Bahir Dar WikiLeaks - BW


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ባሕር ዳር ዊክሊክስ - የአማራውያን የወል ድምፅ!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ድሮ የት ነበራችሁ?" ለምትሉን!

(ከላይ ላሉት ስክሪንሻት ማብራሪያ)

እኛ ድሮውንም በዘመድኩን ጉዳይም ሆነ በሌላው የሚዲያ ሰው ላይ የነበረን አቋም ሁሉም በሚናው ልክ ይንቀሳቀስ ስንል ነበር። እንደ ምሳሌ ማንሳት ከተፈለገም፦

በፈረንጆቹ May 09/2024 (ግንቦት 2016 ዓ.ም) "ዘመድኩንን የትግሉ ደጋፊ እንጅ ሚስጥረኛ ማድረግ ውሎ አድሮ አደጋ እንዳለው እያየን ነው" ብለን የጻፍነውን ማየት ይቻላል።

ሌላኛው ምሳሌ ደግሞ በሚዲያዎች መካከል (በተለይም በሃብታሙና ዘመድኩን መካከል) ያለው መጓተት ትግላችን ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉ እንዳልቀረ July 2024 (ሐምሌ 2016 ዓ.ም) ትዝብታችንን ገልፀን፣ የፅሞና ጊዜ እንዲወስዱ የጠየቅንበት ነው። በዚህ ፁሑፍ ቤተልሔም ዳኛቸው "እንዳንሸጥ እንዳንለወጥ አድርጋ" ሞልጫንም ነበር። ደና ውለሽ ነው?

ሁለቱም ፁሑፎች እዚሁ የቴሌግራም ገጻችን ላይ ስላሉ ማየት ይቻላል። ምንም እንኳን ዛሬ ላይ "ቀድቻቸው" በሚል ከፈረሱ ላይ ለመውረድ ቢሞከርም ነገር ግን ከእነ አኪላ ዋን አማራዎች ጋር አያይዘን የቸከቸክናቸው ፁሑፎችም አሉ። እናም በሚናችሁ ልክ አክት አድርጉ የሚለው ትችታችንን መግለፁ ዛሬ የጀመርነው የሚመስለው ለአዲስ ገቡ ነው።

የሆነው ሆኖ የዘመድኩን በቀለ አካሄድ የአማራን ሕዝብ ወደል ጠላቶች ትቶ፣ አንገት ቀና ያደረጉና የአማራ አይከን የምንላቸውን መቀጥቀጥ ነው። ይህ ወዳጃዊ አካሄድ ሊሆን የሚችለው ለፊደል አይዘልቄ ነሆለሎች ብቻ ነው።

ከላይ ላለውም እጅግ በርካታ መገለጫዎችን እራሳችሁ አንባብያን ልታቀርቡ እንደምትችሉ እናውቃለን። ነገር ግን ዛሬ ዘሜን የቀረበ መስሎ የዘመኔን ወንድሞች ላይ ሲለፋደድ፣ ትናንት በመሪያችን ዘመነ ካሴ ላይስ ምን ሲል እንደነበር ማስታወሱ ጥሩ ነው።

ዘመድኩን በቀለ "ዘመነ ካሴ የቢዝነስ ሰው ነው"

"ዘመነ ካሴ ትግሉን ትቶ ከአማራ ፋኖ በጎጃም የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ጋር ነው ውሎ አዳሩ፤ እሷም ከእሱ ፀንሳለች፤ ከዚህን ያክል ሴቶች ይህን ያክል ልጅ አለው"

"ዘመነ ካሴ አገው ሸንጎ ነው" ሲል አልነበረ ወይ? ይህንን ዛሬም አላልኩም ብሎ በአደባባይ ይናገር። እዚህ ጋር በትችትና በስም ማጥፋት መካከል ያለው ልዮነት ለእነ ግርርርር ግልፅ ይሆናል የሚል እምነት አሁንም የለንም። አንድ አማራን ኢንዶርስ አድርጎ መሪ ማሳጣት በሚመስል አካሄድ የአማራ አይከኖች በሙሉ እሱም እነዛም ሲቀጠቅጡ የተመለከተ ነሆለል እነዚህ ሰዎች የጠላት ስራ አቀለሉለት፣ ተክተው ሰሩለት ብለው እንዲጠይቁ አንጠብቅም።

በነገራችን ላይ ባህርዳር ዊክሊክስም ከስም መደርደሪያ ካሉት ታጎች አንዱ ደርሷታል። ትናንት ተደመምኩባቸው ያለው ዘመዴ፣ ዛሬ ግን "ጋለሞታ፣ ዘራፊ፣ ቆርጣሚ፣ ሹካ አፍ" ሲል በደንብ አስገብቶልናል፤ ይበለን የእጃችንን ነው ያገኘነው 😁። እንግዲህ ይህንን የሚለው አንዲትን ልጅ የBW አድርጎ ስሎ ነው እኮ፣ እኛ ምን አቅም ኖሮን ከሷ እንደርስና? በምን አቅማችን? 😁 ትናንት BW የዘለለችበት ዋናው ምክንያትም እሱ ነበር እንጅማ ወደ ዋና ስራች መመለስ ጀምረን ነበር። ከመደርደሪያው ግን አንድ ሁለት ቀሪ ድርሻ የለንም? ለጥድቅ እንሆንሃለን¡😁

