Фильтр публикаций


ምንድነው የተፈጠረው?

#FastMereja I የድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ማናጀር የሆነው ለሊሳ እንድሪስ የተፈጠረውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ከሰጠው ምላሽ በፋስት መረጃ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።
ንጋት 11:00 ሰዓት ስልክ ተደውሎ «ቀነኒ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች ቶሎ ድረስ» እንደተባለ የሚናገረው ለሊሳ እሱ ሩቅ በመሆኑ በሰዓቱ መድረስ እንዳልቻለ ይናገራል።

ቦሌ አራብሳ ከአመት በላይ በጋራ ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ከአምስተኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ምን እንደተፈጠረ ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በቅርብ በሚገኘው ያኔት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ጠዋት ፖሊስ መጥቶ ሬሳዋን ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ከወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት እስኪወጣ አስክሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ሱሉልታ መሄዱ ነው የተገለፀው።

ድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከሆስፒታል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዛ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምናውቀው እስካሁን አለመታሰሩን ነው ምርመራ እናድርግ ብሎ ነው ፖሊስ የወሰደው ሲል ማናጀሩ ይናገራል።

ለሁለት አመታት በፍቅር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ጋብቻቸውን ለመፈፀም እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቃለሁ ሲል ለሊሳ ይናገራል።


ምንድነው የተፈጠረው?

#FastMereja I የድምፃዊ አንዱአለም ጎሳ ማናጀር የሆነው ለሊሳ እንድሪስ የተፈጠረውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ከሰጠው ምላሽ በፋስት መረጃ እንደሚከተለው እናቀርበዋለን።
ንጋት 11:00 ሰዓት ስልክ ተደውሎ «ቀነኒ ተጎድታ ሆስፒታል ገብታለች ቶሎ ድረስ» እንደተባለ የሚናገረው ለሊሳ እሱ ሩቅ በመሆኑ በሰዓቱ መድረስ እንዳልቻለ ይናገራል።

ቦሌ አራብሳ ከአመት በላይ በጋራ ከሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው ከአምስተኛ ፎቅ እንደወደቀች እና ምን እንደተፈጠረ ፖሊስ እያጣራ መሆኑ ተነግሯል።

ክስተቱ ከተፈጠረ በኋላ በቅርብ በሚገኘው ያኔት ሆስፒታል ከገባች በኋላ ጠዋት ፖሊስ መጥቶ ሬሳዋን ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለምርመራ ከወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት እስኪወጣ አስክሬኗ ወደ ቤተሰቦቿ ሱሉልታ መሄዱ ነው የተገለፀው።

ድምፃዊ አንዱዓለም ጎሳ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከሆስፒታል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዛ የሚገኝ ሲሆን እኛ የምናውቀው እስካሁን አለመታሰሩን ነው ምርመራ እናድርግ ብሎ ነው ፖሊስ የወሰደው ሲል ማናጀሩ ይናገራል።

ለሁለት አመታት በፍቅር ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ጋብቻቸውን ለመፈፀም እየተዘጋጁ እንደሆነ አውቃለሁ ሲል ለሊሳ ይናገራል።


#እመቤታችን ሰማያትን ያሳየችው ቅዱስ

የትውልድ ሃገሩ ሶርያ ውስጥ ሮሃ አካባቢ ነው፡፡ ተወልዶ ባደገባት ሃገር ይህ ቀረው የማይባል ኃጢአተኛ ሰው ቢሆንም እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን በፍፁም ልቡ ይወዳት ነበርና በመዳን ቀን ጥሪ ለንስሐ አበቃችው፡፡  ከዚያች ዕለት ጀምሮም ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው፣ ንጹሕ የቤተ ክርስቲያን መስዋዕት፣ ጽኑዕ የበርሃ ምሰሶ ሆነ፡፡ ድንግል እመቤታችንም ከነሥጋው ወደ ሰማያት ወስዳ ገነትና ሲዖልን አሳይታ፣ ከአዳም ኖኅ፣ ከአብርሃም እስከ ሙሴና ዳዊትን ከመሰሉ ቅዱሳን ጋር አገናኘችው፡፡ ከዚህም በላይ የሆነና በሰብአዊ አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢር አሳይታ ወደ ምድር መልሳዋለች፡፡ ይህም በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት ምሥጢራትን የተመለከተ እየተባለ እንዲጠራ አድርጎታል፡፡

