📚 ከሰለፎች ምክር 📚


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


أبــو مـريـم عــبــدالــســلام
📝🎤አቡ መርየም🎤📝
https://t.me/abduselamabumeryem
👆ሊንኩን ነካ በማድረግ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
አስተያየትም ይሁን ምክር ወይም ወቀሳ ካላቹህ ብትልኩልኝ ለኔ ትልቅ ስጦታ 🎁 ነው
👇👇
በቦት ለመላክ 👇
@Abumeryeem_bot
ወይም 👇
@Abumeryeem

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ይድረስ ሳውዲ ለመምጣት ለሚያስቡ ወንድሞች

በፍሪ ቪዛ ወደ ሳውዲ እናስመጣለን ብለው የሚሉ የወንድሞቻቸው መጉላላት ሳይሆን ለኪሳቸው የሚጨነቁ ስስታሞችን ተጠንቀቁ

አገር ውስጥ የሆነ ነገር መስራት የሚችሉበት ገንዘብ እያላቸው በውሸት ገፋፍተው ያመጡዋቸውና እዚ እየተጉላሉ ነው

ሰባት ወርና ከዛ በላይ እየተጉላሉ ያሉ ሰዎች አሉ

ወንድሞች ተጠንቀቁ
ደሩራ ሆኖ የሚመጣ ካለ እዛው ስራውንም መስፈርት አድርጎ ይምጣ ካልሆነ ከባድ ነው

ስራ ማጣቱ ብቻ ሳይሆን
ለከፊል ወይም ላስመጣቻው ሰው
በየ ጊዜው የሚከፈለው ክፍያ ሌላ ስቃይ ነው

✍️ ወንድማቹህ አቡ መርየም

https://t.me/abduselamabumeryem/5396


🇵🇸ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸 dan repost

ጓደኛ የሆነ ጓደኛ ሲኖርህ…………

ክስተቱ እንዲህ ነው………
ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ። አብረው ጉዞ ወጡና አንድ ሆቴል ክላስ ይዘው አደሩ። በነጋታው ተነስተው ወደ ጉዳያቸው ሊወጡ ሲሉ አንደኛው ከያዘው ገንዘብ 100 ዲናር ያህል ይጠፋበታል።

ለጓደኛው;
"ከነበረኝ ገንዘብ መቶ ዲናር ጠፍቶብኛል አይተህ ነበር እንዴ?" አለው።

ጓደኛው;
"አዎን ለሊት ተነስቼ ነበር የሆነ ዕቃ መግዛት ፈለኩኝና ወስጄብሃለው።" አለው።

"ነው እንዴ? አብሽር" አለውና ወደ ጉዳያቸው አቀኑ።

ጉዳያቸውን ጨራርሰው ወደ ክላሳቸው ሲመለሱ የሆቴሉ የፅዳት ሰራተኛ ያገኛቸውና……
"ክላሳችሁ ላፀዳ ስገባ 100 ዲናር ወድቆ አግኝቻለሁ" ብሎ ይሰጣቸዋል።


በዚህ ጊዜ ገንዘብ ጠፍቶት የነበረው በአግራሞት ወደ ጓደኛው ይዞርና
"እኔ ወስጃለሁ ብለኸኝ አልነበር እንዴ?" አለው።

ጓደኛውም ሲመልስ
"እንደ ምታየው ከእኔና ከአንተ ውጪ ሌላ ሰው አልነበረም። አላየሁም ብልህ ኖሮ ሸይጣን በመሃላችን ገብቶ ስራውን ሊሰራ ይችላል። ያ እንዳይሆን 100 ዲናሩ በራሴ ላይ እዳ አድርጌው ጓደኝነታችን ለገንዘብ ሲባል እንዳይቋረጥ ልጠብቀው ብዬ ነው ወስጃለሁኝ ያልኩህ።" አለው



🤝ሷሊህ ታማኝ ጓደኛ ካለህ ትልቅ ፀጋ ነውና አደራህ ተንከባከበው!!
https://t.me/hamdquante


፡الحمد لله
ፊሊስጤናዊያን ወገኖቻችን ከአስከፊው ጦርነት እርፍ ስላሉ ደስ ብሎናል
የሙስሊሞች ደስታ ያስደስተናል ህመማቸው ያሳምመናል

ከከፊሎች አባባል👇
ቻይና የቁሳቁሶች ማምረቻ ስትሆን
ፊሊስጤን የጀግኖች ማምረቻ ነች

፣ الله أكــبر

https://t.me/abduselamabumeryem/5394


⚠️ ባለትዳሮች አዳምጡት!

