🇪🇹ዘወልድ ምክረ-ሕግ🇪🇹‼️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ቻናሉ ሕጎችንና የፍ/ቤት ዉሳኔዎችን ያጋራል። አጫጭር የሕግ ማብራሪያዎችንና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ጠበቃ ካሊድ ከበደ እና ጠበቃ አማረ እሸቱ
በማንኛዉም የፌዴራል እና የክልል ፍ/ቤት ጠባቃና የሕግ አማካሪ
ስልክ- 0935439820
ኢሜይል- khalidbinkebe@gmail.com

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: Minda Girma Law Office ምንዳ ግርማ ህግ ቢሮ
#የፌዴሬሺን_ምክር_ቤት_ውሳኔ_በዐይነ_ስውራን_ጉዳይ
ፌ/ም/መ/ቁ. 019/08

"የዳኝነት ሥራ ተፈጥሯዊ ባሕርይ  ማየት የተሳናቸው ሰዎችም ተመጣጣኝ ማመቻቸት ከተደረገላቸው ሊሠሩ የሚችሉት ሙያ ስለሆነ  'ማየት የተሳናቸው ሰዎች የዳኝነት ሥራን መሥራት አይችሉም' የሚል ልማዳዊ አሠራርን በመከተል ከዳኝነት ዕጣ ድልድል ውጭ በማድረግ በዐቃቤ ሕግነት የመመደብ ውሳኔ ማየት የተሳናቸው ሰዎች በመረጡት ሙያ የመሰማራት እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊ የእኩልነት መብታቸውን የሚጋፋ ስለሆነ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 41(2)፣ 25 እና 9(1) መሠረት ተፈጻሚነት የለውም።" -የፌደሬሽን ም/ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔ ሰጥቷል።


Forward from: Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
#የሰ/መ/ቁ 252231
በአንድ የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ላይ በመጀመሪያ የዋስትና መብቱ የተነፈገ ተከራካሪ በወ/መ/ስ/ህ/ቁ 74 መሰረት አዲስ ነገር ወይም ክስተት የተፈጠረ መሆኑን መነሻ በማድረግ ተከሳሽ የሆነ ወገን ለ2 ጊዜ የዋስትና ጥያቄ የማቅረብ መብት አለው። ይህ ድንጋጌ ለከሳሽ ዐ/ህግ ብቻ ሳይሆን እንደ ነገሩ ሁኔታ ለተከሳሽም ተግባራዊ ይሆል። ይኸውም ለክስ መመስረቻ የ15 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ በመስጠት የጊዜ ቀጠሮው መዝገቡ ከተዘጋ በኃላ ክሱ ሳይቀርብ ቢቀር ይህን አዲስ ክስተት በመጥቀስ ተከሳሽ የዋስትና ጥያቄ በዚያው መዝገብ በድጋሜ ቢያቀርብ ስነ-ስርዓታዊ ከመሆኑም በላይ የህገ-መንግስቱን አንቀጽ 19(6)፣ 17(2) ስር የተመለከተውን መብት ተግባራዊ ለማድረግ የቀረበ አቤቱታ ስለሆነ የተጠረጠረበት ወንጀል በህግ ከጅምሩ ዋስትና የሚያስከለክል ቢሆንም ዋስትና ሊፈቀድለት የሚገባ ነው ሲል አስገዳጅ የህግ ትርጉም ተሰጥቷል(ዋስትና በሚያስከለክል የሙስና ወንጀልን የሚመለከት ነው)። mutatis mutandis ግድያም ቢሆን እንደማለት ነው።


Forward from: Minda Girma Law Office ምንዳ ግርማ ህግ ቢሮ
የሰበር_መዝገብ_ቁጥር_241561_በፖሊስ_ፊት_የተሰጠ_የቃል_ማስረጃን_በተመለከተ.pdf
683.7Kb
በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.145 መሰረት
የሚቀርብ ማስረጃ ከሌሎች ማስረጃዎች ተገናዝቦ የሚታይ እንጂ ብቻውን አመልካቾች ወንጀል መፈጸም አለመፈጸማቸው የሚያሳዩ እንደ ህጋዊነት፣ ግዙፋዊነት፣ ሞራላዊነት ያሉ መሰረታዊ የወንጀል ማቋቋሚያ ፍሬ ነገሮች ባልተሟሉበት ሁኔታ ወንጀል ፈጽመዋል ተብሎ ጥፋተኛ መባላቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው::https://t.me/mindalaw


Forward from: ስለ ህግ
ሰ-መ-ቁ. 200482

ግራ ቀኙ ኢትዮጵያውያን ሆነው በውጭ አገር ህግ መሰረት በዛው አገር ጋብቻ በመካከላቸው እንደተደረገ በመግለጽ አንደኛ አመልካች ጋብቻ እንዲፈርስ እንዲሁም የጋራ ንብረት ክፍፍል እንዲደረግ ዳኝነት ሲጠይቅ ጉዳዩ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት በመሆኑ አቤቱታውን ተቀብሎ የመዳኘት ስልጣን ያለው በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 መሰረት የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው።

ሕጋዊ ጋብቻ ተፈጽሟል ለማለት የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት ይኖረዋል? የሚለዉ ነጥብ ምላሽ የሚያስፈልገዉ ነው። እንዲሁም በግራ ቀኙ መካከል በውጭ አገር ተፈጽሟል የተባለዉ ጋብቻ፣ በሕግ አግባብ የተፈጸመ ጋብቻ ነዉ የሚባል ከሆነና ጋብቻቸዉ በፍቺ ውሳኔ እንዲፈርስ የሚወሰን እንደሆነ የፍቺ ውጤት በምን አግባብ ይታያል? የሚለዉ ነጥብ ይነሳል። ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙን የጋብቻ ይፍረስልን ክርክር በተመለከተ ተፈጻሚነት ያለዉ ሕግ የትኛዉ ነዉ? የሚለዉን ነጥብ መወሰንን ይጠይቃል ማለት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የግራ ቀኙ ክርክር የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚመለከት ጥያቄ ያስነሳል፡፡

የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ የዉጭ አካል ተካፋይ የሆነበትን የህግ ክርክር የሚመለከቱ መርሆዎችና ደንቦችን የሚያካተት ነዉ፡፡ የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግ ወይም የሕግ ግጭት [Conflict of laws] የሚመለከተዉ በተያዘዉ የህግ ክርክር የትኛዉ ሕግ ተፈጻሚነት እንዳላዉ እና የትኛዉ ፍ/ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን እንዳለዉ የሚወስኑ የህግ መርሆችን ነዉ፡፡ የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 (1፣ ሀ) መሰረት የግለሰብ ዓለም አቀፍ ሕግን በሚመለከቱ የፍትሕ ብሔር ጉዳዮችን ለማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መሆኑን ይደነግጋል፡፡

የፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 5 (1፣ ሀ) እና 11 (1፣ ሀ)


Forward from: Click Ethiopian Laws:- by Mastewal
አለግባብ_የተከፈለ_ደመወዝ_ስለሚመለስበት_ሁኔታ_229247.pdf
880.8Kb
አንድ ሰራተኛ X ከተባለ አሠሪ ጋር የስራ ውል መስርቶ የስራ ውሉ ሳይቋረጥ እንደገና ከሌላ Y በተባለ ድርጅት ተቀጥሮ በተመሳሳይ ጊዜ ሁለት ቦታ ተቀጥሮ ደመወዝ ሲከፈለው ነበር።
ከስምንት ወራት በኋላ Y ሰራተኛው ሁለት ቦታ መቀጠሩን ሲያውቅ የስራ ውሉን አቋረጠው።
ጥያቄው Y ለስምንት ወራት ለሰራተኛው የከፈለውን ደመወዝ ማስመለስ ይችላል? በየትኛው የህግ አግባብ?
አሰሪው የከፈለውን ደመወዝ ማስመለስ ይችላል የሚባል ከሆነ መብቱ የመጀመሪያው አሠሪ (X) ነው ወይስ የኋለኛው አሠሪ (Y)?
ወይስ ሁለቱም ማስመለስ ይችላሉ?
⚖⚖⚖⚖👆👆👆⚖⚖⚖⚖


Forward from: Lawyer_Henok ⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
አንድን ተከሳሽ ከወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 67(ሀ) አኳያ በዋስትና ቢለቀቅ ግዴታውን አክብሮ ሊቀርብ አይችልም ብሎ ዋስትናን ለመከልከል የወንጀል ድርጊቱ አፈፃፀም ሁኔታ እና የወንጀሉ ክብደት ሊመዘን የማይገባ ስለመሆኑ፤ ይህ መመዘኛም በክርክር ሂደት ወደፊት የሚረጋገጥ ከመሆኑ አንፃር ከጥፋተኝነት በፊት ንፁህ ሆኖ የመገመትን መብትኖ የሚጥስ በመሆኑ የዋስትና መብትን መከልከያ ምክንያት ተደርጎ የማይወሰድ ስለመሆኑ የተሰጠ አዲስ የሰበር ውሳኔ በሰበር መዝ/ቁ 269430 ጥቅምት 29/2017
Join👇
https://t.me/ethiolawtips




አሰሪው ለሙከራ ጊዜ የተቀጠረን ሠራተኛ ለስራው ተስማሚ አለመሆኑን ሳይመዝን ካሰናበተ ስንብቱ ህገ-ወጥነው።
ስንብቱ ህገ-ወጥ በመሆኑ ካሳ የሚከፈለው ሲሆን የስንብት እና የማስጠንቀቂያ ክፍያዎች ግን
አገልግልትን ታሳቢ ተደርገው የሚሰሉ በመሆኑ አይከፈሉትም። የካሳው መጠንም ሰራተኛው የሙከራ ጊዜውን (60 ቀናት) ቢጨርስ ሊያገኝ ይችል የነበረውን የ2 ወር ደመወዝብቻ ነው።
ሰ/መ/ቁ.212420




በወንጀል ጉዳይ ተከሳሽ የመኖሪያ አድራሻው ሌላ ቦታ መሆኑ እንዲሁም የስራ ሁኔታው ከአንድ ቦታወደሌላቦታ የሚያንቀሳቅ ሰው መሆኑ
በሚል የዋስትና መብቱ ሊያጣ አይገባም።የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ67 እናየኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገመንግስት አንቀጽ 32 ለማንኛውም ኢትዮጲያዊ ከተረጋገጠው የመዘዋወር መብት አኳያ አመልካቾች በሐገሪቱ አካባቢ የመዘዋወር እና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት መብት አላቸው። ስለሆነም አመልካቾች የሌላቦታ ነዋሪ መሆናቸው ብቻውን በሕገመንግስቱአንቀፅ19 ንዑስአንቀፅ6 የተረጋገጠላቸው በዋስ የመልቀቅ መብት እንዲነፈግ የማድረግ እና በሕገመንግስቱአንቀፅ 25 የተደነገገውን በሕግፊት እኩል የመሆን ናእኩል የሕግ ጥበቃ የማግኘት መብትን የሚጥስ በመሆኑ
ተቀባይነት ያለው ምክንያት አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 233903


ይግባኝ የማቅረቢያው የመጨረሻ
ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይያረፈ ከሆነ በማግስቱ ይግባኙን ማቅረብ ይቻላል የሰ/መ/ቁ 220962



12 last posts shown.