ቅዱስ ጎርጎርዮስ በሰማይ በነበረው ቆይታ ክብረ ቅዱሳንን ተመልክቶ አድንቋል:: በተለይ በፍጹምነት ድንግልናቸውን የጠበቁ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደናግል አኗኗራቸው ከአምላክ እናት፣ ከሰማይ ንግሥት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መሆኑን አይቷል፡፡ "የለበሱት ልብስም በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የሚቻል አይደለም" ይላል፡፡ የደናግል ፊታቸው ከፀሐይ 7 እጅ ያበራልና ግርማቸው ያስፈራል፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ በዚያው በሰማይ ሳለ ደግሞ ይህንን ተመለከተ፡፡ አንድ አረጋዊ፣ ጽሕሙ ተንዠርግጐ፣ የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሶ ይመጣል፡፡ ቅዱሳን መላእክት በፊት በኋላ፣ በቀኝ በግራ ከበውት ሳለ እግዚአብሔርን በበገናው ሊያመሰግን ጀመረ፡፡ "አቤቱ ጌታችን በምድር ሁሉ ስምህ የተመሰገነ ሆነ" ሲል መላእክቱ በዝማሬ አጀቡት::

በዚህ ጊዜም ታላቅ መናወጥ ሆነ፡፡ ደናግሉም የቅዱሱን ሽማግሌ በረከቱን ተሳተፉ፡፡ ይህ አመስጋኝ ሽማግሌ ልበ-አምላክ፣ ጻድቅ፣ የዋህና የእሥራኤል ንጉሥ ዳዊት ነበር፡፡ አንድም እመቤታችን "አባቴ ዳዊት!" ብላ ስትጠራው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሰምቷልና፡፡ በመጨረሻም እመቤታችንን በፍጹም ክብርና ግርማ ተመልክቷት ሐሴትን አድርጓል፡፡ እመ-ብርሃንም "ተወዳጅና ንጹሕ ሰው ነህ" ስትል ቅዱስ ጎርጎርዮስን አመስግናዋለች፡፡ ስለዚህ ዓለምም እንዲህ የሚል መልእክትን ልካለች:: "ልጆቼ ሆይ! ከብርሃን ጨለማን፣ ከደግነት ክፋትን፣ ከጽድቅ ይልቅ ኃጢአትን ምነው መምረጣችሁ? እኔ ስለ እናንተ በየቀኑ እየለመንሁ እነሆ አለሁ:: ወደ ጨለማ ገሃነም እንዳትወርዱ እባካችሁ ንስሐ ግቡ!"

ቅድስት ድንግል ማርያም ይህንን ለቅዱሱ ሰው ነግራው፣ ቅዱስ ዳዊትን አስከትላ በግሩማን መላእክት ታጅባ የእሳት መጋረጃዎች ወደ ተተከሉበት ድንኳን ገባች፡፡ በዚያም ተመሰገነች፡፡ ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫም "ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት፣ ወይብልዋ፣ በሐኪ ማርያም ሐዳሲሁ ጣዕዋ"፤ “መላእክት ማርያምን በመጋረጃዎች ውስጥ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል እያሉ አመሰገኗት” የሚለንም ለዚህ ነው፡፡ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከሰማይ ቆይታው መልስ ያየውን ሁሉ ጽፎ ለአበው ሰጥቷል፡፡ ስለዚህም ረዓዬ ኅቡዓት “ምሥጢራትን ያየ” ይሰኛል፡፡ ቅዱሱ ተረፈ ዘመኑን በተጋድሎ ፈጽሞ በመጋቢት ሁለት ቀን አርፏል፡፡ የቅዱሱ እመቤት ድንግል እመ ብርሃን መዓዛ ፍቅሯን ታብዛልን፡፡ በቅድስና ሕይወት፣ በገዳማዊ ኑሮ ያሉትን እየረዳንና በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




ቤቲ እና ናቲ ላይ ትኩረት አድርጓል የተባለለት «እንግዱ» ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው።

