ከሰው ፊት ቆሞ ደእዋ ሲያደርግ ዱንያ የተረፈው የሚመስለው ወንድማችን ጉዳዩን ስሰማ በጣም ነው ያዘንኩት ።
በዚህ አጋጣሚ አንድን ሰው ለመርዳት ከፈለጋችሁ ቀጥታ እራሱን ብቻ አናግሩ እከሌ ለሚባለው ኡስታዝ አደርሳለሁ ብለው የሚቀበሉና በሰው ስም የሚነግዱ ሰዎችም ስላሉ ተጠንቀቁ።
የነሱ ጀመኣ ብቻ ስላልሆንክ የነሱ ግሩፕ ውስጥ ያልሆንከው ለዱንያ ብለህ እንደሆነ ለሚያስቡ እርጥቦችም የዚህ ሰው መቸገር ትልቅ ማሳያ ነው።
ኡስታዝ ነኝ አምጣ እያሉ የሚቀፍሉ የወረደ የዱንያ ጥማት ልክፍት ተጠቂ ፤በዲን ስም የሚነግዱ አንድ መስጂድ ከደረሱ ምን ያህል አጅር ከአላህ አገኛለሁ ሳይሆን ስንት ልቀበል የሚሉ የዱንያ ባሪያዎች እንዳሉት ሁሉ እየተራበና እየተጠማ እየተቸገረ ለአሏህ ዲን የሚለፋም አለና በደንብ
እየለየን እውነተኛው እየተቸገረ አስመሳዩ ገንዘብ
የሚያካብትበትን ሁኔታ ልናስቆም ይገባል ።
አደራ አደራ የምለው ነገር ቢኖር ሰዎችን ማወቅ ዛሬ ከባድ ሆኗልና ማንንም ሰው አብሮ ከሱ ጋር ሲሄድ አይቻለሁ በማለት በሌላ ሰው በኩል ገንዘብ አትላኩ።
በሰው ስም የሰዎችን ገንዘብ የምትበሉ ደግሞ አላህ በረካ የተባለ ነገር ይንሳችሁ (አሚን በሉ)
https://t.me/Menhajadama