"አርሶአደር ከሌለ ምግብ የለም፣ ነገ የሚበላም አይኖርም'' - የለንደን አርሶአደች
የእንግሊዝ አርሶአደሮች የተጣለባቸውን ግብር በመንቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ ተስተውለዋል።
በለንደን የሚገኙት አርሶአደሮቹ መንግስት ውሳኔውን ካልቀየረ የምግብ ምርቶችን ወደ ገበያ እንደማያቀርቡ በመግለጽ አስጠንቅቀዋል፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩት አርሶአደሮቹ ወደ ሀገሪቱ ፓርላማ እየተጓዙ ተቃውሟቸውን ባሰሙበት ወቅት የእርሻ ትራክተሮችንም ይዘው ታይተዋል፡፡
በእንግሊዝ ገንዘብ ሚኒስትር ራቼል ሪቭ የተወሰነው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ከ1 ሚሊየን ፓውንድ በላይ የሚወጣ መሬት ያለው አርሶ አደር፣ ከ2026 ጀምሮ 20 በመቶ ግብር እንዲከፍል ይደነግጋል፡፡
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ መሬታችንን አሳልፎ የሚሰጥ ነው ያሉት አርሶ አደሮቹ፣ ''አርሶአደር ከሌለ ምግብ የለም፣ ነገ የሚበላም አይኖርም'' ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ #bangkokpost
@thiqaheth