አቡ መርየም አዳማ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


هدفنا الذب عن السنة.....................
ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች የሚሰራጭበት ቻናል ነው። በተጨማሪም ተውሂድንና ሽርክን እንዲሁም ሱናንና ቢድአን እንዲሁም የቢድአ ሰዎችን ለሰዎች በፁሁፍና በሙሀደራ መልክ ግልፅ ማድረግ
https://telegram.me/abumerymadama

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Muhammed Mekonn
የተግባቡ ስኬታማ ባለ ትዳሮች
➶ 👉 ✅

ባል፦ «ውዴ በተቻለ መጠን እናቴን ለመምሰል ሞክሪ እሺ!»

ሚስት፦ «እሺ የኔ ባል እሞክራለሁ»

ባል፦ «ጎበዝ! ሞክሪ እሺ ‛የኔ እናት ማለት አስተዋይ፣ ቁጥብ፣ ብልህ፣ ሰውነቷ ለአጅነብይ የማይታይ፣ ባሏ ከሁሉም በላይ የሚወዳት...

ሚስት፦ «እ.... ምን!?»

ባል፦ አዎ! የኔ እናት ማለት በጀነት የተመሰከረላቸው ሶሃቦች የሚያከብሯት፣ ቅንጣት የማይሰወረው ሀያሉ ጌታ አላህ ንፅህናዋን በማይሻረው ቃሉ ቁርኣን የመሰከረላት፣ ለአለማት እዝነት አድርጎ የላካቸው ነብይ በጣም የሚወዷት፣ አባቷ ከኡማው ሁሉ በላይ ኢማን ያላቸው እውነተኛ ልጅ የሆነች፣ ሙስሊሞች በጠቅላላ እናቴ የሚሏት...»

ሚስት፦ «አሃ የአቡበክርን ልጅ እና የነብያችንን ﷺ ውድ ሚስት የሆነችውን አኢሻን መለትህ ነው!»

ባል፦ «አይዋ ትክክል! አይ የኔ...»

ሚስት፦ «እሷን መምሰል ማለትኮ ጀነትን መውረስ ነው። ታላቅ ክብርና እድል ነው። ያረብ አላህ ይግጠመን! ውዴ በዱዓህ አግዘኝ!»

ባል፦ «ኢንሻአላህ በዱዓ እንበረታለን!

ሚስት፦ «ግን...»

ባል፦ ግን ምን እ?

ሚስት፦ «አንተም ከፍጥረታት ሁሉ የላቁት ባሏ ያዘዙትን በመታዘዝ እውነተኛው አባቷ የተገበረውን በመስራት በርታልኝ! ያኔ እኔም እንደ አዒሻ ለመሆን ያግዘኛል።»

ባል፦ «በዱዓ አግዥኝ»

📝 አቡ ዒምራን

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

---------------⫷⫸-----------------
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
እህቴ ሆይ! እምነትሽ ያዘዘሽን ሒጃብ በአግባቡ ለብሰሽ አክብሪው
———
ሒጃብን ሸሪዓው በሚያዘው መልኩ ዘውትር ለብሶ ማክበር ነው እንጂ የሒጃብ ቀን የሚባል የተለየ ቀን የለውም!!
"
ሒጃብ ማለት እስልምና በሴት ልጅ ግዴታ ያደረገባት ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበት ሰፊ ልብስ እንጂ በአመት አንዴ አናቷ ላይ ብጣሽ ሻሽ ጠምጥማ ቀን ለይታ የምታከብረው ነገር አይደለም!!
"
ሒጃብ ማለት ሴት ልጅ እዚህች አለም ላይ ከተለያዩ ባለጌዎች ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበትና የተለያዩ ጨዋ ወንዶች ደግሞ እርቃኗ በመሄዷ እንዳይፈተኑ የምታደርግበት ከፈጣሪዋ አላህ ዘንድ የታዘዘችው በህይወት ዘመኗ ሁሉ የማትለየው ልብስ ነው።
"
ሒጃብ ማለት ሸይጧን እና የእስልምና ጠላቶች እንደሚፈልጉት የምትለብሰው ልብስ ሳይሆን የፈጠራት ፈጣሪዋ እንዳዘዛት ዘውትር የምትለብሰው ወደ ፈጣሪዋም የምትቃረብበት የፅድቅ ልብስ ነው።
"
ሒጃብሽን ዘውትር ሸሪዓው በሚፈልገው መልኩ በመልበስ አክብሪው!! የባለጌዎችና የጅሎች መዝናኛ የዐይን ማረፊያ አትሁኚ።
"
ሒጃብ ማለት ፈጣሪሽ እንድትለብሺው ከእናቶችሽ ከነ ዓኢሻ፣ ከነ ኸዲጃ፣ እንዲሁም ከታላቁ ነቢይ ልጅ ከነ ፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሁም) እኩል እንዲህ በማለት ያዘዘሽ የፈጣሪ ትእዛዝ ነው:-

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ

«አንተ ነቢይ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አል-አህዛብ 59

የአላህን ንግግር ልብ በይ! እህቴ:- «ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አለ፣ አንቺ ጨዋ ሴት ከሆንሽና በባለጌዎች እንዳትደፈሪ፣ እንዳትለከፊ ከፈለግሽ በስርኣት አላህ ባዘዘሽ መልኩ መልበስ ነው፣ በተቃራኒው ደግሞ ሸሪዓው ከሚፈልገው የሒጃብ አይነት ውጪ ከሆንሽ ራስሽን ለባለጌዎችና ለብልግና እያመቻቸሽ ነው ማለት ነው።
🔸የኢስላም ጠላቶች ይህን ጠንቅቀው ያውቁታል። ለዚያም ነው ሙስሊም ሴቶችን ለባለጌ ወንዶች አጋልጠው ለመስጠት በየ ተቋሙና አቅማቸው በቻለው ሁሉ በት/ት ተቋማትና በመንግስት ተቋማት የሙስሊም ሴቶችን ስርኣት ያለው እምነታቸው የሚያዛቸውን አይነት ሒጃብ እንዳይለብሱ የሚጥሩት። ሙስሊም እህቴን ሒጃቧን ካስወለቋት ለዲኗ ግዴለሽ እንድትሆን ያደርጓታል፣ ምን ይህ ብቻ በመስተፋቅርና በተለያየ መንገድ እምነቷንም የሚያስቀይሯትን ተኩላ ከሀዲ ወንዶችን ይልኩባታል።
"
ሒጃብሽን አላህ ባዘዘሽ መልኩ ከለበሺው ነገ በአኼራ ሰውነትሽ እሳት እንዳይነካውም ይከላከልልሻል። ሒጃብሽ እምነትሽ ነው፣ ሒጃብሽ ስብእናሽ ነው፣ ሒጃብሽ ማንነትሽ ነው!! ሒጃብሽን አውልቀሽ ት/ት የለም!፣ ማንነትሽን ክብርሽን ሽጠሽ ዱኒያዊ ጥቅም ጥንቅር ብሎ ይቅር እንጂ በሒጃብሽ ተደራደርሽ ማለት በእምነትሽ መደራደር እንደሆነ ጠንቅቀሽ እወቂው!! ጥላቻቸው ከእምነትሽ እንጂ ከጨርቁ አይደለም!!።
"
የሒጃብ ቀን ምናም እያሉ ሚያጃጅሉሽን ትተሽ ፈጣሪሽ ከሰባት ሰማይ በላይ ያዘዘሽን ትእዛዝ አክብረሽ ዘውትር አላህ በሚፈልገው መልኩ ሒጃብሽን ጠብቂ!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: Muhammed Mekonn
ከብዙ ጥረቶች በኋላ ተሳካ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
አ ል ሃ ም ዱ ሊ ላ ህ

