“ በ6 ወራት ለ66 ሺህ 741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” - አማኑኤል ሆስፒታል
አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 ዓ/ም፣ “ በ6 ወራት ለ66,741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በዚህም 64,256 የተመላላሽ፣ 257 ህፃናት የአዕምሮ፣ 410 ሰዎች የሱስ ህክምና መሰጠቱን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዩ የኔአለም ገልጸዋል።
እንዲሁም ለ240 የተሃዲሶ፣ ለ921 የአስተኝቶ፣ ለ1,564 ሰዎች ደግሞ የድንገተኛ የህክምና አገልግሎት መሰጠቱን አቶ አብይ አስረድተዋል።
በተመላላሽ፣ በአስተኝቶና በድንገተኛ የህክምና አገልግሎት ከተሰጣቸው ታካሚዎች መካከል 36,300 የጤና መድን ተጠቃሚዎች መሆናቸው ተመልክቷል።
በተመላላሽና በተኝቶ ህክምና በስድስት ወራት የወንጀልና የፍትሃ ብሔር ተመርማሪ ለሆኑ 413 የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱም ተገልጿል።
“ በሆስፒታሉ አማካኝ አስተኝቶ የቆይታ ጊዜ በ2016 ዓ/ም ከነበረው 36 ቀናት በ2017 ዓ/ም 6 ወራት ወደ 33 ቀናት ማድረስ፣ የአልጋ የመያዝ ምጣኔም በመጀመሪያ 6 ወራት መጨረሻ ላይ 85.2% መፈጸም ተችሏል ” ተብሏል።
ሆስፒታሉ ከ1930 ዓ/ም ጀምሮ በተኝቶ፣ በተመላላሽ፣ በድንገተኛ፣ የጭንቅላት ምርመራ፣ በኤሌክትሪክ ንዝረት፣ በህፃት የአዕምሮ፣ ከህግ ጋር የተያያዙ የአዕምሮ ህክምናና ምርመራ እንዲሁም የነርቭ ህክምናዎችን እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ ሆስፒታል ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia