#እንኳን_አስተርእዮ_ማርያም_አደረሳችሁ
አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል።
✅ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።
♦ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፣ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ
ቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል።
✅ ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጿል❗
✅ ባሕረ ጥበባት ፈልፈለ ማኅሌት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችንን ሶልያና በማለት በሐዲስ ቅኔ ይቀኝላታል።
♦ለሶልያና ስመ ተጸውኦ መነሻ ግንዱ “ሴሊኒ” የሚለው ልሳነ ጽር (የግሪክ ቃል) ነው ይላሉ የሀገራችን የሰዋስው ሊቃውንት፤ በትርጉም ሶልያና ያለውን የቅዱስ ያሬድን ስያሜ ከሴሌኒ ጋር በአቻ ፍካሬ “ጨረቃ” የሚል ትርጉም ሰጥተውት እናገኛለን።♦ ቅዱስ ያሬድ “ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና፣ ወረደ ወልድ እም ዲበ ልዕልና፣ ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና” አለ። ሶልያና ባረፈች ጊዜ ክብር፣ የክብርም ክብር የተገባው ወልድ ልጇ ክርስቶስ ከልዕልናው በልዕልና ወረደ እናቱን በጠሊሳነ ንግሥ በዚያን ጊዜ ሸፈናት። “ ጠሊሳነ ንግሥ ያለው የክብሯን መንዲል የንግሥናዋን መጎናፀፊያ ነው።
ሶ ➡ ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ (ኪዳንሽ ባይኖር ምክንያተ ድኂን የለም)
ል ➡ ልሳንየ ላእላእ ይሴብሀኪ (ዲዳው ትብ አንደበቴ ያመሰግንሻል)
ያ ➡ያንቅአዱ ሀቤኪ ኩሉ ፍጥረት(ፍጥረታት ሁሉ ወደአንቺ ያንጋጥጣሉ)
ና ➡ ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለድንግል፥ (እነሆ የድንግል ታላቅነቷ ተገለጠ)
✅ ማኅቶተ ቤተክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የእመቤታችን ዕረፍት የሰርግ ቀን በተባለ የዕረፍቷ ዕለት ሰማያዊውን ሰርግ በዓይነ ሕሊናችን አቅርበን ዕንድናይ እንዲል ሲል ያመሠግናታል።
ዮም ይባቤ የበቡ
ኃጢዓተ እለ ዘገቡ
በኪዳነ ድንግል ካህን ሥርየተ እለ ረከቡ
ከመ ይባኡ ለወልድኪ ውስተ ከብካቡ
የሊቁ ፍቅር ምንኛ ይደንቃል! የድንግሊቱ የአምላክ እናት “ቃልኪዳኗ” ኃጢአት ሲሰሩ ለኖሩ ሥርየተ የሚያሰጥ “ካህን” ነው ይላል። የታመኑባት ኃጥአን በዕለተ ምጽዓት በደስታ እየዘመሩ ወደ ሰርጉ አዳራሽ የሚሻገሩባት አግዓዚት፣ ተጨንቀው ለሚጠሯት ሰማዒት ፣ ወደ ማኅደረ ነፍስ የሚደርሱባት ማዕዶት እርሷው ናትና።
♦የእናታችን የእመቤታችን የእመብርሃን የወላዲተ አምላክ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን አሜን❗
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
@dnzema @dnzema @dnzema╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