🔎 ከዚህ በፊት በሸይኻችን አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸውና በሚከተለው ርዕስ ተለቆ ነበር፦

🏝 الْكَلِمَاتُ النَّافِعَةُ الذَّهَبِيَّة في بَيَانِ أُصُوْلِ وَمَنْهَجِ الدَّعْوَةِ السَّلَفِيَّة

ሸይኻችን ተጨማሪ አስፈላጊ ነጥቦችን በመጨማመር እና ሙሉ ሀረካውን በማስቀመጥ አጠናቀውት ከዛም በሁለት ሙጀለድ ተዘጋጅቶ ቀረበ

👌 𝙥𝙙𝙛 ❴የሁለቱም መጀለድ 𝕤𝕠𝕗𝕥 𝕔𝕠𝕡𝕪❵ በቅርቡ ይለቀቃል። አላህ ከፈቀደ ደግሞ ታትሞ በኪታብ መልኩ በእጃችን የምንይዘው ያድርገን!

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/11913


Репост из: አቡ አዒሻ العلم نور
ቢኢዝኒላህ ነገ ሲነጋ ጉዞ ወደ በሊኖ 🛺🛺

ታላቅ የዳዕዋ ጅሓድ ኑ ነገ ሁላችነም በሊኖ እንሂድ 🛺🛺

በመርሳ  በሀራ   በሀሮ   በድሬሮቃ  ሰዶማ ደንደካሎ  በቀሮራና ግረም   ለምትገገኙ  ሙስሊም ማህበረሰብ  የተዘጋጀውን  ትልቅ የዳዕዋ ዝግጅት  ታድማችሗል   ጥሪን ማክበር ደግሞ  ኢስላማዊ ግደታችን ነው

በሊኖ ማለት በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ (023)ቀበሌ ቀጅማ ውስጥ የሚገኝ  ሜዳማ የገጠር ድቅድቅ መንደር ነው  ።

አስታውሱ እንዳትረሱ የዳእዋው ቀን
🗓ጥር/ 19/5/2017 / (ነገ) ሰኞ ነው

ይህ ታላቅና ደማቅ  የዳዕዋ  ፕሮግራም  ተዘጋጅቶላችሁ  እንኳን  መቅርትና  ማርፈድ ራሱ  ያስነድማል

➖በተባለው ቀንና ቦታ ላይ በመገኘት የዳዕዋው ተካፋይ እንድትሆኑ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
 
🪑የዚህ ደማቅ ዳዕዋ ተጋባዥ እንግዶቻችነን እነሆ ብለናል↩️

1.🎙ሸይኽ    ሙሀመድ ሀያት ከሀራ
2.🎙ሸይኽ    ሁሴን አባስ   ከወርቄ
3 🎙 ሸይኽ   ሁሴን  ከረም  ከሀራ
4.🎙ሸይኽ    ሰይድ ሙሀመድ ከሀራ
5.🎙ሸይኽ    ሙሀመድ  ሲራጅ  ከሀሮ
6.🎙ሸይኽ    ሙሀመድ ሰይድ ከድሬሮቃ
7.🎙ኡስታዝ  መሀመድ  ሰልማን  ከሀራ
8.🎙ኡስታዝ  አብዲረህማን  ከመርሳ

🪑ኢንሻ አሏህ በቦታው ላይ ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይኖሩናል  እኛ እሚጠበቅብን በተባለው ሰአትና ወቅት ከቦታ ላይ ተገኝተን  ደዕዋውን
መካፈል ብቻ ነው

የተለያዩ  ጎጅ ባሀሎች በውስጡ እየተንሸራሸረ
የረበሸው ሰው የጥያቄና መልስ ፕሮግራም ስለሚኖረን በአካል ተገኝቶ ጠይቆ መረዳት ይችላል ኢንሻአሏህ

🌎በ ውጭ አገር ያላችሁ በተለይ ከጭረቲና በቁርቁራ ወንዝ መካከል ተወልዳችሁ
ያደጋችሁ  ውድ የሀገሬ ልጆች እናት አባቶቻችሁን

በማነሳሳት ወደ ውቢቷ ሀገር በሊኖ በመሄድ  የዳዕዋው ተካፋይ  እንድሆኑ እናንተም  ሰበብ ሁኑ

🕒 ኢንሻ አሏህ ዳዕዋው በኢትዮ አቆጣጠር 3:00 ይጀመራል በተባለው ቀንና ወቅት በጧት በመገኘት የአጅሩ ተጠቃሚ ና ተቋዳሽ ይሁኑ

✍የዝግጅቱ አዳሚና አስተባባሪ የበሊኖ ሰለፍያ ወጣቶች በመተባር
ከከተማ ወደ ገጠር ኑ የተውሂድ ችግኝን እንትከል ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
የወንበደ የወጨቃ የቀጅማ የጭሳ የግረም የሰዶማ የበሊኖ የቀሰማ ያረባል  እንድሁም በዙሪያዋ ያላችህ  እህትና ወንድሞች ኑኑኑኑ  የዳዕዋ ክትባት አለ ተብላችኋል


https://t.me/hussenhas


Репост из: Muhammed Mekonn
አሳፋሪዎች ናቸው!

የዲላ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እንኳን ኒቃብ ጥቁር ማስክ መልበስ አይቻልም እያሉ ነው።

👉 እኔ ያልገባኝ ኒቃቡንስ የደህንነት ስጋት ነው አሉ! ማስኩስ? ወይስ የነሱ ደህንነት የሚደፈርሰው የሴት ልጅ ከንፈር እና ጥርስ ሲሸፈን ነው? ኧረ ሸም ነው! በግልፅ መሰይጠን አይሆንባቸውም?

👌 ነቃብ አውልቂ ስትባል አይሆንም ብላ በእምነቷ ለመጣባት እንቅፋት በዱዓ እንደመበርታት ኒቃቧን አውልቃ በማስክ የምትቀይር እንደት ታሳዝናለች!? በማስክም ከለከሉ ቀጥለው ፀጉሯንም አትሸፍኚው ማለታቸው አይቀርም። ምክንያት አሁን ተሸንፋለችና ቀጣይም እና መሸነፏን ያልማሉ።

👉 ዩኒቨርስቲው ❝የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው❞ በማለት የገለፀው ነጭ ውሸት ነው። ለመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድረው የዲላ ዩኒቨርቲን ብቻ ነውን? ኒቃብ የሚፈቀድባቸው ግቢዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ ናቸውን? ሲዋሹ ትዝብትን ከግምት አያስገቡም!

