መናፍቃን በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan



Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


የሕፃናት ጥምቀት በ40 በ 80 ማጥመቅ ተገቢነውን?

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕጻናትን በ40 እና በ80 ቀን ስታጠምቅ ምስጢራትን፣ ምሳሌዎችን፣ ትውፊትን እንዲሁም የጌታንና የሐዋርያትን አስተምህሮ መሠረት አድርጋ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንደሚናገረው ቤተ ክርስቲያን ሕጻናትን የምታጠምቀው ኃጢአትበደል አለባቸው ብላ ሳይሆን ከለጋነት ዕድሜያቸው ጀምረው ፍቅሩን እያጣጣሙ እንዲያድጉ የሚያስችላቸውን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆንን ጸጋ ልትሰጣቸው ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሕጻናትን የምታጠምቀው ያውቃሉ ወይም አያውቁም ብላ አይደለም፡፡ የቤተሰቦቻቸውን እምነትና ፈቃድ ምስክር በማድረግ ነው እንጂ፡፡
መጀመሪያ የጥምቀትን ጥቅም ማወቅ ያስፈልጋል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ገላ 3፡27፤ከክርስቶስ፡ጋራ፡አንድ፡ትኾኑ፡ዘንድ፡የተጠመቃችኹ፡ዅሉ፡ክርስቶስን፡ለብሳችዃልና።👈ስለዚኽ ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ እንኾን ዘንድ እና ልጅነትን እንድናገኘ ከሆነ ክርስቶስ ህጻናት ከሱ ጋ አንድ ይሆኑ ዘንድ አይፈቅድምን እሱስ ህጻናት ወደእኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው ብሏል ምክንያቱም ህጻናት ከክፋት ከተንኮል ከምንፍቅና የራቁ ስለሆኑ ቃሉን በትክክል ከመገብካቸው እንደሚቀበሉ ግልጽ ነው እና ቃሉንም ለመቀበል ጥበብን እንድገልጽላቸው ጸጋው ያስፈልጋቸዋል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ቲቶ 2:12-13፤ይህም፡ጸጋ፥ኀጢአተኝነትንና፡ዓለማዊን፡ምኞት፡ክደን፥የተባረከውን፡ተስፋችንን፡ርሱም፡የታላቁን፡
የአምላካችንንና፡የመድኀኒታችንን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ክብር፡መገለጥ፡እየጠበቅን፥ራሳችንን፡በመግዛትና፡
በጽድቅ፡እግዚአብሔርንም፡በመምሰል፡ባኹኑ፡ዘመን፡እንድንኖር፡ያስተምረናል፤👈 በእውነት ከጸጋው እርቀው ይኑሩ የሚል የዲያቢሎስ ሥራ እንጅ የሰው ሥራ አይደለም አይደለም ህጻናትን ምንም ኃጢያት የማያቁትን ኃጢያቶኞች በኾንበት ግዜ በቸርነቱ አዳነን ጸጋ ከእኛ እርቃ በነበረብት ግዜ እግዚአብሔር ለእኛ ጸጋውን መስጠት ነበረና ፍላጎቱ እሱ ተሰቅሎ ሁላችን የሱ ልጆች እንሆን ዘንድ ፍቃዱ ነው መጽሐፍ ቅዱስ "የዓመነ የተጠመቀ ይድናል ብሏል " ጌታችን ለምን ይሄን አለ ስንል በክህደት ለነበሩት በኑፋቄ ለቆዩት ከጥርጥራቸው ተመልሰው መጠመቅ እንዳለባቸው ሲናገር ነው ምክንያቱም በኑፋቄ ውስጥ ኹነው ቢጠመቁ ሊድኑ ስለማይችሉ ህጻናት ደግሞ ኑፋቄ እንደሌለባቸው እራሱ ጌታችን ነግሮናል መንግሥተ ሰማይ ለእንደነዚኽ ላሉት ናት ብሎ እናም ሰዎች ህጻናት ከእግዚአብሔር እርቀው ከጸጋው ተለይተው ብብሉይ ኪዳን ሥርዓት ይኑሩ የሚል የማን ሃሳብ ይመስላችኃል የዲያቢሎስ ካልሆነ ምክንያቱም ዲያብሎስ ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ የሚያደርገን በብሉይ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ከ እኛ እርቆ የነበረውን የምናገኝበት እንደው ያቃል። ስለዚኽ እስከሚያድጉ እያለ የሚያግዛቸው ጸጋ እንዳይኖር በኃጢያት ወድቀው የእግዚአብሔር ልጆች እንዳይኾኑ ነውና ፍላጎቱ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ከነቤተሰቦቻቸው ይጠመቁ እንደነበር ይነግሩናል
በሐዋርያት ስብከት ያመኑና በማንኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሁሉ ይጠመቁ ነበር (የሐ ሥራ 16፡ 15 1ቆሮ 1፡15) ። በኋላ ግን ወላጆቻቸው ሊያስተምሯቸው ቃል እየገቡ ልጆቻቸውን ወንዶችን በአርባ ሴቶችን በሰማንያ ቀናቸው ማጥመቅ ተጀመረ ።

በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ህጻናት ወላጆቻቸው እንዲሁም ክርስትና እናት ወይም አባት ሃይማኖታቸውን ሊያስተምሯቸው ሃላፊነት ወስደው የክርስትና አባት ወይም እናት በተጨማሪ ቃል ገብተው ክርስትና በመነሳት (በመጠመቅ) የወላጆቻቸውን ርስት መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉ።ከአርባ እና ከሰማንያ ቀን በኋላ የሚመጡ ተጠማቂዎች ግን ሃይማኖታቸውን ተምረው ካመኑ በኋላ በማንኛውም የዕድሜ ክልል መጠመቅ ይችላሉ ። በሕይወት እስካሉ ድረስ መቸም ቢሆን ከመጠመቅ የሚያግዳችው ነገር የለም ።

ሕፃናት በማኅፀን ሳሉ መንፈስ ቅዱስ ከሞላባቸው ሲወለዱ እንዳይጠመቁ የሚከለክለቸው ምንድን ነው (ሉቃ 1፡15 ኤር 1፡4-5)፡፡👈ስለዚህ እግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆነ ገና በእናታቸው ማህጸን ሳሉ መንፈስ ቅደስ ከተቀበሉ ህጻናት መጠመቅ የለባቸውም የሚል የማን ሥራ ነው የዲያብሎስ ካልሆነ ምክንያቱም ሰይጣን ሌላው የጥምቀት ጥቅም ምን እንደው ያቃል መጵሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ጥምቀት የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ እንድንቀበል ያደርገናል ሐዋ 38፤ጴጥሮስም፦ንስሓ፡ግቡ፥ኀጢአታችኹም፡ይሰረይ፡ዘንድ፡እያንዳንዳችኹ፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ስም፡ተጠመቁ፤ #የመንፈስ፡ቅዱስንም፡ስጦታ፡ትቀበላላችኹ።👈 ይሄን ስጦታ እግዚአብሔር እንድቀበሉ አይፈልግምን እሱስ ይፈልጋል ነገር ግን የሰይጣን ፍላጎት እንጅ ሌላው መጠመቃችን ምን ጥቅም አለው ያልን እንደው ሮሜ 8:26-27 መንፈስ ድካማችን እንደሚግዘን ይነግረናል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለን ጌታችንም “ሰው ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ…” ያለው ሕፃናትንም ይመለከታል (ዮሐ 3፡8)፡፡👈 ታዲያ ህጻናት ሰው አይደሉም ይባላልን ነገር ግን የዲያብሎስ ዓላማ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ እንዳንኾን እና የእግዚአብሔር ልጆች እንዳንኾን ነው ከመንግሥቱ እንድንለይ እስኪ እዚኽ ቃል ጋር ተመሳሳይ የሆነ ታሪክ እንይ ትንቢተ ዮናስ Jonah 3

ምዕራፍ፡3።
1፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ኹለተኛ፡ወደ፡ዮናስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
2፤ተነሥተኽ፡ወደዚያች፡ወደ፡ታላቂቱ፡ከተማ፡ወደ፡ነነዌ፡ኺድ፥የምነግርኽንም፡ስብከት፡ስበክላት፡አለው።
3፤ዮናስም፡ተነሥቶ፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ነነዌ፡ኼደ፤ነነዌም፡የሦስት፡ቀን፡መንገድ፡ያኽል፡
እጅግ፡ታላቅ፡ከተማ፡ነበረች።
4፤ዮናስም፡የአንድ፡ቀን፡መንገድ፡ያኽል፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ውስጥ፡ሊገባ፡ዠመረ፤ጮኾም፦በሦስት፡ቀን፡
ውስጥ፡ነነዌ፡ትገለበጣለች፡አለ።
5፤የነነዌም፡ሰዎች፡እግዚአብሔርን፡አመኑ፤ለጾም፡ዐዋጅ፡ነገሩ፥ከታላቁም፡ዠምሮ፡እስከ፡ታናሹ፡ድረስ፡
ማቅ፡ለበሱ።
6፤ወሬውም፡ወደነነዌ፡ንጉሥ፡ደረሰ፤ርሱም፡ከዙፋኑ፡ተነሥቶ፡መጐናጸፊያውን፡አወለቀ፡ማቅም፡
ለበሰ፥በዐመድም፡ላይ፡ተቀመጠ።
7፤ዐዋጅም፡አስነገረ፥በነነዌም፡ውስጥ፡የንጉሡንና፡የመኳንንቱን፡ትእዛዝ፡አሳወጀ፥እንዲህም፡አለ፦ሰዎችና፡
እንስሳዎች፡ላሞችና፡በጎች፡አንዳችን፡አይቅመሱ፤አይሰማሩም፡ውሃንም፡አይጠጡ፤👈 ተመልከቱ እዚኽ ጋ እግዚአብሔር ህጻናት እና እንስሳት ይጹሙ አላለም ነነዌ ትገለባበጣለች እንጅ ነገር ግን የነነዌ መገለባበጥ ለሁሉም ፍጥረት መሆኑን ስላወቁ ምንም የማያቁትን እንስሳት እና ህጻናት ጭምር እንድጾሙ አደረጉ ምክንያቱም ነነዌ ከተገለባበጠች ሁሉም ፍጥረት እንደሚጠፋ ስላወቁ የእኛ እናትና አባትም ሰው ካልተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም የተባለው ለሁሉም ስለሆነ አስጠመቁን ገና በሕጻንነታችን በጥምቀት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ከክርስቶስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ልጆች እንሆን ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል ገላ 3:26፤በእምነት፡በኩል፡ዅላችኹ፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡የእግዚአብሔር፡ልጆች፡ናችኹና፤
27፤ከክርስቶስ፡ጋራ፡አንድ፡ትኾኑ፡ዘንድ፡የተጠመቃችኹ፡ዅሉ፡ክርስቶስን፡ለብሳችዃልና።👈እናም ክብር ምስጋና ለእናት አባቶቻችን ይሁንና ገና ህጻን ሳለን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብለን እግዚአብሔርን እንድናቅ እንድናገለግል ተጠመቅን ለመጥምቁ ዮሐንስ ገና በእናቱ ማህጸን ሳለ አምላኩን እንዳወቀና የቅድስት ድንግል ማርያምን ድምጽ ሰምቶ በደስታ እንደዘለለ እና እንደሰገደ ለእኛም ገና ህጻን ሳለን እሱን አውቀን እንድናድግ ተጠመቅን ።
@haymanote1


: 13 - 14
በጣም የሚገርመውና የሚያሳፍረው እነዚህ
" ሃይማኖት አያድንም " ብለው የሚሰብኩ ሰዎች ይቺ አንዲቷ እውነተኛዋ ሃይማኖት የእኛ ናት አይሉም ፥ የእኛ ሃይማኖት ያድናል ብለው እንኳን በሙሉ ልብ አይናገሩም ፤ ወይ ደግሞ ይቺኛዋ ናት ብለው አይመሰክሩም ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረውና ከሚመሰክረው በተቃራኒ ሄደው በራሳቸው " ሃይማኖት አያድንም " የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰው ይህንኑ ይሰብካሉ ያስተምራሉ ።
መጽሐፍ ቅዱስ " ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ " 1ኛ.ተሰሎ 5 : 21 አለ እንጂ እግዚአብሔር የመሰረታትን ፥ ቅዱሳን የተጋደሉላትን ፥ አንዲቷን እውነተኛዋን ሃይማኖት ፤ በሰው ፍልስፍና ከተመሰረቱት ሐሰተኛ ሃይማኖቶች ጋር አንድ ላይ ጨፍልቀህ ሃይማኖት አያድንም ብለህ ስበክ ብሎ አላዘዘም ። እውነተኛዋን ሃይማኖት ፈልገን ማግኘት ሲገባን ጭራሽ ሃይማኖት አያድንም እያሉ መስበክ የበደል በደል ነው ።
ያለ ሃይማኖት ያለ እምነት እግዚአብሔር የሚገኝ ፥ ክርስቶስ የሚመለክ ፥ እውነት ላይ የሚደረስ ይመስል መጽሐፍ ቅዱስን እንጂ ሃይማኖትን አትከተል ይሉሃል ፤ ወንድሜ መጽሐፍ ቅዱስን የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ ለመቀበል ( ለማመን ) እንኳን መጀመሪያ ሃይማኖት ( እምነት ) እንደሚያስፈልግ አልገባህም ?
ሃይማኖት ( እምነት ) አያድንም ብለን ፤ መልካም ሥራ አያጸድቅም ብለን የት ልንደርስ ነው ? ሃይማኖትም ምግባርም ካላዳነ ካላጸደቀን ታዲያ ምንድን ነው የሚያድነን የሚያጸድቀን ?
✞ አንድ የሚገርመኝ የእግዚአብሔር ቃል አለ ቃሉ
" ሃይማኖቴን አልካድህም።" ይላል ራእይ 2 : 13
ይሄ የምስጋና ቃል የተነገረው በጴርጋሞን ላለው ቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ነው ፤ ለምን ይህ ቃል ለሱ ተነገረ ? ካልክ
በሰይጣን ፈተና ተሸንፎና ወድቆ እምነቱን ሃይማኖቱን
ስላልካደና ስለጸና ነው ። እዚህ ላይ የእውነተኛዋ ሃይማኖት መስራችና ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር ነውና ራሱ እግዚአብሔር በቃሉ
" # ሃይማኖቴን " ሲለው ታያለህ ?
' ሃይማኖት አያድንም ' ለሚልህ ጌታ መገዛት ይሻልሃል ? ወይስ
" ሃይማኖቴን እንዳትክድ " ለሚልህ ጌታ መገዛትና ለቃሉ መታዘዝ ይሻልሃል ?
ወንድሜ ምርጫው ያንተ ነው።
እግዚአብሔር ወደ ቀናችው ወደ ቀደመችው መንገድ ይምራን አሜን ።
@haymanote1