#እንዲያም_ሆኖ ዘመዳችን ከእንግዲህ የሊያ ሾው ሆስት ከመሆን የዘለለ ሚና የሚኖረው አይመስለንም፤ በፋኖዎች አድማስም ከወዲሁ ክርችም ብሏል። ይህችን ጣፋጭ አባባላችንን ንሳማ ቅዳልን።

#በነገራችን_መካከል ይህንን የምንለው "እውነት ሲባልም እሽ፣ ውሸት ሲባልም ደግ… ነጭ ሲባልም ልክ፣ ጥቁር ሲባልም እውነት… ከጠዋት ዘመነ/አስረስ ሲጠለሹ በርታ፣ ከሰዓት ሲሞገሱም በርታ… ጎጃም/ጎንደር፣ አልፎም ምስራቅ ምዕራብ ብሎ ሊከፍልህ ሲላፋውም እልል" የሚለውን ግትልትል ወደ እኛ ለመሳብ ፍፁም ፍላጎት ኖሮን አይደለም። "ከጠላት በላይ የወንድሞቻቸው መጥፋትና ከመደርደሪያ በሚዛቁ ስሞች የወንድም እህቶቻቸው ስም መጠልሸት ሃሴት የሚሰጣቸው መንጋዎች መጥተው ምን ሊጠቅሙን?!" ይልቅ ፍላጎታችን በተግባር የትግል ሜዳው ላይ ያላችሁ ወንድሞቻችን በሙሉ በራችሁ በልኩ እንዲከፈት ብቻ ለማሳሰብ ነው።

#እንዲህም_ሆኖ ግን በመጨረሻ ላይ "የአማራ ፋኖ በጎጃም ድርጅታዊ ጉባዔ ጠርቶ ግምገማ ያካሂድ" ያላት ሃሳብ ጥሩ ነው። እንዲህ አይነት አካሄድ ተቋምንና ተቋማዊ አካሄድን ያከበረ፣ ሚናንም የለየ ጉዞ ይሆናል። እንጅማ የተቋም የሩቅ አባወራ ልሁን አይሰራም፤ "በአንድ ቤት ሁለት አባወራ የለም"። ቅዳው!

11.2k 0 9 136 244

አጭር መጣጥፍ ከታች


የሊቃውንት ጉባዔው "የእናንተ ብዕር አመለኛ ናት፤ አታስተኛም" ይሉናል። ጉባዔው ካለማ እንቀበል እንጅ 😊

ለምሳሌ በይህ ሰሞን ለአንድ ወዳጃችን ምክር ቢጤ ብለን የሰደድናት አንዲት ፁሑፍ ነርቩን ጠርሰቅ እንዳደረገችው የገባን ዛሬ ነው። እንዲያው ምክር ቢጤ ብለን የላክናት ፁሑፍ ከማማው ፈጥፍጣ፣ ዶሮ ጠባቂ ካደረገችማ ችግሩ ተኛ ግድም ነው ማለት ነው 😁

"ከእንግዲህ ውድድሩ 'ከሊያ ሾው' ጋር ነው" ብለን የተውነው "እህ" ባይ ያጣው ነጠላ ቋጭ፣ ሲንከላወስ አይተን ዛሬም በሳቅ ፍርፍር በላን፤ ሳቅ ፍርፍር ግን በዛብነ 😂!

እዛው ምድጃህ ስር ተርመጥመጥ ጌታው። አይዞህ 😁

ዊክሊክሶች ነነ ከሃረርጌ 😉

14.2k 0 2 167 220

ይኼ ጥርስ ዛሬ የለም!

አዎ ይኼ የጋሼ ሃጫ በረዶ የመሰለ ጥርስ አሁን የለም 😁🤣 እናልህ እንዲህ ሆነልህ…

ጋሼ የቀንድ አውጣ አረጋ ከበደ የመሰረተ ልማት አማካሪ ናቸው፤ ስማቸውም አቶ አስናቀ ይርጉ ይባላሉ።

ጥቂት ቀደም ብሎ በዳንግላ ወህኒ ቤት ታጉረው የሚገኙ ታሳሪዎችን ለሚሊሽያነት ሲያሰለጥን ሰንብቶ፣ ኮብራ መኪናው በነበልባሎቻችን ስትማረክ፣ እሱ አምልጦ ባህርዳር ገባ።

ባህርዳር ገብቶም ሌላ የመንግሥት መኪና ያዘ። ይህችን መኪና ይዞ ብዙም ሳይቆይ ግን ከሰሞኑን ባህርዳር ቀበሌ 14 ልደታ አካባቢ ወደ ሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየሄደ እያለ የአገዛዙ ሚሊሽያዎች አስቁመው ከመኪናው በማወረድ ትጥቁንና የመኪናውን ቁልፍ ከቀሙት በኋላ በለብለብ ስልጣናቸው ያልጨረሱትን ካራቴ አስኔ ላይ ጨረሱት።

አስኔም በሚሊሽያ ተመቶ የሞት አፋፍ ላይ የሚገኝ የብልጽግና አመራር በሚል ስሙ የክብር መዝገብ ላይ ሰፍሯል፤
ጥርሱ ግን ተርፏል? 😁

በነገራችን ላይ አንድ ቀን ድንገት ተኝተን ስንነሳ "አረጋ ከበደን ሳንገለው ሞተ (ተገደለ)" የሚል መጣጥፍ የምንጥፍ ይመስለናል። ጭሶቹ 😉

15.2k 0 14 10 310

ብልጼ በፍጥነት ገምግማለች!