🔎 ለማንኛውም ኒቃብ ማለት መልክ የሰውነት አካል ማለት ነው። የሰውነት አካል ደግሞ አይጣልም።

https://t.me/AbuImranAselefy/9701


Репост из: Muhammed Mekonn
በዩኒቨርስቲ ካሉ መጥፎ ልማዶች መካከል፦

➧ እንደሚታወቀው ዩኒቨርስቲ ማለት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚመጣበት የስልጣኔ መስመሩ የሚገኝበት ከሌላው በተሻለ መልኩ ሀገር ለመረከብ ቤተሰብ ለመምራት ወዘተ የተሻለ መንገዶች የሚቀመሩበት መድረክ ነው ተብሎ ይታሰባል።
➜ ከመሆኑም ጋር የሰለጠኑ ሀገር ለመረከብም ሆነ ለየትኛውም ሀላፊነት ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎች እንዲመመረቁ ሁሉ በሌላ በኩልም ከመሰልጠን ይልቅ መሰይጠን፣ ከመትጋት ይልቅ መተኛት፣ ከመለወጥ ይለቅ መቀወጥ፣ ከመማር ይልቅ መሽቀርቀር... የሚያምራቸው በርካቶች ናቸው።
➧ እዚህ ስራ ፈቶች ትምህርቱን ትተዋልና የሚቀላቸው የተለያዩ ፈሳዶችን ወደተማሪዎች ማምጣት ነው። በተለይም ተመራቂ ተማሪዎችን ወደተለያዩ ጥፋቶች ለማስገባት የሚጥሩ የሸይጧን አገልጋዮች በርካታ ናቸው። Half life, GC birth day... እያሉ በርካታ ኮተቶችን ወደተማሪዎች ያስጠጋሉ።
🔎 አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! አንተ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! እነዚህ ስራ ፈቶች ወደፈበረኳቸው ኮተቶች ዘወር እንዳትሉ እናንተን አይመለከትም። እናንተኮ የላቀ አላማ ያላችሁ የዘላለሙን ህይወት ለመውረስ ጉዞ የጀመራችሁ የሀያሉ አላህ ባሮች ናችሁ።

➜ በተለይ ደግሞ አብዛኛው ሙስሊም ተማሪ ጭምር የሚሳተፍበት ተመራቂዎች ከመመረቃቸው በፊት አብረው ለአመታት ከቆዩዋቸው ጓደኞቻቸው ጋር እንዲሁም ከመምህራን ጋር በመሆን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ሴትም ወንድም በተቀላቀለበት መልክ በአንድ ቦታ በማሳለፍ የሚከውኑት ዝግጅት አለ። ይህ ድርጊት በሚከተሉት ሰበቦች አይፈቀድም።
1ኛ ያለምንም አስቀዳጅ ምክንያት ኢኽቲላጥ አለበት። ❴ካፊር ሴቶችም ወንዶችም ሙስሊም ሴቶችም ወንዶች ያለምንም ግርዶሽ ይደባለቃሉ❵
2ኛ አብዛኞቹ እንደሚያደርጉት ሴቶችም ወንዶችም ዝግጅት ያቀርባሉ። ❨ግጥም፣ ምስጋና፣ ጭውውት ወዘተ❩ ሴት ልጅ ወንዶች ባሉበት ማንኛውም ነገር ማቅረብ አትችልም። ❮{ስለሙስሊሟ እያወራሁ እንደሆነ ተገንዘቡ}❯
3ኛ በካሜራ የታጀበ የፎቶ ትርዒት ሊያደርጉት ይችላሉና በቀጥታ ከሸሪዓ ጋር በሚቃረን ተግባር ተሳታፊ ለማድረግ ያቀርባል።
4ኛ ከባድ ፈተና ይፈጠራል።
   🔎 ተማሪዎቹ ወደ ፕሮግራሙ ሲሄዱ ለምርቃት ያሰፉትን ሙሉ ልብስ (ሱፍ) በመልበስ ነው። ሌላም የሚዋቡበት ነገር ካለ ለመፈፀም ወደኋላ አይሉም። በዚህ መልኩ ሙሽራ ከመሰለ በኋላ ከሴቶች ፊት ይቀርባል። እሷም አላህን ካልፈራች ሽቅርቅር ብላ ትመጣለች። በየመሃሉ እየተያዩ ፕሮግራሙ ይቀጥላል። በሱፉ ገጭ ብሎ ፕሮግራም ሊያቀርብ ከፊቷ ገጭ ይላል። ልብ ይባል 98% የሚሆነው ተማሪ ያላገባ (ማግባት የሚፈልግ ነው) በዚህ ሁኔታ ይቀጥላሉ። ታዲያ ሴቶች አይፈተኑምን? በጣም ይፈተናልንጅ! ወንዱም በተመሳሳይ መፈተኑ አይቀርም። በዚህ ላይ የሸይጧን ሴራ እና የነፍስያ ድክመት ሲደመርበት የሚፈጠረውን አስቡት!

➧ በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የምትገኙ ሙስሊም ወንድም እህቶች ሆይ! በዚህ አይነት ዝግጅት ላይ አትሳተፉ! መምህሮቻችንን እናመስግን ካሉ በአግባቡ ይሁን እንጂ በምስጋና ስም በሱፍ ሽክ ብሎ በመገኘት ለምስጋና ነው ብሎ መፎገር ሸም ነው። በዚህ አይነት ቀውጢ ካላመሰገንከኝ የሚልህ ካለ የራሱ ጉዳይ ዋና ያንተ የእምነት ጥንካሬ ነው። አንተ ዛሬን የምትኖር ነገን የማታውቅ ጭፍን አይደለህም። በዚህ ሀገር ዘርተህ በነገው ዘውታሪ ህይወት ምርትህን ትወስዳለህና ተጠንቀቅ!

✅ ነገሮችን ቀለል አታድርጉ! ለሸይጧን በር አትክፈት ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ለትንሽ ደቂቃዎች ነው ምን ችግር አለው አይባልም። በሱፍ ሽክ ብለህ እህትህን አትፈትናት! አንድ ልታገባ 20 መፈተን ምን ይሉታል። በእርግጠኝነት ሴቶች ባይኖሩ እንደሙሽራ መዋቡ ትኩረት አያገኝም ነበር ግን እነሱን ለመፈተን ሽር ማለት የልብ መታመምን ያሳያል። አንቺስ ብትሆኚ እህቶ እውነት ቦታዬ ነው ብለሽ አምነሽበት ነውን? አንቺም ተውበሽ ፊትሽን ቀይረሽ በጠባብ ልብሶች ተወጣጥረሽ ከሆነ የምትሄጅው መጨረሻው ይከፋል። ኒቃቢስቷማ ለምን ትሄድ? እራሷን ለመፈተን? አዎ ጥናት ያላንገላታው በስንፍና የተከነባ ከልቡ ውበት ይልቅ የቆዳው ውበት በሚያሳስበው ሚስኪን በሱፍና በመሳሰሉት ፏ ስላለ በሱ ለመፈተን ትሄድ? በፍፁም ቦታሽ አይደለም አዎ በፍፁም።

🏝 እንደጥቅል እኛ ሙስሊሞች በዘፈቀደ የምንቀሳቀስ አይደለንም እያንዳንዱ ተግባራችን ሸሪዓችንን የማይቃረን መሆን አለበት። ከምንም በላይ ጥንቃቄ በሚያስፈልግበት ሁኔታ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል።

🕌 አቅሷ የወራቤ ዩንቨርሲቲ ሰለፊይ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓህ

🕌 مسجدالأقصى جماعة السلفيين في جامعة ورابي

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏖
https://t.me/wru_selefy_official_chanel

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~ 𝕘𝕣𝕠𝕦𝕡
🏝
https://t.me/Werabeuniversitymuslimstudents

አስተያየት ለመስጠት
➴➘➷➴➘➷
https://t.me/WRU_Student_Bot


Репост из: አቡ ጁለይቢብ
👉 ኢብኑ ሙነወር ከዚህ በፊት ቻናሉ ላይ የፃፈውን ከላይ 👆 ፎቶው ላይ ታገኙታላችሁ👇
https://t.me/YusufAsselafy/4272?single

