ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ dan repost
+ በብርሃን ተናገሩ +
"በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ " ይላቸዋል (ማቴ1.፥27) ። "ጌታችን ለሐዋርያት"
ይህን በሚነግራቸው ጊዜ ፍጹም ጨለማ አልነበረም ። ይህንኑ ራሱ ጠንካራ ምስልን ተጠቅሞ ነግሯቸዋል እንጂ በስውር አልነገራቸውምና ። ይኽውም ማለት ከዚህ በኋላ ሊሰጣቸው ካለው የንግግር ጥብዓት አሁን እየነገራቸው ከነበረው የንግግር ቃና አንጻር ሲታይ ከእነርሱ ጋር ብቻና በአንዲት ትንሽዬ የፍልስጤም ጥግ ላይ እየተነጋገረ ስለ ነበረ "በጨለማ" እና "በጆሮ" አላቸው ። "
ያን ጊዜ የብስን እና ባሕርን ተሻግራቹ ሰው የሚኖርባትንና የማይኖርባትን ቦታ ኹሉ አካልላቹሁ ለመኳንንት ለነገዶችም ለፈላስፎችና ለንግግር ዐዋቂዎች ፈታችሁን ገልጣችሁና በታላቅ ጥብዓት የምትሰብኩት ለአንድ ወይም ለኹለት ወይም ለሥስት ከተማዎች አይደለምና ለዓለም ኹሉ ነው እንጂ ። ስለዚህ ያለ ምንም መሸማቀቅ በነጻነት ፦ "በሰገነት ላይ " እና " በብርሃን " አለ ።
"በሰገነት ላይ ስበኩ " እንዲሁም "በብርሃን ተናገሩ" ብቻ ሳይኾን ጨምሮ "በጨለማ የምነግራችሁን " እና "በጆሮ የምትሰሙትን " ያለውስ ለምድነው ? ይቀጥላል .....
(የማቴዎስ ወንጌል -ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደ ተረጎመው ትርጉም ከብረ እግዚአብሔር ኪደ ገጽ-208-209 )
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