Farankaa - ፈረንካ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


The primary goal of this page is to enhance the financial literacy of Ethiopians by offering valuable insights on investment, banking, insurance, capital markets, and taxation.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ!








ክፉ አሳቢ ሰዎችን ከህይወታችን ስንሰርዝ፣ ህይወታችንን ቀላል ይሆናል።


መልካም ቀን ይሁንላችሁ!




Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ከሶስቱ ሰዎች (A, B እና C) የትኛው የተሻለ ሰው ነው ብለው ያስባሉ? ቪዲዮውን ሲጨርሱ ከመልስዎ ጋር ያስተያዩ።




የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በጨረታ ለመሸጥ ያወጣውን 50 ሚሊዮን ዶላር 12 ባንኮች ለአንዱ ዶላር በአማካይ 31.7095 ዋጋ በማቅረብ አሸንፈው መግዛታቸውን በድረ-ገጹ ላይ አሳውቋል። ባንኮች አንዱን ዶላር ለመግዛት ያቀረቡት አማካይ የመጫረቻ ዋጋ በቅርቡ ከወጣው የአማካይ የጨረታ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የ4 ብር ገደማ ቅናሽ አሳይቷል።

ብሔራዊ ባንኩ ቀጣዩን ጨረታ በሚቀጥለው ሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚያደርግና የጨረታውን ማስታወቂያ ከጨረታው ቀን አንድ ቀን አስቀድሞ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ የሚካሄድ ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ሊያወጣ ነው።

ብሔራዊ ባንኩ የወርቅ አቅርቦትና ሽያጭ በመጨመሩ እንዲሁም የሐዋላ እና የካፒታል ፍሰት በመሻሻሉ በታሪክ ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ ክምችት ለመያዝ ችያለሁ ብሏል።

በእዚሁ መሠረት ብሔራዊ ባንኩ ነገ፣ መጋቢት 23 ቀን 2017፣ 50 ሚሊዮን ዶላር ባንኮች ተጫርተው እንዲገዙ ለገበያ አቅርቧል።








ወቅቱ የጾም እና የጸሎት ነውና ከወቅቱ ጋር የሚሄድ ቀልድ እነሆ..

የቤተሰቡ ሁለተኛ ልጅ ነው። ቤተሰቡ ከተኛ በኋላ በሌሊት ተነስቶ...

"አቤቱ ሰዉ ሁሉ በእንቅልፍ በወደቀበት በእዚህ በውድቅት ሌሊት እኔ ግን እንቅልፌን ትቼ ወዳንተ እወተውታለሁ..."

ምናምን እያለ ወደ አምላኩ ይጮኻል፣ ይጸልያል።

ይሄንን በአንክሮ ሲከታተል የነበረና የጸሎቱ ጩኸት ከእንቅልፉ የቀሰቀሰው ታላቅ ወንድሙ..


"እኔ የምልህ ብሮውውውው??? እየጸለይክ ነው እያቃጠርክ?"

.....

የአንዳንዱ ጾምና ጸሎት ለእራስ ኃጢአት ስርየትን የመጠየቅ አይነት ሳይሆን ሌላው ላይ "የማቃጠር" መንፈስ አለውና እንዲህ ከመሆን እግዚአብሔር ያድነን።

መልካም ጾም!




Petroleum Product Marketing Proclamation Number 1363_2024.pdf
8.7Mb
የነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጅ...


ባንኮቻችን ለሙስሊም ደንበኞቻቸው በሽሚያ የኢፍጣር ፕሮግራም እያዘጋጁ ነው። ይሄ ይበል የሚያስብል ነው። ይሁንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ደንበኞቻቸውም እለት ተእለት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዐት እየጾሙ ነውና መቼ ይሆን ነጠላቸውን ጣል አድርገው ጾም የሚያስፈቷቸው? I am just curious.


በህይወታችን ውስጥ ብዙ ነገሮች በእኛ ቁጥጥር ስር አይደሉም። ይሁንና የሚከተሉትን 22 ነገሮች ልንቆጣጠራቸው እንችላለን።

1. ምልከታችንን
በጎ ምልከታን ይኑረን

2. ታማኝነታችንን
ለእሴቶቻችን ታማኝ እንሁን፣ በከባድ ጊዜ ሳይቀር

3. ድፍረታችንን
ፍርሀታችንን ታግለን እንደግ

4. ደግነታችንን
ትንሿ የደግነት ምግባራችን የሆነ ሰውን ቀን ታብራ

5.  ተጽእኖአችንን
ልንከተለው የምንፈልገው ዓይነት መሪ እንሁን

6. እርምጃዎቻችንን
በኋላ ላይ የምንኮራባቸውን ውሳኔዎችን እንወስን

7. ወሰኖቻችንን
አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ወሰናችን እንዳይጣስ ሀይ ማለትን እንልመድ

