ብስራት ስፖርት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ፣ የዝውውር ዘገባዎችን እንዲሁም ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት እኛ ጋር በላቀ ጥራት እና ብቃት ያገኛሉ!
https://telega.io/c/BisratSportTm
Buy Ads 👆
ለማንኛውም ጥያቄ ሀሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ማስታወቂያ ለማሰራት @jondux ላይ ፃፉልኝ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ጄረሚ ፍሪምፖንግ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከሊቨርፑል ጋር ኮንትራቱን ይፈራረማል።

- ፋብሪዚዮ ሮማኖ

@BisratSportTm


ማትየስ ድሊት ከዋና ቡድኑ ተነጥሎ ለብቻው ልምምድ እየሰራ ይገኛል።

@BisratSportTm


ኬቭን ደብሮይን ለ10 አመታት ያህል ካሸበረቀበት ቤቱ ኢትሃድ ስታዲየም ጋር ዛሬ ምሽት ለመጨረሻ ተጫውቶ ይሰናበታል።

@BisratSportTm


ከዛሬው ልምምድ የተገኙ ምስሎች

@BisratSportTm


ዳሎት ፣ ዮሮ እና ዘርክዜ ለነገው የአውሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዝግጅት ዛሬ ዋና ቡድኑን ተቀላቅለው ሙሉ ልምምድ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

@BisratSportTm


ጆዜ ሞሪንዮ ስለ አውሮፓ ሊግ !

"ከአንድ እስከ አራት ከምጨርስ የአውሮፓ ሊግ ዋንጫን ብበላ እመርጣለሁ! ይሄ የአውሮፓ ዋንጫ ነው በተጨማሪም የቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ያስደርጋል ስለዚህ እኔ ይሄኛውን መንገድ እመርጣለሁ"

@BisratSportTm


ቬንገር የአውሮፓ ሊግ አሸናፊ የቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ መሆን አይገባውም ማለቱን ተከትሎ ሞሪንዮ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቶታል !

"እሱ የአውሮፓ ሊግ አሸንፏል? እሱ የአውሮፓ ሻምፒዮን ነው? አይደለም! ስለዚህ ለምን ያወራል? በታሪክህ የአውሮፓ ሻምፒዮን ካልሆንክ ትኩረት ማድረግ ያለብህ ሊግ ላይ ብቻ ነው!

"ምክንያቱም ቻምፒየንስ ሊግ የአሸናፊዎች እንጂ የደምበኛ ተከታታይ ተሸናፊዎች ውድድር አይደለም!"

@BisratSportTm


የባርሳ ፕሬዚዳንት ስለ ክረምት ዕቅድ !

"በዚህ የክረምት ዝውውር በቡድናችን ውስጥ ለውጦች የሚኖሩ ይሆናል! ተቀናቃኞቻችንም ይጠናከራሉ ምክንያቱም ቡድናችን በአሁኑ ሰዓት ምርጡ እንደሆነ አይተዋል"

@BisratSportTm


የባርሳ ፕሬዚዳንት ስለ ኒኮ ዊልያምስ ዝውውር !

"ባለፈው ክረምት ከዳኒ ኦልሞ ጋር ኒኮን ለማስፈረም ከግምት ውስጥ አስገብተን ነበር በአሁን ሰዓት ግን ክለባችን ሌሎች ተጫዋቾችን እየገመገመ ያለ ይመስለኛል።"

@BisratSportTm


ጆሮጂንዮ በመጪው ወር ፍላሚንጎን ወክሎ የክለቦች የአለም ዋንጫ እንዲጫወት ከአርሰናል ፍቃድ አግኝቷል።

@BisratSportTm


ብራይተን አሸንፏል !

በ37ተኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ብራይተን ሊቨርፑልን 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሊቨርፑልን ግቦች ሶቦዝላይ እና ኤልየት ሲያስቆጥሩ የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች አያሪ ፣ ሚቶማ እና ሂንሼልውድ ማስቆጠር ችለዋል።

በሚገርም ሁኔታ በጨዋታው ብራይተን ሊቨርፑል ላይ 25 የግብ ሙከራ ማድረግ ችለዋል።

@BisratSportTm


BREAKING !

የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ከሊያም ዴላፕ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ንግግር አድርገዋል።

ዴላፕ ወደ ኦልድትራፎርድ ተጉዞ ማንቸስተር ዩናይትድን አይቶ እንዲገመግም እና ወደ ዩናይትድ መዘዋወር ሊያስገኝለት የሚችለውን ጥቅም እንዲመለከት ከአይፕስዊች ታውን ፍቃድ ተሰጥቶታል።

- ላውሪ ዊትዌል ከአትሌቲክ [ታማኝ ምንጭ]

@BisratSportTm


ሳሊም አልዳውሰሪ ከአል ሂላል ጋር እስከ 2027 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል!

@BisratSportTm


ሳላህ ዛሬ ለሊቨርፑል 400'ኛ ጨዋታውን ያደርጋል

@BisratSportTm


ጉዳት ላይ የነበረው የቶተንሃሙ ሚድፊልደር ሉካስ በርግቫል ቡድኑን ተቀላቅሎ ወደ ስፔን ተጉዟል!

@BisratSportTm


የሆላንዱ አንጋፋ ክለብ አያክስ አምስተርዳም አሰልጣኛቸው ፋሪዮሊ በገዛ ፍቃዱ ክለቡን በዛሬው ዕለት መልቀቁ ይታወቃል።

ይህንንም ተከትሎ አያክስ ኤሪክ ቴንሀግን መልሰው ለመቅጠር አምርረው እያሰቡበት ይገኛሉ በማለት ፎሎሪያን ፕሌተንበርግ በመረጃው አውጥቷል።

@BisratSportTm


የ15 አመቱ ታለንትድ የአርሰናል ተጫዋች ማክስ ዶውማን በሚቀጥለው የውድድር አመት የዋና ቡድኑ አካል እንደሚሆን ተነግሮታል።

እንዲሁም መድፈኞቹ በዚህ ክረምት ወደ እስያ ተጉዘው ለሚያደርጓቸው የቅድመ የውድድር ዘመን ጨዋታዎች ከቡድኑ ጋር አብሮ እንደሚጓዝ ተነግሮታል።

@BisratSportTm


እንደ ቴሌግራፍ ስፖርት ዘገባ ቶማስ ፓርቴ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ቢያንስ ለአንድ አመት በአርሰናል መቆየትን ነው። 

ፓርቴይ በክለቡ የማይቆይ ከሆነ አርሰናል ከማርቲን ዙቢሜንዲ በመቀጠል ሌላ ሚድፊልደር ኢላማ ሊያደርግ ይችላል።

@BisratSportTm


🗣 ጋርናቾ ስለ ዋንጫው ጨዋታ

"በጣም ጓጉቻለሁ! በጣም ረጅም ሳምንት ይሆናል! ጎል ባስቆጥርም ባላስቆጥርም ግድ የለኝም ጨዋታውን መጫወት ነው የምፈልገው ጨዋታውን አሸንፌ ከደጋፊዎች እና ከቤተሰብ ጋር መደሰት ብቻ ነው ምፈልገው"

@BisratSportTm


ማንቸስተር ሲቲ የሊቨርኩሰኑን ሚድፊልደር ፍሎሪያን ቨርትዝን ለማስፈረም ከሚደረገው ፉክክር እራሳቸውን አስወጥተዋል።

ማንቸስተር ሲቲ ዝውውሩ በታሪካቸው ከፍተኛ ወጪን ያስወጣቸዋል ብለው ያስባሉ። ለተጫዋቹ አጠቃላይ ለዝውውሩ የሚውለው ገንዘብ 300 ሚልዮን ዩሮ አከባቢ ሊያስወጣቸው እንደሚችልም ተገንዝበዋል።

- ሳሚ ሞክቤል ከቢቢሲ

@BisratSportTm

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.