በጎች እና ተኩላወች
ከተረት አባት፣ ኤዞፕ [aesop] የተውሰደ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላዎች ተመካከሩና መልዕክተኞች ወደ በጐች ላኩ፡፡ የተኩላዎቹ ልዑካን በጐች መንደር ደረሱ፡፡ በጐች ተኩሎች መጡብን ብለው ተሸሸጉ፡፡ አድፍጠው ጋጣቸው ውስጥ ተደብቀው ተቀመጡ፡፡ ተኩሎቹ ግን ረጋ ብለው፣ አደብ ገዝተው፤
“በጐች አትደናገጡ፣ እንደምና ዋላችሁ” አሉ፡፡
“ለድርድር ነው የመጣነው” አሉ ተኩሎቹ፡፡
በጐቹ ቀስ በቀስ ከተደበቁበት ወጡ፡፡
በጐቹም “እኛ በድርድር እናምናለን፡፡ እህስ፣ ምን እግር ጣላችሁ? ምን የድርድር ሃሳብ ይዛችሁ መጣችሁ?” አሉ ፡፡
“አንድ የቸገረ ነገር ገጥሞን ነበርና ልናዋያችሁ ፈልገን ነው” አሉ የተላኩት ተኩላዎች።
በጎቹም ዞር ዞር በለው ተያዩና፣ “ምንድነው? ከተመካከርን የማይፈታ ምንም ነገር አይኖርም፡፡ ዋናው ተቀራርቦ መነጋገር ነው ንገሩን፡፡” አሉ።
ተኩሎችም፤ “እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ የቸገረን ነገር ምን መሰላችሁ? ይኸው ከተፈጠርን ጀምሮ ከውሾች ጋር ነጋ-ጠባ እንታገላለን፡፡ የችግራችን መነሻም መድረሻም ውሾች ናቸው፡፡ እርኩስ ውሾች እኛን ባዩ ቁጥር ይጮሃሉ፣ ይተነኩሱናል፣ ሠፈር ይረበሻሉ!፣ ለእኛና ለእናንተ ወዳጅነትና ሰላም ዋና እንቅፋቶች ውሾች ናቸው፡፡” አሉ
በጐችም፤ “ታዲያ ምን እናድርግ? ምን ዘዴ ብንፈጥር እንቅፋቶቹን ማስወገድ እንችላለን?” ሲሉ፣
ተኩሎችም፤ “እናንተ እሺ ካላችሁማ ዘዴ አይጠፋም ነበር”
“እኮ ዘዴ ካለ ንገሩና?”
“ለጌታችሁ ንገሩ፡፡ ውሾች እንዳልተመቿችሁ፣ ሰላምም እንደነሷችሁ አስረዱ፡፡ ይባረሩልን በሉ!፣ እኛም ለእናተም ከጩሀታችው ሰላም ታገኛላችሁ” ይሉዋቸዋል።
“ይሄማ ቀላል ነው፡፡ እንነግራቸዋለን፡፡”
በዚህ ተስማሙና ተኩሎቹ ሄዱ፡፡
በጐቹ፤ ውሾቹ እንዲባረሩ ለጌታቸው አመለከቱ፡፡ ጌታቸውም ስንት ዘመን ቤት - ደጁን ይጠብቁ የነበሩትን ውሾች ከቤት አስወጥቶ አባረራቸው፡፡
ከዚያን ቀን በኋላ፣ የዋሆቹ በጐች የዘመናት ጠባቂዎቻቸውን አጡ፡፡ ተንኮለኞቹ ተኩሎች እየተዝናኑና በጐቹን አንድ በአንድ እየለቀሙ፤ በሏቸው፡፡
የድርድርን ትርጉም አለማወቅ እርግማን ነው፡፡
በርቱላን፣ አንብቡ። ሌሎችም እንዲያነቡ እሲቲ ከስቅሱዋችው።
እናንብብ፣ ከአይምሮ ባርነትም እራሳችንን ነጻ እናውታ። ቡሀላ እንድበጎቹ ድርድር ላይ ኩማር እንዳንበላ።
***********************
ከውደዳችሁት፣ ላይክ እና ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩት፡፡
👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽👍🏽
***********************
https://nebeb.com/article/604301ce09458e768b616b6cNebeb.comንበብ ለንባብ
እናንብብ፣ እንወያይ፣ ነጻ እንውጣ!
#Ethiopia #Nebeb #ንበብ ለ #ንባብ