ሃይማኖቴን አልካድህም
አብዛኞቻችን መሰረታዊ የሆነ የግንዛቤ ችግር ያለብን ያልተማርን ጨዋ ሰዎች ነን ።
በተለይ " ሃይማኖትን " በተመለከተ የምንሰብከውና የምንሰጠው አስተያየት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገረው እውነት በተቃራኒ ነው ። የገባው አዋቂ ሰው መስለን ፥ በግምትና በመላምት አፋችሁን ሞልተን በድፍረት የምንናገረው ስለማናቀው ነገር ነው ። እንዴት ? እስኪ አብራራልን ካላችሁ
" ሃይማኖት " የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ነው ፥ ሃይማኖት
" ሃይመነ " ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማመን ፥ መታመን ፥ እምነት ፥ አመኔታ ማለት ነው ። አማርኛው መዝገበ ቃላት በፈጣሪ ማመንና መታመንን # እምነት ሲለው የግዕዙ ደግሞ በፈጣሪ ማመንና መታመንን # ሃይማኖት ይለዋል ።
መጽሐፍ ቅዱስ ከግዕዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎም አንዳንድ ቦታ ላይ " ሃይማኖት " የሚለው የግዕዙ ቃል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ " እምነት " ተብሎ ሲቀመጥ አንዳንድ ቦታ ላይ ግን ሳይተረጎም እንዳለ " ሃይማኖት " የሚለውን የግዕዙን ቃል ወርሶ ተቀምጧል ።
ባጭርና ግልጽ አማርኛ
" ሃይማኖት " ማለት እምነት ማለት እንጂ አንዳንዶቻችን ሳናቅ በድፍረት እንደምንለው ተቋም ወይም ድርጅት ማለት አይደለም ። ሃይማኖትና እምነት የቋንቋ ልዮነት እንጂ የትርጉም ልዩነት የላቸውም ፤ እምነት አልክ ፣ ሃይማኖት አልክ ሁለቱም አንድ ናቸው ፣ ያለመማርና ቋንቋን ያለማወቅ ችግር ካልሆነ በቀር ።
ይሄንን በጣም ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎችን ለአብነት እየጠቀስን ማየት እንችላለን ነገር ግን ሰው ላለማሰልቸት ጥቂት ማስረጃ ብቻ እንይ ፦
✞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ለጢሞቴዎስ
" በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ # ሃይማኖትን ይክዳሉ "
ሲል ነግሮታል ።
1ኛ ጢሞ 4 : 1-2
ሐዋርያው ሃይማኖታቸውን ይክዳሉ ሲል ተቋማቸውን ( ድርጅታቸውን ) ይክዳሉ ማለቱ ሳይሆን እምነታቸውን ይክዳሉ ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው ፤ ምክንያቱም የሚያስቱ መናፍስትና አጋንንት ዋና ሥራቸውና ዓላማቸው ሰውን ድርጅት ( ተቋም ) ማስቀየር ሳይሆን አምኖ የሚድንባትን እውነተኛ ሃይማኖቱን
/ እምነቱን / አስክደው ከእግዚአብሔር እንዲጣላና በመጨረሻም እንዲፈረድበት ማረግ ነው ።
ለምን ይመስልሃልጌታ " የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን ? " ሉቃስ 18፡: 8 ብሎ በመጨረሻው ዘመን እምነት ( ሃይማኖት ) ያለው ሰው መገኘቱን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የከተተው ?
ሃይማኖት አያድንም የሚለው ስብከት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የሌለው የሚያስቱ መናፍስትና የአጋንንት ትምህርት ነው ።
✞ ሃይማኖቱን ከካደ ሰው ይልቅ ፤ ምንም ሃይማኖት ( እምነት ) የሌለው Atheist / Pagan ሰው እንደሚሻል ታቃውቃለህ ? ሐዋርያው ቅ.ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በመጨረሻው ዘመን ያሉ ሰዎች ሃይማኖትን ይክዳሉ ብሎ ካስተማረው በኃላ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ ደግሞ " ... ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።"
1ኛ ጢሞ 5 : 8 ብሎ አሰረግጦ እቅጩን ነግሮታል። ሃይማኖት ማለት " ተራ ድርጅትና ተቋም " ቢሆን ኖሮ ሐዋርያው ሃይማኖቱን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው ብሎ ይናገር ነበር ?
ሃይማኖቱን የካደ ፥ ከማያምን ( እምነት ከሌለው ) ሰው የከፋ ነው የተባለበት ምክንያት አንድም ተመለስ ሲባል ከማያምነው ሰው ይልቅ ላለመመለስ ጥቅስ እየጠቀሰ ስለሚከራከር ነው ፤ አንድም ሃይማኖት የሌለው ሰው
ቢበዛ ራሱን ይዞ ነው የሚጠፋው ፥ ነገር ግን ሃይማኖቱን የካደ ሰው ግን ራሱን ብቻ ሳይሆን ብዙዎቹን ይዞ ይጠፋልና ነው ። ለዚህም
እነ አርዮስን ፣ እነ ንስጥሮስን ፣ እነ መቅዶንዮስን ፣ እነ ፓፓ ሊዮንን ፣ እነ ሉተርን ፣ እነ ዊሊያም ሚለርን ወዘተ ... ሃይማኖታቸውን ክደው ለአንዲቷ ቤተ ክርስቲያን መከፋፈልና ለብዙዎች መጥፋት ምክንያት
የሆኑትን ማስታወስ ከበቂ በላይ ነው ።
ሐዋርያው " አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ፥ ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ፥ ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን ፤ መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን ፤ በኋላም # የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው " ዕብ 6 : 4 - 6 ማለቱ ሃይማኖትን መካድ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያሳየናል ።
✞ ሐዋርያው ቅ.ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ " መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ " ብሎታል ።
2ኛ ጢሞ 4 : 7
እስቲ አንተ ራስህ ፍረድ ሐዋርያው ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ ሲል እምነቴን ጠብቄያለሁ ማለቱ ነው ወይስ ድርጅቴን ጠብቄያለሁ ማለቱ ነው ? ሐዋርያው በቃልም በተግባርም ያስተማረን
' ሃይማኖት አያድንም ' እያለ ሳይሆን ሃይማኖታችሁን ጠብቁ እያለ ነው ።
✞ ሃይማኖታችንን መጠበቅ ፥ በሃይማኖታችን መጽናት ብቻ አይደለም ለሃይማኖታችን # እንድንጋደል ሐዋርያው ይሁዳ ባለችው አንዲት መልዕክቱ ሳያሳስበን አላለፈም
" ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ ። " ብሎናል ይሁዳ 1 : 3
ሐዋርያት ሃይማኖታችሁን እንዳትክዱ ፤ ሃይማኖታችሁን ጠብቁ ፤ ለሃይማኖታችሁ ተጋደሉ ያሉት ያለ ምክንያት ይመስልሃል ? ያለ ሃይማኖት ድኀነት ፥ ያለ ሃይማኖት ዘላለማዊ ሕይወት፥ ያለ ሃይማኖት መንግስተ ሰማያት ስለማይገኝ ነው ።
ክርስቲያን የሚያምነውም የሚታመነውም በክርስቶስ ነው ፤ ይሄ ለእሱ ሃይማኖቱ / እምነቱ / ነው ፤ ከውሃና ከመንፈስ የተወለደውን በደሙ የከበረው አንድ ክርስቲያን ሄደህ ' ሃይማኖትህ አያድንህም ' ስትለው የምታምንበት የምትታመንበት ክርስቶስ አያድንህም እያልከው መሆኑ ገብቶሃል ?
ሰይጣን የመጀመሪያ ሥራው
" ሃይማኖት " ሰዎች የፈጠሩት ተራ ድርጅትና ተራ ተቋም እንደሆነ አንተን ማሳመን ነው ፤ ይሄንን ካመንክለት በኃላ ሃይማኖት ማለት ለአንተ ሰዎች ያቋቋሙት አንድ ተራ ነገር ይሆንብሃል ፤ እንዲህ አርጎ በደንብ ለክህደት ካመቻቸህ በኃላ ድርጅት ቀይር ብሎ እምነትህን ያስቀይርሃል ያስክድሃል ።
✞ ያልተበረዘችው ፥ ያልተከለሰችው ፥ እውነተኛዋ ሃይማኖት አንዲት ናት ፤ መጽሐፍ ቅዱስ " አንድ ጌታ ፥ አንድ ሃይማኖት ፥ አንዲት ጥምቀት " በማለት ይህንን እውነት ይመሰክራል ።
ኤፌ 4 : 5
የዚህች የአንዲቷ ሃይማኖት መስራች ደግሞ ሰው ሳይሆን
ራሱ ክርስቶስ ነው ።
" የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ
ክርስቶስን ተመልከቱ " እንደተባለ ። ዕብራ 3 : 1
ማንም ከዚህች አንዲት ሃይማኖት ውጭ ሌላ ሰው ሰራሽ ሃይማኖትን እንዲመሰረት አልተፈቀደለትም
" ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም " ተብሏል ።
1ኛ ቆሮ 3 : 11
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ብዙ ሃይማኖቶች ( እምነቶች ) አሉ ፤ ለምሳሌ ፦
ይሁዲ ፣ ቡድሂዝም ፣ ሂንዱይዝም ፣ ኮንፊዪሽስ ፣ እስልምና ወዘተ ... ሌላውን ትተን በክርስትና ስም ብቻ እየሚጠሩ እንኳን ከ 22,000 በላይ የሆኑ ሃይማኖቶች ( እምነቶች ) አሉ ፤ ሁሉም ሃይማኖቶች ያድነናል ብለው የሚያምኑበትና የሚታመኑበት ፈጣሪ / አምላክ / አላቸው ፤
ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ስንመዝናቸው በነብያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ከታነጸችው ፥ ወደ ሕይወት መንገድ ከምትወስደው ከአንዲቷ እውነተኛ ሃይማኖት በስተቀር ፥ ሁሉም በሰው ፍልስፍና የተመሰረቱ ወደ ሞት የሚወስዱ የጥፋት መንገዶች ናቸው ። ማቲ 7


ስ የጌታን ክብር ተጋፋ አንልም፡፡
ቅዱሳንን የምናመሰግናቸው የእግዚአብሔር ስለሆኑና ነቢዩ እንዳለው "እግዚአብሔርም በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ስለሆነ ነው" ሥዕሉ ሲደነቅለት የሚበሳጭ ሠዓሊ እንደሌለ ሁሉ የእርሱ ድንቅ ሥራዎች ሆነው ፣ እርሱን አገልግለው ሲወደሱ ፈጣሪን ደስ ይለዋል እንጂ አያዝንም። ጠርሙስ ሰብራ ሽቱን በእግሩ ላይ ላፈሰሰለች ሴት "ወንጌል በሚነገርበት ሥፍራ ሁሉ ያደረገችው ነገር ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል" ብሎ የተናገረ ጌታ አንገታቸው ተሰብሮ ደማቸውን ስለ ስሙ ስላፈሰሱ ቅዱሳን በዓለም ሁሉ ቢነገርና ቢዘመር የሚከለክል አይደለም። (ማቴ 26:13)
ምስጋና እንኳን ለቅዱሳን በሃይማኖታችን ከጸናን ለእኛም ለደካሞቹም አልተከለከልንም ፣ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና :–
"ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ" ቆላስ 2: 7
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@haymanote1


