عقيدة السلف الصالح ~{{{ ሰለፊያ}}


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


«ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን፡፡ ከአንተ ዘንድ የኾነን ችሮታም ለኛ ስጠን፡፡ አንተ በጣም ለጋስ ነህና፡፡»
【አል ዒምራን ፡8】
ስህተቴን አይቶ ለነገረኝ ያአላህ እዘነት በሱ ላይ ይሁን
👇👇
@Abdushikurbot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter








Forward from: ከ ቀደምቶች ንግግር🔊
የረመዷንን ሌቦች ተጠንቀቁ!
|•|
አንደኛው ሌባ፦
ቴሌቭዥን ለሥጋም ሆነ ለመንፈስ ከፍታ አጋዥ ካልሆኑ ነገራቶች ውስጥ አንዱ ነው። በተለይ ደሞ የረመዷን ሙሰልሰላቶችን እና አዘናጊ ድራማዎችን ተጠንቀቁ፤ የረመዷን ዉድ ጊዜያት ለዉድ ነገሮች መዋል አለባቸው፡፡

ሁለተኛው ሌባ
ስልክ ብዙ ማውራት ለብዙ ስህተት ያጋልጣል፣ ትርፍ ንግግር ወደ ሀሜትና ያልታሰቡ ወንጀሎች ይመራል፤ለተሻለ ምንዳ በረመዷን በንግግር ጭምር ቁጥብ መሆን ያስፈልጋል፡፡

ሦስተኛ ሌባ፦
ወጣ ገባ ማብዛት/መዞር፡፡ በረመዷን ከመስጊድ እና ከቤት የበለጠ ማረፊያ የለም፡፡ ወደ ከተማም ይሁን ወደ ገበያ ያለበቂ ምክንያት ወጣገባ ማብዛት ዐይንንም ሆነ ጆሮን ያልሆነ ነገር ይጥላል፡፡ፆምን ይሰርቃል፤ ምንዳዉንም ያጓድላል፡፡ 

አራተኛ ሌባ፦
ማምሸት፡ ያለምክንያት ማምሸት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለዉም፡፡ የረመዷን ምሽቶች ምርጥና ዉብ ናቸው፡፡ በቁርኣን፣ ዚክር እና በተለያዩ ዒባዳዎች መዋብ አለባቸው፡፡

አምስተኛ ሌባ፦
ኩሽና:በተለይ ለሴቶች፡፡ሙሉዉን ረመዷን ማዕድ ቤት የሚያሳልፉ ቁርኣንን፣ ሶላትና ዚክርን የረሱ ብዙ ናቸው፡፡ ረመዷን የፆም ወር ነው፡፡ ትልቁን ትኩረት ለሆድ መስጠት ዓላማዉን መሳት ነው የሚሆነው፡፡

ስድስተኛው ሌባ፦
ሶሻል ሚዲያ፡፡ ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ችግር ሆኗል፡፡በቤትም ሆነ በመስጊድ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ነው፡፡ በዚህም ከዚክር፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ እንዳንጠቀም ሆነናል፡፡ እንጠንቀቅ፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan


Forward from: Abdu shikur abu fewzan
ብዙ ጊዚያትን ከሶላት እርቆ፤ ረመዷን ሲገባ ወደ መስጅድ የሚመላለስ ሰዉ  ስታዩ፤ በፈገግታ ተቀበሉት ለምን መጣህ በሚመስል መልኩ አትቀበሉት፤በወንድማችሁ ላይ የሸይጧን አጋዥ አትሁኑ።

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur


🎉 እንኳን ለ1446ኛው የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ

የረመዿን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ቅዳሜ የካቲት 22, 2017 E.C. (March 1, 2025 G.C.) የረመዷን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።


አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!
ረመዷን ሙባረክ! 🌙✨


አልሐምዱ ሊላህ! ሸዕባን አጠናቀናል። ቅዳሜ ረመዷን 1 ነው።
=


ደብቁኝ ትያለሽ
ግጥም
🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur


Forward from: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
〰ምናልባት ነገ ? 🌀

🌙




Forward from: ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
ረሡል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ፦
እናተ  የሴቶች ስብስቦች ሆይ ሶደቃ ስጡ እኔ ብዙወቻችሁ የሳት ሁናችሁ አይቻችኋለሁኝ አሉ።

በምንድን  ነው ብዙ ሴቶች የሳት የሆኑት ብለን ጠየቅን  ይላሉ?
ከዛም ረሡል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም  እንድህ አሉን፦
እርግማን ታበዛላችሁ ባላችሁ የዋለላችሁን ውለታ ትክዳላችሁ  አሉ።
📚ሷሒሕ አል-ቡኻሪ (1452)

✍️...ትርጉም በሙከራ!

📌ነዓም  በዘመናችን ሀቂቃ አላህ ያዘነልን ሴቶች ስንቀር
ምላሳችን ከሰይፍ ፣ከጩቤ ይበልጣል 
ምላሳችን የሰውን ቀልብ ይሰብራል ምላሳችን እንዴ እሾህ ይወጋል!!

በተለይ ባል መልካም እየዋለ አንድ ቀን ሳይመቻችለት ያንን  መልካም ነገር ካላደረገ በፊት ያደረገውን ነገር ሁሉ ገደል የሚሰዱ ካንተ ምንም  መልካም  አላየሁም ምንም አድርገህልኝ አታቅም ብለው የሚክዱ በጣም ብዙ ሴቶች አሉ
እሱን መራገም እንደዚህ ሁን ከዛ ወከዛ
እያሉ የእርግማን መአት የሚያበዙ ብዙ ሴቶች አሉ።
ነሰዓሉላህ  አሰላመተ ወልዓፊያ!!
እህቶች ምላሳችን እንጠንቀቅ ካልተጠነቀቅን  ጀሀነብ ይከተናል!!