የብልጼን ሹማምንት ያልታወቁ ኃይሎች ቆምጨጭ ያለ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸው እና ያለ ምህረት መንደል መጀመራቸውን ተከትሎ የብልጼ ሚዲያዎች ተከታታይ ፁሑፎች እያጋሩ የሃዘንና እንጉርጉሮ ዘገባዎች ሚዲያዎቻቸውን እንዲሞላው አድርጓል።

ታዲያ የዳንግላውን ክስተት ተከትሎ የብልጼ ሰዎች "በሚዲያ እየተለቀቀ ያለው የሃዘን መግለጫ በተቀረው አመራር ላይ ፍርሃትና አለመረጋጋት እየፈጠረ ነው፤ በጠላትም በኩል እንደጀብዱ እየታየ ነው" በሚል መገምገማቸውን ባህርዳር ዊክሊክስ ያገኘችው መረጃ ያስረዳል።

ይህንን ተከትሎም ለብዙ ቀናት እነሱ ሲያለቅሱ፣ እኛ ቡጊ ቡጊ እንጨፍራለን የሚለው እቅዳችን ላይ ውሃ ቸልሰውበታል¡ አይዞን BW ሌላ ቀን ይመጣል 😁


ዘወር ብለን ስንመለስ ከብልጼ መንደር እሮሮ እንጉርጉሮ እየየው በዝቶ ጠበቀን። በሰላም ነዋ?

"ባልታወቁ ኃይሎች የተጎበኙ የጨፍጫፊው አገዛዝ ሹማምንት ይኖሩ ይሆንን?" ብለን መጠየቅ ፈልገን የነበረ ቢሆንም… ይልቅ "እየየውና ለቅሶው ለስንት ቀን ይቀጥላል" በሚል ጥያቄውን አንድ ደረጃ ከፍ አድርገነዋል።

አይዞን ይቀጥላል 😁


ትናንት አንድዬ የአማራን ልሳን አስራት ሚዲያን ያፈረሰች ቅንጭራም አሜባ፣ ዛሬ ደግሞ መረጃ ቴሌቪዥን የከሰመና የሚጠፋ መስሏት እስክስ እያለች ትኩረት ፍለጋ እየተንከላወሰች ትገኛለች። የቴሌቪዥን ተቋማችን አለ፤ እንዲኖርም ከወዲሁ እየሰራን ነው። ይህችን መክፈልና መከፋፈል የሚያስደስታትን ደቂቅ ፍጡር፣ "ቅንጭራም አሜባ" ብለናት ብንቀጥል በደንብ ይገልጻታል።

20.7k 0 4 119 441

ለመረጃ ቲቪ ቤተሰቦችና ተከታታዮች፣

የቴሌቪዥን ጣቢያው ለኢትዮጵያ ሕዝብ እያቀረበ ያለውን የመረጃ አገልግሎትና በተለይም የአብይ አህመድ አገዛዝ ጦርነት የከፈተበት የዐማራ ሕዝብ እያካሄደ ባለው የወቅቱ የህልውና ትግል የሚዲያውን ድርሻ ለመገምገምና ቀጣዩን ጉዞ ለመቀየስ የፅሞና ጊዜ እንደሚያስፈልግ ስላመንበት ከዛሬ ጥር 1 / 2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከትምህርት ፕሮግራሞች በስተቀር ሌሎች ፕሮግራሞችን እንደማይተላለፉ እያሳወቅን የሕብረተሰባችን ድጋፍ እስካልተለየን ድረስ በአዲስና በተጠናከረ ሁኔታ እንደምንመለስ እናሳውቃለን።

