ እንደሱ አባባል ‹‹አብዛኛው ሰው የሚመራው ነገሮችን እያሰበና እያገናዘበ ሳይሆን ይልቁንም በስሜትና በራስ ወዳድነት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎችን በፍርሀትና በጦርነት ስጋት ውስጥ እንዲዘፈቁ ያደርጋል፡፡ ስለዚህም ሰዎች አንድ ወጥ የሆነ የማህበራዊ ውል ስምምነት ኖሯቸው ጠንካራ መንግስት ካላቋቋሙ በስተቀር የአበዛኛው ሰው ቅጥ የለሽ ስግብግብ ባህሪይና ዝና ወዳድነት የለት ተዕለት ኑሮውን በአስተማማኝ ሁኔታ መምራት እንዳይችልና ህይወቱም ፍጹም አስቀያሚና ጭካኔ የተሞላ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡››
‹‹መንግስት›› የሚባለው ተቋም የመኖሩ አስፈላጊነትና ፋይዳ ይህ ከሆነ ዘንድ፣ የዚህ መንግስት የሚባል ተቋም ስልጣኑ አስከምን ድረስ ነው? ለሚለው ጥያቄ ሆብስ፤ ሰዎች ለሚመሰርቱት መንግስታዊ ተቋም ተፈጥሮአዊ መብቶቻቸውን ሙሉ በሙሱ አሳልፈው መስጠት እንደሚገባቸውና ይህ የመረጡት አካል ከሁሉም በላይ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ማዘዝ እንደሚገባው ብሎም ስልጣኑ ገደብ የለሽ መሆን እንዳለበት ያስረዳል፡፡ በዚህም እ.አ.አ በ1651 ለህትመት ያበቃውና በባህር እንስሳት ገዢ የተሰየመው 'ዘ ሴቪያታን› የተሰኘው መጽሀፍ ሆብስ ስሰው ልጅ ያለውን ጨለምተኛ አስተሳሰብ ያሳበቀበትና በብዙ ፖለቲካ ተንታኞች ዘንድም ፍጹማዊ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ስርዓት አቀንቃኝ' ተብሎ እንዲታማም አድርጎታል፡፡
በአንጻሩ እ.አ.አ ከ1632-1704 የኖረውና ለዘመናዊ የፖለቲካ ስርዓት መፈጠር ፈር ቀዳጅ እንደሆነ የሚነገርለት አንግሊዛዊ ፈላስፋ ጆን ሎክ እንደ ሆብስ ለሰው ልጅ ያለው አመለካከት ጨለምተኛ ሳይሆን የሰው ልጅ በተፈጥሮው ደግና ሩህሩህ እንዲሁም በጎና ቅን አሳቢ እንደሆነ ያምናል፡ ፡ እንደሱም አባባል ሰዎች መንግስት ባልነበረበትና በተፈጥሮ ስርዓተ ህግ ስር በሚተዳደሩበት ወቅት በነጻነትና በራሳቸው ፍላጎት የመመራት መብት ስለ ነበራቸው የሌላውን ሰው ህይወትም ሆነ ንብረት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ፈጽሞ አያደርጉም፡፡ ‹‹ነገር ግን . . ›› ይላል ሎክ ‹‹ . ነገር ግን ማንም አብዛኛው ሰው ነገሮችን በማመዛዘን የሚኖር ፍጡር ቢሆንም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ሁኔታዎች ሰውን ወደ ጸብ አጫሪነት ሊያመሩት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የሰው ልጅ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላሙን ለማረጋገጥ እንዲያስችለው ተፈጥሮ የቸረችውን ነጻነቱን በመስጠት ማህበራዊ ውል ስምምነት እንዲፈጽም ማህበራዊ ተቋም (social institution) እንዲመሰርቱ ይመክራል፡፡
ሎክ ሀሳቡን ሲቀጥልም ‹‹በማህበራዊ ውል ስምምነት የሚመሰረተው ማህበራዊ ተቋም (መንግስት) ውስን የሆነ ስልጣን አንዳለውና ይህም ተቋም በህግ የበላይነት ስር የሚተዳደር እንደሆነ በዜጎች መሰረታዊ መብቶች ውስጥም ጣልቃ መግባት እንደሌለበት ... የዜጎችን መብት የሚሸራርፍ ድርጊቶችን ቢፈጽም ህዝቡ የሰጠውን ስልጣን የመገፈፍ መብት እንዳለው ይናገራል፡፡ ታዲያ የዚህ ታላቅ ስልጣን ባለቤት ሊሆን የሚችለው በህዝቡ ይሁንታ የተመረጡ ሰዎች የሚያቋቁሙት የህገ አዉጪ አካል ሲሆን ተጠሪነቱም በቀጥታ ለህዝቡ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥቶ ይናገራል፡፡
✍ ይቀጥላል✍
@zephilosophy