ደስታ
ምንጭ ፦ ከፍስሀ ጋር መወለድ (ኦሾ)
ተርጓሚ፦ በዩሐንስ አዳም
መደሰት አስቸጋሪ የሆነው ደስታ መጥፋት እንዳለበት ስለሚታሰብ ነው፡፡ መደሰት የሚቻለው ራሳችሁን ሳትሆኑ ነው፡፡ አናንተ እና ደስታ በአንድ ላይ ልትኖሩ አትችሉም፡፡ ደስታ እዚያ ሲኖር አናንተ ቀሪ ናችሁ፡፡ አናንተ እዚያ ስትኖኑ ደስታ ቀሪ ይሆናል፡፡ ደስታ እና አናንተ ልክ እንደ ብርሃን እና ጨለማ ናችሁ፡፡ ሁለታችሁም ተመሳሳይ ቦታ ላይ መከሰት አችትሉም፡፡
በዚህ ምክንያት የተነሳ መደሰት አስቸጋሪ ነው፡፡ ደስታ ቀላል አይደለም፤ ምክንያቱም መሞት አስቸጋሪ ነው፡፡ እናም በእያንዳንዷ ቅፅበት እንዴት መሞት እንዳለባቸው የሚያውቁ ብቻ ናቸው እንዴት መደሰት እንዳለባቸው የሚያውቁት፡፡ ብዙ የመሞት ብቃት በኖራችሁ ቁጥር ደስታችሁ የጠለቀ፣ የፍስሃችሁ ነበልባልም በጣም ታላቅ ይሆናል፡፡
መደሰት አስቸጋሪ ነው ፦ ምክንያቱም መከረኛ ሆናችሁ እንድትቀሩ የሚያደርጉ በጣም በርካታ ኢንቨስትመንቶች አሉ ይህንን ሁኔታ ካላያችሁት በስተቀር ለመደሰት መሞከራችሁን መቀጠል ብትችሉም ቅሉ በጭራሽ ደስተኛ አትሆኑም፡፡ እነዚህ በመከራችሁ ውስጥ የሚያገኙት ኢንቨስትመንቶቻችሁ መወገድ አለባቸው፡፡ እናም እያንዳንዱ ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ መከራ ሊከፍል የሚችል መሆኑን ተምሯል፡፡ አናንተ ደስተኛ እና ጤነኛ ከሆናችሁ ማንም ስለ አናንተ ደንታ የለውም፡፡ ጥሞናን አታገኙም፤ እናም ጥሞና የእኔነት ዋናው እስትንፋስ ነው፡፡ ልክ አካል ኦክስጂን እንደሚያስፈልገው እኔነት ጥሞና /ትኩረት/ ያስፈልገዋል፡፡
ጤነኛ ፣ ደስተኛ ስትሆኑ ሰዎች ጥሞና አይቸሩዋችሁም፡፡ ጥሞና አያስፈልግም፡፡ ዳሩ ስትታመሙ፣ መከረኛ ስትሆኑ፣ ስታለቅሱ፣ ስታስቡ ግን ሁሉም ቤተሰብ ወደ ፍላጎቶቻችሁ ትኩረትን ይሰጣሉ፡፡ ልክ ድንገተኛ አደጋ እንደ ደረሰባችሁ ስራቸውን ያቆማሉ፡፡ እናት ከማዕድ ቤት እየሮጠች ትመጣለች ፤ አባትም ጋዜጣውን ያሽቀነጥራል፡፡ እናም ሁሉም ሰው ትኩረቱን ከእናንተ ጋር ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ታላቅ የእኔነት እርካታን ያጎናፅፋል፡፡ እናም ቀስበቀስ የእኔነትን መንገድ ትማራላችሁ፡፡ መከረኛ ሆኖ መቅረት... እናም ሰዎች ለእናንተ ጥሞና ይሰጣሉ፡፡ መከረኛ ሆናችሁ ቅሩ እናም እነሱ ለእናንተ ያዝኑላችኃል፤ ደስተኛ ስትሆኑ ማንም ያንን ስሜታችሁን አይካፈልም፡፡ ለዚያ ነው ሰዎች ለባህታዊዎች ትኩረትን የሚሰጡት፡፡ አንድ ሰው ይፆማል እናም ሰዎች ተመልከቱት እንዴት ያለ ቅዱስ ነው" ይላሉ፡፡