አሏህ ከመገለባበጥ ይጠብቀን

➡️እኛ አሁንም የምንለው ለኢብኑ ሙነወር  ድሮ አንተ ሰትል ወደነበረው አቋም ተመለስ ነው።

✍Abu yasir https://t.me/YusufAsselafy


Репост из: Bahiru Teka
👉  የሙመይዕና የደካማ ሰለፍይ ልዩነት

በአሁኑ ጊዜ በሚያሳዝን መልኩ ድሮ ከኢኽዋን ከተብሊግና ከሱፍይ ሚንሀጅ አራማጆች ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ ሲተናነቁ ለተውሂድና ለሱና ሲሉ ከወንድምና እህታቸው የተለያዩ የነበሩ የወላእና በራእ ድንበር እንዳይደፈር ዘብ በመቆም ውድ ዋጋ በመክፈል ወጣቱ የተውሂድና የሱና ባንዲራ ከፍ እንዲያደርግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ከቻሉ በአውቶብስ ካልቻሉ በእግራቸው ኑ ወደተባሉበት በመሄድ ከውስጥ እንደ ነበልባል እየነደደ በሚወጣ የቁጭት ስሜት ህዝቡ የተዘፈቀበትን የሽርክ ረመጥ እያወገዙ የተውሂድ ዘር ሲዘሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው ።
ዛሬ ያኔ ባላወቅንበትና ባልበሰልንበት ጊዜ ነበር አሁን አውቀናል በስለናል የሰለፍያ ዳዕዋ ማለት እንደሱ አይደለም ። ማጠንከር አያስፈልግም ዳዕዋ በማለስለስ ነው የሚደረገው የሰው ስም መጥራት አያስፈልግም ይለያያል ሰዎችን ያርቃል የሚፈለገው አንድነት ነው የሚሉት ።
በምን ላይ ? ሲባሉ
አይታወቅም ብቻ ሰዎችን አታባሩ በሚል ወደኀላ ተመልሰው ለሌላው ወደኀላ መመለስና ለዘብተኛ መሆን ጥብቅና በመቆም ይህን አልቀበልም ያለና ሌላውም እንዳይቀበል ያደረገን ወሰን አላፊ ሂክማ የሌለው መስለሃ የማያውቅ በማለት ከዚህ አልፎም ሀዳዲ እያሉ ስም በማጥፋት ሰው ትክክለኛው የሰለፍያ ዳዕዋ እንዳይረዳ ውዥንብር ውስጥ እንዲገባ በማድረግ አሳፋሪና አስነዋሪ ድርጊት ሲፈፅሙ የሚታዩት ። ይህ ድርጊት ብዙ ሙሪዶች እንዲያገኙ አድርጓቸዋል ። አብዛኛዎች ዲናቸውን በእውቀት ሳይሆን በሰው ላይ በመንጠልጠል የያዙ ናቸው ። ስለሆነም የያዙት ያ ሰው ወደ ዞረበት ነው የሚያዞሩት ። ከእገሌ የበለጠ አንተ ታውቃለህ ወይ ነው ። የዚህ አይነቱ አካሄድ አብዛኞችን ሰለፍይነታቸው ደካማ እንዲሆን አድርጓል ። እነዚህ አካላት በዛው ከቀጠሉ ሰለፍይነታቸው ሟምቶ ወደ ሙመዪዕነት መሸጋገራቸው አይቀርም ። ነገር ግን በሙመይዕና በደካማ ሰለፍይነት መካከል ያለው ልዩነት ለብዙዎች ግልፅ ባለመሆኑ በወንድሞች መካከል አለመግባባትና ንትርክ እየተፈጠረ ስለሆነ በአላህ ፈቃድ  ልዩነቱን ላስቀምጥ
ወደድኩኝ ።

     🔹 ሙመይዕ ማለት

ከነበረበት አቋም በመንሸራተት ሰለፍያ ሚንሃጅ ሁሉንም የሚያቅፍ ሰፊ ሚንሃጅ ነው በማለት በሰለፎች የማይታወቅ ቀመር ( ቃዒዳ ) በማምጣት ሰዎች ኢኽዋኖችም ሆነ ተብሊጎች ከጠማማ አንጃዎች መሆናቸውን እንዲጠራጠሩ የሚያደርጉ ፣ ማግራራት የሚል አዲስ ሚንሀጅ የሚያመጡ አታጥብቁ ስዎችን አታርቁ የሚሉ ሚንሀጅ ሚንሀጅ አትበሉ ተህዚር ተህዚር አትበሉ በሚል ፍልስፍና ሁሉንም በሰለፍያ ስም ማቀፍ የሚፈልጉ ማለት ነው ።

    🔹 ደካማ ሰለፊ ማለት

እነዚህ አባባሎችን የሚቃወም በአቋም ሁሉንም የሰለፍይ ሚንሀጅ መርሆችን የሚቀበል ተብሊግም ሆነ ኢኽዋኖች ከጥመት አንጃዎች ናቸው እያለ በሙመዪዓና ኢኽዋን ላይ ረድ የሚያደርጉትን  የማይቃወም ሰለፍዮችን የማይተች ነገር ግን ኢኽዋኖችንና ሙመዪዓዎችን ለማኩረፍ አቅም የሌለው የተለያየ ምክንያት እያመጣ ከእነርሱ ጋር የሚቀራረብ ነው ።
በመሆኑም እንደነዚህ አይነት ወንድሞች ብዙ ስለሆኑ እባካችሁን ጠንካራ ሰለፍዮች እንዲሆኑ ልንረዳቸው ይገባል እንጂ ማራቅ አያስፈልግም ። ካልሆ ሸይጣን በመካከላችን ገብቶ ለመበታተን ስለማይተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ።
አላህ ሁላችንንም በሀቅ ላይ ያፅናን ።

ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር ከንደገና የተለቀቀ ።

http://t.me/bahruteka


Репост из: አቡ ያሲር ዩሱፍ አስሰለፊይ
👉 ትናንትና ባስጠነቀቁት ነገር ላይ
ዛሬ የወደቁ ጉዶች


   ክፍል አራት

የኢብኑ ሙነወር የድሮ ፁሁፍ፦
https://t.me/YusufAsselafy/4272?single

➡️ ይህ ከላይ የምታዩት ኢብኑ ሙነወር  የፃፈው ነው።

እህት ወንድሞች ሁለቱንም ፅሁፎች       በደንቡ አንብቡና ተረዱት 

የተናገረው ጀይላንን ስህተት ቢኖርበትም ሰለፍይ ነው የሚሉ አካላቶችን ነው።

ማነው ጀይላንን ስህተት ቢኖርበትም ሰለፍይ ነው ያለው ካላችሁኝ ኤሊያስ እና መሰሎቹ ናቸው።

እኛም ለኢብኑ ሙነወር እንለዋን እኔ ሱፍይ ነኝ፣ ወጣቱን እንዴት አድርገን ከጡሃ ኋላ እንዲሰግድ እናድርገው፣ ወጣቱን እንዴት አድርገን ከሙፍቲ ኋላ እናሰልፈው፣ ተብሊጎችን የሚተች የሚያወግዝ ከሸይጧን ነው የሚልን አካል ሰለፍይ ነው እደሚል አካል ቀላል (የወረደ፣ የቀለጠ) የለም እንለዋለን።

➡️ ማነው አቋሙን የቀየረው?