ጥያቄ - አንዲት ሴት ባለቤቷ በዲኑ ጠንካራ, ለሷም መልካም ሆኖላት ልትወደው ስላልቻለች ብቻ ፍቺ መጠየቅ ትችላለች? ምንስ ትመክራታለህ❔

➦ ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ለባል እና ለሚስት ጥሩ ምክር አለበት።

🎤 መልስ - ታላቁ ወንድማችን አቡ መርየም አብድሰላም ሸምሱ አላህ ይጠብቀው።

🎧 ድምፁን ለማግኘት ↴
🔗
https://t.me/abduselamabumeryem/5393


አል ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱዲዮ dan repost

   "1አምላክ" vs "44ታቦት"

   ቀጥታ ከቃሉ እንደ ምንረዳው "አምላክ" ማለት የሚመለክ ማለት ነው። የሚመለክ ማለት………
   የሚሰገድለት፣ ድረስልኝ፣ ጠብቀኝ፣ አድነኝ፣ እርዳኝ የሚባል፣ ስለት የሚደረግለት፣ በእሱ የሚማል፣ እና አጠቃማይ የአምልኮ ተግባር የሚሰጠው ማለት ነው።

🔥  ክርስቲያኖችን ካየን ግን  ለአርባ አራት አካላቶች በአጠቃላይ የተጠቀሱትን አምልኮ ይፈፅማሉ።
  
🔥 ታቦቱስ ምንድን ነው
 
ታቦቱ የሚዘጋጀው ከተለያዩ እንጨትብረታ ብረት፣ ወርቅብር ወይም ከሌላ ማቴሪያል
  ተጠርቦተሰንጥቆበልኩ ተቆርጦ የሚገጠም፤
  ከዝያም የተመረጠለትን ቅርፅ የሚወጣለት፣ የተመረጠ ስያሜ የሚሰየምለት፣ የተመረጠ ቀለም የሚቀባ እና
  በተመረጠለት ቦታ የሚቀመጥ ቁስ አካል ነው። የአሰራሩ ቅደም ተከተል ብሳሳት አያሳስብም።

ይህ ማለት……
   አንድ ሰው የሚፈልገውን ሳጥን በሚፈልገው ቁስ፣ በሚፈልገው ቅርፅና ቀለም እንደ ሚያሰራው ማለት ነው።

  በዚህ መልኩ ተጠርቦና ተቀልሞ የተዘጋጀው 🔥 "ታቦት" 🔥 የሚባለውን ቁስ አካል  "ሊጠቅምና ሊጎዳ ይችላል" ተብሎ ለእሱ መስገድ፣ ከእሱ እገዛና ከለላ መፈለግ፣ በእሱ መጠበቅና እሱን መለመን
  ምሽትና ንጋትን ለይቶ ከሚያውቅ ጤነኛ ሰው የሚፈፀም ተግባር አይደለም።

🔥   የሀገራችን ክርስቲያኖች ግን ይህንን ነው የሚፈፅሙት¡¡

  ስለ "ታቦቶች" ከተነሳ ጥያቄው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም። ስለኾነም አያይዤ መጠየቅ የምፈልገው ጥያቄ አለኝ……
  እንዳሳለፍነው የታቦቶቹ ብዛት አርባ አራት ናቸው ክርስቲያኖች ደግሞ ብዙ ጊዜ ስናያቸው አንዱ "ገብርኤል ጠብቀኝ" ይላል፣ ሌላኛው "ሚካኤል ጠብቀኝ" ይላል፣ ሌላኛው "ኡራዔል ጠብቀኝ" ይላል፣ ሌላውም ሌላ ይላል።
ልብ በሉ አርባ አራቱንም በአንድ ጊዜ እየጠራ ሳይሆን በንጥል ነው የሚጠራው።

ጥያቄዬ………
   "ገብርኤል ጠብቀኝ" ያለው እንደው ገብርኤል "እሺ" ቢለውና ሚካኤል ግን ለገብርኤል በመጠየቁ ቅር ብሎት ሊያጠፋው ቢፈልግ የማን ፍላጎት ነው ተፈፃሚ የሚሆነው?? የገብርኤል ፍላጎት ወይንስ የሚካኤል ፍላጎት??
    ዋነኛው ፈጣሪና መመለክ የሚገባው አምላክስ ተትቷል ነው??