8. ጥረቶቻችንን
ነገሮች እጅግ አዳጋች በሆኑ ቁጥር ወደፊት መግፋታችንን አናቁም

9. በማን እንደምንከበብ
በሚደግፉን ሰዎች ዙሪያችንን እንክበብ


10. በራስ መተማመናችንን
ማድረግ እንደምንችል እንመን፣ ችለንም እናሳያለን

11. ሰበቦቻችንን
ህልሞቻችንን ሳይገድሉ በፊት ሰበቦቻችንን እንግደል

12. ትኩረታችንን
ምን ላይ ማተኮረ እንዳለብን እንምረጥ

13. አጥሮቻችንን
አጥሮቻችንን ሰብረን፣ ሌሎች ሰፋፊ አጥሮችን እንገንባ

14. ግቦቻችንን
ከፍ ያሉ ነገር ግን የሚደረሰባቸው ይሁኑ።

15. ጊዜያችንን
አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ቅድሚያ እንስጥ

16. ቃሎቻችንን
ለእራሳችንም ሆነ ለሌሎች በጎ ነገርን እንናገር

17. እራስን መንከባከብን
በየእለቱ ለእራሳችን ጊዜ እንስጥ

18. ዝምታችንን
ባይወደድ እንኳ መናገራችንን እናቁም

19.የህሊና ወቀሳችንን
ተገቢውን ቦታ እንስጠው

20. አእምሮአዊ እሳቤአችንን
አንድ ቦታ ከተቸነከረ እሳቤ ተላቀን በማደግ ላይ የተመሰረት እሳቤን እንገንባ

21. አላማዎቻችንን
ድርጊቶችን በተልእኮአችን ጋር ይጣጣሙ

22. ምስጋናችንን
በረከታችን ትንሽ ብትሆን እንኳ ማመስገናችንን አንርሳ

መልካም ሰንበት!


ECMA- Securities Dematerialization Directive No. 1047_2025.pdf
10.4Mb
አክሲዮኖችን ወደ ኤሌክትሮኒክ ቅርጽ በመቀየር/Dematerialize በማድረግ በህግ ስልጣን በተሰጠው ማእከላዊ የአክሲዮን አስቀማጭ/Central Securities Depository ማስቀመጥን በተመለከተ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ያወጣው መመሪያ ጸድቆ ስራ ላይ ውሏል።

በእዚህ መመሪያ መሠረት ከእዚህ ቀደም ለህዝብ ተሽጠው በወረቀት ሰርተፊኬት ማስረጃ የተሰጠባቸው አክሲዮኖች በኤሌክትሮኒክስ ቅርጽ ተቀይረው በማእከል ይቀመጣሉ። አክሲዮኖች በማእከል መቀመጣቸው ባለአክሲዮኖች ያለ ብዙ ውጣውረድ እርስ በእርስ እንዲሻሻጡ እድልን ይፈጥራል።፣ ግብይቱ ስርዐት ይይዛል።

አክሲዮኖች በህግ በተቀመጠ ቀነ-ገደብ ከሻጭ ወደ ገዢ በፍጥነት ይዘወራሉ፣ ሻጭም በእዚህ ቀነ-ገደብ ክፍያውን ያገኛል። በአክሲዮን ግብይት ውስጥ ማን ለማን ይሽጥ በማለት ጣልቃ የሚገቡ አካላት አይኖሩም (አክሲዮኑን የሸጠው ተቋም የትኛው አክሲዮን ለማን መሸጥ እንዳለበት የመወሰን ስልጣን አይኖረውም)።

ከእንግዲህ የተቋማትን አክሲዮን ለሚፈልጉትና ለመረጡት ቡድን ብቻ መሸጥ የሚችሉበት ዘመን አክትሟል። ባለአክሲዮኖች በአክሲዮን ብሮከሮች አማካይነት ለማያውቁት ሰው አክሲዮን የሚሸጡበት ዘመን መጥቷል። ሻጭና ገዥ በማንነት ሳይሆን በገበያ ዋጋ ላይ የተመሰረት የአክሲዮን ሽያጭ ይፈጽማሉ።

ከእነዚህም ባሻገር መመሪያው አክሲዮኖች የህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ መደበቂያ እንዳይሆኑ ተቋማት ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የማንነት ማጣሪያዎች /Due Diligence/ ግልጽ ትንታኔን አስቀምጧል።

An interesting time awaits Ethiopian shareholders and corporations.


ሁልጊዜ ሌሊት እመንገድ ዳር ካለው ኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቴ አጠገብ ያለው መንገድ በመጥረጊያ ሲጸዳ በሚወጣ ድምጽ እነቃለሁ።

በሞቀ አልጋዬ ውስጥ ሆኜ የአጽጂዎቹን የእለት ተእለት ትጋት፣ የሌሊት ብርድ ሳይበግራቸው ሰውና መኪና ሳይሰማራ በሥራ ቦታቸው መገኘትና ጽዳታቸውን መከወን እንዲሁም የሥራቸውን ክብደት እኔ በሥራና በህይወት ውስጥ ከሚገጥሙኝ ተግዳሮቶች ጋር አነጻጽርና እራሴን እታዘባለው፣ ስንፍናዬን እነቅፋለሁ።


ክብር በየእለቱ ህይወትን ለማሸነፍ እንቅልፍ አጥተው ጎዳናዎቻችንን ለሚያጸዱ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሥራ ሰርተው ቤተሰቦቻቸውን ለሚያኖሩ ሴቶች ሁሉ ይሁን!
----
የምስል ምንጭ Chat GPT

20 last posts shown.