👌 አሁንም ቢሆን ሰከን ብላችሁ ወደ ጤናችሁ ብትመለሱ ይበጃል።

  ✍ አቡ ያሲር ኢብን ሙዘይን!

https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy


Репост из: 📝Abu Nuh ሚስባህ ሙሐመድ
🚫ሙብተዲዕን ለመከራከርም ይሁን የሚለውን ለመፈተሽ ብሎ መቅረብ ያለው አደጋ

♨️የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ)እንዲህ ይላሉ ፦

عَنْ أَبِي أُمَامَةَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " مَا ضَلَّ قَوْمٌ بَعْدَ هُدًى كَانُوا عَلَيْهِ إِلَّا أُوتُوا الْجَدَلَ ". ثُمَّ تَلَا رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ هَذِهِ الْآيَةَ : " { مَا ضَرَبُوهُ لَكَ إِلَّا جَدَلًا بَلْ هُمْ قَوْمٌ خَصِمُونَ } " [الزخرف: 58] قال الترمذي: حسن صحيح، وحسنه الألباني في ((صحيح الجامع)) (5633).

"የትኞቹም ህዝቦች ከነበሩበት ቅን መንገድ አይጠሙም ክርክርን የተሰጡ ቢሆን እንጂ " ከዚያም የሚከተለውን ቁርኣን አነበቡ ለሙግት እንጂ ለአንተ ምሳሌን አላደረጉልህም። ይልቁንም እነርሱ  ተከራካሪ ህዝቦች ናቸው

♨️ አል ኢማም አልበርበሃሪይ እንዲህ ይላሉ ፦

👈واعلم رحمك الله أنه ما كانت زندقة قط ولا كفر ولا شك ولا بدعة ولا ضلالة ولا حيرة في الدين إلا من الكلام وأهل الكلام والجدال ،

እወቅ አላህ ይዘንልህና: እነሆ ኒፋቅም ክህደትም ጥርጣሬም ቢድዐህም ጥመትም መወዛገብም በዲን ውስጥ አልተከሰተም በፍልስፍና ፣ ከሞጋቾችና ከተከራካሪዎች በኩል ቢሆን እንጂ።

👉በዚህ ላይ  የሰለፎቾ አቋም ከሙብተዲዕ ግማሽ የቁርን አንቀፅ እንኳን አልሰማም የሚሉ ነበሩ።
ከሙብተዲዖች አካባቢ ሹብሃን ብዥታን አልፈራም የምትል ወንድሜ  ለዐቂዳህ እዘንላትና ከሙመይዐዎች ተላቀቅ !

قال محمد بن النضر الحارثي – رحمه الله :-
"من أصغى سمعه إلى صاحب بدعة، وهو يعلم أنه صاحب بدعة، نزعت منه العصمة، ووكل إلى نفسه".
     الإبانة    (471)

🔹 መሐመድ ኢብኑ ነድር አል ሓሪሲይ  ረሒመሁላሁ  እንዲህ ይላል፦
የቢዳዓ ባልተቤትን የቢደዕ ሰው መሆኑን እያወቀ ንግግሩን ያዳመጠ የአላህ ጥበቃ ከሱ ላይ ይነሳል ።

ዒልምን ከቢደዕ ሰዎች ከመያዝ ጅህልና ይሻለዋል !

👉አላሁ ተዓለ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል ፦

( وَاتَقَوا اللَّهَ وَيُعَلِّمُكُمُ اللّهُ وَاللّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ )

መጀመሪያ አላህን ፍሩ ከዚያም አላህ የሳውቃችኋል አላህ በሁሉም ነገር ለይ አዋቂ ነው

አላህን ከመፍራት ውስጥ ከሐቀኞች መሆን የጥፋት ሰዎችን መራቅ ነው

✍️ قال العلامة  الشيخ ربيع_بن_هادي_المدخلي حفظه الله تعالى

👈لا يطلب العلم منهم ولايطلب عليهم فوالله لأن يبقى جاهلا سليم العقل والفطرة والقلب خير له من أن يتعلم من صاحب الهوى فتفسد عقيدته ويفسد منهجه

📚الفتاوى (٣٠١/ ١)

ቢድዒይዯችን አበጥረው የሚያውቋቸው የሆኑት ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሓዲይ አል-መድኸሊይ ሀፊዘሁሏህ
እንዲህ ይላሉ ፦

"ከቢድዐ ባለቤቶች  እውቀት ከመያዝ ጅህልና ይሻላል። እውቀት ከነሱ አይፈለግም። በአላህ ይሁንብኝ  ከቢደዕ ሰዎች ተምሮ እነ ቀልቡና ሚንሐጁ ከሚበላሽበት ከጅህልናው ጋር ጤነኛ ቀልብ ያልተበከለ ፊጥራ ያልተበረዘ ሚንሓጅ ይዞ
መቆየቱ  ይሻለዋል ።


የሙመይዖዎችን መሳጂዶች አከባቢ ደርስ አለ ሙሃደራ አለ እያልክ የምትባዝን  ተጠንቀቅ መጨረሻ በሌላው የተምይዕ ባህር ገብተህ እንዳትሰምጥ !!

የሱና አስተማሪዎች አልሃምዱሊላህ ሞልተዋል መድረሳቸው ጋ በመሄድ ዲንህን ዐቂዳህን  ተማር ።
በተለያየ ምክንያት እነሱ ጋ መሄዱ ከልተመቻቸልህ በሪከርዶቻቸው እነ በኦንላይን ገብተህ ተማር ።

👌ከሙብተዲዕ መራቅ ሲባል በአካልም በቀልብም  መራቅ ማለት ነው ።
ትምህርቶቹን በማንኛውም መንገድ አለማዳመጥ
ፁሑፎቹን አለማንበብ
ከግሩፑንም ይሁን ቻናሉ መራቅ ማለት ነው

👉ሙብተዲዕን ለየትኛውም ጉዳይ ብሎ ከመቅረብ ተጠንቀቅ !!!

📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት
   ቻነሉን    ይቀላቀሉ
➘➷➴➘➷➴➘➷➴➘➷➴
https://t.me/MisbahMohammed_6682


