🔴 የሴት ልጅ ኢዕቲካፍ በተመለከተ
በመሰረቱ ሴት ልጅ ልክ እንደ ወንዶች ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። በነቢዩ ዘመንና ከእሳቸው ህለፈትም በኃላ ሚስቶቻቸው ኢዕቲካፍ እድርገዋልና።
የተወሰኑ ሊቃውንት በመሰረቱ ሴት ልጅ ተገዳ ካልሆነ በስተቀር ከቤት መውጣቱ የተወገዘ ስለሆነ ኢዕቲካፍ ማድረጓም የተጠላ ይሆናል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በእድሜ ከፍ ላሉ ሴቶች እንጂ ለወጣትና ታዳጊ ልጃገረዶች ኢዕቲካፍ አይቻልም የሚል አቋም አላቸው:: ከባሏ ጋር ከሆነ ትችላለች ካልሆነ አትችልም ያሉም አሉ።
ይህን ያሉት ወጣትና ታዳጊ ሴቶች በእድሜ ከገፉት ይልቅ ለፈተና ስለሚጋለጡ ወይም ወንዶችን ለፈተና ስለሚያጋልጡ ነው፤ በተለይ ኢዕቲካፍ ከቤት ውጪ ውሎ ማደርን ስለሚያስከትል።
ከዚህም አንጻር ሴት ልጅ ኢዕቲካፍ በማድረጓና ለኢዕቲካፍ ብላ ከቤት በመውጣቷ ምክንያት ከወንድ ጋር የምትቀላቀል ወይም ከወንድ ጋር ተገልላ የምትቀመጥ ከሆነ፣ እራሷ ፈተና ላይ የምትወድቅ፣ ወይም ሌሎችን ፈተና ላይ የምትጥል ከሆነ፣ ወይም ደግሞ ደህንነቷ በአስተማማኝ ሁኔታ የማይጠበቅ ከሆነ ከኢዕቲካፍ ትከለከላለች።
የባል ፈቃድ
ሴት ልጅ ባሏ ወይም ኃላፊዋ ከፈቀደላትና ሌሎች መስፈርቶች ከተሟሉ በኃላ ለደህንነቷ የማያሰጋ የትኛውም መስጂድ ላይ ኢዕቲካፍ ማድረግ ትችላለች። በባሏ ፈቃድ ኢዕቲካፍ የገባች ሴት ባሏ ኢእቲካፍ እንድታቋርጥ ከፈለገ ይችላል። ያለርሱ ፈቃዱ የምታደርገው ኢዕቲካፍም ትክክለኛ አይሆንም። ወንጀለኛ ከመሆን ጋር ኢዕቲካፉ ትክክል ይሆናል የሚል አቋም ያላቸው ሊቃውንት አሉ። ለሱንናህ ብሎ ግዴታ የሆነን የባል ሐቅን መጠበቅ መተውም አግባብ አይደለም፣ ለተጨማረ ዒባዳህ ብሎ ወንጀለኛ መሆን ብልህነት አይደለምና ሴት ልጅ ያለ ባሏ ፈቃድ ኢዕቲካፍ ልታደርግ አይገባም። ባለትዳር ያልሆነች | ሴትም ብትሆን በስሩ ያለችን አባቷንም (ወላጆቿን) ወይም ወንድሟን ሰታሳውቅና ሳታስፈቅድ ኢዕቲካፍ ልታደርግ አይገባም። ባልና ወላጆችም | በቂ ምክንያት ወይም ስጋት እስከሌላቸው ድረስ፣ የኢዕቲካፉ ቦታ ደህንነቱ አስተማማኝ እስከሆነ ድረስና ቦታው ላይ እምነት ወይም ስነ-ምግባራቸው እንዲበላሽ የሚያደርግ ነገር መኖሩን እስካላረጋገጡ ድረስ ከመልካም ነገር ሊከለክሉ አይገባም። ባል ፈቅዶ ሚስት ሱንናህ የሆነን ኢዕቲካፍ ከጀመረች ኋላ ሀሳቡን ቀይሮ እንድትወጣ ቢያዛት እሺ የማለት ግዴታ አለባት። | “በነዝር” (በስለት) ምክንያት ግዴታ የሆነ ኢዕቲካፍን ግን አስፈቅዳው ከጀመረች በኋላ | ሳትጨርስ ባሏ ማስቋረጥ አይችልም።
|ምንጭ፦ አል መጅሙዕ ሊን-ነወዊይ 8/4፣ አል-ኢትሓፍ 29
( ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚይያህ የሚከተለውን ብለዋል፤ "ሐይድ ላይ | ያለች ሴት ልድ አስገዳጅ ለሆኑ ነገሮች መስጂድ መግባት ትችላለች፤ ነገር ግን | ለመስገድና ለኢዕቲካፍ ብላ መግባት አትችልም፤የ “ነዝር” የስለት ኢዕቲካፍ እንኳ | ቢሆን፡፡ ኢዕቲካፍ ላይ ያለች ሴት ሐይዷ ከመጣ ከመስጂድ ወጥታ ግቢው ላይ ድንኳን ተጥሎላት እዛ ላይ ትቆያለች፤ … ሐይድ | ኢዕቲካፏን | አያበላሽም፤ ምክንያቱም እሷ ፈልጋ የምታደርገው ነገር ስላልሆነ፤ | ከመስጂድ ትውጣ የተባለው ለመስጂዱ ክብር ሲባል ነው ... ከመስጂዱ እንጂ ከኢዕቲካፉ አይደለም ምትከለከለው.. :: ይሁንና ከኣወዛጋቢ ነገሮች ለመራቅ ሲባል ሴቶች ሐይድ ላይ ሆነው ኢዕቲካፍ ባያደርጉ ይመረጣል።
|ምንጭ፦ አል-ሙሐላ 5/322፣ ተስሂሉል- ፊቅህ 1/594። 3 መጅሙዕ አል-ፈታዋ 26/210፣ አል-መጅሙዕ ሊን-ነወዊይ 8/44።
http://t.me/sultan_54