መረጃ ቴሌቪዥን
~~~~

ህዝባችን ይህንን የችግር ጊዜ ልሳኑ ለነበረን የሚዲያ ተቋም አስፈላጊ እገዛዎችን አድርጎ፣ ተቋሙም እንዳለው በጠንካራ ጎኖቹ ላይ ይበልጥ excel በማድረግ ወደ ሙሉ ህዝባዊ ቁመናውና ስርጭቱ መመለስ ይገባል የሚል መልዕክት ባህርዳር ዊክሊክስ አላት።

26.5k 0 7 104 389

መረጃ ቴሌቪዥን የእኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። እስካለን መረጃ ድረስም ሰሞኑንም ይህን የሚዲያ ተቋም ስሙን ጠርቶ የዘመተበት ወይም በማኔጅመንቱ ላይ በቀጥታ ተፅዕኖ ያደረገ ሰው የለም። ምክንያቱም ተቋሙ ከሰሞኑናዊ ጉዳዮች ጋር ፍፁም የቀጥታ ግንኙነት ያለው ባለመሆኑ ነው።

እርግጥ ነው ተቋሙ በሰሞኑን ጉዳይ የሁኔታ ዳሰሳና ግምግማ ሰርቶ ቀድሞ የወሰደው እርምጃ እንዳለና ከዛም በጊዜያዊነት ከአየር መውረዱን ከውስጥ ሰምተናል። ነገር ግን የሚዲያ ተቋሙ ተቋማችን በመሆኑ ከስርጭት ወርዶ እንዲቀር በፍፁም መፍቀድ የለብንም፤ የችግር ጊዜ ድምፅ የሆነንን ሚዲያ የፋይናንስ ችግሩንም ቀርፎ ወደ አየር መመለሱ የሁላችንም አስቸኳይ የህሊና አደራችን ይሆናል።
~
ባልተያያዘ መረጃ ደግሞ የአንዱ ወዳጃችን ጥያቄም ከጊዜ ጊዜ በእጅጉ እየከበደንና እያንገዳገን መምጣቱን መደበቅ አንፈልግም። በተለይ ዛሬ "ለምንድን ነው ምስራቅ ጎጃሞች ብቻ የሚሾሙት? ሲል ያቀረበልን ጥያቄ ኧረረ አስብሎናል - ደግነቱ ባህርዳር ዊክሊክስ ይህ ጥያቄ ከቀረበላት በኋላም ያለማቋረጥ ለ6 ዓመት ከመንፈቅ ምርምርና ምርመራ አድርጋ መልሱ ላይ ደርሳለች - "ለምን ተሿሚዎች በሞላ ከጠለዛሞ ጎጥ ወይም ከቀራንዮ መንደር አይሆኑም! ምን ጭንቅ?!" ብላለች። የመጨረሻዋ የተመዘዘች ካርድ ክፍል ክፍልፍል፣ ልባችን ውልቅ ውልቅልቅ አደረገችን (በሳቅ) 😁

ተው ለዓመታት የገነባኸውን ስም በጀንበር አትናድ! ተው ግድ የለህም።

21.7k 0 10 247 391

ለካንስ እኛ ዞር ብለን እስክንመለስ ነበልባሎቻችን የአራዊት ሰራዊቱን 64ኛ ክፍለጦር በትኩሱ ፉት ፉት በማለት የመሳሪያ ጎተራቸው ቁንጣን ይዞት ጠበቀን።

በእውነቱ ይህንን የራስ ጉና ብርጌድ እና የጄኔራል ነጋ ተገኝና የአንበሳው ጋይንት የፋኖ ክፍለጦሮቻችንን ምትሃታዊ ጀብዱ አለማድነቅና አለመኩራት ንፉግነት ነው።


……የቀጠለ

ይህ አረመኔ ሥርዓት በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ የሚገኘውን የጦርወንጀል ለማድበስበስና የሥልጣን ፍትወቱን ለማጽናት ምናልባትምሥርዓተ መንግሥቱን ከውድቀት ለመታደግ የሚጓዝባቸው መንገዶችደመ ነፍሳዊ፣ አላዋቂ፣ ሕገ ወጥ፣ መርኅ አልባ፣ ከምንም በላይ ሀገርንየመምራት ሞራል፣ ክህሎትና እውቀት የሌለው ፍጹም አቅመ ቢስ መሆኑን ያረጋግጣል። ብልጽግናን መታደግ የሞተን ሰው ከመቃብር እንደ ማስነሳት ነው፤ ብልጽግናን እንደ መንግሥት ማስቀጠል የጸሐይን መውጫ በምዕራብ እንደመጠበቅ ነው፤ የብልጽግናን የሥነ መንግሥት ውቅር መሠረታዊ እሳቤዎችን ማስቀጠል በአማራሕዝብ ላይ የሚፈጸምን የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደ ማስቀጠል ብሎም የጦር ወንጀሉም ተባባሪነት ነው፤ ብልጽግናን በገሐድ ማስቀጠል አይደለም ሥርዓቱ እንዲቀጥል በንግግርና በሀልዮም ጭምር መደገፍ ታሪክ ይቅር የማይለው አማራ እንደሕዝብየሚጠፋበትን ጦርና ጎራዴ እንደማቀበል ነው።

ስለሆነም ሥርዓቱን ከነእኩይ አስተሳሰቡ ለማስወገድ የሚደረገውን የአማራ ሕዝብየኅልውና ትግልን ለማኮላሸትና ለመጎተት የሚታትሩ ከብልጽግናው መዋቅር ሹማምንት እስከ የሃይማኖት አባትነትና የሽምግልና ጭምብል አጥላቂዎች፣ የአማራን ሕዝብ በምጣኔ ሃብት እያደቀቀ ለሚገኝ ሥርዓት በፋይናንስ ደጋፊ ባለሃብቶች እስከ ሳይበሩ ዓለም የተኮለኮሉ እኩይ የሥርዓቱ ሎሌዎች መኖራቸውን በውል እናውቃለን።

የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ አደረጃጀቶችበሚከተሉት ጊዜ የማይሰጡ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን አቋም፣ አቅጣጫና ማስጠንቀቂያዎችንም ጭምር ለሕዝባችንና ለሠራዊታችን ከምንም በላይ ላላዋቂ የሥርዓቱ ዘቦች መግለጽ እንወዳለን። በዚህ መሠረት፦

1ኛ. ሽምግልና ትርጉሙ፣ አፈጻጸሙ፣ ተሳታፊዎቹ፣ ተጠቃሚዎቹና መሰል ዝርዝር ጉዳዮችን በወጉ ስንመረምር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሐቀኛ የፍትሕ ተቋም ነው። እንዲህ ያለ ሐቀኛ ተቋም ደግሞ መርሁፍትሕን በሐቅ ምርኩዝነት መዳኘት ዘወትራዊ ግብሩ ነው። በሽምግልና በዳይን ይገስጹበታል፤ ነውረኛን ያርሙበታል፤ ገዳይን ይቀጡበታል፤ ሸረኛን ቀጥቅጠው ያስተካክሉበታል፤ ሐገርን ሕዝብን ግለሰብንም ጭምር የበደሉ አካላት ያለአንዳች ማኅበራዊ ደረጃ እኩል በሐቅ ይበየንባቸዋል። የተበደሉ አካላትም ይካሳሉ፤ ፍትሕን በልኩ ያገኛሉ። ቅሉ የሽምግልና ወጉ ይህ ሆኖ እያለ ሐቀኛውን ነባር የፍትሕ ተቋም ለሆድ፣ ለጥቅም ማዋል፣ በዳይም ተበዳይም በዓለም አደባባይ እየታወቀ የአይሁድ ሸንጎ አስፈጻሚ የሃይማኖት አባትነትን ጭምብል ያጠለቃችሁ፣ የፍትሕን ምንነት የማታውቁ ነገር ግን በቁሳዊ ሃብታችሁ የታወቃችሁና በልዩ ልዩ ጉዳዮች እውቅናን ያገኛችሁ አካላት በቅንጅት የጦር ወንጀለኛውን በርባን አብይ አሕመድን ነጻ እንዲሆን ሽታችሁ እንደ ክርስቶስ ያለበደሉ መስቀል ላይ የተቸነከረውን አማራውን የማስጨረስ ፕሮጀክቱ ተባባሪ ሆናችሁበማግኘታችን እጅጉን አፍረንባችኋል፤ አዝነንባችኋልም።

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው መንግሥት መር የዘር ማጥፋት ድርጊት ከሽምግልና የተሻገረ፣ ሥርዓታዊ ሥር ነቀል ለውጥን የሚሻ፣ ወንጀለኞችም በዓለም አቀፍ የጦር ወንጀልና በዘር ማጥፋት ወንጀል የሚጠየቁበት ጊዜ ሩቅ ስላልሆነ ከወንጀለኛ ጋር የዘረጋችሁትን ተባባሪነት እግራችሁንም እምሯችሁንም እንድትሰበስቡ እየመከርን በየቀኑ የሚገደለው ሰው መሆኑንም ተገንዝባችሁ ለእውነትና ለፍትሕ ያላችሁን ውግንና ጨፍጫፊውን ሥርዓት በአደባባይ በማውገዝ እንድታሳዩንም እንጠይቃለን።

2ኛ. የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል በሥርዓቱ ወራሪ ሠራዊት ላይየውጊያ የበላይነትን ሙሉ ለሙሉ ከመውሰዱ ባሻገር ምድር ላይ ያሉሐቀኛ ሁነቶችን በመግለጥ የሚዲያና የፕሮፓጋንዳ የበላይነት ተወስዶበት መንፈራገጥ ላይ ይገኛል። የተወሰደበትን የሚዲያ የበላይነት ለማካካስ በሚመስል መልኩ በተለያዩ ቀናት የተነገሩትንየድምጽ ቅጅዎች በማገጣጠም የኅልውና ታጋዩን መስተጋብር አበላሻለሁ የሚለው አስተሳሰብና ድርጊትም የሥርዓቱን አላዋቂነት ከመግለጡ ውጭ ከቶ ምንም ሊባል አይችልም። እንደዚህ ያለው የሳይበሩ ዓለም ተግባርም ቀድመን ያወቅነው፣ ድሮን፣ ታንክና ሞርተር ያልበገረው ሠራዊታችንም በወጉ የሚገነዘበው የጠላት እቅድና ፍላጎት መሆኑን እያስገነዘብን፣ አንዳንድ አመራሮቻችን ላይ የሚደረጉ ፍረጃዎቸም የዚህ ፕሮጀክታቸው አካል መሆኑን መግለጥ እንወዳለን።

3ኛ. በመጨረሻም የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል ብዙ ነገራችንን ያጣንበት በአንጻሩ የብልጽግናን መዋቅር በአጭር ጊዜያፈራረስንበት፣ ሕዝባችንን አስተባብረን በአሸናፊነት መንገድእየተጓዝን የምንገኝበት ግዙፍ አብዮት ነው። እንዲህ ያለውን ሕዝባዊ አብዮት የሚጎትት፣ የሚያቀጭጭ፣ የሚያኮላሽ ምድራዊ አደረጃጀትና መዋቅሮችም ፈርሰዋል። ስለዚህ የማይድን ሥርዓት ውስጥ የምትገኙ የሚሊሻ፣ የአድማ ብተና እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት አባላት እስከ ጥር 15/2017 ዓ.ም ድረስ በየቀጠናው ለሚገኘው የፋኖ አደረጃጀት በሠላማዊ መንገድ እጃችሁን እየሰጣችሁ፣ የተሃድሶ ሥልጠናዎችን እየወሰዳችሁ ሥምሪት ተቀብላችሁ ትግላችንን ወደፊት እንድናስፈነጥረው የመጨረሻ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።   
 