Репост из: Bahiru Teka
👉 እነርሱም ተውሒድ ያስተምራሉ ።

የነሲሓዎች ሙሪዶች ግራ ተጋብተው ሌሎችንም ግራ ከሚያጋቡበት ብዥታ አንዱ የነሲሓ ዱዓቶች እናንተ የምታስተምሩትን አይነት ተውሒድ ያስተምራሉ ታዲያ ልዩነታችሁ ምንድን ነው የሚል ነው ። !!!!!
ይህ ብዥታ በርግጥ ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ሊሆን የሚችል ሲሆን እውነታው ግን የሰማይና የምድር ያክል ርቀት ያለው ነው ። ነሲሓዎች ምስኪኑን ለመሸንገል ኪታቡ ተውሒድን ፣ ዋሲጢያን ፣ ተድሙሪያን ፣ አል ኢርሻድንና ከሽፉ ሹቡሃትን የመሳሰሉ ኪታቦች ሊያስቀሩ ይችላሉ ። ታዲያ ልዩነታችሁ ምንድን ነው ለሚለው ጥያቄ መልሱ የሚከተለው ሲሆን ምናልባት የእንቅልፉ ክኒን የዘጋውን ዐቅላችሁን ለመክፈት ይረዳችሁ ዘንድ ጭንቅላታችሁን ከአንገታችሁ በላይ ግራና ቀኝ በማወዛወዝ ነቅነቅ አድርጉትና አይናችሁን ዘግታችሁ ክፈቱት ።
ወደ መልሱ : –
ልዩነታችን እኛ ኪታቡ ተውሒድን ስናስቀራ " ከዚህ ኡመት ውስጥ ከፊል ጣኦት አምላኪያኖች አሉ " የሚለውን ባብ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር አገናኝተን አልከሶ ፣ ቃጥባሬ ፣ አብሬት ፣ ዳና ፣ ከረም ፣ ጌታው ሸኽዬ ሐድራ ፣ ጀማ ኑጉስ ፣ ዓንዬ ሐድራ ፣ ሸከና ሑሴን ባሌ ፣ አባድር ሐድራ ሐረር የሚሰራውን ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ የሚመለከት መሆኑን ገልፀን እናስጠነቅቃለን ። እነዚህና ሌሎችም ከአላህ ውጪ ያሉ አካላት የሚመለኩባቸው አካባቢዮች ላይ ይህን ተግባር የሚፈፅሙትን አላህን ፍሩ የሽርክና ኩፍር ተግባር እየፈፀማችሁ ነው ። ተውበት ሳዳደርጉ ወደ አኼራ ከሄዳችሁ የሚጠብቃችሁ ዘላለማዊ ክስረት ነው እንላለን ።
ነሲሓዎች ዘንድ እንደነዚህ አይነት ባቦች ለበረካና ኡማውን ለመሸንገል ነው የሚቀሩት እንጂ ከላይ የተጠቀሱ አካባቢዮችን ስም ጠርቶ እዛ አካባቢ የሚፈፀሙ ሽርኮችን ማውገዝና ማስጠንቀቅ ራሱ የተወገዘና ሽብርተኝነት ፣ ሒክማ አልበኝነት ፣ አክራሪነት ፣ በታታኝነት ነው ። እነዚህን አካባቢዮችና ከአላህ ውጪ የሚመለኩትን መሻኢኾች ስም ማንሳት ሰዎችን የሚያርቅ ስለሆነ አያስፈልግም የሚል ፍልስፍና ለተከታዮቻቸው ይግታሉ ።
ሱፍዮችና ኢኽዋኖች ተውሒድ ተውሒድ አትበሉ ሰዎችን ያርቃል ይሉ ነበር ። አሻዒራዎች ዐዋሞች ዘንድ ቁርኣን መኽሉቅ ነው አትበሉ ይልቁንም ቃለላሁ በሉ ምክንያቱም ቁርኣን መኽሉቅ ነው ማለት ዐዋሙን ስለሚያርቅ ይላሉ ። አሁን ደግሞ ሰለፍይ ነን ባዮች ሽርክ የሚፈፀምባቸው ቦታዎችና ሽርክ የሚፈፅሙ አካላትን ስም አትጥሩ እንደውም በግልፅ ከአላህ ውጪ የሚመለኩትንም ስም አታንሱ ምክንያቱም ሰዎች ይሸሻሉና እያሉ ነው ።
ነሲሓዎች ዐቂደቱል ዋሲጢያና ተድሙሪያን ሲያስቀሩ አሻዒራ ፣ ማቱሪዲያ ፣ ኩላቢያዎች አስማእ ወስሲፋት ላይ ሙዓጢላዎች ( የአላህን ከፊል ስምና ባህርይ ውድቅ የሚያደርጉ)ና በዚህም አህሉ ሱናን የኻለፉ የቢዳዐ አንጃዎች መሆናቸውን አይገልፁም ። ይልቁንም በድፍኑ በገሀዱ ዐለም ላይ ያሉ እስከማይመስሉ ለተበሩክና ለሽንገላ ነው የሚያስቀሩት ። የትኛውንም የዐቂዳ ኪታብ ሲያስቀሩ አሁን ካለው አንጃ ጋር አያገናኙትም ። ምክንያታቸው ይህን ቢያደርጉ ከኢኽዋን ፣ ሱፍይና አሕባሽ ጋር ስለሚጣሉ ነው ።
እስኪ በየአካባቢያችሁ ያለውን የቀብር አምልኮ ተመልከቱና የነሲሓ ዱዓቶች የሚያደርጉትን ዳዕዋ ስሙ በፍፁም በዛ አካባቢ ያለውን የቀብር አምልኮ አይናገሩም ። የአልከሶ ሸይኽ ነስሮ ከሸይኽ ዐ/ሐሚድ ጋር ሲነጋገሩ እኔ ስለ አብሬት እናገራለሁ ነገር ግን አልከሶ ላይ ስላለው ሽርክ አልናገርም ነው ያለው ።‼
የነሲሓዎች መሪ አዩብ ደርባቸው እንኳን ከቃጥባሬና አብሬት ሊያስጠነቅቅ አረቅጥ ላይ በአብሬት ሸይኾች ስምና በቃጥባሬ ሸይኾች ስም መቶ መቶ ሺህ ብር ቃል ገብቶ ሙሪዶችን ነው ያስጨፈረው ።
በነሲሓዎች ኪታቡ ተውሒድ ማስቀራት ለተሸወዳችሁ እውነታው ይህ ነው ። አላህ ከልቦና አይናችሁ ላይ ሒጃቡን ይግፈፍላችሁ ።

https://t.me/bahruteka


ትናንትና ባስጠነቀቁት ነገር ላይ
ዛሬ የወደቁ ጉዶች


        ክፍል ሶስት

👉 ኸዲር ከሚሴ  ከዚህ በፊት ከተናገራቸው፦ 👇


⚠️
አህመድ አደም ችግር አለበት ስንል ከመሬት ተነስተን አይደለም መስረጃዎችን መሰረት በማድረግ ነው።
አህመድ አደም ከማን ጋር ነው የሚነቀሳቀሰው ብንል?
ከኢብኑ መስዑድ ኢ/ሴነተር፣ ከነ ኤልያስ አህመድ መሰል ከሆኑ አካለቶች ነው።

⚠️ ኢልያስ እና መሰሎቹ ስህተታቸው በግልፅ በማስረጃ የታወቀ እስከሆነ ግዜ ድረስ ይህ አካል ከነሱ ነው ሚመደበው።

በአህለል ቢደዓ ላይ ረድ አለማድረግ ሙስሊሞችን ማታለል መሸንገል ነው

⚠️ ሰዎቹ እየተጓዙበት ያለው ጎዳና ድሮ ከተጓዙበት ጎዳና የተለወጠ ሆኖ ነው ያስተዋልነው ለማህበረሰቡ ማስጠንቀቅ ግድ ይላል።

⚠️ ዛሬ ላይ እየተጓዙ ያሉበት የሆነው መንገድ እጅግ በጣም ሙስሊሞችን ከባድ ለሆነው አዘቅጥ በመጣል ረገድ ከባድ ስራን ሰርቶ ነው ያስተዋልነው

⚠️ የቢደዓ
ባልተቤቶች እና ኢኽዋኒዮች እና መሰል አካለቶች እነሱን መጠቀሚያ ድልድይ አድርገው  እየተጠቀሙባቸው እንደሆነ እና.....
አትመለከቱም እንዴ
እነ ኢልያስ አህመድ ከኛጋ አብረው እየሰሩ ነው ብለው እነሱን እንደ ጋሻ
እየተጠቀሟቸው እነደሆነ ቀጥታ አስተውለናል። በዜና ደረጃ በኸበር ደረጃሳይሆን ጉዳዩ ውስጥ በቀጥታ ገብተን የተመለከትነው ነገር ነው።

👉 ከቢዳዓ ባልተቤቶች ጋር መተጋገዝ እና መረደዳት የተሰኘው ቀዒዳቸው በእጅጉኑ  የወደቀ የዘቀጠ የሆነ ቀዒዳ መሆኑን ይህ ነገር በእጅጉን ያስረዳናል ያሳያናል

👉 ማነው አቋሙን የቀየረው?