📌ይቀላቀሉ፦http://t.me/tdarna_islam


Forward from: الشباب السلفيين
ከምቀኝነት እንውጣ!!
-------------------------
በበታችነት ስሜት ከምትሰቃይ፤
          ለምን መክሊት አትፈልግም፡
ሌሎች ላይ ሴራ ከማሰብ፤
          እርክሰት ጋር ከምታዘግም፡

እኔም የራሴን ከያዝኩ፤
          አንተም የራስህ ካለህ፡
እስኪ ቆመህ ተጠየቅ!?
     ምን ሊጠቅም ትመቀኛለህ??

ከዱንያ ስቃዩ በላይ፤
      ይከፋልና የነገው ጣጣ፡
እባካችን እንተሳሰብ፤
         ከምቀኝነት እንውጣ፡

➥እንደ ምቀኝነት ራስን አቃጥሎ የሚጨርስ መርዛማ በሽታ የለም።
እየተቀባህ የማያወዛ
እየሸጥክ ፈፅሞ አትገዛም
ምቀኝነት ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ አደገኛ ቫይረስ ይመስለኛል...ብቻ ሁላችንም እንከልከል ሐቂቃ!!

◎قال الشيخ صالح آل الشيخ حفظه الله

لا تحسد من هو أحفظ منك
أو أعلم منك
أو أنفع للعباد منك

ሷሊህ አሉ-ሸይኽ ይህን ይላሉ፦

ከአንተ የተሻለ ለፊዝ፣
ከአንተ የተሻለ አዋቂ፣
ከአንተ የተሻለ ለዑማው ጠቀሚ የሆነን ሰው አትመቀኝ።

بل افرح أن يقوم قائم بحق الله عز وجل وحق العباد

በል እንደውም በአላህ ሐቅ ላይና በባሮቹ ሐቅ ላይ በመቆሙ ልትደሰት ነው የሚገባው ይላሉ።

الطريق إلى النبوغ العلمي ص:115 رقم 537
.....✍️ኑረዲን አል-ዓረብ

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi








Forward from: الشباب السلفيين
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
👉አይረዱህም ውሸታቸውን ነው!!

وكأنهم يردون مساعدتك
ولكنهم فى الحقيقة أبدا لايفعلون

ስታያቸው አዝነው ሊረዱህ እንደሚፈልጉ ይመስሉሀል በተግባር ግን መቼም አያደርጉትም።

....ኑር.....

t.me/nuredinal_arebi


Forward from: الشباب السلفيين
🔹ሀብታም ባል ለምትፈልገው ላክላት....

«ሀብታም ፈልጊ»

አግኝቼ ባልሽቀረቀር
ሞልቶልኝ ኪሴ ባይወዛም፡
የቁስ ሀብት ምን ቢትረፈረፍ
የልቤን እዝነት አይገዛም፡

.....አውቃለሁ.....

አዕምሮሽ ጥያቄ አስልቶ፤
ለምላሽ ክብሪት ይጭራል፡
ታውቂያለሽ ከሳቅሽ ይልቅ፤
ሐዘኔ እጂጉን ያምራል...!!

ጎደሎ ከሰው ባይጠፋም፤
ቢያጋጥም የኑሮ ስንኩል፡
ችግሬ ነውር አይጠራም፤
ቢለካ ከፅድቅሽ እኩል፡

ቁስሌን አትንኪው እንጂ
ተይ እንጂ እንተሳሰብ፡
አንድ ወንዝ ያፈራን ልጆች
አይደለን እንደ ቤተሰብ!?

.....ሐቁን ግን ልንገርሽ....!?

የተፈጠርኩት ከአፈር ነው፤
ለአፈር ክብር ይሰጣል፡
አልጋዬ መሬት ቢሆንም
ገላዬ በአፈር ያጌጣል፡
እንቅልፍሽ ምቾት ቢኖረው
ህልሙ ግን የኔ ይበልጣል፡

የተናገርሽውን ንግግር፤
መቼም እንዳትዘነጊ፡
ለኔ ድህነት ሀብት ነው፤
አንች ግን ሐብታም ፈልጊ...!!

...... ሰላም ሁኝ....

በኑረዲን አል አረብ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi


Forward from: Abdu shikur abu fewzan
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የአደባባይ ዳእዋ

በኡስታዝ አቡል አባስ

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur


"هذا الدعاء إذا استكثر منه الإنسان يرى والله أثره على نفسه في حياته."

الشيخ :عبد الرزاق البدر حفظه الله.

https://t.me/Umu_fewzan_4u


Forward from: Abdu shikur abu fewzan
🎉መልካም ዜና! ለአሶሳ ከተማ ሙስሊሞች
~
ለ ሶስት ቀናት ብቻ የሚቆይ ልዩ  የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅተናል!

🕌የሚሰጥበት ቦታ ሰለፊያ መስጅድ
🗓 ቀናት፦  ጁሙዓ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ
⏰ ሰዓት፦ከመግሪብ -ኢሻእ 
👤 አስተማሪ፦አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

📚 የኪታብ ስም፦ ለይሰል_ጘሪቡ
(قصيدة ليس الغريب)
🖋 የ ኪታቡ አዘጋጁ፦ ኢማም ዐሊይ ብኑል ሑሰይን ረሂመሁሏህ

የግጥሟን ፒዲኤፍ ለማግኘት👇
https://t.me/abu_fewzan_abdu_shikur/5837

20 last posts shown.