#FastMereja I በልባም ፒክቸርስ ተዘጋጅቶ በሳዳም ፊልም ፕሮዳክሽን እና በሶሎዳ ስቱዲዮ የቀረበው «እንግዱ» ፊልም ለእይታ ሊቀርብ ነው።

ፊልሙን ለማዘጋጀት ከ8 ወር በላይ እና በወጪ በኩል 2.5 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት የተገለፀ ሲሆን በፊልሙም ላይ በትወና ሰለሞን ሙሄ፣ ኤደን ገነት፣ ደረጄ ሀይሌ፣ ጌዲዮን ፍቃዱ፣ አሰፋ ገ/ሚካኤልና ሌሎች ከ35 ሰዎች በላይ ታዋቂ እና አጃቢ ተዋናዮች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

የፊልሙ ይዘት ልብ አንጠልጣይ ትሪለር ይዘት ያለው ሲሆን በሶሻል ሚዲያ የሚታወቁ ቤቲ እና ናቲ ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ እንዲሁም ተዋናይ ጌድዮን ፍቃዱ ሰባት ካራክተር ወክሎ በፊልሙ ላይ መተወኑ ተነግሯል።

በቀይ ምንጣፍ ስነ ስርዓት መጋቢት 1/2017 ዓ.ም በአለም ሲኒማ የፊልም ተዋናዮች የተለያዩ የሚድያ ሰዎች ተፅኖ ፈጣሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

#ኪነ_ጥበብ


የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ - ለሰላም፣ ለመተባበር እና ለአብሮነት
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ
መጋቢት 2 ቀን 2017
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ


በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሠጠ መግለጫ

“የሃይማኖት ንጽጽር - በከፍተኛ የሃይማኖት ሊቃውንቶች መካከል በሕግ፣ በሥርዓት እና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመራ በዶግማዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ የሰከነ ውይይት ነው፤ በአማኞች መካከል የሚደረግ ሥርዓት የለሽ እና አንዱ ሌላውን የሚያውገዝ፣ የሚያጠልሸ እና ክብረ-ነክ መሆን ወንጅል ነው፤” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማኅበራዊ ሚዲያውን እድገትና ተደራሽነት መስፋትን ተከትሎ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ አጀንዳዎች ላይ በአወንታዊነት እና በአሉታዊነት የሚፈረጅ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ተሠርተው አየር ላይ ሲውሉ እናያለን፤

አንዳንዶች ደግሞ የራሳቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ በመክፈት የተለያዩ ግለሰቦችን ወደመድረካቸው በመጋበዝ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በደጋፊነት እና በነቃፊነት ላይ ተሰልፈው የጦፈ ክርክር ሲደርጉም እንመለከታለን፡፡

ዘርፉና የመገናኛ መድረኩ የራሱ የሆነ የአጠቃቀም መመሪያ ያለውና በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ የሚጠበቅ ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች መድረኩን ከዓላማው ውጪ ለሆነና ለግልና ቡድናዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ በማድረግ በተለያዩ ሃይማኖት/እምነት ተከታዮች መካከል መተማመኑ እና መከባበሩን የሚሸረሽሩ ይዘቶችን፣ ክብረ ነካዊ በሆነ አቀራረብ ግልፅ ጥላቻን የመስበኩ ልምምድ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ይገኛል፡፡

ይህ ዓይነቱ አቀራረብና ልምምድ አልፎ አልፎ በአንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በመደበኛ የአምልኮ መርሀ ግብር ላይ በፊት ለፊት መድረኮች ሲቀርብ አይተናል፡፡ ልምምዱና አቀራረቡ ከወዲሁ ሊታረምና በሕግና ሥርዓት ሊከናውን እንደሚገበው ጉባኤያችን በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህ አንፃር ከሰሞኑ የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች የተቀደሰ የጾም፣ የጸሎትና በከፍተኛ ደረጃ የመንፈሳዊ እነፃ ላይ በሚገኙበት ጊዜ ከመንፈሳዊነትና ከሃይማኖቶች መሠረታዊ ዕሴት ጋር የሚቃረን ተግባር በማኅበራዊ ሚዲው በስፋት እየተሠራጨ ይገኛል፡፡

