🎖🎖 #ለቁርአን_ያለን_ቦታ_እኛና_ሱሀቦቹ🎖🎖
✍ አሚር ሰይድ
አላህ በተከበሩ ቃሉ እንዲህ ይላል
{ وَإِذَا قُرِئَ ٱلۡقُرۡءَانُ فَٱسۡتَمِعُوا۟ لَهُۥ وَأَنصِتُوا۟ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ }
ቁርአንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ፀጥም (ዝም) በሉ ይታዘንላችኋልና፡፡(አል-አዕራፍ 204)
✨✨ በሀዲሰል ቁድስ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚 እንዲህ ብለዋል፡-
በሌሊት ሁለት ረከዓ ሶላት እየሰገደ ቁርአን ከሚያነብ ሰው የበለጠ አላህ ማንንም አያዳምጥም፡፡ ባሪያው በሶላት ላይ እስካለ ድረስም የአላህ እዝነት በእርሱ ላይ ይሰፍናል፡፡ ባሪያው አላህን ከማንም በላይ ይበልጥ የሚቀርበው ቁርአንን በሚያነብበት ጊዜ ነው፡፡" (ቲርሚዚ)
✨✨ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
ቁርዓንን ተማሩ፣ ከዚያም አንብቡት! ሌሎችም እንዲያነቡትና እንዲሰሩበትም ገፋፉ፡፡ ምክንያቱም ቁርአንን የተማረ፣ ያነበበና የሰራበት ሰው በጠርሙስ ውስጥ እንደታሸገና መዓዛው ሁሉንም እንደሚያውድ ሚስክ ብጤ ነው፡፡ #ቁርአንን_ተምሮ_የማይሰራበት የታሸገበት ክዳን ላልቶ እንደተከደነ ሚስክ ማለት ነው፡፡ (ቲርሚዚ)
✏️✏️ ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ💜 እንዲህ ብለዋል፡-
ቁርአንን አንብቡ! ምክንያቱም በፍርዱ ቀን እርሱ በሚገባ ላነበበዉ ሰው አማላጅ ሆኖ ይመጣልና፡፡' (ሙስሊም)
📌 በሌላ ዘገባ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል
አንድ ሰው በልቡ ውስጥ ምንም አይነት የቁርአን አንቀጽ የማይገኝ ከሆነ እንደ ወና ቤት ይቆጠራል፡፡" (ቲርሚዚ)
📌 በሌላ ሀዲስ ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ልብ ብረትን እንደሚያገኘው ዝገት ብጤ ይዝጋል፡፡"ሲሉ
የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይህን ዝገት በምን ማስለቀቅ ይቻላል?" በማለት ባልደረቦቻቸው ጠየቋቸው፡፡
የአላህን ቁርአን በብዛት በማንበብና አላህንም በብዛት በማውሳት" በማለት መለሱላቸው፡፡ (አሊ አል-ሙተቂ)
⚡️⚡️ አንድ ሰዉ በነብዩ ﷺ ዘመን ቁርአን አጠናቀቀ የሚባለዉ በህይወት ሲኖረዉ ሲተገብረዉ ለሌሎችም
ሲያስተምረዉ ነዉ፡፡
ኡመር ረዐ እንዲህ አሉ፡-እኔ ሱራ አል-በቀራህን በአሥራ ሁለት አመቴ አጠናቀቅኩ፡፡ ለዚህም ምስጋና ይሆን ዘንድ አንድ ግመል አረድኩ፡፡”ብለዋል (ቁርጡቢ)
☞ በተጨማሪ አብደላህ ኢብኑ ኡመር (ረ.ዐ) ሱራ አል-በቀራህን በስምንት ዓመታት አጠናቅቀዋል፡፡ (ሙወጠእ)
✨✨ ኡመር ኢብነልኸጧብ ለቁርአን ለሚቀሩትና ለሀፊዞች እንዲህ ብለዉ መክረዋቸዋል፡-
ቁርአን የክብራችሁ ምንጭና ከፈጣሪ የተሰጣችሁ ሽልማት እንደሆነ እወቁ፡፡ እርሱን ተከተሉ እንጂ እንዲከተላችሁ አታድርጉ፡፡ ቁርአንን ከኋላቸው ለማስከተል የሚሞክሩ ጭንቅላታቸው ተዘቅዝቆ ወደ ጀሀነም እሳት እንደሚጣሉ አትዘንጉ፡፡ ለቁርአን ታማኝ የሆነ በላእላይ ጀነት ፊርደውስ እንደሚሰፍር ተስፋ ያድርግ፡፡ ሁላችሁም አቅማችሁ የቻለውን ያክል የቁርአንን አማላጅነት ለማግኘት ጥረት አድርጉ እንጂ በናንተ ላይ መስካሪ አድርጋችሁ አትያዙት፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ያማለደው ሰው ጀነት እንደሚገባና በእርሱ ላይ የመሰከረበት ደግሞ ጀሀነም እንደሚወርድ እሙን ነውና፡፡ ቁርአን ወደ ቀናው መንገድ መመራትና የእውቀት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ ከአዛኙ ፈጣሪ ወደ ሰብአዊው ፍጡር የተላከ የመጨረሻው መፅሐፍ ነው፡፡ እነሆ የታወሩ አይኖች፣ የተደፈኑ ጆሮዎች፣ የተዘጉ ልቦች በእርሱ ይከፈታሉ…” ብለዉ መክረዋቸዋል፡፡