፡፡ ‹ትውልድ ሁሉ› አለች እንጂ ሰው ሁሉ አላለችምና ከየትውልዱ የማያመሰግኗት ቢገኙ አይደንቅም ፤ ከእኛ የሚጠበቅብን እንደ ኖህ ‹በትውልዳችን ጻድቅ› ሆኖ መገኘት ብቻ ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል ‹ደስ ይበልሽ› ቢላትም እኛ ‹ደስ ይበልሽ› አንላትም የሚሉ ሰዎች መላእክት ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› የሚሉትን እግዚአብሔርም ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ› ለማለት እንዴት ፈቃደኞች ሊሆኑ ይችላሉ?
ለቅዱሳን የሚቀርበው ምስጋና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን የምንደመድመው መድኃኔዓለም ክርስቶስ ራሱ ለመጥምቁ ዮሐንስ የተናገረው ምስጋና ነው፡፡ ‹‹ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን … እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም›› (ሉቃ. 7፡26-28) ከዚህ በላይ ምስጋና ከየት ይመጣል? በዜማ መሆኑ ከሆነ ችግሩ በንባብ እንለዋለን።
የመጥምቁ ምስጋና በቅዱስ ገብርኤልም አንደበት ተነግሮ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የዮሐንስን ልደት ሲገልጥ ‹‹በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነበር ፤ ወደ መዝሙር ሲለወጥ ‹ዮም ፍስሓ ኮነ በእንተ ልደቱ ለዮሐንስ› እንደማለት ነው፡፡
አባቱ ዘካርያስ ደግሞ ‹‹አንተ ሕፃን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ›› ብሎ ነበር ይህም ‹ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ፤ አርኩ ለመርአዊ ትሰመይ›› የሚለው መዝሙር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዱሳን ስትዘምር ቃላትና ግጥም የምትዋሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡
‹‹ሐውፅ እምሰማይ ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ›› (ፀሐይ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ከሰማይ ሆነህ ጎብኝ)
የሚል መዝሙር ቢዘመር ‹‹ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ›› የሚለውን የተስፋ ቃል ይዞ ነው፡፡ (ማቴ. ፲፫፥፵፫)
‹‹ጊዮርጊስ ኃያል ኮከበ ክብር›› ተብሎ ቢዘመር ‹‹ብዙዎችን ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ›› የሚለውን ይዞ ነው፡፡ (ዳን. 12፡3)
‹‹አቡነ አረጋዊ ሆይ ነፍሴ ዛሬ በአንተ ፊት የከበረች ትሁን!›› ‹‹ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም ፤ ወባርከኒ አባ አረጋዊ›› ተብሎ ሲዘመር ብንሰማ አንድ የመቶ አለቃ በነቢዩ ኤልያስ ፊት ተንበርክኮ ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ነፍሴ አሁን በፊትህ የከበረች ትሁን›› ብሎ ካቀረበው ልመና ተወስዶ ነው፡፡ (2ነገሥ. 1፡13)
በአንዳንድ ሥፍራ ለቅዱሳን በሚቀርቡ ምስጋናዎች ላይ ለፈጣሪ የቀረቡ የምስጋና ቃላት ተወስደው ለቅዱሳን ሲቀርቡ ይታያል፡፡ ይህንን የሚያዩ ሰዎች ቅዱሳን የተመለኩ ፣ የፈጣሪ የባሕርይ ክብሩ ለቅዱሳን የተሠጠ መስሏቸው ይተቻሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ለቅዱሳን በሚዘመሩ መዝሙራት ሁሉ ላይ የሚታረም ነገር አያጡም፡፡ ሆኖም ይህንን ዓይነት እርማት ላድርግ ብሎ የሚነሣ ሰው መጽሐፍ ቅዱስንም ማረም ሊኖርበት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር የተነገረን ቃል ለቅዱሳን ሲሠጥ በተደጋጋሚ እናገኘዋለን፡፡
ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት ፡-
‹‹ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዓለም ብርሃን ናቸው›› ሲባል ‹‹የዓለም ብርሃን ክርስቶስ ብቻ ነው›› ብሎ የሚቃወም ቢኖር ራሱ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ‹‹እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ፤ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ›› ብሏል፡፡ የእርሱ ብርሃንነት የባሕርይው የቅዱሳን ብርሃንነት ግን ከእርሱ የተሠጠ ነው ብለን እንከፍለዋለን እንጂ የቅዱሳንን ብርሃንነት አንክድም፡፡ (ማቴ. 5፡14)
አንዳንድ ምእመናን ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ሲመሰክሩ ‹‹ለእመቤቴ የሚሳናት ነገር የለም›› ሲሉ የሚሰማ ሰው ራሱን እየነቀነቀ ‹የእኛ ሰው Bible ላይ ብዙ ይቀረዋል› ብሎ ሊመጻደቅ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያውቅ ከሆነ ግን ‹‹እምነት ቢኖራችሁ የሚሳናችሁ ነገር የለም›› የሚለውን የጌታ ቃል ፣ ‹‹ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ›› የሚለውን የጳውሎስ ቃል በሰማበት ጆሮው ‹ያመነችው ብፅዕት› ‹የልዑል ኃይል ያደረባት› ድንግል ‹የሚሳናት የለም ሲባል ከመቆጣት ይልቅ ለምእመናን የተሠጠውን እምነትና ማስተዋል ያደንቃል፡፡ (ማቴ. 17፡20 ፣ ፊል. 4፡13 ፣ ሉቃ.1፡35፣45)
ለእግዚአብሔር የተነገሩ ቃላት ለቅዱሳን ተደግመው ብናገኛቸው እንኳን ትርጉሙን እንረዳለን እንጂ የእግዚአብሔርን ክብር ቅዱሳን ወሰዱ አንልም፡፡ ለምሳሌ ጌታ መጥምቁ ዮሐንስን ‹የሚያበራ መብራት ነበር ፤ በብርሃኑ ደስ ሊላችሁ ወደዳችሁ› ሲለው ወንጌላዊው ደግሞ ‹‹እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ብርሃን አልነበረም›› ብሎታል፡፡ የማንን እንቀበል? የጌታችንን ንግግር ወይስ የወንጌላዊውን? ዮሐንስ ብርሃን ነው ወይንስ አይደለም? መልሱ ግልጥ ነው ዮሐንስ ብርሃን ነው ፤ የዮሐንስ ብርሃንነት ግን ከክርስቶስ ብርሃንነት ጋር ሲተያይ የሻማና የፀሐይ ብርሃን ያህል ነውና ብርሃን አልነበረም ተብሏል ብለን እንረዳዋለን፡፡(ዮሐ. 1፡8 ፤ 5፡35)
የእግዚአብሔርን ክብር አስጠብቃለሁ ብሎ የትርጉም ልዩነቱን ሳይረዳ ለቅዱሳን የሚቀርብን ምስጋና የመተቸት ዝንባሌ ያለው ሰው ግን ይህ አካሔዱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚያጣላው ነው፡፡ ሰሞኑን አንዳንድ ሰዎች ‹የአዳም ፋሲካው ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ› የሚለውን ቃል በመጥቀስ እንዴት ድንግል ማርያም ፋሲካ ትባላለች ‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል› ይል የለምን እንዳሉ ሰማን፡፡ ስለ እንክርዳድ ማውራት እንክርዳድን ዝነኛ እንጂ ስንዴ ስለማያደርገው ተናጋሪዎቹን ትተን ጉዳዩን እናስተውለው፡፡
ወደ ሌላ ዝርዝር ሳንገባ አንድ ጥያቄ እናንሣ ፤ ክርስቶስ ፋሲካ ነው ወይንስ የፋሲካ በግ? ፋሲካ የሚባለው በዓሉ ነው? ወይንስ በጉ ነው? የታረደው በዓሉ ነው? ቢባል ምን ይመለሳል? "ፋሲካን እረድ" ሲል በጉን ነው (2ዜና 35:5)፣ "ይህ ፋሲካ ለእግዚአብሔር ተፈሰከ" ሲል በዓሉን ነው። (2ነገሥ 23:23)
ፋሲካ ሲል በዓሉን ከሆነ መሻገሪያ ፣ ደስታ ማለት ነውና ለድንግል ማርያምም ሊነገር ይችላል፡፡ ‹ታርዶአል› የተባለው ግን በጉን ነውና እመቤታችንን እመ በግዑ (የበጉ እናት) እንጂ የታረደችው በግ ብለናት እንደማናውቅ ግልጥ ነው፡፡ ጨርሶ ለክርስቶስ የተነገረ ቃል ለእርስዋ ለምን ይደገማል? ከሆነ ደግሞ እስቲ የቅዱስ ጳውሎስን ንግግር እንመልከት፡-
ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 2:20 ላይ ፡- ‹‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ›› ብሏል፡፡ አልፎ ተርፎም ‹‹እኔ ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› ብሏል፡፡ (ገላ. 6፡14)
የዚህ ንግግር ትርጉም ምንድን ነው? ቅዱስ ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎ ነበር ማለት ነው? የተሰቀለው በቀኙ ነው የግራው?"ለዓለም ተሰቀልኩ" እንዴት አለ? እውን ለዓለም የተሰቀለው ጳውሎስ ነውን? ክርስቶስ አይደለምን? የፋሲካው ሲገርምህ ለዓለም ተሰቅዬአለሁ ያለ መጣ? ጳውሎስ የተሰቀለውን የክርስቶስን ክብር መሸፈኑ ነውን?
እንደዚያ እንዳንል ደግሞ ራሱ ጳውሎስ ‹‹ጳውሎስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ብሎ አሳርፎናል፡፡ (1ቆሮ 1፡13) ስለዚህ መተርጎም መብራራት አለበት እንጂ ቃሉ ተመሳሰለ ተብሎ አይብጠለጠልም። ጫማ ይስተካከላል እንጂ እግር አይስተካከልም እንደሚባለው መስተካከል ያለበት የእኛ አረዳድ እንጂ የመጽሐፉ ቃል አይደለም።
ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ሲል የክርስቶስን የመከራ መንገድ ተከትያለሁ ፣ የመከራው ተሳታፊ በመሆን የክብሩ ተካፋይ እሆናለሁ ሲል ነው። "ለዓለም ተሰቅልኩ" ያለው ደግሞ በክርስቶስ መከራ በማመኔ ለዓለማዊ የኃጢአት ሥራ ሙት ሆኜአለሁ ማለቱ ነው ብለን እናብራራለን እንጂ ጳውሎ


+++ ኦርቶዶክሳውያን ለቅዱሳን ለምን ይዘምራሉ? +++
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት ብዙ መገለጫዎች አንዱና ዋነኛው ‹ምስጋና የሚገባውን› እግዚአብሔርን ሳታቋርጥ የማመስገን አገልግሎትዋ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማመስገን ለዓመታት የዜማ ስልት ተምረው የተመረቁ የስብሐተ እግዚአብሔር ሊቃውንት ያሏት ይህች ቤተ ክርስቲያን ዝማሬዋ ፣ ማሕሌትዋና ቅዳሴዋ የሃያ አራት ሰዓታት ጊዜ የማይበቃው ፣ ለሰዓት ሲባል በንባብ እየተባለ ፣ ዜማው እያጠረ የሚተው በመሆኑ ፀሐይ በማይጠልቅበት በዘላለማዊው መንግሥት ለማመስገን ዝግጁ ሆና የምትጠባበቅ ቤተ ክርስቲያን ያሰኛታል፡፡ ከዚህ እንደ ባሕር ጥልቅ ከሆነው ስብሐተ እግዚአብሔር ጋር የእግዚአብሔር ቅዱሳንንም በሰፊው ታመሰግናቸዋለች፡፡
በዚህች አጭር ጽሑፍ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው እግዚአብሔር ከሆነ ፍጡራን ለሆኑ ለቅዱሳን ሰዎች ፣ ለቅዱሳን መላእክትና ለድንግል ማርያም የሚዘመረው መዝሙርና የሚቀርበው ውዳሴ ምን ያህል ተገቢ ነው? ለቅዱሳን መዘመር ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ተገቢ ነው ወይ? የሚለውን እንመለከታለን፡፡
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሳስብ በመጽሐፍ ቅዱስ ወደር ያልተገኘለትን ዘማሪ ለመጠየቅ ወደድኩ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ በስሙ መቶ አምሳ መዝሙራት የተጻፉለት ፣ ራሱ ሰማኒያ ሰባት መዝሙራትን የዘመረና በሥሩ ያሉ መዘምራን ደግሞ አብረውት ብዙ መዝሙራትን የዘመሩበት የዝማሬ ባለ ጠጋ ንጉሥ ዳዊትን ‹‹እውነት ለፍጡራን ምስጋና ይገባል ወይ?›› ብዬ ልጠይቀው አስቤ ወደ መዝሙረ ዳዊት ገሰገስኩ፡፡
ፈጣሪ እንደ ልቤ ያለው ዳዊት የልቤን ማን እንደነገረው እንጃ የእኔን ጥያቄ ለመመለስ ቸኩሎ ጠበቀኝ፡፡ ገና የመጀመሪያው መዝሙሩን ‹‹ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›› ብሎ ጀምሮት አገኘሁት፡፡ (መዝ. 1፡1) ዳዊት በዚህ ዝማሬው ‹ምስጉን ነው› ያለው ፈጣሪን ነው ወይንስ ፍጡርን? እግዚአብሔርን ነው እንዳልል ‹በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል› ይላል፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዝማሬውን የጀመረው ‹በክፉዎች ምክር ያልሔደ ፣ በኃጢአተኞች መንገድ ያልቆመ ፣ በዋዘኞች ወንበር ያልተቀመጠ›ን ሰው በማመስገን ነው፡፡
ወደ መዝሙሩ ስገባ ዳዊት ምስጋናውን ሰፋ አድርጎ ‹ለቅኖች ምስጋና ይገባቸዋል› ‹ለችግረኛ የሚያስብ ምስጉን ነው› ‹አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው› ‹እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው› ‹እልልታን የሚያውቅ ሕዝብ ምስጉን ነው› ብሎ ከግለሰቦች አልፎ ሕዝብን ሲያመሰግን አገኘሁት፡፡ ከሁሉ ያስደነቀኝ ግን ‹‹መተላለፉ የቀረችለት ፣ ኃጢአቱ የተከደነችለት ሰው ምስጉን ነው›› የሚለው ዝማሬው ነው፡፡ ኃጢአቱን እግዚአብሔር ይቅር ያለውና በደሉን ፈጣሪ የሸፈነለት ሰው በታላቁ ዘማሪ በዳዊት አንደበት መዝሙር ከተዘመረለት በሃሳብዋ እንኳን ኃጢአትን ስላልሠራችው ድንግል ምን ዓይነት መዝሙር ይዘመርላት ይሆን?
ንጉሥ ዳዊት ሕይወት ላላቸው ሰዎች ብቻ ዘምሮ አላቆመም ፤ ለማትናገረውና ከእንጨት ከድንጋይ በሰው እጅ ለተሠራችው ከተማው ለጽዮን የእግዚአብሔር ማደሪያ በመሆንዋ ዝማሬን አዝንሞላታል፡፡
‹‹እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል ፤ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዷታል፡፡ እንዲህ ሲል ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት ፣ መርጫታለሁና በእርስዋ አድራለሁ››
‹‹እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል ፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የከበረ ነገር ይባላል››
‹‹በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ፤ ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን ፤ የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን ፤ የእግዚአብሔርን ዝማሬ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ፤ ባላስብሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ጋር ይጣበቅ ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ›› ብሎ ስለ ቅድስቲቱ ከተማ ሲዘምር አገኘሁት፡፡ ከራሱ አልፎም በዙሪያው ላሉት በመዝሙሩ እንዲህ ሲል ጥሪ አቀረበ ‹‹ጽዮንን ክበቧት በዙሪያዋም ተመላለሱ ፤ ግንቦችዋን ቁጠሩ ፤ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ ፤ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ›› የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንን ለማይወድዱ ደግሞ በመዝሙሩ ‹‹ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ›› ብሎ ዘምሮአል፡፡
ዳዊት ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮት ለሚውልና ለሚያድርባት ከተማ የእግዚአብሔር ማደሪያው እንድትሆን እንደ መረጣት አውቆ እንዲህ ሲዘምር ማየቴ ‹መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል› ለተባለችዋ ቅድስት ድንግል ማርያም ‹የጌታዬ እናት ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ› ብዬ ለመዘመር እንድችል ኃይል የሚሠጥ ሆነልኝ፡፡ ባቢሎን በተባለ በኃጢአት ሥፍራ ሆኜ ድንግልን ባሰብኳት ጊዜ እንዳለቅስና ‹‹ድንግል ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ›› ብዬ እንድዘምርላት ድፍረት ሠጠኝ፡፡
የዳዊት ሲደንቀኝ ልጁ ሰሎሞን ደግሞ ‹ከመዝሙራት ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር› (መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን) በተባለ ውብ ድርሰቱ ከአባቱ የባሰ የመዝሙር ቅኔን ሲቀኝ አገኘሁት፡፡ በዚህ ዝማሬው ላይ በፍቅረኛሞች መካከል የሚደረግን የፍቅር ቃል ልውውጥ ሰበብ አድርጎ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሙሽራው ስላደረጋትና እርስዋም ‹ውዴ› ብላ ስለምትጠራው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውብ ስንኞችን ጽፎ አገኘሁት፡፡
በዚህ ዝማሬው ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውድዋ የሆነውንና ነፍስዋ የወደደችውን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ስትፈልገው ፣ በከተማ የሚጠብቁ ጠባቂዎች የተባሉ መላእክትን ስትጠይቅ ፣ ቤተ ክርስቲያን በቀዳም ስዑር የምትዘምረው ‹እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት› ብላ አልጋ በተባለ መቃብር ስለ ሰው ልጅ ፍቅር የተኛውን ክርስቶስን እርሱ ወድዶ ሞትን ድል አድርጎ እስከሚነሣ በእምነት እንዲጠብቁ ስትናገር ፣ ውዴ ወደ ገነቱ ወረደ ብላ ነፍሳትን ይዞ ወደ ገነት ስለ መውጣቱ ስትዘምር በሰሎሞን ዝማሬ ውስጥ አገኘሁ፡፡ በዚህ ዝማሬ ላይ ሙሽራው ስለ ሙሽራዪቱ ቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ውበት ፣ ጡቶችዋ ስለተባሉ የቃሉ ወተት ስለሚፈስስባቸው ብሉይና ሐዲስ ኪዳን ማማር ፣ ድንቅ ቅኔ ሲዘምር አገኘሁት፡፡
በሰሎሞን መዝሙር ላይ ‹ወዳጄ ሆይ ነይ ውበቴ ሆይ ተነሽ› ‹ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው ነውርም የለብሽም› የሚሉት ውብ ዝማሬዎች ለፍጡር እንጂ ለፈጣሪ የቀረቡ ምስጋናዎች አይደሉም፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ውብ ዝማሬ ሁለተናዋ በቅድስና ለተዋበችው ድንግል ማርያም መዝሙር አድርጋ የምትዘምረው፡፡ አባቱ ዳዊት ‹ልጄ ሆይ ስሚ እዪም ጆሮሽን አዘንብዪ› ብሎ ለጠራት ድንግል ልጁ ሰሎሞን ‹እኅቴ ሙሽራ ሆይ› ብሎ መዘመሩን የምንቀበለውም ከዚህ ተነሥተን ነው፡፡
ቅዱሳንን ማመስገን በዳዊትና በሰሎሞን አላበቃም ፤ መላእክትም ለቅዱሳን ሲዘምሩ ታይተዋል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ‹ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ› ብሎ ለድንግል ማርያም ያቀረበው ሰላምታ ‹ከእንዴት ውለሻል› ሰላምታ ያለፈ ምስጋና አይደለምን? ለዘካርያስ ‹አንተ ከካህናት ተለይተህ የተባረክህ ነህ› ያላለው ይህ መልአክ ለድንግል ለይቶ ያቀረበው በእርግጥም ምስጋና ነበር፡፡ ስለሆነም የገብርኤልን ሰላምታ ተውሰን ድንግሊቱን ለዘወትር እናመሰግናታለን፡፡ ገብርኤል ያቀረበውን እኛ ማቅረብ አያስፈልገንም የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ሆኖም ድንግሊቱ ‹ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል› ብላ መናገርዋ ለማመስገናችን ምክንያት ነው