በተለይም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ የእስልምና ሃይማኖት ነቢይ በሆኑት በነቢዩ መሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ላይ ድፍረት የተሞላበት ክብረ ነክና ጽያፍ ንግግር ሲያደርጉ ታየረተዋል፡፡ ይህም ሙስሊሙን ወገን ብቻ ሳይሆን ሰላም ወዳዱን ወገን ሁሉ አሳዝኗል፡፡

ጉባኤችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነምግባራዊ እና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጤኑና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እንመክራለን፡፡

በአንፃሩ አንዳንድ ሙስሊም ነን የሚሉ ግለሰቦች ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚነቅፍና የሚያጠለሽ፣ መላውን ክርስቲያን በሚያዋርድ መልኩ ምላሽ ሲሠጡ እና ድርጊቱን በፈፀመው ግለሰብ ላይ የደቦ ፍርድ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡

ይህም ሕገ-ወጥነትን ከማስፋፋት ባለፈ ጥፋትን በሌላ ጥፋት ማረም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊታቸው በመታረም የሕግ የበላይነትን እንዲስቀድሙ ጉባኤያችን በአጽንኦት ይመክራል፡፡ በየትኛውም አካል የተፈፀሙትና የሚፈፀሙት ይህን መሠል ሕገ-ወጥ ተግባራት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ተቀባይነት
የሌላቸው ብቻ ሳይሆን የሚወገዙ ተግባራት መሆናቸውን ጉባኤያችን እያስገነዘበ ድርጊቱ በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑም ለማስታወስ ይወዳል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሀይማኖት መገኛና መኖሪያ ከመሆኗ አንፃር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትኛውንም ዓይነት የሃይማኖት ተቋማትን፣ አስተምህሯቸውንና መገለጫዎቻቸውን የሚያንቋሽሹና የሚያዋርዱ ንግግሮችንም ሆነ ተግባራትን በጽኑ ያወግዛል። እንዲህ ያሉት ክብረ-ነክ የሆኑ ተግባራትና አስተያየቶች ሁሉ ድርጊቱ ለተፈፀመባቸው እምነት ተከታዮችን በእጅጉ የሚያስቆጡ ብቻ ሳይሆኑ መላ ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ የሚያስቆጡ ናቸው፡፡ የመከባበርና የአብሮነት እሴቱን በመሸርሸር በሀገራችን የሰላምና የሰላማዊ ማህበረሰብ ግንባታ ሂደቱንና ጥረቱን እንዳይያሳካ ያደርጋሉ፡፡

ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አንዱ የሌላውን እምነት ለመስደብ ወይም ለማዋረድ በፍፁም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። የእምነት ነፃነት እና የማምለክ መብት ለሁሉም ማህበረሰቦች የተጠበቀ ሲሆን ይህ መብት የሌሎች አማኞችን መብት በመጋፋና ስሜት በመንካት ለጠብ ማነሳሽነት ሲውል በዝምታ ሊታለፍ አይገባውም፡፡
ይህንን ከባድ ጥፋት በዘላቂነት እንዲታረም የሚመለከታቸው አካላት አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ይህንንና ተመሳሳይ ተግባር በፈፀሙና በሚፈጽሙ አካላት ላይ አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን። ለእንደዚህ አይነት ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ለወደፊቱ የሃይማኖትን ስም ማጥፋት ለመከላከልና የሁሉም እምነት ተከታዮች ክብርን ለመጠበቅና
ለማስጠበቅ በእጅጉ ይረዳል።

በተጨማሪም የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃይማኖት ምሁራን እና መላ ሕብረተሰቡ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር፣ መግባባትና መረዳዳት ይበልጥ ሊያጠናክሩ በሚያስችሉ የጋራና የተመረጡ አጀንዳዎች ላይ በሕግ፣ በሥርዓትና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመሩና ግልጽ ዓላማና ግብ የተቀመጠላቸው ውይይቶችና ምክክሮች በተጠናከረ መልኩ በማከናውን በሃይማኖቶች መካከል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን እንደ ሚያጠናክሩ ይጠበቃል፡፡