ምን ይሄ ብቻ………
  እንደ ሚታወቀው በየ አመቱ "ጥምቀት" ብለው የሚያከብሩት በዓል አላቸው።

በዚህ ቀን ሁሉም ታቦቶች ተሰብስበው ወደ ወንዝ (ሜዳ) ይወሰዱና ይጠመቃሉ። ከተጠመቁ በኋላ ወደየመጡበት ይመለሳሉ። ታድያ በዚህ ጊዜ ከብልጥ በፊት ሞኝ የሚስቅበት የኾነ አባባል አላቸው። ታቦቶቹን ተሸክመው በሚወስዱበት ጊዜ……
"ታቦቱ አልሄድ አለ" ይላሉ።

የሰው ልጅ ከጨለመበት መጨረሻ የለውም።
ተመልከቱ………
   ታቦቱ ጠርቦ፣ ቀርፆ፣ ቀልሞ የሰራው የሰው ልጅ ነው፤ ራሳቸው ተሸክመው ወስደው አጥበውት፤ ራሳቸው ተሸክመው እየመለሱት "ታቦቱ አልሄድ አለ" እያሉ ይጃጃላሉ። ተከታዮቻቸውም «እውነት» ብለው ይቀበላሉ።

  እኔ ግን እንዲህ ዐይነት የቂል ጨዋታ «ሀይማኖታዊ ስርዓት» ተብሎ አይደለም የሰፈር ህፃናት ተሰብስበው በዚህ መልኩ ዕቃቃ ሲጫወቱ ባገኛቸው "አዕምሯችሁ ይጀዝባል" ብዬ ነበር ጨዋታ የማስቀይራቸው።

   እ ያ ሰ ብ ን  እንጂ ወገን!!
👆👆👆👆👆👆👆
✍️ @islmina_min_ale

🔗 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17701


👌 ሊጆች ስትወልዱ ኢህቲሳብ አድርጉ ጥሩ ኒያ ይኑራቹህ

ወልዳቹህ በጥሩ ተርቢያ አሳድጋቹህ ለዲን ታጋዮች እንዲሆኑ ይሁን ጭንቀታቹህ

በዚህ ኒያ ከወላዱቹህ ማይቋረጥ ሀሰናት ነው ምንዳንቹህ

ረበና ይወፍቀን

https://t.me/abduselamabumeryem/5391


አዲስ ግጥም❗️(ወይ አሜሪካ ደካማ ነሽ ለካ።)

ዛሬ ልዩ ቀን ነው እንኳን ደስ አላችሁ።

ሸይጣኗ በሀጃዋ ስትገባ የጋዛ ሰላም ተስፋ አሳይቷል።

ጥር 7/2017

በጁሀር ኡመር

https://t.me/OfficialDemas/6311
👆
👇
https://t.me/abduselamabumeryem/5390


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ፊሊስጢናውያን ህፃናቶች ሴቶች ወገኖቻችን ከነቤቶቻቸው ሲያጋይዋቸው ሰንብተዋሉ