ኅልውናችን በተባበረ አንድነታችን!!!
አርበኛ ሐብቴ ወልዴ.............የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ዋና አዛዥ
አርበኛ ባዬ ቀናው................የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ


በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ በጎንደር እና ከአማራ ፋኖጎንደር እዝ የተሰጠ የጋራ መግለጫ!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል በሐቅ፣ በፍትሕና በሰብዓዊ ክብርዓለትነት ላይ የታነጸ ብርቱ አብዮት ነው። አብይ አሕመድ መራሹየብልጽግና ሥርዓት በሕዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት አዋጅን አውጆ፣ የሃገሪቱን ጦር አዝምቶ ሠላማዊዉን ወገናችንን መጨፍጨፍ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ መላው የአማራ ሕዝብ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሥነ ልቡናዊ ምስቅልቅል ውስጥ እንዲገባ አድርጓል።

ሥርዓቱ ጸረ አማራነት አስተሳሰቡን ፍጹም ጭካኔበተሞላበት አረመኔያዊ ግብሩ በገሐድ አሳይቷል። ሕዝባችን ከላይ፦ ድሮንና መርዛማ ቦንቦችን የታጠቁ ጀቶች፣ ከታች፦ መድፍ፣ ታንክ፣ ቤኤም፣ ሞርተርና ዲሽቃ በአማራዊ ማንነቱ ብቻ እንደ በረዶ እየወረዱበት ዘሩ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ መንግሥት መር የዘር ማጥፋት ድርጊት እየተፈጸመበትም ይገኛል።

ይቀጥላል…


አንዳንድ ወስከምቢያ አናት ነሆለሎች ስለ አማራ ፋኖ አንድነት ሲቸከችኩ እየዋሉ፣ ለእነ ወግደረስ ጤናው በአማራ ፋኖ በጎጃም ኃላፊነት መሰጠቱን ግን ሲተቹ እያየን ነው። ይህንን የሚለው ከእኛ እኩል አፋጎን ሲጠብቅ፣ ተቋማዊ ውሳኔዎችና አካሄዶች ይከበሩ ሲል ውሎ ነው።

ታዲያ የጎራን መስመር አልፈህ ካልተነጋገርክና ካልተቀራረብክ፣ ከታች ባለ አንድ ዕዝ ደረጃ መቀራረብን እየተቃወምክ እንዴት ብሎ የታላቁ የአማራ ፋኖ አንድነት ይምጣልህ? በትንሹ ሳትሰባሰብ፣ በትልቁ እንዴት አንድነት ይምጣልህ? ታጥቦ አይጠሬን አንተኛውን ነው - ደና ውለህ ነው?


የፖለቲካ ሀሁ

ወዳጅን ማብዛት፣ ጠላትን መቀነስ (ወይም በአንድ ጊዜ በርካታ የጠላት አውደግንባሮችን አለመፍጠር)፣ የጠላትን አቅምና ምሰሶዎችን መናድ፣ የእራስን ውስጣዊ አንድነት ማጠናከር… እነዚህን መሰል ጥበቦች የፖለቲካል ሳይንስ መባቻዎች ናቸው።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ዛሬ ያወጣው መረጃም ከላይ ባለው የፖለቲካ መርህ ትይዮ ሆኖ አግኝተነዋል። ትናንት በቁርሾ ውስጥ በተለያየ ጎራ የነበሩትን ወንድሞች በማቅረብና የዓላማ ብቻም ሳይሆን የአካሄድ መግባባትን በመፍጠር በኃላፊነት መደብ ላይ መቀመጡን ዛሬ የሰማነው ዜና ነው -

▪︎ፋኖ ወግደረስ ጤናው - የአፋጎ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዝግጅት ክፍል ኃላፊ

▪︎ፋኖ ጥጋቡ መኮንን - የአፋጎ የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ

የተሰባሰበ ይድናል፤ ያሸንፋልም - ደና ውላችሁ አድራችሁ ነው?


ይህ ልባዊ መልዕክታችን ነው!

እኛ በትግል ሜዳ ላይ የተግባር መስዕዋትነት እየከፈሉ ላሉ ፋኖ ወንድሞቻችን ትልቅ ክብር አለን፤ እኛ ብዙን ጊዜ የምንወቀስበት መሃል ሰፋሪ ናችሁ በሚል ነው። ለዚህ ትችትና ፍረጃ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ በፋኖዎቻችን መካከል ያሉ ልዮነቶች በተለሳለሰ መልኩ በምክክር ይፈቱ ስለምንልና ፋኖዎቻችን ያለስም ስም ሲሰጣቸው በዚህም በዛም ጥብቅ ስለምንቆም ነው።

