''ሶማሊያ ባቀረበችልን ጥያቄ መሰረት የግብጽ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ተልዕኮው ይካተታሉ'' - ባዲር አብደላቲ
ግብጽ በአዲሱ የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይል (AUSSOM) ውስጥ እንደምትሳተፍ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ አረጋግጠዋል፡፡
ይህ የተባለው የግብጽና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከካይሮ በሰጡት መግለጫ ነው።
ባዲር አብደላቲ፣ "ሶማሊያ ባቀረበችልን ጥያቄ መሰረት የግብጽ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ተልዕኮው ይካተታሉ'' ብለዋል።
ሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚንስትር ደኤታዋን ወደ ኢትዮጵያ ስትልክ፣ ሚኒስትሩ አህመድ ሞዓሊም ፊቂ ደግሞ ግብጽ ገብተዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አሸማጋይነት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ከተስማሙ በኋላ ውይይት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያ ነው፡፡ #ahramonline
@ThiqahEth