እነሱም በተራቸው የሀያሉ ጌታችን ጁንድ የሆነችውን እሳት 🔥

አይናቸው እያየ በዚ መልኩ ቤቶቻቸው እያጋየች ነው


ኢስራኤል ማለት አረብ ሀገር ውስጥ የሰፈረች የአሜሪካ ሰራዊት ቅርንጫፍ እንጂ ሌላ አይደለችም

ያለ አሜሪካ አንድ ሳምንት የመቆየት አቅም የላትም

ኢስራኤል ለምታደርሰው በደል ሁሉ ተጠያቂዋ አሜሪካ ናት ።

https://t.me/abduselamabumeryem/5389


📖 አስተንትነህ ቅራው! ⤵️

♻️ በሚል ርዕስ ከተፍሲር ደርስ የተቀነጨበ መደመጥ ያለበት ምክር።

🎙 በኡስታዝ አቡ ዐብድልመናን ኻሊድ ቢን ጠይብ አላህ ይጠብቀው።

📅 እሁድ 04/05/2017E.C 📅

🕌 በፉርቃን መስጂድ {አለም-ባንክ}

📎
https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/17660


የሎስ አንጀለስዋ ታሪካዊ እሳት
እስካሁን ቀጥቅጣ የበላችው ቦታ ስፋት 👇

👉 15,309 ሄክታር
👉 153 ካሬ ኪሎ ሜትር

https://t.me/abduselamabumeryem/5387


የሎስ አንጀለስ ከንቲባ ከተማዋ ላይ የጅምላ ጨራሹ ኑክሌር የተጣለባት ይመስላል ብሏል

እስካሁን የተቃጠለው ንብረት 150 ቢሊየን ዶላር ይገመታል ብለዋሉ

እሳትዋ ከሆነች ጌታዋ ካልሆነ በስተቀር ማንም አያስቆማትም


https://t.me/abduselamabumeryem/5386


ሙወሂዶችና / የሽርክ ባልተባተቤት ሱፊዮች መቃብራቸው እራሱ የተለያየ ነው

https://t.me/abduselamabumeryem/5385


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
{ وَیَشۡفِ صُدُورَ قَوۡمࣲ مُّؤۡمِنِینَ }
[سُورَةُ التَّوۡبَةِ: ١٤]

አላህ ከባዱን በላእ ያውርዶባቸውና ልቦቻችን ያሽርልን

https://t.me/abduselamabumeryem/5384


እነዚህ ሰዎች በዚ ሰሞን ገናን ካከበሩ ሰዎች በምን ይለያሉ ❓


እነዚያ እየሱስ ጊታ ነው ቢሉም
እነዚህ ወሊይ ጌታ ነው እያሉ ነው

https://t.me/abduselamabumeryem/5383


👇👇👇


👉ሌላው ትርፋማና አዋጭ የሆነው የንግድ አይነት

ሰደቃ የሚባል የንግድ አይነት ነው


👉 ቸር የሆነው ጊታችን ለአላህ ብላቹህ የምትሰጡትን እኔ እተካዋለሁ ብሎ ቃል ገብቷል

አንዴ ለሰጠሀው ሁለት ጊዜ ነው የሚተካልህ

1⃣ ዱንያ ላይ ከሰጠሀው በላይ ሪዝቅህ ላይ ይጨመርልሀል

2⃣ አኼራ ላይ ደግሞ ምንዳ ይሰጠሀል

ነብያችን ﷺ ለዚህ ነው👇
፡ ما نقصت صدقة من مال
ሰደቃ ገንዘብን አታጎድለውም ያሉት

👌 ኒያህ ካስተካከልከው ሰደቃ እራሱ ንግድ ነው ።

አላህና አንተ እንጂ ሌላ ማንም የማያውቀው ሰደቃ ሰጥተህ ታውቃለህ ?

አንቺስ ታውቂያለሽ ?