ሳለ የትኛውን የሚጎዳውን ሞት ፈራ ይባላል?
👉 ጌታችን ቀጥሎም "አባ አባት ሆይ ሁሉ ይቻልሃል ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን አንተ የምትወደው
ይሁን እንጂ እኔ የምወደው አይሁን" አለ:: ይህን ማለቱ ከሞት ለመዳን ፈልጎ አይደለም። ምክንያቱም ወደ
ኢየሩሳሌም እንደሚሄድና ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ እንደሚቀበል ለደቀ
መዛሙርቱ በነገራቸው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ "አይሁንብህ ጌታ ከቶ አይደርስብህም" በማለት እርሱን
ከመውደዱ የተነሳ አትሙትብኝ የሚል ቃል ሲናገረው ጌታችን ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን "ወደ ኋላዬ ሂድ
አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" ብሎ ገስጾታል።
ማቴ.16:21-23:: አትሙትብኝ የሚለውን ጴጥሮስን ዕንቅፋት ሆነህብኛል በማለት ገስጾታልና ሞትን ፈርቶ
ለመነ ማለት አይቻልም። ሊይዙት በይሁዳ እየተመሩ የመጡትን ጭፍሮችና የካህናት አለቆች
ፈሪሳውያንንም ማንን ትፈልጋላችሁ ብሎ ጠይቆ የናዝሬቱን ኢየሱስን ሲሉት "እኔ ነኝ ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ
አፈግፍገው በምድር ላይ ወድቀዋል። ዮሐ. 18:4-6:: ሞትን ፈርቶ ቢሆን ኖሮ ያን ጊዜ ጠላቶቹ ሲወድቁ
ከእጃቸው ያመልጥ ነበር።
👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደ ሚችል ከብርቱ ጩኸትና
ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን አቀረበ እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ተሰማለት።" ዕብ. 5:7 የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ሲተረጉም "ቢቻልስ ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ ባለ ጊዜ ከሞት ይድን ዘንድ ወደ አብ ማለደ
ትላለህን? እስኪ ንገረኝ ብሎ ይጠይቃል:: እንዲህ ከሆነ (ከሞት አድነኝ ብሎ ከጸለየ) ለምን ስለ ትንሳኤው
አልጸለየም? (ለምን ያስነሳው ዘንድ አብን አልጠየቀም) ስለ ትንሣኤው ሲናገር "ይህን ቤተ መቅደስ
አፍርሱት በሦስተኛውም ቀን አነሣዋለሁ" ዮሐ. 2:19-20:: ብሏል እንጂ አብ ያነሳዋል አላለም።
ሁለተኛም ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁ። ዮሐ.10፥16 ብሏል እንጂ አብ ያነሳታል አላለም።
"እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎችም ይሰጣል የሞት ፍርድም
ይፈርዱበታል። ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።
በሦስተኛውም ቀን ይነሳል" ማቴ. 20:18-19 በማለት መከራ ወደ ሚቀበልበት ቦታ በፈቃዱ እየሄደ
እንዴት አድነኝ ብሎ ይለምናል" ይላል።

ታድያ መጽሐፍት ጸሎቱ ተሰማለት ይላል ጸሎት ከተሰማለት ታድያ ለምን ሞተ ስልን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ሞትን ፈርቶ ሳይሆን የጸለየው በአዳም እና በሰው ልጆች ተገብቶ የጸለየው ጸሎት ነው የአዳም እንጂ የኢየሱስ ክርስቶስ ጩኅት አየደለም ይች ሞት ከእኔ ትለፍ ብሎ የአዳምን ሞት አሳለፈለት እንድሁም የሰውን ልጆች እንል አለን እንጂ እንዴት አማለደን እንል አለን

✔️ለአስተምህሮ ስል ክርስቶስ እርሱ መምህር ነው አያናድንዱ የጸለየው ጸሎት እኛ እንድት ብለን መጸለይ እንደአለብን ለማስተማር ነው እንል አለን እንጂ እሱን አማላጅ እንዴት እንል አለን በርሃን ዓለም ጳወሎስ ምሳሌን ትቶላችኋል እንዳለ ጌታ ኢየሱስ ሥርዓት እየሠራልን ነው የሄደው ለምሳሌ ብናነሳ ምግብን አብርክቶ ሲመግባቸው ምግብን ባርኮ በመስጠት የዲያቆንን ሥራዓት ሲሠራልን እግር በማጠብ የንፍቀ ዲያቆኑን ሥራ እፍ ብሎ ሐዋሪያትን በመሾም የጳጳሳትን ወዘተ ሥርዓት ሲሰራለን እንጂ ለሱ ጸሎት አስፈልጎት ነው መቼም አልንልም እንደዚሁ ሁሉ የክርስቶስ ጸሎት ለአስተምህሮ እንል አለን እንጂ እዴት አማላጅ እንለው አለን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው ብሎ ጸለየ ተማሪ ቅዱስ እስጢፋኖስም ሲወግሩት የሚያደርጉትን አያቁም እና ይቅር በላቸው ብሎ ከመምህሩ የተማረውን ተናገር በነገራችን ላይ ይሄ ጸሎት ጌታ ኢየሱስ ለሰዎች የምንጸልየውንም ጸሎት ሰማያዊ እንድሆን የቀደሰበት ነው ለሌሎች የምንጸልየው ጸሎት ተሰሚነት እንዲኖረው እንጂ እንዴት አማላጅነት እንለው አለን ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እግራቸውን አጥቦ ሐዋሪያትን ምን እያደረገ እንዳለ በመንገር እነሱም እንድያደርጉት ያንን ነገር ሲያዛቸው እናይ አለን ምክንያቱም እሱ መምህራቸው ነውና።


✔️ለመቀደስ ስል ጌታ ኢየሱስ ከጽነሰቱ እስከ ዕረገቱ ድረስ ሁሉን ነገር እየቀደሰልን ነው የመጣው እንደ ህጻን ህጻን ሁኖ ህጻናትን ለመቀደስ እንደ ልጅ ሁኖ ልጅነትን ለመቀደስ እንደ ጎልማሳ ጎልማሳ ሁኖ ጎልማሳነትን ለመቀደስ ነው እንድሁም በመጾሞ ጾምን ለመቀደስ በሰይጣንም በመፈተን ፈተናን ሁሉ ድል ማድረግ እንደልችል ሲቀድስልን እንጂ መቼም ሰይጣን ክርስቶስን ለመፈተን አቅም ኑሮት አይደለም አይተና ቀናችን ሳይደርስ ልታጠፋን መጣህን ሲሉ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጸለይ ጸሎታችን ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የምንችልበት እንድሆን ሲቀድስልን ነው የብሉይ ኪዳን ጸሎት ሰማያዊ አልነበረም የእኛ ጸሎት ግን ሰማያዊ እንድሆን ለማስቻል ጸለየ እንል አለን እንጂ እንደት ልመናውን አማላጅነት እንለው አለን የእኛን ልመና ለመቀደስ እንል አለን እንጂ

ይቀጥላል

@haymanote1


ኢየሱስ በምድር ሳለ አማልዷልን?

✔️ክፍል አንድ

ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ሲመላለስ አምልዷል ከተባል መለኮት ሥጋን አልተዋሐደም እንደማለት ነው እንደተዋሐደ ካመን ግን ሥጋ የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጓል ስለዚህ ሥጋ የቃል ገንዘብ ገንዘቡ ስላደረገ ሥጋ የአብን ልብነት የመንፈስ ቅዱስን እስትንፋስነትም ገንዘቡ አድርጓል ብለን ማመን አለብን ባሕርየ ሥላሴ ሥጋን ተዋዷል ብለን ማመን አለብን ያ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር በአብ ልብነት በመነፍስ ቅዱስ እስትንፋስነት ነው የተናገረው ስለዚህ ሥላሴ አንድት ፍቃድ ስለሆነች ያለቻቸው አማልዷል ልንለው አንችልም ለማማለድ ሁለት ፈቃድ ስለሚያስፈልግ ሥላሴ አንድት ፍቃድ እንጂ ተመሳሳይ አንድ አይነት ፍቃድ አይደለም ያላቸው ያማለት ያች አንዷ ፍቃድ ማማለድ ነው ወይስ መማለድ አማለደ ካልን አንዱ አምላክ ስጋን አልተዋሃደም ሌላ አምላክ አለ ፈቃዱን የሚቀበለው እንደማለት ነው በምድር ሳለ አማልዷል ማለት ተገናዝቦን የረሳ ትምህርት ነው ስለክርስቶስ ስንናገር ተገናዝቦን የረሳ ቃል አንናገርም ለምሳኤ ብረት አለ በሳት የጋለ ብረት ብነካው አያቃጥለኚም አንልም የማያቃጥልበት መንገድም በጭራሽ አይኖርም እሳቱ እስካልተለየው ድረስ ክርስቶስም የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ እስካደረገ ድረስ አምላዷል ልንል በጭራሽ አንችልም ምክያቱም ኃጢያትን ይቅር ማለት ገንዘቡ ስላደረግ ይህ ገንዘቡ ሊለየው ስለማይችል ። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢያትን ይቅር ማለት እና ኃጢያትን ማንጻት ገንዘቡ ከሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ሲለን እና እሱ ሲያነጻን ከኃጢያታችን ነጽተናል ማለት ነው ስለዚህም ኢየሱስ አማልዷል ከተባለ ግን ኢየሱስ ያላነጻልን ኃጢያት ኑሮ ሌላ ኃጢያት የሚያነጻ አስፈልጎት እርሱ ስለማይችለው ሌላ አነጻነት እንደማለት ነው ይሄ ደግሞ ትልቅ ክህደትም ኃጢያትም ነው መጽሐፍ ቅዱስ እንድህ ይለናል " እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤"
(ወደ ዕብራውያን 1:3) ጌታ ኢየሱስ እሱ እራሱ ኃጢያታችን ያነጻ እንጅ ሌላ ኃጢያት የሚያነጻ አላስፈለገውም። በሥላሴ ዘንድ የፍቃድ ልዪነት ስለሌለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ሲል በዚያች በአንዷ ፍቃድ ይቅር ተብለናል ። ሥላሴ አንድት ፍቃድ እንዳላቸው ካመን ኢየሱስን አማልዷል አንለውም ሥላሴ ሌላ ፍቃድ አላቸው ማለት ግን 3 አምላክ አለ እንደማለት ነው ይሄ ደግሞ ትልቅ ክህደት ነው።

አዎ ክርስቶስ መጸለዩን መለመኑን እኔም ያማልከደው እውነታ ነው ነገር ግን አማላጅነት እና ምልጃ የተለያዩ ናቸው
ግልጽ ለማድረግ አማላጅ ሁሉ ምልጃን ያቀርባል ምልጃ ሁሉ ግን አማላጅነት አይደለም ምልጃ ማለት፦የጧጥ ግሥገሣ ፤ ልመና፤ደጅ ጥናት የሚል ትርጉም ሲሰጠን አማላጅነት ማለት ግን ፦ አማላጅ ማለት በሁለት ተቃራኒ አካላት መካከል ቆሞ ሁለቱን ወደ አንድነት ለማምጣት 3ኛ ወገን ሁኖ የሚሠራ ማለት ነው ስለዚህ የለመነ ምልጃን ያቀረበ ሁሉ አማላጅ ነው እያማለደ ነው አንለውም።

የክርስቶስን ጸሎት
እኔ በ 4 አይነት መልኩ አየው
1. ለመስዋዕት
2.ለቤዛነት
3.ለአስተምህሮ
4.ለመቀደስ ✔️ለመስዋት ስል ክርስቶስ እራሱን መስዋት አድርጎ ነው ያቀረበው ጸሎትም መስወት ነው ስለዚህ ሥጋውን መስዋት አድርጎ እራሱ አቅርቦ እራሱ ተቀበለ እንደምንለው ጸሎትም መስዋት ስለሆነ እራሱ አቅርቦ እራሱ መሰዋቱን ተቀባይ ሁኖ ከራሱ ጋር አስታረቀን እንል አለን እንጂ እንዴት አማለደን እንል አለን በተገናዝቦ በሥጋ ገንዘቡ እራሱን ሥጋውን መስዋት አድርጎ እንዳቀረበ ሥጋም መለኮትን ገንዘብ ስላደረገ መስዋቱን ተቀበለ እንል አለን እንጂ መሥዋት ለማቅረብ ሥጋ መዋሐድ እንዳስፈለገው ሁሉ መሥዋትንም ለመቀበል ሥጋን መለኮት ተዋሕዶታል ስለዚህ በተገናዝቦ መስዋት እራሱን ያቀርባል እራሱ መስዋዕቱን ይቀበላል እንል አለን እንጅ እንዴት አማለደ እንል አለን ✔️ሌላው ለቤዘነት ስል ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ቤዛ ሊሆነን እንደመጣ ግልጽ ነው ቤዝ ማለት ደግሞ
ቤዛ ማለት ‹‹የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋ÷ ካሣ÷ ለውጥ››
መድኃኒት፤ ዋጋ ፤ ስለ፤ ፋንታ፤
ለውጥ ካሣ ባንድ ሰው መከራና ሞት ተላልፎ መሞት ታዳጊን ምትክን መኾን ለሞት ለመከራ መለወጥ መሥዋዕት መገረፍ መሰቀል። የሚል ትርጉም ነው ያለው
ትርጉሙ ይሄ ከሆነ ታድያ አንድ ንጉሥ ጥፋት ያጠፋ ሰው ይቀጣል በሎ ሕግ ቢያወጣ ይሄ ንጉሥ ኝ እናቱ ያን ጥፋት ብታጠፋና እናቱ ያንን ቅጣት እንድትቀጣ ስላልፈለገ እራሱ በሷ ቦታ ሁኖ ቢቀጣላት ቤዚአ ሆናት ተቀጣላት ይባላል እንጂ አማለዳት አይባልም ልክ እንድሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በአዳም እና በሰው ልጆች ተገብቶ የእኛን ሞት ሙቶ የእኛን እርሃብ ተርቦ የእኛል ልመና እና ምልጃ በእኛ ምትክ ቤዝ ሆነን እንላለን እንጂ እንዴት ቤዛነቱን አማላጅ እንለው አለን ለምሳሌ ኢየሱስ እንድህ ብሏል

📖 "አባት ሆይ ሁሉ ይቻልሃል ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው
አይሁን አለ::" ማር. 14:36
👉ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ሁሉም እንደሚሰናከሉ ጴጥሮስም ሶስት ጊዜ እንደሚክደው ለደቀ
መዛሙርቱ ነግሯቸው ነበር። ከዚያም ወደ ጌቴ ሴማኒ የአትክልት ቦታ ጴጥሮስን ያዕቆብና ዮሐንስ ይዞ
ማዘን ጀመረ። እኚህ የምስጢር ሐዋርያት ክብሩን በደብረ ታቦር ሲገልጥ የነበሩ ናቸው በጌቴ ሴማኒ ደግሞ
ክብሩን ሲገልጥ ሳይሆን አዘነ ተከዘ ሲባል አይተዋልና መለኮት ከትስብዕት ጋር ያለ መጠፋፋት
ያለመቀላቀል በተዋሕዶ እንዳለ የስጋዌውን ነገር ያለ መሰናከል ይረዱ ዘንድ ይዟቸው ሄዷል። ሦስቱን ይዞ
ሊጸልይ እስኪሄድ ድረስ አዘነ ተከዘ ተብሎ አልተጻፈልንም። "ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ አዘነች" የተባለው
ለራሱ ሳይሆን ለወሰዳቸው ለእነርሱ ነው ያዘነው። ስለዚህም ያዘነው መከራውን ስለፈራ አይደለም።
የመጣው መከራን ሊቀበል ነውና። ይልቁኑ ስለ ርጉም ይሁዳ ስለ ሐዋርያት መሰናከልና ስለ አይሁድ ፍርድ
ከመንግስተ እግዚአብሔር ውጪ ስለ መሆናቸው ነገር ነው አዘነ ተከዘ የተባለው ሲሉ ሊቃውንት
ተርጉመዋል።
🔷 ቅዱስ ሂላሪም ጌታችን ይህን ያለው ሞትን ስለፈራ ነው የሚሉትን ሰዎች ከሐዋርያት ላይ የሞትን
ፍርሃት ያጠፋላቸው ስለ እርሱ እስከ ሞት ድረስ ምስክር ይሆኑ ያበረታቸው እንደምን ሞትን ፈራ ይባላል?
እንዲህ ማለትስ ምክንያታዊ ነውን በማለት ይሞግታቸዋል:: ዳግመኛም ስለ እርሱ ምስክር ሆነው የሚሞቱትን አክሊል የሚያቀዳጅ ጌታ ሞትን ፈርቶ አዘነ እንዴት ሊባል ይችላል? በፈቃዱ ለመሞት መጥቶ


ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል?

የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል ይላሉ።ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮ እሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው። በቅዳሴ ላይ ቅዱስ ሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤ ሁለተኛው ካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለም የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን አሜን አሜን እንላለን።ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት
እንዲህ ነው..አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦ ዲያቆኑ ይህን በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤ ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤ ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው።
እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው። ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤ ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና ነው
በእግዚኦት ላይ የሚሰማው ቃጭል፦ በእግዚኦት ላይ የሚሰማው ቃጭል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በቀራንዮ ልጇን ፊት ለፊት በመስቀል ላይ እያየችው ያዘነችው ኃዘን ያለቀሰችው ልቅሶ ምሳሌ ነው። አረጋዊው ስምኦን ወላኪሰ ይበውእ ውስጠ ልብኪ /በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል እንዳላት/ ሉቃስ 2:35 ይህ ሃዘን ከባድ ነውና ፤ መላእክት ባያጽናኗት ኖሮ ሃዘኑ ለሞት ባበቃት ነበር ይላል!! ታላቅ ሃዘን ነበርና; በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል የተባለውም ይህ ከባድ ሃዘን ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@memhrochachn


.★በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱአምላክ አሜን★


☞ማዕተብ በአንገታችን ላይ † ለምን እናስራለን???
==============

☞ማዕተብ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም ምልክት ማለት ነው::

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ ልዩ ልዩ የክርስትና መለያ ምልክቶችን ማድረግ ከብሉይ ኪዳን በትውፊት/ውርስ/ የተገኘ ነው::

በአምልኮተ እግዚአብሔር የተለዩ ውሉደ አብርሃም በግዝረት ይለዩ እንደነበር:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥርዓትና ትውፊት ውስጥ ማዕተብ የተለየ ክብር ያለው የክርስትናችን መለያ/ምልክት/ ነው::

☞ማዕተብ ማሠር በቤተ ክርስትያን ማን ጀመረው? ማዕተብ በአንገት ማሠር የጀመረው አባት ያዕቆብ ዘአልበረዳኢ የተባለ በ6ኛውመቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ ይኖር የነበረ ቅዱስ አባት ነው፡፡

☞መስቀል በአንገት ማሠራችን፡---> እኛ መስቀልን የምናከብረውና በአንገታችን አሥረን የምንታየው በሌላ ምክንያት ሳይሆን የክርስቶስ ኢየሱስ ኃይል ስለተገለጠበት፣መንፈሳዊ ነፃነት ስለተገኘበት፣ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ታላቅ ድልድይ ሆኖ ስለሆነ ነው፡፡

☞መስቀል በአንገት ማሠራችን ፡---> በዚህ ባመንኩት እምነት ክርስቶስ ለኔ በተቀበለው መከራ ታማኝ እሆናለሁ ማለት ነው፡፡ ክርስቲያን እንደመሆናችን መጠን የክርስቶስ የመከራው ተካፋይ መሆናችንን ያመለክታል፡፡

☞ጠቢቡ ሰሎሞን “ልጄ ሆይ የአባትህን ትዕዛዝ ጠብቅ፡፡ የእናትህንም ሕግ አትተው፡፡ ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፡፡ በአንገትህም እሰረው፡፡” ምሳ. 6÷20-22 በማለት የተናገረው ይህንኑ ለማመልከት ነው፡፡”

☞ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ መልዕክቱ “እኔ የኢየሱስን ማኅተም በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ስንኳ አያድክመኝ።” (ገላትያ 6፡17) ማለቱ ባመንኩት እምነት ክርስቶስ ለኔ በተቀበለው መከራ ታማኝ እሆናለሁ ማለት ነው::


☞የዘመኑ ተቃዋሚዎች እምነት በልብ ነው ይላሉ፡- አዎ እምነት በልብ ነው ግን በልብ የምናምነውን ደግሞ ለሰው መመስከር መጽሀፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡

☞ማዕተብ ከአህዛብ የተለየን እና የክርስቶስ ተከታይ መሆናችንን የምንመሰክርበት ነው፡፡ክርስትያን የክርስቶስ ተከታይ መሆናችንን ለአለም የምንመሰክርበት ነው!

ክርስቶስም እንዲህ ብሏል፡-“በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤” ማቴዎስ 10፡32 ዛሬ ተቃዋሚዎች መስቀሉን መመኪያ መጠጊያ ከማድረጉ ይልቅ የመስቀሉን ክብር ማቃለል እና መናቅ እና እንደ ዘመናዊነት በመቁጠር የክርስቶስ መስቀል ሕይወቱ በማድረግ ሊገኝ የሚገባውን ፍፁም ሰላም አጥተዋል፡፡ስለዚህ ምዕመናን በክርስቶስ ደም በተቀደሰው ክቡር መስቀል ተሻሽተን በረከትን ድህነትን ለማግኘት በእምነት በምግባር እስከመጨረሻው ሕቅታ ፀንተን ልንኖር ይገባል፡፡

"ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ!" ገላትያ 6:14

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@memhrochachn


🍀ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
ክፍል ሦስት 

ከዚህ ቀደም ተከታታይ ባቀረብናቸው ጽሑፎች #ወላዲተ_አምላክ_ድንግል ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደማይመለከታት ከብዙ በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል።በክፍል ሁለት ጽሑፋችን #ወለደት_ድንግል_ዘፀንሰቶ_እንዘ_ኢተአምር_ብእሴ_በሥጋ_ዘፈጠሮ_ለርእሱ_ወወለደቶ_ዘእንበለ_ደነስ_ወሕማም_ወኢረሰስሐት_በሐሪስ_ሐፀነቶ_ዘእንበለ_ፃማ_ወድካም_ወአጥበቶ_ዘእንበለ_ድካም_ወአልሐቀቶ_በሕግ_ዘሥጋ_ዘእንበለ_ትካዝ ።ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ 28፥19
••●◉ ✞ ◉●••
#ለተዋሕዶ_የፈጠረውን_ሥጋ_ያለ_ወንድ_ዘር_ያለ_ኃጢአት_ያለምጥ_ወለደችው_የአራስነት_ግብርም_አላገኛትም_ያድካም_ያለመታከት_አሳደገችው_ያለድካም_አጠባችው_ለሥጋ_በሚገባ_ሕግ_ምን_አበላው_ምን_አለብሰው_ሳትል_አሳደገችው። ሃይማኖተ አበው ዘአትናትዮስ 28፥19 ትርጉም  ማብራሪያውን በቀጣዩ ጽሁፋችን እንመለከታለን ብለን ነበር ያቆምነው።

👉ሐዋርያዊው ቅዱስ አትናቴዎስ ካስተማረው ትምህርት እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት በሚገባ ማስተዋል ይቻላል ግልጽ ለማድረግም የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ይቻላል፡፡
••●◉ ✞ ◉●••
👉፩. ያለ ኃጢአት ከሚለው ቃል ወላዲተ አምላክ ጌታን ምንም ምን ኃጢአት ሳያገኛት እንደወለደችው ያስረዳናል      
••●◉ ✞ ◉●••
፪. ያለምጥ የአራስነት ግብርም ሳያገኛት ከሚለው ደግሞ ሌሎች ሴቶች በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት በምጥ በአራስነት የሚወልዱ ሲሆን እርሷ ግን ከመርገመ ከእዳ ከበደል የተለየች በመሆኗ ምጥና አራስነት አልነበረባትም ይህም ከመልአኩ የምስጋና ንግግር ተስማሚነት ያለው ነው #ቅዱስ ገብርኤል ሲያበሥራት ከላይ ከተጠቀሱት የመርገም ምልክቶች እመቤታችን የተለየች መሆኗን ሲያስረዳ #አንች_ከሴቶች_መካከል_የተባረክሽ_ነሽ  ሉቃ 1፥28 በማለት አመሰግኖአታል።ለመሆኑ እርሷ በሌሎች ሴቶች ያለ የመርገም ፍዳ ካለባት ከሌሎች ሴቶች መለየቷ ምን ላይ ሊሆን ነው ❓ ስለዚህ እመቤታችን የመርገም ፍዳ ይመለከታታል ብሎ ማስተማር ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ የራቀ ትምህርት ነው ማለት ነው ። ወላዲተ አምላክ የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ቅዱስ አትናቴዎስ ብቻ ሳይሆን በርካታ ቅዱሳን አበውም መስከረዋል  

👉ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #ድንግል_ማርያም የጥንተ አብሶ ፍዳ እንደማይመለከታት ሲያስረዳ በሚደንቅ ንግግር እንዲህ ይላል #ከመገባሪ_ጠቢብ_ሶበ_ይረክብ_ግብሮ_ዘይትጌበር_ይገብር_እምኔሁ_ንዋየ_ሰናየ_ከመዝ_እግዚእነ_ሶበ_ረከበ_ሥጋሃ_ቅዱስ_ለዛቲ_ድንግል_ወነፍሳ_ቅድስት_ፈጠረ_ሎቱ_መቅደስ_ዘቦቱ_ነፍስ » ሐይ አበ ዘአፈወርቅ 66 ፡14
••●◉ ✞ ◉●••
#ጥበበኛ_ንጹሕ_አፈር_ባገኘ_ጊዜ_ጥሩ_እቃ_እንደሚሰራበት_ጌታችንም_የድንግልን_ንጹሕ_ሥጋዋን_ንጹሕ_ነፍሷን_ባገኘ_ጊዜ_ይዋሐደው_ዘንድ_ነፍስ_ያለውን_መቅደስ_ሰውነቱን_ፈጠረ 
••●◉ ✞ ◉●••
👉መቼም የቀናች የተረዳች ርትዕት የሆነች የተዋሕዶ ምዕመን ሆኖ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን የማያውቅ አለ ማለት ይከብዳል ምንም በማያሻማና ግሩም በሆነ አገላለጽ ሊቁ እነዳስቀመጠልን አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነው ምንም ምን እንከን ከሌለው ሰውነቷ ነው  ሊቁ #የእመቤታችንን ነፍስና ሥጋዋን በንጹሕ አፈር መስሎታል በዚህ አገላለጹ ከሰው ወገን ተመርጣ #የለጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እናትነት የበቃች መሆኗን አስረዳን ምክንያቱም የሰው ሁሉ ተፈጥሮው ከአፈር ነውና ። #ወላዲተ_አምላክ እንደሰው ሁሉ ተፈጥሮዋ ከአፈር ቢሆንም ቅሉ ሊቁ እንደተናገረው ንጹሕ አፈር የሚለው አገላለጽ በሰዎች ከደረሰ አዳማዊ መርገም የተለየች መሆኗን ያስረዳናል

👉ቅዱስ ኤፍሬምም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም #ዘር_ያልተዘራባት_እርሻ በማለት በንጹሕ እርሻ መስሎአታል

👉ልበ አምላክ ዳዊትም #እንደ_ዝናብ_በንጹሕ_እርሻ_ላይ....ይወርዳል   መዝ 71፥6 በማለት #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን በዝናበ ሕይወት እመቤታችንን ደግሞ አረም ተዋስያን በሌሉት ንጹሕ መሬት መስሎ ትንቢት ተናግሮአል ይህም ምንም ተፈጥሮዋ ከሰው ወገን ብትሆንም የኃጢአት አረም ህዋስ ያልነካት ንጽሕት ዘር መሆኗን ያስረዳናል። ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በንጹሕ አፈር የመሰላት ።
••●◉ ✞ ◉●••
👉ሊቁ በመቀጠልም #ንጹሕ_ሥጋዋን_ንጹሕ_ነፍሷን_ባገኘ_ጊዜ  በማለት #የወላዲተ አምላክ ነፍሷ ሥጋዋ ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ ንጹሕ ቅዱስ መሆኑን ይመሰክራል ባገኘ ጊዜ አለ እንጂ ሊዋሐደው ሲል አነጻው አላለም ስለዚህም እውነተኞች ቅዱሳን አበው በጥንቃቄ የመሰከሩትን #የእመቤታችንን ንጽሕና ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊያስተባብል አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም ።

👉ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን  #እኛ_ብንሆን_ወይም_የሰማይ_መልአክ_ከሰበክንላችሁ_ወንጌል_የሚለይ_ወንጌል_ቢሰብክላችሁ_የተረገመ_ይሁን።ገላ 1፥8 ባለው መሠረት ዛሬ ማንም ተነስቶ ሊሽረው ወይም ሊለውጠው አይችልም። ቢሞክር እንኳን የተለየ የተረገመ ነው።#ቅድስት_ቤተክርስቲያን የምትመራው ቀደምት ቅዱሳን ባስተማሩን እውነተኛ ትምህርት እንጂ አዲስ ዛሬ የሚፈጠር ምንም የለም ስለዚህ ከአንዳንድ የዘመናችን ሰዎች የተሳሳተ ትምህርት ብንሰማ እነሱ የተለዩ ይሆናሉ እንጂ የሰማይ መልአክ ነኝ የሚል ቢመጣ እንኳን የቤተክርስቲያን አስተምሮ አይለወጥም፡፡  
++++++++++++++++++++++++++++++

የመጨረሻ ክፍል አራት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"
++++++++++++++++++++++++++++
የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1


🍀ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?
ክፍል ሁለት    
⚡️፫. #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም የውርስ ኃጢአት አለባት ማለት #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጹሐ ባሕርይውን መዳፈር ነው  #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አለምን ለማዳን ሰው ሲሆን ሥጋና ነፍስን ከሰማይ ይዞ አልወረደም ሰው የሆነው የእኛን ባሕርይ ተዋሕዶ ነው።#እንግዲህ_ልጆቹ_በሥጋና_በደም_ስለሚካፈሉ_እርሱ_ደግሞ_በሞት_ላይ_ስልጣን_ያለውን_እንዲሽር_እንዲሁ_ተካፈለ_የአብርሃምን_ዘር_ይዞአል_እንጂ_የያዘው_የመላእክትን_አይደለም ዕብ 2፥14-15

