የኬንያ ፖሊስ የተቆራረጠ አስክሬን በቦርሳ ይዞ ሲጓዝ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አዋለ።
የ29 ዓመቱ ጆን ኪያማ ዋምቡያ አስክሬኑ የ19 ዓመት ሚስቱ እንደሆነ ተናግሯል። ፓሊስ በናይሮቢ ሁሩማ ግዛት ቅኝት ሲያደርግ ነው ግለሰቡን የያዘው።
ግለሰቡ ሕገ ወጥ ነገር እንደያዘ በመጠርጠር ፖሊስ አስቁሞት ቦርሳውን ሲፈትሽ የተቆራረጠ አስክሬን አግኝቷል።
የኬንያ ወንጀል ምርመራ "በጣም አስደንጋጭ ነበር" ሲል የገጠመውን ገልጿል። ሴቶች ላይ የሚፈጸም ግድያ ከፍተኛ ከሆነባቸው አገሮች መካከል ኬንያ አንዷ ናት።
ግለሰቡ ላይ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ነው አስክሬኑ የባለቤቱ ጆይ ፍሪዳ ሙናኒ እንደሆነ የደረሰበት።
ፖሊስ የአስክሬኑን ቁርጥራጭ ሲያገኝ ግለሰቡ "እምብዛም እንዳልተደናገጠ" ተገልጿል። ፖሊሶች ቤቱ ሲሄዱ ቢላ፣ ደም የተነከረ ልብስና ተጨማሪ የሰውነት ክፍሎች አግኝተዋል።
የኬንያ ወንጀል ምርመራ ድርጊቱን "አሰቃቂ" ሲል ገልጾታል። ተጠርጣሪው በቅርቡ በግድያ ክስ ፍርድ ቤት የሚቀርብ ይሆናል።
እአአ በ2024 ከነሐሴ እስከ ጥቅምት 97 ሴቶች መገደላቸውን የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ ገልጿል። #BbcAmharic
@ThiqahEth