🌹🌹🌹🥀ሴተኛ አዳሪ ነኝ🥀🌹🌹🌹
🌺🌺🌺ክፍል 3⃣5🌺🌺🌺
💋💋💋💋Brak Tube💋💋💋💋
እውነትም ወይዘሮ ወይንሸት በጣም ደስ የሚሉ እና ተግባቢ ናቸው በዛ ላይ ቀልድ አዋቂ ነታቸው ብዙ ሰው እንዲወዳቸው አድርጓል። ቤታቸው አዲስም ስለሆ ይሁን አላቅም እንግዳ አያጣውም የመጣው ሁሉ ደስ ብሎት ይሄዳል።
እንደሁሌውም ዛሬም እንግዳ ይመጣል ብለን እየተዘጋጀን ነው። ወይዘሮ ወይኗ አብረውኝ ይሰራሉ እንደውም ቀደም ብለው ስራየጀመሩት ወይዘሮ ወይኗ ናቸው።
፨ ዛሬስ ማነው የሚመጣው አልኳቸው ገና በጠዋቱ ሽር ጉድ ሲሉ
፨ትልቅ እንግዳ አለብን ልጄ ቶሎ ቶሎ እንጨርስ አሉኝ እና ወደስራ ገቡ።
እኔም የወትሮ ማብራሪያ ስላልተሰጠጭ ትንሽ እየከፋኝ ፨ ከየት ነው የሚመጡት ብዬ ጠየኳቸው።
፨ከደብረዘይት ነው ይገርምሻል በቅርቡ ነው ከአሜሪካ የመጣችው
፨ ደብረዘይት ለምን ሄዱ ታድያ አልኩኝ
፨ አንቺ ወሬኛ እንደው ወረ ስትወጂ ብለው ሳቁብኝ ከዛ ትንሽ አሳኮርፍ
፨ ቤቲዬ ስቀልድ ነው ስራችንን እንጨርስና ነግርሻለው ብለው ወደስራ ገቡ እኔም ደስ ብሎኝ ስራውን ቀጠልን ወሬው ሳያጓጓኝ አልቀረም ስራ በዮሎ ለመጨራረስ ቸኩዬ ነበር። ወይዘሮ ወይንሸት ብዙ አመት ከኖሩበት ኢንጊልዝ ከመጡ ወራቶችን አስቆጥረዋል ብዙ አመት ቢኖሩም ቋንቋቸውንና ባህላቸውን መርሳት አይደለም አላጓደሉም እዚ ቤት ከገባው ጥቂት ጊዜ ባስቆጥርም ስለ እህታቸው ግን ምንም ብለው አያቁም ነበር።
ስራችንን ስንጨርስ ምሳ ሰአት እያለፈ ነበር የሚጠበቁት እንግዳ ግን እስካሁን መምጣት ነበረባቸው ብቻ መቼም ይምጡ እኔ ታሪኩን ለመስማት ወደ ወይዘሮ ወይኗ ጠጋ ብያለው።
፨ወይዘሮ ጥሩ ቅድም እኮ የጀመሩልኝ አልጨረሱልኝም
፨ አንቺ ልጅ ይህን ወይዘሮ ወይኗ ተይኝ አላልኩም እማ ብትይኝ ምን አለበት ብለው ተቆጡኝ
፨ ውይ ወይዘሮ ወይኗ አልኩ እንዴ ልምድ እኮ ነው አፌ ላይ የመጣውን ነው ያልኩት ይቅርያ እናቴ አልኳቸው እና ሳኩኝ እሳቸውም ሳቁ
፨ ነይ ልንገርሽ አንቺ ወረኛ ብለው ተቀመጡ እኔም ተከተልኳቸው። አሁን የምትመጣው እህቴ ነች አብረን ነው እሷ ከአሜሪካ እኔደሞ ከኢንግሊዝ የመጣነው ከዛም ይህን ቤት የገዛነው እኔ ብዙም እዚ ስለማልቆይ የሷ ነው ማለት ይቻላል ቢሆንም ግን እሷም አትቆይም አሉኝ
፨ እንዴ ታድያ ለምን ቤቱን ገዙት አልኳቸው
፨ አንቺ ደሞ ልነግርሽ አይደል እንዴ። ይሄውልሽ ዋና የመጣችበት ጉዳይ አንድ የድሮ ተከራዩአን ፍለጋ ነው።