👌 አሁንም ቢሆን ሰከን ብላችሁ ወደ ጤናችሁ ብትመለሱ ይበጃል።

  ✍ አቡ ያሲር ኢብን ሙዘይን!


https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy


ትናንትና ባስጠነቀቁት ነገር ላይ
ዛሬ የወደቁ ጉዶች


        ክፍል ሶስት

👉 ኸዲር ከሚሴ  ከዚህ በፊት ከተናገራቸው፦ 👇


⚠️
አህመድ አደም ችግር አለበት ስንል ከመሬት ተነስተን አይደለም መስረጃዎችን መሰረት በማድረግ ነው።
አህመድ አደም ከማን ጋር ነው የሚነቀሳቀሰው ብንል?
ከኢብኑ መስዑድ ኢ/ሴነተር፣ ከነ ኤልያስ አህመድ መሰል ከሆኑ አካለቶች ነው።

⚠️ ኢልያስ እና መሰሎቹ ስህተታቸው በግልፅ በማስረጃ የታወቀ እስከሆነ ግዜ ድረስ ይህ አካል ከነሱ ነው ሚመደበው።

በአህለል ቢደዓ ላይ ረድ አለማድረግ ሙስሊሞችን ማታለል መሸንገል ነው

⚠️ ሰዎቹ እየተጓዙበት ያለው ጎዳና ድሮ ከተጓዙበት ጎዳና የተለወጠ ሆኖ ነው ያስተዋልነው ለማህበረሰቡ ማስጠንቀቅ ግድ ይላል።

⚠️ ዛሬ ላይ እየተጓዙ ያሉበት የሆነው መንገድ እጅግ በጣም ሙስሊሞችን ከባድ ለሆነው አዘቅጥ በመጣል ረገድ ከባድ ስራን ሰርቶ ነው ያስተዋልነው

⚠️ የቢደዓ
ባልተቤቶች እና ኢኽዋኒዮች እና መሰል አካለቶች እነሱን መጠቀሚያ ድልድይ አድርገው  እየተጠቀሙባቸው እንደሆነ እና.....
አትመለከቱም እንዴ

እነ ኢልያስ አህመድ ከኛጋ አብረው እየሰሩ ነው ብለው እነሱን እንደ ጋሻ
እየተጠቀሟቸው እነደሆነ ቀጥታ አስተውለናል። በዜና ደረጃ በኸበር ደረጃሳይሆን ጉዳዩ ውስጥ በቀጥታ ገብተን የተመለከትነው ነገር ነው።

👉 ቢዳዓ ባልተቤቶች ጋር መተጋገዝ እና መረደዳት የተሰኘው ቀዒዳቸው በእጅጉኑ  የወደቀ የዘቀጠ የሆነ ቀዒዳ መሆኑን ይህ ነገር በእጅጉን ያስረዳናል ያሳያናል

👉 ማነው አቋሙን የቀየረው?

👌 አሁንም ቢሆን ሰከን ብላችሁ ወደ ጤናችሁ ብትመለሱ ይበጃል።

  ✍ አቡ ያሲር ኢብን ሙዘይን!


https://t.me/YusufAsselafy
https://t.me/YusufAsselafy


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: Bahiru Teka
🚫 ከሀዲያንን በባአላቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት

በመለኮታዊ የሕይወት መመሪያ በሆነው የአላህ ቃል የሚመራው እንከን የለሹ ኢስላም ካስቀመጣቸው ግልፅና የማያሻሙ ህግጋቶች ውስጥ ከሃዲያንን በባአላቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት ክልክል መሆኑ ነው ።
ተህኒኣ ( እንኳን አደረሳችሁ ) ለከሀዲያን ማለት ሐራም መሆኑ አጠቃላይ የኢስላም ሊቃውንቶች በአንድ ድምፅ ያፀደቁት መሆኑ ኢብኑል ቀዪም አሕካሙ አህሊ ዚማህ በሚለው ኪታቡ የጠቀሰው ሲሆን በኩፍር መደሰትን ስለሚያሲዝ ወደ ኩፍር ሊያደርስ እንደሚችል በዚሁ ኪታቡ ላይ ያብራራል ። ቀድሞ እንኳን አደረሳችሁ ማለት ብቻ ሳይሆን እነርሱም ሲሉ እንኳን አብሮ አደረሰን ማለትም ተመሳሳይ ብይን እንዳለው የኢስላም ሊቃውንቶች ያስቀምጣሉ ።
በዚህ ጉዳይ ላይ አራቱም አኢማዎች ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ሲሆን ከዘመናችን ዑለሞች እንደነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ, ሸይኽ ዑሰይሚንና ሸይኽ ፈውዛን የመሳሰሉት ሐራም መሆኑን አስቀምጠዋል ።
በመሆኑም ይህ ጉዳይ የቀደምቶች ስምምነት ያለበት ስለሆነ መወዛገብ አይፈቀድም ። የኻለፈ አካል ትንሹ ብይኑ የስሜት ተከታይ ( ሙብተዲዕ) ይሆናል ። ከፍ ሲል በኩፍር ላይ የደስታ መልእክት ማስተላለፍ ስለሆነ ያከፍራል ።
በጣም የሚገርመው እንዲህ አይነት ግልፅ የሆነ ሸሪዓዊ ብይን የተሰጠበትን ከባድ የመሰረታዊ የእምነት ነጥብ በሚቃረን መልኩ ለዛው በአላህ ቤት መስጂድ ላይ ይህን ወደ ኩፍር ሊያደርስ የሚችል መልእክት በአደባባይ የቅርብም የሩቅም በሚያየው መልኩ ተሰቅሎ መታየቱ ነው ። ይህ የሆነው ቄራ ሰላም መስጂድ ላይ ነው ። ይህን መልእክት በገፃችን ላይ መለጠፉ ስለሚቀፍ በሚቀጥለው ሊንቅ ገብታችሁ ተመልከቱት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://drive.google.com/file/d/11ISLKe4SHvZ_5tf3MRxdCKK2sdcqi0yf/view?usp=drivesdk

የሚያሳምመውና የሚያሳዝነው በአላህ ቤት ላይ መሆኑ እንጂ የተጠቀሰው መስጂድ የሚያስተዳድረው ዲኑን ለስልጣንና ለግል ጥቅም የሚሸጠው የኢኽዋን አንጃ አካል ስለሆነ አይገርምም ። ምክንያቱም ፈለጋቸውን የሚከተሉት የግብፅ, የቱርክና ሱዳን ኢኽዋኖች ወደ ሀይማኖት አንድነት ነውና የሚጣሩት ። በመሆኑም ከሀገራችንም ኢኽዋኖች አላህ ይምራቸው እንጂ እንኳን አደረሳችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ሀይማኖት አንድነት ይጣራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።
መሪዮቻቸው ከእንጀራ አባቶቻቸው ጋር የተለጠፉት የነሲሓ ቲፎዞዎች ምን ይሰማቸው ይሆን ? ነው ወይስ 30 ክኒኖቹ ይህም እንኳን እንዳይሰማቸው አደንዝዟቸው ይሆን ? ወይስ በሱፍይ ሙሪዶች ቀመር ስለሚጓዙ ሸይኾቻቸው የሰሩት ነገር ለምን አይባልም ? አላህ ሆይ ልባችንን ሐቅ ካሳወቅከው በኋላ አትቀይረው ።

https://t.me/bahruteka


Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa




Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
عيسى_عليه_السلام_في_ميزان_الإسلام_جديد_1.pdf
1.0Мб
⤵️⤵️

