#ልሳነ #ግእዝ #Ge'ez #Language
ገቢር ተገብሮ = አድራጊ ተደራጊ / Direct and indirect Object/
✍️
ገቢር/ አድራጊ /፣ ተገብሮ /ተደራጊ/ ማለት የማይሸጋገሩትንና የሚሸጋገሩትን ግሶች የምንለይበት ሰዋስዋዊ ሙያ ነው፡፡
➾
የሚሻገሩ ግሶች /Transitive Verbs /፦ ማለት ከባለቤቱ ወይም ከድርጊት ፈጻሚው ድርጊቱን በማሳለፍ በድርጊት መፈጸሚያው ላይ ማረፉን የሚያመለክቱ ግሶች ናቸው።
ለምሳሌ፦ አበበ አንበሳ ገደለ፤ ብንል "
ገደለ" የሚለው ግስ አበበ የተባለው የዐረፍተ ነገሩ ባለቤት በአንበሳው ላይ ድርጊት መፈጸሙን የሚጠቁም ስለሆነ ነው። ነገር ግን አንበሳ ተገደለ ብንል ድርጊቱ እዚያው አንበሳው ላይ ብቻ መቅረቱን እንጂ ከማን ወደ ማን መኼዱን የሚያመለክት አይኾንም።
➾
የማይሻገሩ ግሶች /Interansitive Verbs በተገብሮ/ passive ይነገራሉ። ነባር አንቀጽና የማለት አንቀጾች የማይሻገሩ አንቀጾች ናቸው።
ገቢር/ተሻጋሪ----ተገብሮ/የማይሻገሩ
አቅረበ - አቀረበ ------ ሞተ - ሞተ
ጸፋአ - መታ ------- ነበረ - ተቀመጠ
ሰበረ - ሰበረ -------- ሖረ - ኼደ
አኀዘ - ያዘ -------- ቆመ - ቆመ
አንበረ -አስቀመጠ
አጥረየ - ገዛ
✍️ ተሻጋሪ ግስ ያለበት ቃል ተሳቢን ያስከትላል።
ምሳሌ፦
የማይሳቡ - Indirect ☑️ የሚሳቡ - Direct ☑️
እምከ - እናትኽ እመከ - እናትኽን
እምኪ - እናትሺ እመኪ - እናትሽን
ወልድከ - ልጅኽ ወልደከ - ልጅኽን✍️
ተሻጋሪ ግሶች ምሳሌ፣ ቀተለ/ገደለ/፣ ቀደሰ / አመሰገነ/፣ በልሀ /በላ/ እናም ሲተረጎም “ን” የሚለውን ትርጉም ያመጣል፡፡
ረከብነ ሕይወተ = ሕይወት
ን አገኘን ሲሆን በግእዝ ግን
ተረክበ ሕይወተ = ሕይወት ተገኘ ቢል ግን አይለውጥም /ስሕተት የለበትም/ ምክንያቱም ተረክበ ተቀተለ እና የመሳሰሉት ተገብሮ/ የማይሻገሩ ናቸውና፡፡
ምሳሌ፦
ባለቤት /ተገብሮ/ (subject)
ዝ ቤት ሐዲስ ውእቱ -- ይህ ቤት አዲስ ነው፤
ተወልደ ለነ -- ተወለደልን
ተሰቅለ ለነ -- ተሰቀለልን
ሖረ ኀበ ገዳም -- ወደ ገዳም ኼደ።
ተሰብረት ሐመርየ ውስተ ባሕር - መርከቤ በባሕር ውስጥ ተሰበረች።
ቀረብከ አንተ ኀበ እሳት - ወደ እሳት ቀረብክ።
መጽአ ብየ ከይሲ - እባብ መጣብኝ
እነዚህ ከላይ ያየናቸው የማይስቡ/የማይሻገሩ ናቸው።
✍️
ተሳቢ / ገቢር/ (direct object)
ምሳሌ፦
ወልድየ ሐነፀ ቤተ = ልጄ ቤትን ሠራ፤
ወለደት ወልደ ማርያም -- ማርያም ልጅን ወለደች፤
አንተ ሰበርከ ሐመረ - አንተ መርከብን ሰበርክ።
አቅረበ ለነ ማየ - ውኃን አቀረበልን።
መኑ ሰቀለ ወልደኪ፧ -- ልጅሽን ማን ሰቀለው?
አነ ቀተልኩ ከይሴ - እባብን ገደልኩ፤
ከላይ ያየናቸው የሚስቡ/ የሚሻገሩ ናቸው።
📖
ለማጠቃለል የሚከተሉት ሕግና ሥርዓት አሉት።1. ከላይ እንዳየነው የመጨረሻው ሳድስ ፊደል ወደ ግእዝ ይለወጣል፡፡
ቤት = ቤተ ይሆናል፡፡
2. ካእብ ወደ ሳብእ ይለወጣል፡፡ ኩሉ= ኩሎ ይሆናል፡፡
ወሖረ ኩሉ ኀበ ቤቱ - ሁሉ ወደ ቤቱ ሄደ።
እግዚአብሔር ያፈቅር ኩሎ - እግዚአብሔር ሁሉን ይወዳል።
3. ሳልስ ወደ ኀምስ ይለወጣል፡፡ ብእሲ--- ብእሴ ዊ=ዌ ይሆናል፡፡
☑️ ተገብሮ =ብእሲ ሖረ ኀበ ሐቅል
☑️ገቢር =ርኢኩ ብእሴ ውስተ ቤተ
☑️ ተገብሮ = አቤሜሌክ ኢትዮጵያዊ ውእቱ።
☑️ ገቢር = ወባረከ
እግዚአብሔር ውእተ ኢትዮጵያዌ - እግዚአብሔር ኢትዮጵያዊውን ባረከ።
4. የተጸውኦ ስሞች
ምሳሌ ሃ ሲጨምር፡፡
ሙሴ = ሙሴሃ ይሆናል።ተለውነ ✍️
https://t.me/geeztheancient