፨ ሲገርም ምን ያህል ብትወዳት ነው ብዬ በልጅቷ ቀናው
፨ እሱም ለኔም የሚገርመኝ ነገር ነው ግን ልጅቷ ልጅ ነበራት እና በጣም ልጁን እንደምትወደው አቃለው ብቻ እህቴን ባህር አቋርጣ የመጣችፐት ጓዳይ በጣም ቀላል መስሏት ነበር። ግም ሁሉም ነገር እንዳስውበችው አልሄደም ልጅቷን የበላ ጅብ አልጮህ ብሎ እንዲው ትንከራተታለች።
፨ ምነው ቤተሰብ ምናምን የላትም እንዴ
፨ አላት ለዛነው ይህን ሳምንት ደብረዘይት የነበረችው እንግዲ ይሳካላት አይሳካላት አላቅም አሉኝ።
፨ እና የህቶት ስም ማነው ሳይነግሩኝ ብዬ ሳልጨርስ የመኪና ክላክስ በቤቱ ውስጥ አስተጋባ
፨ቶሎ በይ ክፈቺ መጣች መሰለኝ አሉኝ እኔም ይቺን ደግ ሴት ለማየት ሩጫየን ወደበሩ አረኩኝ።
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
እንግዳዋን ለማየት ቸኩያለው ቶሎ ብዬ የጊቢውን በር ከፈትኩት ከዛም አንድ የምታምር ነጭ ማርቸዲስ መኪና ወደውስት ገባች እና ቆመች በፍጥነት ስለነበር የገባችው ውስጥ ያለውን ሰው ማየት አልቻልኩም ነበር ።
ከዛም ሹፌሩ ቀድሞ ወረደና በሩን ከፈተ ወስጥ ያለችውል ሴት ለመውረድ ሳቸኩል አቀረም ገና በሩ እንደተከፈተ ቶሎ ብላ ወርዳ ወደእኔ መምጣት ጀመረች በጣም ደነገጥኩኝ ትንፋሼ መቆራረጥ ጀመረ የልብ ምቴም ለአፍታ ያህል ዝም ሲል ታወቀኝ። በፍጽሙ ይሆናል ብዬ ያልገመትኩት እና ያልገመትኩት ነገር ነበር የሆነው እንያ ሳደንቃቸው የነበሩ ሰው እንያ ምነው እናቴ በሆኑ ሳላቸው የነበሩ ሰው የኔዋ ወይዘሮ ጥሩ እማማ ሆነው ተገኙ ያቺ እሷን ባረገኝ ስል የነበረችው ልጅ እኔው ሆኜ አራፍኩት።
ወይዘሮ ጥሩ እንዲያ በፍጥነት መተው ተጠመጠሙብኝ እኔም የናፍቆቴን አቀፍኳቸው ተቃቅፈን ተላቀስን፨ ወይ እግዚብሄር አሉ ወይዘሮ ጥሩ
፨ምን ሆናቹ ብለው ወይዘሮ ወይኗ ከቤት ደንግጠው ወጡ
፨ አይ ምንም አልሆንም ወይንዬ ምንም አልሆንን አሉ ወይዘሮ ጥሩ እየደጋገሙ..............ይቀጥላል.............
✍ ደራሲ ማርጌት
ክፍል 3⃣6⃣ እና የመጨረሻው ክፍል ነገ ይለቀቃል አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን
@brak_tube @brak_tube @brak_tube ✍ ደራሲ ማርጌት
ክፍል 3⃣5⃣
................ይቀጥላል...................
Share & join as
@brak_tube Comment
@braks_bot.