Postlar filtri

Below are some of the kind messages of appreciation you’ve shared with us.

በዚህ ዓመት የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፋችሁ ተማሪዋች እንኳን ደስ አላችሁ። መልካም የስራ ዘመን ይግጠማችሁ።

በዚህ ዓመት ውጤት ያልመጣላችሁ ተማሪዎች ደግሞ አይዞን ቀጣይ ከፈጣሪ እና ከልፋታችሁ ጋር መልካም ይሆናል ተስፋን በፍጹም እንዳትቆርጡ።

በተለያየ መንገድ ሁላችሁም ስለሰጣችሁን ምስጋና ከልብ አመሰግናለሁ።

መላ ቱቶሪያልስ ከዚህም በላይ ጠንካራ ተቋም ሆኖ ብዙዎችን መጥቀም እንዲችል ማገዝ የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ልታወሩኝ ትችላላችሁ @melakubeshaw

መላ ቱቶሪያልስ
የጥበብ ቋት

Congratulations to all the students who passed this year’s exit exam! Wishing you a successful and fulfilling career ahead.

To those who didn’t get the results they hoped for; don’t lose hope. With God’s help and your continued effort, next year can be your turning point. Keep pushing forward.

I am sincerely grateful for all the kind messages and support you’ve shown in so many ways.

If you’d like to help Mella Tutorials grow into a stronger institution that can support even more students, feel free to reach out and support us in any way you can. Contact us through this link: @melakubeshaw

Ermi E-learning dan repost

ውጤት online ላይ ተለቆል ቤተሰቦች

Tikvah-University dan repost
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የፈተና አገልግሎት ክፍያ (Exam Service Payment) የከፈሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት ዛሬ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የተለቀቀ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጠናል።

በዚህም የፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈሉ ተቋማት የተፈታኞቻቸውን ውጤት እንዲያውቁት የተደረገ ሲሆን፤ የግል ተፈታኞች ወደ ተማሩበት ተቋም በመሔድ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል። 

@tikvahuniversity

Sincerest congratulations on your graduation 🎓

Mella Tutorials

#ExitExamResult

“ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” - ኤባ መጂና (ዶ/ር)

በዘንድሮው መውጫ ፈተና ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል። 

የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ መጂና (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽም “ ዳታውን አናላይዝ እያደረግን ነው ገና። ውጤት ግን ተለቋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ስንት ተማሪዎች አለፉ ? ስንት ተማሪዎች ወደቁ ? የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ አናላይሲሱ እየተሰራ እንደሆነ፣ ነገ ማብራሪያ እንደሚሰጡን መሪ ሥራ አስፈጻሚው የገለጹ ሲሆን፣ ነገር ግን ውጤቱ ስለተለቀቀ ተማሪዎች ማየት እንደሚችሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ከዚህ ቀደም ውጤት በሚለቀቅበት በተለመደው ድረ ገጽ ውጤት ማየት እንደሚቻል መሆኑን ጠቁመዋል። “ ውጤት የሚታየው ያው ከዚህ በፊት በነበረው ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት በበኩሉ፣ ተማሪዎች እያዩ መሆኑን፣ ማለፊያው 50% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። ምን ያህል ተማሪዎች እንዳለፉና እንዳላለፉ መረጃው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

https://result.ethernet.edu.et

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA dan repost
#ExitExam

የ2017 ዓ/ም የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች እየተላከ ይገኛል።

ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ውጤት ለተቋማት እየላከ እንደሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋማቱ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

ውጤቱ የደረሳቸው የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸው ውጤታቸውን በሬጅስትራር በኩል እንዲያዩ መልዕክት እያስተላለፉ ናቸው።

ካስፈተኗቸው ተማሪዎች መካከልም ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንዳለፉም ይፋ ማድረግ ጀምረዋል።

የመውጫ ፈተናው ውጤት እስካሁን ሁሉም ተማሪ ባለበት ሆኖ እንዲያይ ከዚህ በፊት ውጤት በሚታይበት ድረ-ገጽ https://result.ethernet.edu.et ላይ አልተለቀቀም።

ውጤት በድረ-ገጽ ማየት  ሲጀመር ተከታትለን መረጃ እናደርሳለን።

በሌላ በኩል ፥ በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች በሳምንቱ መጨረሻ ያስመርቃሉ።

20 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ቅዳሜ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች እሑድ ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ያካሒዳሉ።

🎓 አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ 
🎓 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ 
🎓 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ 
🎓 ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ 
🎓 እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ራያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ወልድያ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 አክሱም ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ፣
🎓 መቱ ዩኒቨርሲቲ እና
🎓 የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስመርቁ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia @tikvahuniversity