አዲስ PDf

ተሻሽሎ የቀረበ

‎⁨عيسى عليه السلام في ميزان الإسلام
ዒሳ (እየሱስ) - ዐለይሂሰላም- በኢስላም ሚዛን

بقلم الشيخ حسين بن محمد بن عبد الله السلطي الإثيوبي نازل مكة المكرمة حفظه الله

✍🏻አዘጋጅ:- የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ረቢዕ እና በቅርብ ወደ አኼራ የሄዱት የታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም ተማሪ በሆነው በሸይኽ ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ) ከሳዑዲ ዐረቢያ
https://t.me/Menhaj_Alwadih

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት)

👉 ይህ ኪታብ ከዚህ በፊት በወንድማችን ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን (ሀፊዘሁላህ) ተቀርቶ በተከታታይ ሲቀርብ የነበረ ሲሆን
https://t.me/shakirsultan/1331
ከዛ በኋላ ሸይኹ በድጋሚ አሻሽለው በ pdf አቅርበውታል
በአላህ ፈቃድ ወደፊትም በአማርኛ ተተርጉሞ ይቀርባል

#Share_ሼር ይደረግ

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


Репост из: Muhammed Mekonn
ሰላማዊ ሰልፍ እና በዳይ አካል ከበደሉ እንዲቆጠብ ማድረጊያ ስልት የጅሐድ መዳረሻ ነውን?

✅📝 መልስ፡- ይህ ትክክል አይደለም፡፡ የነብዩ ﷺ መመሪያ ከሁሉም መመሪያ የበለጠ ነው፡፡ በረሡል ﷺ ዘመን ያልነበረ አዲስ የጅሐድ ስልት የሚፈጥርን አካል ሰለፎች ይቃወሙ ነበር፡፡ ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያህ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፦
(ጦርነትን አስመልክቶ ሱናው ድምጽን መቀነስ ነው፤ ይህ እየዘለሉ መሬትን
በእግር መደብደብ፤ ልክ እንደአይሁዶች ጡሩንባ መንፋት፤ ልክ እንደነሷራዎች ደዎል መደወል፤ በኹለፋኡ ራሽዲን (በቅን መሪዎች) ዘመን እና ከእነርሱ በኋላ በነበሩ የሙስሊም መሪዎች አልነበረም፤ ይህን ቢድዓ በምስራቅ የነበሩ የፋሪስ ንጉሶች የፈጠሩት ይመስለኛል፤ ንግስናቸው በዓለም በሰፊው ተሰራጭቶ ስለነበር ያን ጊዜ በመሪዎች ላይ ሲያምጹና ሲያስገድሉ በርካታ አዳዲስ ነገሮችን ፈጥረዋል፤ በዚሁ ቢድዓ ላይ ህጻኑም አደገ ትልቁም አረጀ፤ ከዚህ ውጭ ሌላ አያውቁም፤ እንዴውም በእነርሱ ተቃራኒ አንድ ሰው ከተናገረ ወዲያውኑ ይቃወማሉ፤ እንዴውም አንዳንድ ሰዎች ይህን ቢድዓ ዑስማን ኢብን አፋን እንደፈጠረው አድርገው የሚሞግቱ አሉ፤ ነገሩ ግን እንደዚህ አይደለም፤ እንዴውም ከዑስማን በኋላ የመጡ መሪዎች ሁሉ ያልፈጸሙት ተግባር ነው፡፡


ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ነብዩ ﷺ የተናገሩት ትንቢት ይፋ ሆኖ እየተመለከትን ነው ረሡል ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ከእናንተ በፊት የነበሩ ማህበረሰቦች የያዙትን በእርግጥ ትይዙታላችሁ፤ ስንዝር በስንዝር፤ ክንድ በክንድ፤ “ፋርስ እና ሮም ነው እንዴ?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁ፤ “እነርሱ ካልሆኑ ማን ሊሆን ይችላል?” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡
ቡኻሪ

በሌላም ሐዲስ ረሡል ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“ከዚህ በፊት ያለፉ ህዝቦችን መንገድ ላባ በላባ በእርግጥ ትከተላላችሁ፤ የአርጃኖ
(የወከሎ) ጉድጓድ ቢገቡ እንኳ በእርግጥ ትገባላችሁ፤” በማለት ተናገሩ፤ ከዚያም
“የአላህ መልክተኛ ሆይ! አይሁድ እና ነሷራን ነውን?” በማለት ሶሃቦች ጥያቄ
አቀረቡ፤ “እንግዲያ ማንን ነው?” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡

አህመድ፡ 17135, አልባኒ

አስሶሂሃ 7/915 ኢብኑ ከሲር በተፍሲራቸው፣ ሀይሰሚይ መጅሙዑ ዘዋኢድ ላይ ዘግበውታል ሐዲሡ ሶሂህ ነው፡፡)

ሁለቱም ሐዲሶች ከረሡል ﷺ የተሰሙ ትክክለኛ ሐዲሶች ናቸው፡፡ ረሡል በዚህ
ማህበረሰብ ውስጥ አይሁድ እና ነሷራን ወይም ፋርስ እና ሮማዎችን የሚመሳሰሉ ማህበረሰቦች እንደሚኖሩ ነው የጠቆሙት፡፡ ይህን ርዕስ የምናብራራበት ቦታ ከዚህ ባይሆንም በመሪዎች በንጉሶች በርካታ አዳዲስ ነገሮች ተፈጥረዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ
ቦታ ዋናው አላማችን ጅሐድን አንስተው የጩኸት ቢድዓን በፈጠሩ ሰዎች ላይ ነው፤ አመዛኝ ጥቅም ሊኖረው ይችላል ብለው ገምተው እንኳ ቢሆን መልካሙን ነው አጥብቀው መያዝ ያለባቸው፤ አመዛኙ ጥቅም የዚክር ድምጾች፤ ሶላት እና ከእርሱ ጋር የተያያዙ ዱዓዎች፤ ቁርኣን መቅራት እና መስማት ናቸው፤ ሌሎች ጥቅም የሚያስገኙ ሸሪዓዊ ጉዳዮች አሉ…. ከዚህ በፊት የነበሩት ቀዳሚዎች ታብዒዮች በማንኛውም ነገር ከኋለኞች የተሻሉ፤ የሚከተሉት መንገድም የተሟላ ነው፤
ነገር ግን አንድ ሙስሊም ስራዎችን በአቅሙ ሊፈጽም ይገባል፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፦
فَاتَّقُوا اللَّهَ مَا اسْتَطَعْتُمْ
“አላህንም የቻላችሁትን ያህል ፍሩት፤”
ተጋቡን 16

ነብዩ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
“አንድ ነገር ካዘዝኳችሁ የቻላችሁትን ያህል ፈጽሙት፡፡”
ቡኻሪና ሙስሊም

https://t.me/AbuImranAselefy/6935


አዲስ ሙሃዶራ

ርእስ:- አላዋቂነትና በደል የሸሮች ሁሉ መነሻ ነው

🎙ኡስታዝ ሙሐመድ አል-ኪርማኒ (ሀፊዘሁላህ)

በአሊቾ ዊሪሮ ወረዳ በገድራት ቀበሌ ጮል  መንደር በአል-አቅሳ መስጂድና መድረሳ የቀረበ

#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

Показано 20 последних публикаций.