ምናልባትም በእስክንድር ነጋ ላይ ካቀረብነው ሃሳብ ውጭ ምናልባትም የፋኖ መሪዎቻችንና አባላቶች ስም ስናጠለሽ አንድም ሰው አንዲትም መስመር ፁሑፍ ሊያቀርብብን አይችልም። ምክንያታችን ደግሞ ልዮነቶች ላይ የሚዲያዎች ሚና ማጋጋል እንጅ ስንጥቆችን መድፈን አይደለም ብለን በፅኑ ስለማናም ነው።

ወደ ሰሞኑናዊ ጉዳይ ስንመጣም ዘመድኩን በቀለን መስመር ባለፈ መልኩ እንደሄድንበት ግልፅ ነው። ምክንያት - የእሱም አካሄድ defamation ላይ ያተኮረ እና ተቋማዊ መስመርን የጣሰ ግብታዊ አካሄድ ነው ብለን ስላመን ነበር።

ይህ አካሄዳችን አሸናፊና ተሸናፊ ለመፍጠር አይደለም። በተመሳሳይ ትናንትና ዛሬ ያጋራናቸው የአማራ ፋኖ በጎጃም መግለጫዎችም "አየህ ተሸነፍክ" ለማለትም አይደለም፤ በፍፁም። በሌላ በኩልም የዘመድኩንን ያለፉ አበርክቶዎችንም አፈር ለማስበላት አይደለም። ነገር ግን በትግሉ ላይ የሚኖረን ሚና እንደ ሚዲያ ሰው በልኬታው ልክ መሆን አለበት የሚል ፅኑ እምነት ስላለን ነው።

በጠላት ላይ አነጣጥረው የነበሩ አቅሞችን በሙሉ በትኖ፣ እርስበራስ ለመጠቃቃት መጠቀም ልክ ሊሆን አይችልም። አቅሞችን ሁላ ጠላትን ለማጥፋት በማሟጠጥ፣ ውስጣዊ ተቋማዊ አሰራሮች እየጎለበቱ ውስጣዊ ችግሮችን እያረሙ እንዲሄዱ ማድረግ ያስፈልጋል።

ምንም መካድ የማይቻለው ነገር የሚዲያዎች ፈትፋችነት በጋለው ትግላችን ላይ በረዶ ይዞ ቀርቦ ሊረሳ በማይቻል መልኩ ከጠላት በላይ አጥቅቶናል። እሱ ይቅርና (ለትግላችን አዎንታዊ አመለካከት ያለው ሁሉ) ምናልባትም ባለፉት ጥቂት ወራቶች በሚዲያው ሚናችን ምን ያክሉን ሰዓታችንን ጠላትን ለማጥቃት ተጠቀምንበት ብለን እራሳችን መጠየቁ ጥሩ ነው።

የሆነው ሆኖ ትግላችንን ከመጠበቅ አንጻር እንጅ በዘመድኩን በቀለ ላይ ግለሰባዊ ግጭት ውስጥ ገብተን አይደለም በእላፊ ቃላት ሁላ ስንወርፈው የሰነበትነው። ለትግላችን ቀናዒ አመለካከት እስካለህም ድረስ ይቅርታ እንጠይቅሃለን።

በነገራችን ላይ ትናንት ዶ/ር ጋሹ ክንዱን ወይም ከዛ በፊት ሌሎቹን ይቅርታ የጠየቅንበት ምክንያት ኢጎን በመግራትና ስብር በማለት ይበልጥ መሰባሰብን ካመጣልን በሚል ነው። የእልህ፣ የግትርነት እና "የማርያምን አታሸንፉኝም" አካሄድ ወገን ለምንለው እንደማይሆን መረዳት ያስፈልጋል። ይህ ምክራችን ለፋኖ መሪዎቻችንም ይሁንልን - ለወገን የተባለ ግለሰባዊ መሸነፍ፣ የወል አሸናፊነትን ያመጣል

20.4k 0 5 236 338

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ውድ ወገናችን - ይህንን ቪዲዮ ከልብ አዳምጡት!

አርበኛ ዘመነ ካሴ የገናን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስከትሎ ይህን መልዕክትም አስተላልፏል። ከልብ ከልብ አዳምጡት።

ስንት መስዕዋትነት የተከፈለበት ትግላችን ዳር መድረስ ካለበት ልብ ለልብ እንደማመጥ፣ እንቅስቃሴያችን በሙሉ አዎንታዊ ይሁን፣ መሪዎቻችንን እናክብር እናዳምጥ፣ ሚናችንንም እንለይ።

ተቋም ገንብተናል፤ ከገነባነው ተቋም በላይ ሆኖ "የበላይ ጠባቂ" ጣልቃገብነት የሚያስፈልግበት ጉዳይም የለም። ተቋም ግንባታ ሂደት እንደመሆኑም ተቋማችን እየተማረ፣ እራሱን እያነፀ ለአማራዊ ተቋም ግንባታ አበርክቶ የሚኖረው ጠንካራ አለት ይሆናል።

ሚዲያ ላይ ያለን ሰዎች አርበኛ ዘመነ ካሴ እንዳለው "አበርክቷችን በሚናችን ልክ ይሁን"። ለትግሉ አዎንታዊ እይታ ኖሮን ነገር ግን ለእራስ የተሰጠ ያልተገባ ግምት አፍራሽ ነው። እናም ከልብ ከልብ ለትግሉ የምናስብ ከሆነ፣ ሚናችንን ለይተን ችግሮችን ከስር ከስር መፍታት የሚችሉ አሸናፊና የገለበተ ተቋማዊ ግንባታ ላይ እናተኩር የሚል መልዕክት አለን።

20.7k 0 17 83 252

ዋይ ዋይ ባይ ውሻ ነኝ ባዮቹን፣ ተቋማችን የአማራ ፋኖ በጎጃም በ uppercut መንጋጭላቸውን አጉኖላቸው "ውሾች ይጮሃሉ፣ ግመሎች ግን ጉዟቸውን ይቀጥላሉ" የሚል ተረት ወርወር አድርጎ ጉዞውን ቀጥሏል፤ ትኩረት የወል ዓላማችን ላይ ብቻ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል።