እግዚአብሔር ይመስገን

የዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርኩባቸው ጊዜያት ጥሩ ውጤት እንደመጣ ከአገዙኝ ዘዴዎች አንዱ የYoutube ቶሪያል ቪዲዎችን መመልከት ነበር። በወቅቱ በአማርኛ የተዘጋጀ ቪዲዮ ስለማይገኝ ብዙ ጊዜ የመመለከተው በህንዳውያን የተዘጋጁ ቪዲዎችን ነበር በተለይም ቁጥርና ትምህርቶችን በቀላሉ ለመረዳት ጥሩ አማራጮች ነበሩ። ከተመረኩ በኋላ ለእኔ Youtube ብዙ የህይወት ትምህርቶችን ያገኘሁበት መድረክ ነው።

የ Youtube ገጽ ከፍቶ የማስተማር ህልም የነበረኝ ከግቢ ተመርቄ መምህር በሆንኩበት አጋጣሚ ነበር፣ በተለይም አብዛኞቹ ትምህርቶች በምናውቀው ቋንቋ አለመኖሩ ከዛሬ ነገ እጀምራለሁ እያልኩ ሳልጀምር ብዙ ጊዜ ከቆየው በኋላ ከሁለት ዓመት በፊት በ 2015 ነበረ ልክ በዛሬዋ ቀን በጓደኛዬ ኤርምያስ ነጋሽ (ermi e-learning) ወትዋችነት ቪዲዮ መልቀቅ የጀመርኩት በወቅቱን የመጀመሪያው የ Exit Exam የሚሰጥበት ጊዜ በመሆኑ ተማሪዎችን ያግዛል ብዬ ያሰብኳቸውን የተለያዩ ትምህርቶችን ጥያቄ ከነማብራሪያቸው በእጅ ስልኬ አማካኝነት መስራት የጀመርኩት።

እዚህ ጋር ኤርሚን፣ የ2015 ተመራቂ ተማሪዎችን በተለይ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማመሰግን እወዳለሁ በመጀመሪያ ሰብስክራይብ በማድረግ እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርስቲ ለሚማሩ ተማሪዎች በማጋራት እንድታወቅ ስላገዙኝ። በመቀጠልም ጓደኞቼን እንዲሁም ወንድሜ ገሬን የ You tube thumbnail ውብ በሆን መንገድ እየሰራ ስለሚያግዘኝ ላመሰግን እወዳለሁ።

አሁን ላይ መላ ቱቶሪያልስ ከ 31000 በላይ ሰብስክራይበር (subscribers) ከ 2600000 በላይ እይታን (views) ከ 260000 በላይ የእይታ ሰዓት (watch hour) ላይ ደርሰናል ይህ ደግሞ ያለ እናንተ ጥረት አይሳካምና ሁላችሁንም ከልብ አመሰግናለሁ። መላ ቱቶሪያልስ ከዚህም በላይ ጠንካራ ተቋም የመሆን ምኞትና ህልም እንዲሁም እቅድም ስላለው በጉዟችን ሁሉ የእናንተን ውለታ ሁሌም ያመሰግናል።

መላ ቱቶሪያልስ አሁንም ከዚህ በላይ መቶ ሺ ሰብስክራይበር ይኖረን ዘንድ በተለያየ መንገድ ለምታውቋቸው ሁሉ እንድታጋሩ እና ቤተሰብ እንዲሆኑ ትጋብዙልን ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ።

መላ ቱቶሪያልስ
የጥበብ ቋት

Praise God

One of the key methods that helped me achieve good results during my time as a university student was watching YouTube tutorial videos. At that time, there were no videos available in Amharic, so I often relied on videos created by Indian educators. These videos were excellent for helping me easily understand numbers and various lessons. After graduating, YouTube also became a platform where I learned many valuable life lessons.

After completing my studies and becoming a teacher, I dreamed of starting my own YouTube channel to teach others. The main motivation was the lack of educational content in our own language. However, I kept postponing it, thinking, "I’ll start tomorrow." Finally, two years ago, in 2015 (E.C.), on this very day, I launched my first videos with the help of my friend Ermias Negash (Ermi E-Learning). This was during the period when the first national Exit Exam was being conducted, so I began creating a variety of lessons, including questions and detailed explanations, using just my phone.

I would like to express my special thanks to Ermias and the 2015 graduates—especially the students of Arba Minch University—who supported me early on by subscribing and sharing the videos with students across different universities. I also want to thank my friends and my brother Gere, who has been helping by designing beautiful YouTube thumbnails.

Today, Mela Tutorials has grown to over 31,000 subscribers, more than 2,600,000 views, and over 260,000 watch hours. None of this would have been possible without your support, and for that, I sincerely thank you all. Mela Tutorials has a vision and plan to evolve into an even stronger educational platform, and we will always value your continued support along this journey.

I humbly and respectfully ask that you continue to share our channel with everyone you know so we can reach hundreds of thousands more subscribers and grow our learning community.

Mela Tutorials
Hub of Wisdom

14 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.