በቅርቡ ጉባኤያችን ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በመዳሰስና በመተንተን ሀገራዊ ዓውዱንና ተግዳሮቶች ታሳቢ በማድረግ፣ እንዲሁም ተቋሙ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል የመተዳደሪያ ደንቡን አሻሽሏል፡፡ የተሻሻለው ደንብም በተቋማት መካከል አለመከባበርን፣ አለመቻቻልን የሚሰብኩ፣ ጥላቻን የሚቀሰቅሱና ግጭትን የሚያባብሱ ተንኳሽና ክብረ-ነክ ንግግሮችንና ተግባራትን የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በራሳቸው ተቋም ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት እንዲኖር የሚያደርግ ድንጋጌ በደንቡ ላይ እንዲካተት ተደርጓል፡፡

የችግሩ ስፋትና ጥልቀት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ችግሮን በዘላቂነት ለመፍታትም ከአባል የሃይማኖት ተቋማት የሚወከሉ የሕግና አግባብነት ያላቸው ባለሙያዎች የሚካተቱበት የተከላካይ ግብር-ኃይል አደረጃጀት በጊዜያዊነትና በቋሚነት በማደራጀት የቅደመ መከላከል ሥራዎች ለመስራት ተዘጋጅቷል፡፡

ግብር-ኃይሉም ችግሮችንና የችግር አዝማሚያዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና የመፍትሔ ሀሳቦችን በመስጠት ሙያዊ እገዛ በማድረግ ሕግና ሕጋዊነትን የማስጠበቅ ሥራ በመስራት የሀገር ሰላምንና የሃይማኖት ተቋማትን ክብርና ልዕልና የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡

የሁለቱም እምነት ተከታዮች እና አማኞች በማኅበራዊ ሚዲያው ባለው አሉታዊ ዘመቻና በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ሳይረበሹ የጾም፣ ጸሎትና የንስሀና ተግባሮቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ ጉባኤያችን ይመክራል፡፡

የሕግ አስከባሪ አካሉም፣ በአማኞች መካከል ያለው ሰላምና መከባበር የሚያውኩ፣ ሕገ-ወጥ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታረሙ በማድረግ ሕግና ሥርዓት የማስጠበቅ የተለመደ ሕጋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤያችን ጥሪውን ያቀርባል፡:

በመጨረሻም ሁላችንም የሃይማኖት ተቋሞቻችንንና የአስተምህሯችንን ክብር፣ ልዕልናና ቅድስና እንጠበቅ በማለት ጉባኤያችን የአደራ መልዕክቱንና ጥሪውን ያቀርባል፡፡




“የጊዜያዊ አስተዳደሩ በሶስት ጄነራሎች ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ተቋማዊ አሰራርን እና ህግን ያልተከተለ ነው” - የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ በተለያዩ ግንባሮች አዛዦች መሆናቸው የተገለጸ ሶስት ጄነራሎችን፤ ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሀይለ በግዜያዊነት ማገዳቸውን አስታወቁ።

በፕሬዝዳንቱ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ጄነራሎቹ በግዜያዊነት የታገዱት “ከመንግስት ውሳኔ ውጭ መላ የክልሉን ህዝብ እና ወጣቱን ወደ ግርግር፣ የጸጥታ ሀይሉን ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚያስገባ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ በመሆኑ ነው” ብሏል፤ የጀነራሎቹ እንቅስቃሴ “ህዝቡ ወደማይወጣው አዘቅት የሚከት ነው” ሲል አስታውቋል።

የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ “የወንጀለኞች ጠበቃ መሆን ይብቃ” በሚል ርዕስ ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን እንደማይቀበለው አስታውቋል፤ “ያልሾመውን ያወረደ ነው” ሲል ገልጿል።

በተመሳሳይ በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ውሳኔን ህገወጥ ሲል ኮንኗል፤ “የትግራይ ሰራዊትን ለማፍረስ ሲያደርግ የነበረው ሴራ ወደ ከፍተኛ እና አደገኛ ደረጃ አሸጋግሮታል” ሲል ገልጿል።




