... ✍ ካለፈው የቀጠለ
የጆን ሎክ የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር ንድፈ ሀሳብ በዘመናችን ውስጥ የዳበረ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን እያራመዱ ለሚገኙት እንደ አሜሪካና ምእራብ አውሮፓ ላሉ ሀገራት ፈር ቀዳጅ ሆኖ የሚጠቀስ ፍልስፍና እንደሆነና የዘመናዊ ሊበራል ዲሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም ጠንሳሽ እንደሆነም ተንታኞች ይናገራሉ፡፡
እንደ ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኝ ሀሮልድ ላስኪ (Harold Laski) አገላለጽ ‹‹የጆን ሎክ ንድፈ ሀሳብ በእንግሊዝ የፖለቲካ ታሪክ ሙስጥ ቋሚ አሻራ ትቶ ያለፈ በዚህ ላይ ደግሞ በአሜሪካ ፓለቲካ ስርዓት ጠንሳሾች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ከማሳደሩም በላይ የአሜሪካ ህገ መንግስት የተወሰኑ አንቀጾች ቃል በቃል ከእርሱ ስራዎች የተገለበጡ ናቸው›› በማለት ይናገራል፡፡
ቀጥለን የምናየው ከ1712-1778 ድረስ የኖረውን ፈረንሳዊ ፈሳስፋ ጂን ጃኩስ ሩሶ (Jean Jacques Rousseau) ን ሲሆን ይህም ፈስስፋ ከቶማስ ሆብስና ጆን ሎክ ቀጥሎ ከመንግስት ስርዓት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ፍልስፍናዊ የመከራከሪያ ሀሳቦች ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳደረ እንደነበርም ይነገርለታል፡፡ ታዲያ ይህ ፈላስፋ በስራዎቹ ታሪክ የማይረሳቸውን የ1789ኙን የፈረንሳይ አብዮት በማነሳሳትና የህዝባዊ ሉአላዊነት ንድፈ ሀሳብ (the theory of popular soveneity ) በማመንጨት ጉልህ ሚና የተጫወተ ሰው ነው፡፡
ጂን ጃኩየስ ሩሶ እንደ ሎክ 'የሰው ልጅ በተፈጥርው ቅንና ሩህሩህ መሆኑን› ቢያምንም ነገር ግን እነዚህ መልካም ባህሪያት በግል ሀብት መፈጠርና በህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት ሰውን ራስ ወዳድ እንዲሆንና በሌሎች ዘንድም ገዝፎ ለመታየት አንዲጥር ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ አላስፈላጊ ወደ ሆነ የርስ በርስ ፉክክር ውስጥ ተገብቶ ሰላም እንዲደፈርስና መሰረቱም አንዲናጋ ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡ እናም የማህበረሰቡን ሰላምና መረጋጋት ለማስከበር ሰዎች በስምምነት ማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር ኖሯቸው አንድ የፖለቲካ ተቋም መመስረት
እንደሚገባቸው ይገልጻል፡፡
የሩሶ የማህበራዊ ውል ስምምነት ንድፈ ሀሳብ ከቶማስ ሆብስ ጋር ተመሳሳይ የሚያደርገው ሰዎች ለሚያቋቁሙት የበላይ አካል ነጻነታቸውን አሳልፈው መስጠት እንደሚገባቸው ማመኑ ሲሆን በአንጻሩ ‹‹ከፍተኛ ስልጣን የሚይዘው ህብረተሰቡ ነው›› የሚለው ሀሳቡ ከጆን ሎክ ጋር ቁርኝት እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡ .
አንዳንዶች የሩሶ የበላይ ተቋም (higher institution) አወቃቀርና አደረጃጀት ወጥነት የጎደለውና ብዥታን የሚፈጥር (para- doxical) ነው ሲሱ ይተቹታል፡፡ ስአብነት ያህል እስቲ the general will የሚለውን ሀሳብ ለመረዳት እንሞክር፡፡
እንደ ሩሶ እምነት በማንኛውም ህብረተሰብ ዘንድ ሁለት ፍላጎቶች ይንጸባረቃሉ፡፡ ከነዚህም አንደኛው በህብረተሰቡ ያለ ልዩነት በጋራ የሚስማሙባቸውና የሚፈቅዱአቸው ፍላጎቶች (the will of all ) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከጋራ ፍላጎቶች ጋር የማይስማሙ የእያንዳንዱ ሰው ግላዊ ፈቃድ ድምር (the general will) የሚባለው ነው፡፡ ታዲያ የአንድ ህብረተሰብ የጋራ ደህንነት (common good) ሊረጋገጥ የሚችለው የእያንዳንዱን ልዩነት በማጥበብ ለጋራ አላማ የሚል ስራ በመስራትና ለውጥ ለማምጣት በመታገል መሆን እንዳለበት ያስገነዝባል፡፡ ይህም የሚሆነው የሚመሰረተው ተቋም በግለሰቦች ልዩነት ድምር ላይ የተገነባ ስራ ሲሰራ ይሆናል፡፡
የሩሶ የማህበራዊ ውል ስምምነት ቀመር ሁለት አበይት አደረጃጀት ሲኖረው አንደኛው ሰዎች ነጻነታቸውን ሙሉ ለሙሉ አሳልፈው በመስጠት የሚያቋቁሙት ማህበራዊ ተቋም (community based institution) ሲሆን ሁለተኛ ለዚህ ማህበራዊ ተቋም ተጠሪ ሆኖ የሚያገለግለው አካል መንግስት (government) ይሆናል፡፡ በነዚህ አደረጃጀቶች ውስጥ የህዝብ ስልጣን ከፍተኛና ፍጹም ስለሆነ በማንኛውም መልኩ ሊነጣጠስ ሊከፋፈል፣ ሊገረሰስ እንዲሁም ሊወድቅ አይችልም፡፡
የሩሶ የማህበረሰብ ስልጣን ልክ እንደ ሆብስ ምሉዕ በመሆኑ ለግለሰብ ቅሬታዎችና ፍላጎቶች ቦታ የማይሰጥ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደ ሩሶ ግንዛቤ ይህ አካል ህብረተሰቡ በጋራ የተስማማበትና የመምራት ነፃነቱንም ሙሉ ለሙሉ የሰው አካል በመሆኑ የሁሉንም ሰው ፍላጎት የማንጸባረቅ ውስጣዊ (በውስጠ ታዋቂነት) ስምምነት እንዳለው ስለሚቆጠር ነው፡፡ የዚህ ማህበረሰባዊ ስልጣን ከፍተኛው አካል ህግ አውጪ (legislative body) ሲሆን እያንዳንዱ የመንግስት ተግባራትና ክንውኖች በህግ የተገደቡ በመሆናቸው ለህዝቡ ሰላምና መረጋጋት በመፍጠር በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ... ይላል ሩሶ
ታዲያ የጆን ሎክ ፖለቲካዊ ፍልስፍና በአሜሪካ ህገ መንግስት (American Constitution) ተጨባጭ መነሻ እንደሆነ ሁሉ የሩሶም ማህበራዊ ዉል ስምምነት ቀመር ደግሞ ለፈረንሳይ ህገ መንግስት መሰረት ከመሆኑም ከላይ ከሩሶ ፍልስፍናዊ እሳቤዎች በቀጥታ የተወሰዱ አንቀጾችም ይገኙበታል፡፡
እኛም መንግስታችን የቱ ይሁን? ብለን እንጠይቅ....
ምላሹን በልባችን እናሳድር!!
@zephilosophy