👉 ዶክተር አቡበክር
ዛሬ አንድ የፈትዋ ፕሮግራም ተብሎ የአህባሽ ተከታይ ለሆነው ለዶክተር አቡበክር የተጠየቀ ጥያቄን በጣም በሚያሳፍር ሁኔታ ድብን ያለ ውሸት እየዋሸ መልስ ብሎ ሲያወራ ሰማሁኝ
ዶክተሩ የተጠየቀው አል ኡሱሉ ሰላሳ የተባለውን ኪታብ ኡለማዎች እንዳይቀራ አስጠንቅቀዋል ይባላል ምክንያቱ ምንድነው? የሚል ነበር
አዎ በርካታ አሊሞች ኪታቡ እንዳይቀራ አስጠንቅቀዋል አለ ግን አንድ አሊም አልጠቀሰም
የተከለከለበት ምክንያት ደግሞ ሲያብራራ
🔹አንደኛ ተውሂድ በሶስት ይከፈላል ብሎ ያስተምራል አለ ይህ ሌላኛው ውሸቱ ነው እስቲ በዚህ ኪታብ የት ጋር ስንተኛው ገፅ ላይ ነው ተውሂድ በሶስት ይከፈላል ያለው? አብዛኛው ወጣት አል ኡሱሉ ሰላሳ ተምሯል ይህ ማለት ያንተን ውሸትም አውቋል ማለት ነው
🔹ሁለተኛ የአሁኖቹ ሙሽሪኮች ከቀደምቶቹ ሙሽሪኮች የባሱ ናቸው ብሎ ይናገራል በዚህም የተነሳ ላኢላሃ ኢለሏህ ያለን ግለሰብ ያከፍራል እያለ ቅጥፈቱን ይቀጥላል ይህ ግለሰብ ዶክተር የተባለው በውሸቱና በማጭበርበሩ ሳይሆን አይቀርም ። አል ኡሱሉ ሰላሳ ላይ ስለዚህ ርእስ የሚያወራ የለም
በጣም የሚያሳዝነው ያ በደዊ ያ አብሬት ብሎ መጣራት አይቻልም ሽርክ ነው ብሎ ያስተምራል ስለዚህ እኛን ሙስሊሞችን ነው ከቀደምት ሙሽሪኮች የባሱ ናቸው ብሎ የሚናገረው ይላል። ሙስሊሞች ያ አላህ ብለው ወደ ፈጣሪያቸው ይጣራሉ እንጂ ወደ ሌላ አካል ፈፅሞ አይጣሩም።
👉 ማስገንዘቢያ
1ኛ~ ተውሂድ ለሶስት እንደሚከፈል በርካታ መረጃዎች ያሉ ሲሆን ይህን ለመረዳት ሱረቱል ፋቲሀን በጥሞና ማንበብ ተገቢ ነው
2ኛ~ የዘመናችን ሙሽሪኮች ከቀደምት ሙሽሪኮች የባሱ ለመሆናቸው ይህን አንቀፅ አስተውለህ አንብብ
”فَإِذَا رَكِبُوا فِي الْفُلْكِ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ فَلَمَّا نَجَّاهُمْ إِلَى الْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ“
«በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡» አል አንከቡት 65
3ኛ~ ሙታንን ድረሱልኝ ብሎ መጣራት ከእስልምና የሚያስወጣ ትልቁ ሽርክ ነው ። አላሁ ተአላ እሱን ብቻ እንድንለምነውና ከእሱ ውጪ ማንንም እንዳንጣራ ከልክሎናል ።
”وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ“
«ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡ »ጋፊር 60
”وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ“
«እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡» አህቃፍ 5
ከእንዲህ አይነት ጠሞ አጥማሚ አላህ ይጠብቀን ። ቤተሰቦቻችን በተለይ እናት አባቶቻችን በዚህ ሰውዪ እንዳይሸወዱ ቻናሉን ሙሉ በሙሉ አስወግዱላቸው ።
T.me/dawudyassin