#Update
ኢትዮጵያ የሱማሊያን ሉዓላዊነት ታከብራለች፣ ሶማሊያም ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ተጠቃሚ መሆን እንዳለባት ታምናለች ተባለ።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነታቸውን ለማደስ መስማማታቸው ተሰምቷል።
በፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን አማካኝነት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ መግባባት ለመፍጠር መስማማታቸው ተዘግቧል።
ሦስቱም መሪዎች ከስምምነቱ በኋላ ስምምነቱ በተፈጸመበት አንካራ በሰጡት የጋራ መግለጫ፣ "የአንካራ ስምምነት" መፈጸሙን አስታውቀዋል።
በስምምነቱ መሰረት በቱርክ አሸማጋይነት የሚመራ የተደራዳሪ ቴክኒክ ቡድን እስከ የካቲት 2025 ድረስ ለመመስረት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በአንካራ በተደረገው ውይይት ሁለቱ ወገኖች ልዩነት ከሚያሰፉ ነገሮች እንዲቆጠቡ እና ለጋራ ብልጽግና እንዲሰሩ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በቱርክ በተካሄደው ንግግር መሰረት ኢትዮጵያ የሱማሊያን ሉዓላዊነት ታከብራለች፣ ሶማሊያም ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ተጠቃሚ መሆን እንዳለባት ታምናለች ተብሏል። #dailysabah
@ThiqahEth