የአርሹ ጥላ ስር ከሚሆኑት ሰዎች ውስጥ እኮ ቀኞቻቸው የሰጡትን ግራዎቻቸው የማያውቁባቸው የነበሩት ይገኙበታል

፡ والسلام عليكم


✍️አቡ መርየም

https://t.me/abduselamabumeryem/5381


ቶሎ መቆጣትና የፀባይ መቀያየር ሴቶች ሁሉ የሚጋሩት ባህሪ መሆኑን ሴቶች እራሳቸው መስከረዋሉ


ወንዶች ከዚ መማር ያለባቸው ነገር

አንዲትን ሚስት በዚ ባህሪዋ የመጣ ከመፍታት ወይም አስተካክላታለሁ ብሎ ወዳልሆነ ኩርፊያም ይሁን ፀብ መግባት ተገቢ እንዳልሆነ


ቶሎ በተቆጣች ሰአት የዛ አፀፋ አለ መመለስና በዝምታ ማለፍ
ምክንያቱም ትንሽ ቆይታ እራስዋ ትመለሳለች

https://t.me/abduselamabumeryem/5380


ባለቤቴ በትንሽ ነገር ትበሳጫለች ሲል ይህ የባለቤትህ ባህሪ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ወይም የአብዛኞቹ ሴቶች ባህሪ ነው ትንሽ ነገር ያስደስታቸዋል ትንሽም ነገር ያስቆጣቸዋል ፍች በእነሱ እጅ ቢሆን ኖሮ ሁላችንም አባቶቻችን ቤት ነበርን አሁን ካንተ ጋር መኖር በቃኝ ትልህና አንተ ከቤት ስትወጣ ወይኔ አስቀየምኩት ትላለች አልኩት ። ጥያቄ ለሴቶች 👇 ያልኩት ነገር ትክክል ነው ወይስ አይደለም ?
So‘rovnoma
  •   ትክክል ነው በዚህ ባህሪ አንድ ነን
  •   ትክክል አይደለም
193 ta ovoz



     ይህ ነገር የታዘበው አለ??

  ዐይታችሁ እንደሆነ የሌላ እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ወደ ስልጣን ሲወጣ ወይም ከትላልቅ ባለስልጣኖች ጋ የሚያገናኘው መስመር ላይ ሲደርስ እሱም የእምነቱ ተከታይ የሆኑ ወዳጆቹ ይደሰታሉ።

ምክንያቱን፦
  እሱ ስልጣን ላይ በመውጣቱ ከቻለ በቀጥታ በመወሰን: ካልሆነም እንዲወሰን ድምፅ በመሆን ለዛ እምነት ተከታዮች ከመንግስትም ይሁን ከሀገሪቱ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያገኙ ሽፋን ይሰጣል። ስልጣኑን በመጠቀም እምነቱ እና የእምነቱ ተከታዮች ሀገሪቷ ላይ ፍላጎታቸው እንዲሟላላቸው (ለእምነቱ) ወጥሮ ይሰራል።


  በተቃራኒው አንድ ሙስሊም የሆነ ወንድም ስልጣን ላይ ከተመቻቸ: ወይም ከትላልቅ ባለ ስልጣኖች መቀማመጥ እና መወያየት ከጀመረ ነገሩ ከላይ ባየነው ተቃራኒ ይሆናል። አይደለም እስልምና ወይም ሙስሊሞች ሊረዳ ይቅርና እሱ ለራሱ የራሱን እስልምና በግልፅ ለማራመድ ይሳቀቃል።
  ትላልቅ ወይም "የሀላፊ ቢሮ" የሚባሉ ዐይነት ቢሮዎች ገብታችሁ እዛ ቦታ ላይ የሚቀመጡ ሙስሊሞች ብታዩ ለዚህ ሁነኛ ምስክር ናቸው። ፂማቸው ከመከርከም ጀምሮ ልብሳቸው ለማሳጠር ሁላ ይሳቀቃሉ። አንተ ገብተህ ራሱ "አሰላሙ ዐለይኩም" ስትላቸው: አጠገባቸው ሌላ ሰው አለመኖሩ እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ነው ሰላምታህን ድምፃቸው እየሰማህ የሚመልሱልህ።

ከዚህ ሁሉ የከፋው………
  እነዚህ በሀላፊነት ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሙስሊም ባለስልጣኖች ከስሮቻቸው ወዳሉ ተቋሞች ሄደው ሌሎች ሙስሊሞች ላይ ጫና እንዲያደርጉ ይገደዳሉ። እነርሱም ይተገብሩታል።