ክብረ በዓልን ብታከብሩ ማንም ያንን ስሜት ከአናንተ ጋር አይቋደስም:: ከአንድ ሰው ጋር በፍቅር ውስጥ ብትሆኑ ማን ነው ከአናንተ ጋር ስሜታችሁን የሚጋራው? በተቃራኒው ሰዎች በጣም ቀናተኛ ይሆናሉ፡፡ አናንተ ተወዳዳሪ ሆናችኃል፡፡ እነዚህ ሰዎች አንድ ዓይነት ሰውን ለራሳቸው ይፈልጋሉ፤ አናንተ ጠላት ናችሁ።
እኛ የተወለድነው ከፍስሐ ጋር ነው፤ ፍስሐ የኛ ዋናው ፍጥረት ነው፤ ደስተኛ ለመሆን ምንም ነገር አያስፈልግም፤ አንድ ሰው ዝም ብሎ ብቻውን በመቀመጥ ደስተኛ መሆን ይችላል፡፡ ደስታ ተፈጥሯዊ ሲሆን - መከራ ደግሞ ተፈጥሮዊ ያልሆነ ነው:: ግን መከራ ትርፋማ ያደርጋል፡፡ እናም ደስታ ዓላማ - ቢስ ነው፡፡ ማንኛውንም ትርፍ አያመጣላችሁም፡፡
ስለሆነም አንድ ሰው መወሰን መቻል አለበት፡፡ ደስተኛ መሆንን ከፈለጋችሁ ተራ ሰው መሆን መቻል አለባችሁ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ውሳኔው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለጋችሁ ማንንም ያልሆናችሁ መሆን ይኖርባችኃል፡፡ ምክንያቱም እንዳችም ጥሞና አታገኙም፡፡ በተቃራኒው ሰዎች ቅናት ይሰማቸዋል። ሰዎች ከእናንተ
በተቃራኒ ውስጥ ይሆናሉ፡፡ ሰዎች አይወዱአችሁም፡፡ ሰዎች የሚወዱአችሁ በመከራ ውስጥ ከሆናችሁ ብቻ ነው:: ከዚያም ያዝኑላችኃል፤ ችግራችሁን ይካፈሏችኃል፤ በሁኔታው የእናንተ እኔነት ይረካል፤ እናም የእነርሱም እኔነት ጨምሮ ይረካል፡፡ ከአንድ ሰው ሀዘኑን ሲጋሩ እነሱ የበላይ እናም አናንተ የበታች ናችሁ፡፡ እነርሱ ወሳኝ እጆች ናቸው፡፡ የመተዛዘን የበላይነት ጨዋታ ደስ ያሰኛቸዋል፡፡
ዝም ብላችሁ ታዘቡ-አናንተም ራሳችሁ እነዚህን ታደርጋላችሁ፡፡ አንድ ሰው የእሾህ አልጋ ላይ ቢተኛ ሰውየው ለሰው ልጅ የተወሰነ ደስታን ይዞ የመጣ ይመስል፣ ታላቅ ድርጊትን የፈጸመ ይመስል- ወዲያውኑ ትሰግዱለታላችሁ፡፡ እሱ እኮ ዝም ብሎ ራሱን ማሰቃየት የሚወድ ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ትወዱታላችሁ ፤ ታከብሩታላችሁም፤ አክብሮታችሁ ግን ጤናማ ያልሆነ ነው፡፡ ይህ ሰው የአናንተን ጥሞና ይፈልጋል፡፡ እናም ይህ መንገድ ደግሞ የአናንተን ጥሞናን ለማግኘት በጣም ቀላሉ መንገድ ነው፡፡ የእርሱ እኔነት ይሟላል፤ ይረካል፡፡ ስለዚህ በእነዚያ እሾሆች ላይ ለመተኛት እና ለመሰቃየት ዝግጁ ነው፡፡
ይህ ነገር ሁሉም ቦታ በትንሽም ሆነ በትልቅ መጠን እየተከሰተ ነው፡፡ ልብ በሉት! ይህ በጣም ጥንታዊ ወጥመድ ነው፡፡ እናም ከዚያ በኋላ መደሰት ትችላላችሁ፡፡ ከደስታ በቀር ምንም የለም፤ ማንንም ላለመሆን ዝግጁ ከሆናችሁ፣ የሌሎችን ጥሞና የማትሹ ከሆነ ከናካቴው ምንም ዓይነት ችግር አይኖርም ደስተኛ መሆን፣ ዘና ማለት ትችላላችሁ፡፡ በጣም ትናንሽ ነገሮች የሚቻለውን ታላቅ ፍስሐ ሊሰጡአችሁ ይችላሉ፡፡
@Zephilosophy