+++++++++++++++++++++++++

👉እንግዲህ#ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰው ሲሆን ሥጋንም ነፍስንም #ከድንግል_ማርያም ከነሳ እርሷ ደግሞ መርገም ነክቶአታል ከተባለ ክብር ምስጋና ይግባውና #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃጢአት ያለበትን ሥጋ ተዋሐደ ልንል ነውን ❓እንዲህማ ካልን ተረፈ አይሁድ ሆነናል ማለት ነው ምክንያቱም ደፍረው  #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን ኃጢአት አለበት ያሉት አይሁድ ናቸውና  #ይህ_ሰው_ኃጢአተኛ_መሆኑን_እኛ_እናውቃለን ዮሐ 9፥24

👉እኛስ #ከእመቤታችን ምንም ምን ኃጢአት ያላወቀውን ሥጋ እንደነሳ እንመሰክራለን እንደ እውነተኞቹ አባቶቻችን #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጽሕት ቅድስት ከምትሆን #ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን እናምናለን እንመሰክራለን #ኦ_ድንግል_አኮ_ዘተአምሪ_ርስሐተ_ከመ_አንስት_እለ_እምቅድሜኪ_ወእምድሬኪ_አላ_በቅድስና_በንጽሕና_ስርጉት_አንቲ (#ድንግል_ሆይ_ካንቺ_አስቀድመው_ካንችም_በኋላ_እንደ_ነበሩ_ሴቶች_አደፍ_ጉድፍን_የምታውቂ_አይደለሽም_በቅድስና_በንጽሕና_ጸንተሽ_ኖርሽ_እንጂ ቅዳሴ ማር 5፥42  
 
+++++++++++++++++++++++++

👉መቼም አባቶቻችን እነ ቅዱስ ኤፍሬም እነ አባ ሕርያቆስ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የደረሱአቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት የማይቀበል ኦርቶዶክሳዊ አለ ማለት እጅግ ይከብዳል ፡፡ እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስትያን ስለነገረ ማርያም በጥንቃቄ የምታስተምረው ስለድንግል ማርያም የምናምነው ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ #ከጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ማንነት ጋር ተያያዥነት ስላለው ነው እግዚአብሔር ይግለጥልንና #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን መርገም ያለበትን ሥጋ ተዋሐደ ማለት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ተቃርኖዎችን ያስነሳል። 

👉፩. የድንግል ማርያም ሥጋ የውርስ ኃጢአት ወይም የጥንተ አብሶ ፍዳ አለበት ከተባለ #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከርሷ ሲወለድ ኃጢአት የወረሰውን ሥጋ ወሰደ ሊባል ነው ❓ይህ ማለት ደግሞ  በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ትምህርት ነው ምክንያቱም #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ባሕርይ ኃጢአት ፈጽሞ  አይስማማውምና ኃጢአት የነካውን ሥጋ ተዋሐደ  ከተባለ መለኮት ኃጢአት ይስማማዋል እንደማለት ነው።ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዘው ክህደት ነው ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች መመልከት ይቻላል

++++++++++++++++++++++++++++
?#ቅዱስና_ያለ_ተንኮል_ነውርም_የሌለበት_ከኃጢአተኞት_የተለየ_ከሰማያትም_ከፍ_ከፍ_ያለ ዕብ 6፥27
👉#ከኃጢአት_በቀር_በነገር_ሁሉ_እንደኛ_ተፈተነ………… ዕብ 4፥15
👉#ኃጢአት_ያላወቀውን_እርሱን_ስለኛ_ኃጢአት …2ቆሮ5፥20
👉፪. #የድንግል_ማርያም ሥጋ የጥንተ አብሶ ፍዳ ወይም የውርስ ኃጢአት  አለበት ማለት #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የማዳን ሥራ  አለመቀበል ነው ። ምክንያቱንም ከዚህ እንደሚከተለው ማብራራት ይቻላል ።#የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከድንግል_ማርያም መርገም ያለበትን ሥጋ ከነሳ ክብር ምስጋና ይግባውና  መርገም ባለበት ሥጋ መርገምን አራቀ ማለት በጭራሽ አያስኬድም። ይህ ደግሞ አለም እንዲድን የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበትም ምክንያት ከንቱ ሊሆን ነው ። የአምላክ መውረድ መወለድ ያስፈለገበት ምክንያትኮ ሰው  ሁሉ የመረገም የእዳ የበደል ተጠያቂ ስለነበር ንጹሕ የሚያድን በመጥፋቱ ነው።ለዚህም ነው በነብዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው?#እግዚአብሔር_አየ_ፍርድም_ስለሌለ_ተከፋ_ሰውም_እንደሌለ_አየ_ወደ_እርሱ_የሚማልድም_እንደሌለ_ተረዳ_ተደነቀም_ስለዚህም_የገዛ_ክንዱ_መድኃኒትን_አመጣለት_ጽድቁም_አገዘው ኢሳ49፥17  

 ++++++++++++++++++++++++++++

🙏አዎን እግዚአብሔር ያጣው ንጹሕ ሆኖ ስለ ሌላው የሚማልድ ካሳ ቤዛ የሚሆን ሰው ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእዳ ከበደል በታች ስለነበሩ ንጹሕ መርገም የሌለበት ጠፋ ስለዚህም በንጹሐ ባሕርይው #ጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ንጹሕ ሥጋን ተዋህዶ  ወደ እኛ መጣ ።ነብዩ የገዛ ክንዱ መድኃኒትን አመጣለት ማለቱ  እርሱ እራሱ ሰው ሆኖ አዳነን ማለቱ ነው ።  እርሱ በባሕርይው ኃጢአት ስለማይስማማው  ኃጢአት የሌለበትን ሥጋ ለመዋሐዱ ምንም ሊያከራክር አይችልም ።መርገም ያለበት መርገም ያለበትን ማዳን ቢችል ኖሮ ከብዙ ነብያት አንዳቸው አለምን  ማዳን በተቻላቸው ነበር። #የድንግል_ማርያምን ንጽሕና በጥንቃቄ ከተረዳን ነገረ ድኅነትን እንዳናፋልስ ይረዳናል ለዚህም ነው ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ስለ #የጌታችንን_የመድኀኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰው መሆን ሲገልጽ #ስለእመቤታችን  ንጽሕና አስረግጦ የተናገረው #ወለደት_ድንግል_ዘፀንሰቶ_እንዘ_ኢተአምር_ብእሴ_በሥጋ_ዘፈጠሮ_ለርእሱ_ወወለደቶ_ዘእንበለ_ደነስ_ወሕማም_ወኢረሰስሐት_በሐሪስ_ሐፀነቶ_ዘእንበለ_ፃማ_ወድካም_ወአጥበቶ_ዘእንበለ_ድካም_ወአልሐቀቶ_በሕግ_ዘሥጋ_ዘእንበለ_ትካዝ ።ሃይማኖተ አበው ዘአትናቴዎስ 28፥19

#ለተዋሕዶ_የፈጠረውን_ሥጋ_ያለ_ወንድ_ዘር_ያለ_ኃጢአት_ያለምጥ_ወለደችው_የአራስነት_ግብርም_አላገኛትም_ያድካም_ያለመታከት_አሳደገችው_ያለድካም_አጠባችው_ለሥጋ_በሚገባ_ሕግ_ምን_አበላው_ምን_አለብሰው_ሳትል_አሳደገችው

👉ማብራሪያውን በክፍል ሶስት እንመለከታለን፡፡

+++++++++++++++++++++

ክፍል ሦስት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"
+++++++++++++++++++++++++++
የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1


🍀ድንግል_ማርያም_የውርስ_ኃጢያት_ይመለከታታልን ?

👉ክፍል አንድ👈   

👉ድንግል ማርያም የዘር ኃጢያት የለባትም ለዚህም እጅግ በርካታ ማረጋገጫዎችን መዘርዘር ሲቻል በዚህ ጽሁፍ ግን ለጊዜው የሚከተሉትን ሶስት ነጥቦች እንመለከታለን     

፩. አስቀድመው ነብያት የዘር ኃጢአት #ጥንተ_አብሶ እንደሌለባት አስረግጠው ተናግረዋል ከነዚህም ጥቂቶቹ ለመመልከት ያህል፡

++++++++++++++++++++++++++++++             

 ፩.፩ ነብዩ ኢሳይያስ #እግዚአብሔር_ዘርን_ባያስቀርልን_ኖሮ_እንደ_ሰዶም_በሆንን_እንደ_ገሞራም_በመሰልነ_ነበር ኢሳ 1፥9 ዘር የተባለች ዓለም የዳነባት አምላክ ሰው የሆነባት #ድንግል_ማርያም ናት ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን ክታቡ #የአብራሃምን_ዘር_ይዞአል_እንጂ_የያዘው_የመላእክትን_አይደለም ዕብ 1፥17 በማለት ጌታ ሰው የሆነባትን ዘር የአብርሃም ዘር እያለ ይጠራታል ነቢዩ ኢሳይያስም እግዚአብሔር ያስቀራት ዘር ያላት #እመቤትችንን ነው #አምላካችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ሲሆን ከመርገመ አዳም ከመርገመ  ሔዋን ለይቶ በንጽሐ ሥጋ በንጽሐ ነፍስ ጠብቆ ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ለማዳን ምክንያት ያደረጋት ዘር ናት።

++++++++++++++++++++++++++

፩.፪ ነብዩ ዳዊት #የወርቅ_ልብስ_ተጎናጽፋና_ተሸፋፍና_ንግስቲቱ_በቀኝህ_ትቆማለች_ልጄ_ሆይ_ስሚ_እይ_ጆሮሽንም_አዘንብይ_ወገንሽን_የአባትሽን_ቤት_እርሺ_ንጉሥ_ውበትሽን_ወዶአልና መዝ 49፥9-11 ወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ሲሆን ተጎናፅፋ የተባለው ደግሞ ንጽሓ ስጋ ላይ #ንጽሓ_ነፍስ_ንጽሃ_ነፍስ ላይ ንጽሓ ልቦና መደራረቧን የሚያስረዳ ነው ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ የተባለው ደግሞ ከሰው ዘር በሙሉ መለየቷን የዘር ኃጢአት እንዳላገኛት የሚያስረዳ ነው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ እመቤታችንን ልጄ እያለ መጥራቱ ከሱ ዘር እንደምትወለድ ያስረዳናል ጌታም ከሷ ስለተወለደ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠርቷል ማቴ 1፥1 ንጉሥ የተባለ ልጇ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሲሆን ውበትሽን ወዷልና ማለት ውበት ንጽሕናሽን ሊዋሃደው ወዷልና ማለት ነው፡፡

+++++++++++++++++++++++++++

 ፩.፫ ጠቢቡ ሰሎሞን #ወዳጄ_ሆይ_ሁለንተናሽ_ውብ_ነው_ነውርም_የለብሽም መኃ4፥7 ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ተቃኝቶ እመቤታችንን ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየ ንጹሕ ነው ብሎ አመስግኗታል፡፡
፪. የቅዱስ ገብርኤል ብሥራታዊ ሰላምታ እመቤታችን የጥንተ አብሶ ፍዳ #የዘር_ኃጢአት እንደሌለባት በሚገባ ያስረዳል ይህንንም እንደሚከተለው በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን
 
#ጸጋን_የሞላብሽ_ሆይ_ደስ_ይበልሽ_ጌታ_ካንቺ_ጋር_ነው_አንቺ_ከሴቶች_መካከል_የተባረክሽ_ነሽ"  ሉቃ 1፥28  

++++++++++++++++++++++++

፪.፩ #ጸጋ_የሞላብሽ_ሆይ እናስተውል የሰው ልጆች ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል በተባለበት ዘመን ጸጋ የሞላብሽ የሚል ልዩ ምስጋና የቀረበላት #እመቤታችን ብቻ ናት በጥንተ አብሶ ፍዳ ምክንያት ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲህ ነበር የተባለው #ሁሉም_የእግዚአብሔር_ክብር_ጎሎአቸዋል ሮሜ 3፥24 እንግዲህ ሁሉ ጸጋ ጎሎአቸዋል የተባለው ሁሉ ኃጢአት ስለሠሩ አይደለም ነገር ግን አዳማዊ መርገም በሁሉ ስለደረሰ ነው ለዚህም ነው #ኃጢአት_ባልሰሩት_ላይ_እንኳን_ሞት_ነገሰ ሮሜ 5፥14 ተብሎ የተጻፈው ታድያ ሰው ሁሉ መረገመ አዳም ስለደረሰበት ከጸጋ በታች ከተባለ ድንግል ማርያም እንዴት ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ❓ ይህ በርግጥም #እመቤታችን የዘር ኃጢአት ፍዳ እንደማይመለከታት ያስረዳናል ድንግል ማርያም ይህ የምስጋና ቃል የቀረበላት ጌታን ገና ከመጽነሷ በፊት ነው ይህ ማለት ደግሞ ጌታችን ሰው ሆኖ ጸጋ ለጎደለው አለም ካሳ ቤዛ ሳይሆንለት  ድንግል ማርያም ጸጋ የሞላብሽ ተባለች ማለት ከእናቷ ማህጸን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን ጠብቋታል ማለት ነው፡፡

+++++++++++++++++++++++++++++

፪.፪ #ከሴቶች_መካከል - ሁለተኛው ነጥብ #ድንግል_ማርያም ከሴቶች ተለይታ የተባረከች እንድትባል ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ በዘር ኃጢአት ምክንያት በሌሎች የደረሰ መረገም በእርሷ ስላልደረሰ ነው እንዲህ ባይሆን ኖሮ ይህ ምስጋና ባልተገባትም ነበር ስለ ሌሎች የሰው ልጆች መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጽ #ልዩነት_የለም_ሁሉ_ከበደል_በታች_ናቸው ሮሜ 3፥22 ይላል።ስለእመቤታችን ሲናገር ግን ከሴቶች መካከል ብሎ መለየቷን በግልጽ ያስቀምጣል እንግዲህ ሰው ሁሉ ያለ ልዩነት ከበደል በታች በተባለበት ዘመን እርሷ የተለየች ከተባለች በእርግጥም #ወላዲተ_አምላክን የውርስ ኃጢአት ፍዳ አይመለከታትም ማለት ነው ። #እመቤታችን ክብር ምስጋና ይግባትና የጥንተ አብሶ ፍዳ ይመለከታታል ከተባለ የእርሷ መለየት የቱ ጋ ሊሆን ነው? ስለዚህም የመልአኩ የሰላምታ ቃል ስህተት ነው እንላለን❓ አንልም እውነታውን ይዘን ድንግል ማርያም በእውነት ከመርገመ አዳም ከመርገመ ሔዋን የተለየች ንጽሕት ቅድስት መሆኗን እንመሰክራለን እንጂ፡፡

++++++++++++++++++++++
 
፪.፫ #የተባረክሽ_ነሽ - በሶስተኛ ደረጃ ከመልአኩ የምስጋና ቃል #ድንግል_ማርያም የውርስ ኃጢአት እንደሌለባት የሚያስገነዝበን የተባረክሽ ነሽ የሚለው ኃይለ ቃል ነው 
⚡️በአጠቃላይ ድንግል #ድንግል_ማርያም ከላይ በመልአኩ የሰላምታ ንግግር ከብዙ በጥቂቱ እንደተመለከትነው የዘር ኃጢአት በፍጹም እንደማይመለከታት ነው ይህም አምላክ አለምን ለማዳን ከእርሷ ከሥጋዋ ሥጋ ክነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ለመሆን ያዘጋጃት በመሆኗ የእርሷ ንጽህና በሰው ልጆች መዳን ውስጥ በምክንያትነት ወደፊት በቀጣዩ ክፍላችን የምንመለከተው ይሆናል፡፡

+++++++++++++++++++++++++++++

ክፍል ሁለት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"
++++++++++++++++++++++++++
የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1


