ገድለ አቡነ ጸጋ ዘአብ ወእምነ እግዚእኀረያወገድለ አቡነ ታዴዎስ ጽላልሽ....
ገድላት ኹሉን አቀፍ የመረጃ ምንጮች ናቸው። ዘመን፤ በአንድ አካባቢ፤ በአንድ ተመሳሳይ ሁኔታ የሚጓዙ አለመሆናቸው፤ በተለያዩ የዓለም ክፍል በተለያዩ ዘመናትና ጊዜያት የተነሡ የቅዱሳንን ሕይወት የተመለከቱ፤ ከምእመናን እስከ መዐርገ ጵጵስና ድረስ በተራ ዜግነት ከተሰለፉት እስከ ንጉሥነትና ንግሥትነት ደረጃ እስከ ደረሱት ድረስ ምእመናንንና ምእመናትን በእኩልነት የያዘ በመኾኑ ከሃይማኖት ጥቅሙ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰዎችን እኩልነት በማሳየቱ የበለጠ አጎልቶ ይሳያል።
❞ስለዚኽ ይኸ
የካህኑ ጸጋ ዘአብ፣የብፅዕት እግዚእ ኀረያ እና የአቡነ ታዴዎስ ገድል የነፍስና የሥጋ በረከት የምንቀበልበት፤ ኹሉን አቀፍ መረጃ የምናገኝበት በመኾኑ በ፯ቱ ዕለታት በመክፈል በግዕዝና በአማርኛ በመተርጎም ቀርቧል።
❞ይኸም ቅዱሳኑ በሕይወተ ሥጋ እያሉም ኾነ ከዕረፍታቸው በኋላ በዐጸደ ነፍስ ሳሉ ያደረጓቸውን ልዩ ልዩ ድንቅ ተኣምራትን መልክዐቸውንም አካቶ የያዘ
የካህኑ ጸጋ ዘአብን፣ የብፅዕት እግዚእ ኀረያንና አቡነ ታዴዎስን ዝክረ ስም የሚናገር የምስጋናጸሎት ስለኾነ በዚኸ የጸሎት መጽሐፍ ተጠቅመን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እናገኝ ዘንድ ይህን ገድል ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም እነሆ ይለናል ።
❞
ይኽን የቅዱሳን ተጋድሎ እና ምስጋና የያዘ ገድል በግዮን መጻሕፍት የሚያገኙት ሲሆን በሀገር ውስጥ እንዲሁም ከሀገር ውጭ ለምትገኙ አንባብያን በDHLእና በEMS በመላክ የ Delivery አገልግሎት በመስጠት ተደራሽ እናደርጋለን።https://t.me/GhionBookStore1623