ለምሳሌ፦
   አካዳሚ እያለን የጁሙዐ ሰላት ከመስገድ ስንከለከል እና እኛም የመስገድ መብታችን ስንጠይቅ "በትምህርት ስርዓት ላይ እስካለን መስገድ እንደማንችል" እንዲነግሩን ይላኩና ይመጡ የነበሩት ወረዳው ላይ የነበሩ ሙስሊም አመራሮች ነበሩ። "እኛ እንደናንተው መስገድ የምንፈልግ ሙስሊሞች ብንሆንም ያለንበት የስራ ህግ ስለማይፈቅድልን ወጥተን እንደ ማንሰግደው ሁሉ: እናንተም ትምህርታችሁ እስክትጨርሱ ድረስ አትስገዱ" ይሉን የነበረችው ማሳመኛ አሁን ድረስ ትታወሰኛለች።


እውነቱን ለማውራት………
   ከላይ የጠቀስናቸው ዐይነት ባለስልጣኖች ትምህርታቸው በሚማሩበት ጊዜ "እንደምንም ተምሬ የሆነች ቦታ ልያዝና ቢያንስ ለእስልምና እና ለሙስሊሞች የሆነ ነገር አደርጋለሁ።" የሚል መልካም ምኞት የነበራቸው ናቸው።የኋላ ኋላ ግን ዕድሜያቸው የጨረሱበት የስልጣን እርከን ላይ ሲደርሱ ያሳለፉት ድካም፣ የወንበሩ ምቾት፣ የገቢው ጥፍጥና እና የተገኘው ዕውቅና ተሰብስበው ይሸነግሉትና ለእስልምና የሆነ ነገር ቢፈይድ ከዚህ ወንበር እንዳይሰናበት እየፈራ ለስልጣኑ ሰስቶ እስልምናውን ይደብቃል። እንዴት ያለ ሙሲባ ነው??

  ለዚህ ሁሉ ውድቀት ምክንያቱ ከተጠየቀ ምላሹ አንድና አንድ ነው………
   እነዚህ ሰዎች በየዋህነት ወደ ፊት እስልምና ለመርዳት አልመው እድሜያቸው በአካዳሚ ጨረሱ እንጂ:
  ሊረዱት የተመኙት እስልምና ምን እንደሆነ ለመረዳት አንድም ቀን ጊዜያቸውን ሰጥተው እስልምናን ተምረው አያውቁም። እስልምናን የተማረው እና ያወቀው ሰውማ አይደለም ስልጣኑን ሕይወቱን ፊዳ ያደርጋል እንጂ በፍጹም እስልምናው ላይ አይደራደርም!!

በመሆኑም…………
  አካዳሚም ይሁን ሌላ ዐይነት መስክ ላይ መሰማራት የፈለገ ሙስሊም: ከምንም ነገር በፊት እስልምናውን መማር እና ማወቅ አለበት።

ወላጅ ሆይ!!
   "ልጆ ተምሮ ቦታ ይያዝና እስልምና ላይ የሆነ አሻራ ያሳርፋል" ብለህ አካዳሚ ላይ የምትማግደው ልጅህ ነገ ያሰብክለት ደረጃ ላይ ሲደርስ ለእስልምና አሻራ ሊያሳርፍ ሳይሆን የራሱ እስልምና እንዳይንሸረሸር ከዚህ ትምህርት ውሰድና ቆም ብለህ አስብ!!


📖{قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ}
{ሰላቴንም እርዴንም መኖሬንም መሞቴንም የዐለማት ጌታ ለሆነው አላህ ነው በል።}



🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante
👆
👇https://t.me/abduselamabumeryem/5376


ለአንድ ሴት ኒካህ ማሰር የሚችለው ከዘመዶችዋ ማን ነው ?

1⃣አባት
2️⃣የአባት አባት
3️⃣ልጅ
4️⃣ወንድም በእናትም በአባትም
5️⃣በአባት የሚገናኙት ወንድም
6️⃣የሸቂቅ ወንድም ልጅ
7️⃣በአባት የሚገናኙት ወንድም ልጅ
8️⃣የአባት ወንድም ሸቂቅ
9️⃣በአባት የሚገናኙት የአባት ወንድም

እነዚህ በቀጥታ ወይም ውክልና ሰጥተው ማሰር ይችላሉ

❌ በእናት በኩል ያሉ ዘመዶች ኒካህ አያስሩም ።


ስደት ላይ ላሉ እህቶች ወሳኝ ነጥብ ተወስቶበታል



https://t.me/abduselamabumeryem/5375

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.