🔥ነገረ ድኅነት🔥 ክፍል አሥራ አምስት
እግዚ አብሔር እኛን አዳነን ስንል የሐጥያት ደሞዝ ከሆነው ከሞትና ከቅጣት መዳን ብቻ ወይም ከኩነኔ መዳንና ማምለጥ ብቻ አይደለም።መዳን የሐጥያት ስርየት ማግኘት ከቅጣት መዳን ብቻ ሳይሆን ከዚያ እጅግ ያለፈ ጥልቅና ሁለንተናዊ ነው።ይህ መሰረታዊና ዋና ነገር ነው።ሆኖም ግን ይህ እንዳለ ሆኖ በዚያ ላይ የተሰጡን ብዙ ጸጋዎችና ሀብታት አሉ።ጌታችን ያደረገልን የመዳን ቸርነት እና ስጦታ ስለኛ ተገብቶ የሐጥያታችንን እዳ መክፈልና እኛን ነጻ ማውጣት ብቻ አይደለም ከዚያ በላይ የሆነ እጅግ በጣም ብዙና ድንቅ ነገር ነው እንጂ።

++++++++++++++++++++++++++++++++++++

በአጠቃላይ መዳን ስንል 4መሰረታዊ የእግዚ አብሔር ስጦታዎችን ያጠቃልላል እነዚህም
1ሐጥያት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን
2ፈጣሪውን እንዲያውቅ መሆን
3ሐዲስ ተፈጥሮ
4በቅድስና(እግዚአብሔርን በመምሰል)ማደግ ናቸው።

1🌱ሀጥያት ካመጣው ፍዳ ሁሉ መዳን
በአዳምና ሔዋን ምክንያት በባሕሬችን የደረሰብን ጉዳት ሁለት ዘርፍ ያለው ነው።ይህም በአንድ በኩል ሕጉን በማፍረሳቸውና ቃሉን ባለመጠበቃቸው ምክንያት ህግ አፍራሾች እና ወንጀለኛ ሆንን።ከዚህም የተነሳ(ህጉን በማፍረስ ምክንያት)በሕግ አፍራሾች ላይ የሚደርሰውን የህግ ርግመት ደረሰብን።ስለዚህም ቅጣት የሚገባን ወንጀለኞች፡ሕጉን በሚተላለፉ የሚደርሰው የሕግ ርግመት የሚደርስብን ሆንን።በሌላ በኩል ደግሞ ባህሪአችንን በሐጥያት ምክንያት መለወጥና መጎስቆል አገኘው፡ ሕይወትን አጣን ለሞት ተገዛን።ሞት ወደ ባሕሪ አችን ዘልቆ ገብቶ ተቆጣጠረን።ስለዚህም መዳናችን ይህንን መንገድ የተከተለ ይሆን ዘንድ ይገባ ነበር።በአንድ በኩል በሕጉ ከመጣብን ርግመት ነጻ ያወጣንና ጸጋውን ይመልስልን ዘንድ በሌላ በኩል ደግሞ በሐጥያት ምክንያት ሙታን የሆነውን ሕያዋን ያደርገንና ሕይወትን ይሰጠን ዘንድ ያስፈልገን ነበር።

+++++++++++++++++++++++++++++++++++

የእግዚአብሔርን ሕግ በማፍረሳችን ያመጣናው ርግመትና እዳ በሞቱ ከፈለልን ካሰልን።በአዳምና በሔዋን ውድቀት ምክንያት የሰው ልጅ በሐጥያትና በዲያቢሎስ ባርነት ስር ወድቆ ነበር።ስለዚህ ሰው ለመዳን ይህ ባርነትና ርግመቱ መወገድ ነበረበት።ይህንንም የእግዚ አብሔር አንድያ ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገንዘብ ባደረገው በእኛ ባህሪ በመስቀል ላይ በመሞቱ፡በመነሳቱ፡በማረጉና፡በአብ ቀኝ በመቀመጡ፡እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን ለቅዱሳን ሐዋርያት በመላኩ ፈጽሞታል።

+++++++++++++++++++++++++++++++

ክፍል አስራ ስድስት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"

+++++++++++++++++++++++++++++++++

የቻናሉ ሊንክ @haymanote1
@haymanote1
@haymanote1


🔥ነገረ ድህነት🔥ክፍል አሥራ አራት
እግዚአብሔር ሰውን እንዴት አዳነው?
አበው እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ይላሉ።ምክንያቱም ባሰቡት ቁጥር ሕሊናን የሚያስደንቅ ምሥጢር ተፈጽሟልና።

🍁የአዳምን እዳ ፍጡራን ሊከፍሉት አልቻሉም። እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ ዕዳችንን ከፈለልን።አዳም ሊቀበለው ይገባው የነበረውን ሁሉ ተቀብሎ አዳምን ነጻ አወጣው።

🍁አዳም በበደሉ ከገነት ወደ ሲኦል ቢሰደድ፡መድሐኔዓለም ክርስቶስ ያለ በደሉ የገነት ምሳሌ ከሆነች ከነዓን የሲኦል ምሳሌ ወደሆነች ግብጽ ተሰደደ።

🍁አዳም ከዓለመ መላእክት ተሰድዶ በእንስሳት መካከል ቢገኝ መድሐኔዓለም ክርስቶስ በከብቶች በረት ተወለደ።
🍁አዳም ከኅቱም መሬት ተገኝቶ ቢሳሳት መድሐኔዓለም ክርስቶስ ከኅቱም ድንግል እመቤታችን ተወልዶ አዳነው።

🍁አዳም ከንጹሕ ምድር/መርገም ካልደረሰባት/ ተገኝቶ ቢሳሳት መድሐኔዓለም ክርስቶስ መርገመ ነፍስ ከሌለባት ከንጽሕት እመቤታችን ተወልዶ አዳነው።

🍁አዳም የሠላሳ ዘመን ጉልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ፡ሰባት ዓመት በገነት ኖሮ፡በምክረ ከይሲ ተታሎ ልጅነቱን ቢያጣ፡መድሐኔአለም ክርስቶስ በሠላሳ ዓመቱ ተጠምቆ አዳነው።

🍁አዳም በመብል ድል ተነስቶ ከገነት ቢወጣ፡መድሐኔዓለም ክርስቶስ"ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም በእግዚ አብሔር ቃል ጭምር እንጂ"ብሎ ፈቃደ ሥጋን ስስትን ድል ነሳለት።

🍁ዲያብሎስ አዳምን ከምድር ተለይታ በምትገኝ ገነት ለብቻው በመብል ድል ቢያደርገው ጌታም ዲያብሎስን ከከተማ ርቃ በምትገኝ ገዳመ ቆሮንቶስ በጾም ድል ነሳው።

🍁አዳም ሕግ ጥሶ ከጸጋ ቢራቆት መድሐኔዓለም ክርስቶስ ራቁቱን በመልዕልተ መስቀል ተሰቀለለት።

🍁የአዳም እጅና እግር ወደ ዕጸ በለስ ቢያመሩ የመድሐኔዓለም እጅና እግር በቅንዋት ተቸነከሩ ።

🍁ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አምላክ ወልደ እግዚአብሔር ፍጹም ካሳን ካሠልን።የአዳም ዐጽም ካረፈበት በጎልጎታ ተሰቅሎ ሞትን መውጊያ አሳጣው፡የመቃብርም ኃይል ተሻረ።ርቀን የነበርነውን ልጆቼ አለን።(ማቴ27፥33፣1ቆሮ15፥56)

የተዘጋች ገነት ተከፈተች እድሜውን በሙሉ ለሐጥያት ሲናወዝ ለነበረው ለፌያታዊ ዘየማን ታላቁ ብስራት ተነገረው "ከእኔ ጋር በገነት ዛሬ ትሆናለህ"(ሉቃ23፥43)ገነት ከኃጥያት ወደ ጽድቅ ተመልሰው በቀኙ ለሚቆሙ መከፈቷን አበሰረን። ሞት በሞት ሞተ።

+++++++++++++++++++++++++++++++++++

ክፍል አሥራ አምስት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"

++++++++++++++++++++++++++++++++++++

የቻናሉ ሊንክ 👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1


🔥ነገረ ድኅነት🔥ክፍል አሥራ ሦስት
❤️እግዚአብሔር ለምን ሰው ሆነ?
ይህ ሚስጢር ታላቅ ነው።ከፍጥረት መካከል አሟልቶ አጠናቆ ያወቀው ይመረምረው ዘንድ የሚቻለው የለም። መንፈስ ቅዱስ የገለጠላቸው አበው የነገሩን:-
🍃እግዚ አብሔር ሰውን ሲፈጥር"ንግበር ሰብአ በአርአያነ ወበአምሳልነ"ብሎ ከምድር አፈር አበጀው።ይህ በአብ ልብነት አስበው፡በወልድ ቃልነት ተናግረው፡በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት የፈጠሩት ሰው ቢወድቅ"ንግበር ሰብአ"ብሎ የተናገረው ቃል ወደ አዳም መጣ።ከመሬት ያበጀው ክንድ ተዘረጋ።

🍃"ኦ አዳም መሬት አንተ ወትገብእ ውስተ መሬት"ብለው ሥላሴ በአብ ልብነት አስበው፡በወልድ ቃልነት ፈርደው፡በመንፈስ ቅዱስ ሕያውነት አጽንተውት የኖሩትን ፍርድ ሊያነሳ የፈረደበት ቃል ወደ አዳም መጣ።

🍃ዓለም በኃጥያቱ ምክንያት የእግዚ አብሔርን ድምጽ ፈርቶ ይኖር ነበር።ዘፍ3፥10-13።እሥራኤል እግዚአብሔር በሲና ተራራ በተናገራቸው ጊዜ ሙሴን "አንተ ተናገረን፡ እኛም እንሰማለን፡እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን" ዘጸ20፥18 እንዳሉት ይህን የኃጥያት ፍርሀት ከሰዎች ያርቅ ዘንድ እግዚ አብሔር ሰው ሆኖ ከእኛ ጋር ተገኘ።አማኑኤል የሰው ቋንቋ እየተናገረ በሰው ሥርአት ተመላለሰ።ድምጹን አሰምቶ በበለስ ሥር የተደበቀውን አዳም ፈለገው አገኘውም

🍃የሰው ልጅ በትእዛዛት የተሰጠውን ሕግ ይፈጽም ዘንድ አልቻለም።ሰርቶ ፈጽሞ አድርጎ ያሳየው የለምና። በመሆኑም እግዚአብሔር ወደ እኛ መጥቶ ሠርቶ አዲሲቷን ሕግ(ወንጌል) ሰጠን።

+++++++++++++++++++++++++++++++++++

ክፍል አሥራ አራት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"

+++++++++++++++++++++++++++++++++

የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1


🔥ነገረ ድኅነት🔥 ክፍል አስራ ሁለት
በተዋህዶ ነውን? አዎ
ተዋህዶ ከሚጠት፣ውላጤ፣ቱሳኤ፣ትድምርትና ቡዐዴ የተለየና አምላክ ሰው የሆነበትን ሚስጢር የሚገልጥ ቃል ነው።ሁለት አካላት አንዱ አንዱን ሳያጠፋ ሳይለወጠው፥ያለ መቀላቀል ያለ መደራረብ /በተዐቅቦ/በመጠባበቅ አንድ ሲሆኑ ተዋሐዱ ይባላል።
ለምሳሌ:-የብረትና የእሳት ውሕደት/አንድነት/።ብረትና እሳት ሲዋሐዱ ብረት የእሳትን ገንዘብ ገንዘቡ ያደርጋል።አስቀድሞ የማያቃጥል የነበረው ኋላ ማቃጠል ማፋጀት ይጀምራል። የእሳቱን ብርሀን ወርሶ የሚያበራም ይሆናል።እሳትም የብረትን ባሕርይ ባሕርይው ያደርጋል።በቀደመ አኗኗሩ ቅርጽ የሌለው ሲሆን ኋላ ከብረት ሲዋሐድ የብረቱን ቅርጽ ወርሶ ቅርጽ ያለው ይሆናል።አስቀድሞ የማይጨበጥ፣የማይዳሰስ፣ የማይመታው ኋላ ብረቱን በመዋሐዱ መጨበጥ፡መዳሰስ፡ መመታት ይጀምራል።

+++++++++++++++++++++++++++++++++

እንደዚሁ ሁሉ መለኮት አስቀድሞ እንደቀድሞ በአኗኗሩ ረቂቅ ሲሆን ነገር ግን እሳት ብረቱን ተዋሕዶ እሳቱን እንደማይታይ እርሱም ሥጋን ተዋሕዶ በግዙፍ ታየ፡ተገለጠ። እሳት ከብረት ጋር ሆኖ በመዶሻ እንደሚመታ ነገር ግን መዶሻው ባሕርይውን እሳትነት እንደሚያናውጽበት ሁሉ መለኮትም ከተዋሐደው ሥጋ ጋር በአንድነት በመኖሩ አብሮ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ።ይህን ግን መለኮታዊ ባሕርይውን አላገኘውም/በመለኮት አልሞተም/በለበሰው ሥጋ እንጂ።በሌላ በኩል ብረቱም አስቀድሞ የሌለው የማቃጠል ባሕርይ ከእሳት ወርሶ እሳት ይሆናል፡ያቃጥላል። በዚህ አይነት ደካማ የነበረ ሥጋ ከመለኮት ጋር በተዋሕዶ ሞትን ድል የሚያደርግ ተአምራትን የሚሰራ ሆነ።ይህ ቅዱስ ቄርሎስ ስለ መለኮት የመሰለው ምሳሌ ነው።

+++++++++++++++++++++++++++++

ይህው አባት በሌላ ስፍራ ለተዋሕዶ ምሳሌ እንዲሆን የነፍስንና የሥጋንም ተዋሕዶ ያነሳል።"የሚረዳህስ ከሆነ የትስብእትና/የሥጋን/የመለኮትን ተዋሕዶ በእኛ ነፍስና ሥጋ ተዋሕዶ መስለን እንነግርካለን።እኛ በነፍስ በሥጋ የተፈጠርን ነንና አንዱን የሥጋ አንዱን የነፍስ ብለን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አናደርገውም።ሰው ከሁለት አንድ በመሆኑ አንድ ነው እንጂ።ከሁለቱ ባሕርያት አንድ በመሆኑ ሁለት ሰው አይባልም።በነፍስ በሥጋ የተፈጠረ ሰው አንድ ነው እንጂ። ይህንንስ ካወቅን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶ በፊት እርስ በእርሳቸው አንድ ካልነበሩ ከተዋሕዶም በኋላም ከማይለያዩ ከሁለይ ባሕርያት አንድ እንደሆነ እናውቃለን"

(ሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ 78፥19)

በእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች እንደተመለከትነው ሁለት የተለያዩ ባሕርያት ያላቸው አካላት ተዋሕደው ያለ መለያየት ያለመጠፋፋት አንድ ባሕርይ ስለሆኑ ተዋሐዱ ይባላል። ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ሥግው ቃል) ሥጋን የተዋሐደ የእግዚአብሔር ቃል ነው።ከተዋሕዶ በኅላ መለያየት አንችልም።ይህ የመለኮት ነው ይህ የሥጋ ነው አይባልም።ሁለቱ በፍጹም ተዋሕዶ አንድ ሆነዋልና።

