የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ አዲስአበባ ገቡ።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ለፕሬዚዳንቱ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሶማሊያዉ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ገብታ የነበረውን የባህር በር ለማግኘት የሚያስችል ስምምነትን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጹ፣ ኢትዮጵያንም በአለማቀፍ መድረኮች ላይ ሲወነጅሉ መቆየታቸው ይታወሳል።
ሁለቱ ሀገራት በቅርቡ በአንካራ ቱርክ አሸማጋይነት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ዉጥረት ለማርገብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት እና በአዲስ አበባ ስለሚኖራቸው ቆይታ እስካሁን የተገለጸ ነገር ባይሮርም ስለአንካራው ስምምነት ለመወያየት እንደሆነ ይጠበቃል።
የሶማሊያው ኘሬዝዳንት አዲስ አበባ ሲገቡ የግብጽ የኤርትራና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በግብጽ የሶማሊያን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ እንሰራለን ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሶሚሊያ ፕሬዝዳንቷ አዲስ አበባ፣ የኤርትራና የሶማሌ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደግሞ ካይሮ ይገኛሉ። #pmoffice #villasomalia
@ThiqahEth