✏️✏️ ኢማሙ ሻፊዒ ረ.ዐ እንዲህ ይሉ ነበር፦
ቁርዓን ያለበት ቤት ውስጥ መተኛት አይቻልም ይላሉ፤ምክንያቱም በመኝታ ሰዓት ራስን መቆጣጠር ስለ ማይቻል የሚጮህ ከሆነ ፣ህልም ላይ መናዘዝ፣ ዉዱዕ የሚያስፈታ ነገር ስለሚፈፅም
ይህ ሁሉ ጥንቃቄ ቁርዓንን ይዞ ሳይሆን ቁርዓን ቤት ውስጥ ካለ ሌላ ቤት ማደር ነው። ይላሉ።
ውዱዕ ካላደረጋችሁ ቁርዓንን እንዳትነኩ ይላሉ።
🌙🌙 የአቡበከር (ረ.ዐ) ልጅ የሆነችው አስማ (ረ.ዐ) አንድ ጊዜ በልጇ ልጅ በአብደላህ የሚከተለው ጥያቄ ቀርቦላት ነበር-
“አያቴ! የነቢዩ ባልደረቦች ቁርዓንን ሲያዳምጡ ምን ያደርጉ ነበር?''
.....አስማ እንዲህ አለች፡- #ከዓይኖቻቸው_እንባ ይፈሳል፡፡ እንዲሁም በቁርዓን እንደተገለፀው መላ አካላቸው ይንዘፈዘፋል፡፡ ኃያሉ አላህ ቁርዓንን በጥልቅ ተመስጦ የሚያነቡ ባሮቹ ምን ሁኔታ እንደሚታይባቸው እንዲህ በማለት ገልጿል፡-
{ وَیَخِرُّونَ لِلۡأَذۡقَانِ یَبۡكُونَ وَیَزِیدُهُمۡ خُشُوعࣰا ۩ }
እያለቀሱም በግንባራቸዉ መሬት ላይ በስግደት ይወድቃሉ አላህን መፍራትንም ይጨምራላቸዋል፡፡
(አል-ኢስራእ 109)
{ ٱللَّهُ نَزَّلَ أَحۡسَنَ ٱلۡحَدِیثِ كِتَـٰبࣰا مُّتَشَـٰبِهࣰا مَّثَانِیَ تَقۡشَعِرُّ مِنۡهُ جُلُودُ ٱلَّذِینَ یَخۡشَوۡنَ رَبَّهُمۡ ثُمَّ تَلِینُ جُلُودُهُمۡ وَقُلُوبُهُمۡ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ ذَ ٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ یَهۡدِی بِهِۦ مَن یَشَاۤءُۚ وَمَن یُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٍ }
አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ፡፡ ከእርሱ (ግሣጼ) የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ፡፡ ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ (ተስፋ) ማስታወስ ይለዝባሉ፡፡ ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ የሚሻውን ሰው ይመራበታል፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
(አዝ ዘሙር 23)
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከማሳለፍ ቁርአን ያለን ቦታ ያለንን ቁርኝት እንፈትሽ...ከቁርአን ከራቅን ገነ ጀነት የመግቢያ ካርዳችን እንደራቀን ልናቅ ይገባል፡፡
እናም ከዛሬ 6-10 አመት በፊት የነበረን ለቁርአን ቦታ እና አሁን ያለንበት ከቁርአን የራቅንበትን ራሳችንን እንፈትሽ ⚠️
█
┻┻
╚▩
PubLished by ▩╗ ISLAMIC UNIVERSITY
◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━
4 another channal👇
t.me/Islam_and_Science💐_⭐️
💐⭐️___💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group t.me/IslamisUniverstiy_public_group