++++++++++++++++++++++++++++

ለምሳሌ:-ጌታችን የሰራቸው ተአምራት ለዚህ ማስረጃ ይሆናሉና።ዓይነ ስውሩን በምራቁ አፈር ለውሶ በመቀባት አዳነው።ምራቅ የሥጋን ገንዘብ የነበረ ተአምር የመስራት ኃይል ያልነበረው ሲሆን አሁን ግን ሥጋ ፍጹም ከመለኮት ጋር ተዋሕዷልና ጌታችን በምራቁ ዓይን አበራ።ይህን ዓይተን ተአምር የሰራው በሥጋው ነው በመለኮት ነው ብለን መነጣጠል አንችልም።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ነስቶ ሰው የሆነ አምላክ ነው ስንል ሰው በመሆኑ ከባሕርይው ተዋራጅነት የለበትም።በሰማይ በዙፋኑ እየተመሰገነ በምድር ዞሮ እያስተማረ መከራን ተቀበለ እንጂ።በአጠቃላይ ስንመለከት ተዋሕዶ ማለት እንደ አውጣኬ ተጣፍቶ አንድ ባሕርይ ብቻ ሳንል እንደ ንስጥሮስ በመደረብ ሁለት ባሕርይ ነው ሳንል እንደ ሌሎቹ መናፍቃን በመቀላቀል የሚል ሃሳብ ሳናስገባ በመለኮት ከሥጋ ጋር ፍጹም በመወሐዱ የኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ባሕርይ በተዋሕዶ መሆኑን የምንመሰክርበት ነው።

+++++++++++++++++++++++++++

ለመሆኑ ጌታችን በተዋሕዶ ሰውን ያዳነው ለምንድነው?
ቅዱስ አትናቴዎስ እንደተናገረው:-
ሀ⚡️ሞት በተዋሕዶ ከኛ ጋር ይኖር ነበርና ሞትን ይሽረው ይነቅለው ዘንድ መለኮት ከእኛ ሥጋ ጋር ተዋሐደ።
ለ⚡️ዲያብሎስ በእባብ ሥጋ ተሰውሮ አዳምና ሔዋንን አሳስቷቸው ነበርና።መለኮትም የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ ድል ነሳው።ምሥጢርን በምሥጢር መመለስ የእግዚአብሔር ጥበብ ነውና።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሲያስተምር በነበረበት ወቅት ሙት ያስነሳ፡ድውያንን ይፈውስ፡ማዕበሉን ይገስጽ ነበር።እነዚህ በፍጡር ሊሰሩ የማይችሉ ናቸው።

+++++++++++++++++++++++++++++

እርሱ አምላክ ስለሆነ አድርጓቸዋል።በሌላ በኩል ይራብ ይጠማ መከራ ይቀበል ነበር።አምላክ የማይራብ የማይጠማ መከራ የማይቀበል ነው። እሱ ግን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነውና ይሕን በፈቃዱ አድርጎታል።ይህን ለይተን እዚህ ላይ አምላክ ነበር።በዚያ ቦታ ሰው ሆነ አንልም።ይልቁንስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም/የአብ ልጅ የማርያም ልጅ/ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው በመሆኑ ይህን አደረገ እንላለን እንጂ። እሱ በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ በመሆኑ የሥጋንም የመለኮትንም ሥራ ሰራ።በእርሱ ባሕርይ ተከፍሎ መለያየት የለበትም።
ስለ ጌታችን ጳውሎስ ሲናገር።"በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዜብሔርን ቤተክርስቲያንን ትጠብቋት ዘንድ..."ሐዋ20፥28ይላል።መለኮት በባሕርይው ሥጋና ደም ያለው አይደለም ረቂቅ ነው እንጂ።ነገር ግን የሥጋን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ ከሥጋ ጋር ፍጹም ተዋሕዷልና እግዚአብሔር ደሙን አፈሰሰ ተባለ።ከተዋሕዶ በኋላ መለኮትን ለብቻ ሥጋን ለብቻ መነጠል ስለማይቻል ይህ ተናገረ።

++++++++++++++++++++++++++++
ክፍል አስራ ሦስት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"

የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1


🔥ነገረ ድሕነት🔥
በቡዐዴ ነውን?አይደለም ቡዐዴ መለየት መለያየት ማለት ነው።ሁለት ነገሮች አንድ ላይ ሲሆኑ በኋላ መለየት መነጠል ሲቻል ቡዐዴ ይባላል።ለምሳሌ:-በቆሎና ስንዴን/በጥሬአቸው እነዚህ ሁለት የእህል ዘሮችን ከቀላቀልናቸው በኃላ ስንፈልግ መለየት እንችላለን።አብረውም ሳሉ በቆሎውን በቆሎ ስንዴውን ስንዴ እንላለን።የክርስቶስ ሰው የመሆን ምሥጢር ግን ከዚህ የተለየ ነው።ከተዋሕዶ በኋላ ሥጋና መለኮትን ለያይቶ ለየብቻ ይህ መለኮት ነው ይህ ሥጋ ነው አይባልም። እንደ ብረትና እሳት ፍጹም ተዋሕዶ ስለሆነ መነጣጠል አይቻልም።ስለዚህ ክርስቶስ ስርው የሆነው እንበለ ቡዐዴ ነው።


🔥ነገረ ድኅነት🔥ክፍል አስራ አንድ
እግዚአብሔር ሰው ሆነ ስንል እንዴት ነው ከሚለው የቀጠለ...

💥በቱሳኤ ነውን?አይደለም።ቱሳኤ ቅልቅል ማለት ነው። ይህም እንደ ማር እና እንደ ውኃ ነው፡ውኃና ማር ሲቀላቀሉ ስም ማዕከላዊ ይገኝባቸዋል።መልክ ማዕከላዊ እንደ ማር ሳይነጣ እንደ ውኃ ሳይጠቁር መካከለኛ መልክ ይይዛል፡
ጣእም ማዕከላዊ እንደ ማር ሳይከብድ እንደ ውኃም ሳይቀል መካከለኛ ጣዕም ይኖረዋል።ወተትና ቡናም ሲቀላቀሉ እንዲሁ ነው።ቡናው እንደ ወተት አይነጣም ወተቱም እንደ ቡና አይጠቁርም፡መካከለኛ ቀለም ይኖራቸዋል።
በምሥጥረ ሥጋዌ ግን ሥጋና መለኮት አንድ የሆኑት ያለመቀላቀል ነው።ሥጋ ወደ መለኮትነት መለኮት ወደ ሥጋ ባሕርይ መጥቶ መካከለኛ የሆነ ነገር አልመጣም።ሥጋም ሥጋዊ ባሕርይውን ሳይለቅ መለኮትም መለኮታዊ ባሕርይውን ሳይተው በመጠባበቅ ተዋሕደዋል።ያለመቀላቀል ሌላ አዲስ ነገር ሳይፈጥሩ አንድ ሆነዋል።ሥጋም የመለኮትን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ፡መለኮትም የሥጋን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ ተዋህደዋል።

+++++++++++++++++++++++++++++++++++

ምሳሌ:-ሙሴ ባያት ዕጸ ሐመልማሉ ከነበልባሉ/ቅጠሉ ከእሳቱ/ጋር ተስማምተው ነበር።አንዱ ሌላውን አላጠፋውም።ቅጠሉ እሳቱን ሳያጠፋ እሳቱ ቅጠሉን ሳያቃጥል ያለመጠፋፋት አንድ ላይ ታይተዋል።እንደዚሁም መለኮት የሥጋን ባሕርይ ሳያጠፋ ሁለቱ ያለመጠፋፋት አንድ ሆኑ።ከዚህ ውጪ ተቀላቀሉ ካልን ግን ባሕርይአቸውን ለቀዋል፡ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ አይደለም፡ሌላ አዲስ ባሕርይ አለው ስለሚያስብልብን በሰውነቱ መብላት መጠጣቱን የሰውን ስራ መስራቱን ምትሐት ነው እንድንል በአምላክነቱ ሙት ማስነሳቱን፡ተአምር መሥራቱን፡እንዳናምን እንድንጠራጠር ያደርገናል።በመቀላቀል ወደ ሌላ ባሕርይ ተቀይሯል ካልን ፍጹም አምላክ ነው ልንል አንችልምና ነው።

💥በትድምርት ነውን?አይደለም ትድምርት መደረብ መደመር ማለት ነው።ልብስ ቢደርቡት ይደረባል፡ቢነጥሉት ይነጠላል። መለኮት ከሥጋ ጋር አንድ የሆነው ግን እንዲህ በመደረብ አይደለም፡በተዋሕዶ እንጂ።ምክንያቱም በትድምርት ከሆነ ሲፈልጉ መነጠል አለ።ቀድሞውንም በአንድ ላይ ይደረባል እንጂ አይዋሐዱም።መለኮትና ሥጋ ግን በመጀመሪያም በተዋሕዶ አንድ ሆነዋል በኋላ ያለመነጣጠል ኖረዋል።መለኮትን ከሥጋ ከተዋሐደ በኋላ መነጣጠል አይቻልም።

+++++++++++++++++++++++++++++++++
ክፍል አሥራ ሁለት ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"

+++++++++++++++++++++++++++++++++
የቻናሉ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1


🔥ነገር ድኅነት🔥 ክፍል አስር
እግዚ አብሔር ሰው ሆነ ስንል እንዴት ነው ከሚለው የቀጠለ...

💥በኅድረት ነውን?አይደለም ይህ ሐሳብ የመጣው በምንታዌ(በሁለትነት)ከሚያምኑ በ2ተኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ መናፍቃን ነው።እነርሱም ሁለት አምላክ አለን። አንዱ ክፉ ሌላው ደግ፡ክፉው ይህን ዓለም/ሥጋን/ፈጠረ።ደጉ የማይታየውን ዓለም/ነፍስን/ፈጠረ።ስለዚህ ነፍስ በደጉ፡ሥጋ የተፈጠሩ በመሆናቸው ሁለቱ አይዋደዱም።ነፍስ በሥጋ ታስራ ስትሰቃይ ትኖራለች፡አምላክ እርሷን ነጻ ሊያደርግ መጣ፡በሥጋ ላይ አድሮ ተመላለሰ፡ግን ሥጋ አልተዋሃደውም ምክንያቱም ሥጋ የክፉ አምላክ የእጁ ሥራ የረከሰ ፍጥረት ነውና ይላሉ።

ይህ አስቀድሞ በነበሩ በሁለት አማልክት በሚያምኑ መናፍቃን የተጀመረ የኅድረት ትምህርት ሥር በስተመጨረሻ "በአንድ አምላክ እናምናለን"ወደ ሚሉ መናፍቃንም ደረሰ።
ስለዚህም ከቤተክርስቲያን የተነሱ እነ ንስጥሮስም አምላክ ከድንግል ማርያም በተወለደው በኢየሱስ ላይ አደረበት እና የጸጋ አምላክ አደረገው እንጂ ሥጋን አልተዋሐደም አሉ።/ንስጥሮስ 431ዓ,ም በኤፌሶን የተወገዘ መናፍቅ ነው።/ይህ መናፍቅ ዳዊት በምኅደሩ እንደሚያድር በማርያም ልጅ ኢየሱስ ላይ አምላክ አደረበት።ድንግል ማርያም የወለደችው ሰውን ነው/ወላዲተ ሰብእ ይላታል/።ሁላ እርሷ በወለደችው ላይ ፈጣሪ አደረ ብሎ በድፍረት ያስተምር ነበር።ይህንን የክህደት ትምህርት ይዘው ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ ነው።ሥጋን አልተዋሃደም የሚሉ መናፍቃን ዛሬም አሉ።ይህ ዓይነት አስተምሮ ግን ፍጹም ስህተት ነው።ምክንያቱም:-

1☀️ከጽንሰቱ ጀምሮ በልደቱ ጊዜ የተደረገውን ነገር የተነገረለትን ቃል መሻር ስለሚሆንብን ነው። ኢሳይያስ"ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች"ኢሳ7፥14 አማኑኤል ትርጓሜው"እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ"ብሎ ተናግሯል። ማቴ1፥23 የተወለደው ሕጻን አማኑኤል የተባለው ሲወለድም አምላክ በመሆኑ ሥጋን ነስቶ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነበር።ከዚህ ሌላ አሁንም በትንቢት"ሕጻን ተወልዶልናል"ወንድ ልጅም ተሰቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል"የሚል ቃል እናገኛለን።ኢሳ9፥6በቤተልሔም ዋሻ ድንግል ማርያም የወለደችው ሰብአ ሰገል ወርቅ እጣን ከርቤ መብአ አድርገው ያቀረቡለት ሕጻን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ስለሆነ ስሙም ኃያል አምላክ ተብሎ ይጠራል ተባለለት።ይህን ሕጻን ኤልሳቤጥ በማሕጸን ሳለ ገና ጌታዬ ብላ ጠርታዋለች።ሉቃ1፥43።ስለዚህ መናፍቃን እንደሚሉት ድንግል ማርያም ወላዲተ ሰብእ አይደለችም።የአምላክ እናት ናት እንጂ።ኢየሱስ ክርስቶስም አስቀድሞ ሰው የነበረ በኅላ በጸጋ የከበረ አይደለም።ከድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ ሰው #የሆነ አምላክ እንጂ።

2☀️ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ ነው፡መለኮትና ሥጋ አልተዋሐዱም ከተባለ ሰው ገና አልዳነም ማለት ይሆናል።
በተዋህዶ መለኮትና ሥጋ አንድ ካልሆኑ ኢሳይያስ
"በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሟል ስለመተላለፋችን ቆሰለ ስለበደላችንም ደቀቀ...ተጨነቀ ተሰቃየ አፉንም አልከፈተም"ኢሳ5፥3 ብሎ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ባልተናገረ ነበር።እርሱስ በተዋህዶ መለኮትና ሥጋ አንድ መሆናቸውን በመንፈስ ተገልጾለት ተናገረ።ለምን ቢሉ መታመምና መቸገር የመለኮት ባሕርይ አይደለምና፡በተዋሐደው ሥጋ ታመመ፡ተቸገረ፡ቆሰለ ለማለት።ሥጋ ብቻውነው ካልን ግን ሰው የራሱን መከራ ራሱ ተቀብሎአልና ገና አልዳነም ወደ ሚል ክህደት ይወስዳል።ሰውም በሰው አይድንምና አዳም አልዳነም ማለትን ያስከትላል።በተዋሕዶ ምሥጢር ግን መለኮት የሥጋን ገንዘብ የራሱ በማድረጉ መከራን ሁሉ ታገሰና ተቀበለ እንላለን።ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ አይደለም።በመሆኑም ኅድረት የሚለው አስተምሮ ክህደት ነው።

3☀️እግዚአብሔር አብ ስለ ባሕርይ ልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምወደው ልጄ እርሱ ነው በማለት መስክሯል። መለኮትና ሥጋ በተዋህዶ አንድ ባይሆኑ ኑሮ በነ ቅዱስ ጴጥሮስ ፊት የቆመውን ኢየሱስ ክርስቶስን ልጄ ብሎ ባልጠራው በዚህ ፈንታ የልጄ ማደሪያ ባለው ነበር።ነገር ግን ሥጋ ከመለኮት ጋር በመዋሐዱ ማደሪያ ሳይሆን ልጄ ተብሎ ሥጋ የመለኮትን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጎ የአብ የባሕርይ ልጁ ተባለ።ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነው በኅድረት ሳይሆን በተዋህዶ ነው።

+++++++++++++++++++++++++++++++

ክፍል አስራ አንድ ይቀጥላል

"እምነትክን እወቅ እንዳቶን መናፍቅ"

++++++++++++++++++++++++++
የቻናሊ ሊንክ👉@haymanote1
👉@haymanote1
👉@haymanote1

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

572

obunachilar
Kanal statistikasi