ጥሬ ካካ ሊዘበሉልብን የሞከሩትም ሆኑ ባለሹካ ተቋዳሽ መንጋዎች ሁሉም ኩም ተደርገዋል። በዚህም መደዴው ሁላ ደብሮት ይሆን? እንዳሻው! እኛ ግን አልደበረንም - ከፈለጋችሁ ውለዱለት 😁

መደዴው ግን ደና ውሎ አድሮ ይሆን? 😁

(እዚች ገጽ ላይ አንዲትም ማንም የሚነዳው መደዴ የመደዴ ልጅ ማየት አንፈልግም፤ በፈቃድህ ጥፋ ከዚህ።)

21.1k 0 3 250 361



የአማራ ፋኖ በጎጃም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እና መግለጫ

በመጀመሪያ በዱርና በገደሉ፣ በሃሩርና በብርዱ፣ በከተማ ኦፕሬሽንም ሆነ ምሽግም ውስጥ፣ በሰፊዉም ሆነ ጠባቡ እስር ቤት ዉስጥ ያላቹህ፤ ቆላ ወርዳቹህ ደጋን ወጥታቹህ ከጠላትት ጋር ግብ ግብ የገጠማችሁ፣ በምትሰሩት ተጋድሎ ሁሉ የኅሊና ወቀሳ የሌለባቹህ፣ ከጠላት ጋር እየተናነቃችሁ ለህዝባችን ማህበራዊ እረፍት ማግኘት ለምትታገሉ ፋኖዎቻችን በሙሉ... እንኳንም አብሮ አደረሰን!! በዓሉን ለምታከብሩ የሰው ልጆች ሁሉ እንኳንም "ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል" አደረሳችሁ።
-
-

የአማራ ፋኖ በጎጃም ድርጅታዊ ዕዝና ሰንሰለት ያለው፣ ተጠየቅን ያነገበ ተቋም መሆኑ ይታወቃል። በዚህ አሰራርም ከዓላማችን በተፃራሪ የሄዱ ወንድሞቻችን ላይ የእርምትና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ውስጣዊ አንድነቱን ያስጠበቀ ኃይል መገንባታችን ውሎ ያደረ ሃቅ ነው። ለጉድለቶች ተጠየቅን፣ ለመሻሻሎችም ምስጋናን የሚያቀርብ አሰራርም አለን። እለት ከእለት ለመሻሻል ከመስራት፣ ለአንድነትም ከመስራት የማያሳልስ ጥረት ከማድረግ ተቆጥበን አናውቅም።

ዳሩ ግን አንድም ወታደራዊ ሽንፈቱን በውጊያ ሜዳ የተጋተው አገዛዙ ከውጭ በኩል፣

ሌላም የአንድነትን አስፈላጊነት በውል ያልተረዱና የዉጊያን ሜዳ አስከፊነት የማያውቁ ውስጣዊ እቡዮች ተባብረው በሚፈጥሩት ውስብስብ አጀንዳ ምክንያት 'ጠላት በሚዲያ የሐይል አሰላለፉ' በኩል የደረሰበትን ምት በማስተባበልና የጣረ ሞት መንፈራገጥ ላይ ይገኛል። በዚህም በድርጅታችን የአማራ ፋኖ በጎጃም ውስጥ "የተለየ ነገር የተፈጠረ ለማስመሰል" የሚደረገው ጥረት ሁሉ የበሬ ወለደ ወሬና ፍፁም ተጨባጭ ያልሆነ አጀንዳ መሆኑን በማወቅ የውጊያም የስንቅም ደጀን የሆነው ህዝባችን ትኩረቱን ሁሉ የጠላት ሐይል ላይ ብቻ እንዲያደርግ ስል ወንድማዊ ጥሪየን አቀርባለሁ። የፋኖ ሰራዊታችን በዓሉን በወትሮ ዝግጁነት እንዲሁም ከጠላት የድሮን አሰሳና ጥቃት በተጠንቀቅ እንዲያከብር እያሳሰብኩ በዓሉን ለምታከብሩ ሁሉ በድጋሜ መልካም በዓል እላለሁ።

ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ደለለ
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ


ሚሊሽያ - በግራ ምህረት በቀኝ እርሳስ ቀርቦለታል። በዚህም መሰረት አራዊት ሰራዊቱን እንዲጠብቅ የተሰማራው ሚሊሽያ እድል የቀናው እጅ እየሰጠ ሲሆን ገሚሱ ደግሞ አፈር መቅመሱን ቀጥሏል።

ከአርበኛ አስረስ ማዕረይ (🙃 😁) እንዳገኘነው ተጨማሪ መረጃ ከሆነ 35 ሚሊሽያዎች በአባይ ሸለቆ ብርጌድ ጥቃት ከምድር በታች ሲደረጉ፣ 12 ሚሊሽያዎች ደግሞ እጅ መስጠታቸው ታውቋል።

በተመሳሳይም ከሁለት ቀናት በፊት በድቦ ኪዳነ ምህረት አካባቢ 27 ሚሊሻዎች መነደፋቸውን ተከትሎ፣ አገዛዙ እንደማያድናቸው የተረዱ በርካታ ሚሊሽያዎች እጅ መስጠታቸውን ከአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢ አርበኛ አስረስ ማረ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

ደና ውላችሁ አድራችሁ ነው? 😊

20 last posts shown.