«ለአንዳንድ የቃላት አጠቃቀሜ ትላልቅ ሰዎች እና ህፃናት ሲሰሙት ስለሚከብድ ለቃላት አጠቃቀሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ! ከዛ ውጪ ያጠፋውት ነገር የለም። በግልፅ ክርስትናን የሚሳደቡ ግለሰቦችም ይቅርታ እንዲጠይቁ ይደረግ!» በቲክቶክ ስሙ "እፎይ"

5.8k 0 13 57 190

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በጥላቻ ንግግር ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

ኢትዮጵያ ብዝሃ ሀይማኖት የሆነች ሀገር እንደ መሆኗ የተለያየ እምነት ተከታዬች ለዘመናት ተፈቃቅደውና ተከባብረው ኖረውባታል። እየኖሩባትም ይገኛሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ይህንን በጎ እሴት በመሸርሸር ውዝግብና ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩ አካላት እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡

በተለይም የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ተረድቷል።

ጠቅላይ ም/ቤቱ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጠቅላይ ም/ቤቱ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ በመሆኑ የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የጥላቻ ንግግር በየትኛውም ወገን ቢሰነዘር ጠቅላይ ም/ቤቱ በጽኑ እንደሚያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንደሚሰራም ማወቅ ይገባል፡፡

በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብርየሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ ያሳስባል።

በመሆኑም፡-
1. የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጉዳዩ ከዚህ በላይ ከመክረሩ በፊት የጋራ አቋም በመያዝ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲወስን።

2. ይህ በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም በአግባቡ በመረዳት የሚመለከታቸው የፀጥታና የህግ አካላት ተጨማሪ ጥፋት ከመከተሉ በፊት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ፤

3. የሰሞኑ የጥላቻ ንግግር ምንጩ የተራ ግለሰብ ቢመስልም ከጀርባ የአጀንዳና የሃሳብ ተጋሪዎች ያሉት በመሆኑ ህዝባዊ ቁጣ ከመቀስቀሱ በፊት የሀገርና የህዝብ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ከጠቅላይ ም/ቤቱ ጋር በመቆም ትንኮሳውን እንዲያወግዙ፤ እንዲሁም

4. ወቅቱ በሙስሊሞች እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የፆም ወቅት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ከሀይማኖትና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጡ የጥላቻ ንግግሮች የሚገሰፁበትና የሚታረሙበት የፅሞና ወቅት እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ጠቅላይ ም/ቤቱ የእስልምና አንኳር እሴቶችን በተለይም የፈጣሪያችንን አሏህ፣ የነቢያትን፣ የመለኮታዊ መፃህፍትንና የደጋግ ተከታዮችን ክብር የሚያጎድፉ ማንኛውም አይነት የጥላቻ ትንኮሳና ድርጊት በህግ አግባብ እንዲታረሙ ተቋማዊ ኃላፊነቱን የሚወጣም ይሆናል፡፡

ለእውነተኛ ሰላምና አብሮነት የሚቆረቆሩ አካላት ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዙና ለፍትህ እንዲሰሩም ጠቅላይ ም/ቤቱ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

6.4k 0 8 12 105



ኦክሎክ ሞተርስ ከማህበራት ጋር እርቅ መፈፀሙን አስታወቀ።

#FastMereja I ኦክሎክ ሞተርስ ከማህበራት ጋር እርቅ መፈፀሙን ዛሬ መጋቢት 01/2017 ዓም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለፀ።

ኦክሎክ ሞተርስ ለ65 ማህበራት ተሽከርካሪ ለማቅረብ ውል ፈፅመው ወደ ስራ ገብተው የነበረ ሲሆን በኦክሎክ እና በማህበሩ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት 16 ማህበራት በድርጅቱ ላይ ክስ መስርተው የነበረ ሲሆን ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ ስድስት ማህበራት ክስ አቋርጠው እርቅ መፈፀማቸውን አስታውቋል።

በእርቁ መሰረት የማህበሩ አባላት መኪና የሚፈልጉ በሶስት ወራት ውስጥ መኪና ማስረከብ፣ ለቅድመ ክፍያ የከፈለው ክፍያ ተመላሽ እንዲደረግለት የፈለገ ደንበኛ በ45 ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ተመላሽ እንዲደረግ ተግባብተን ወደ ትግበራ ስራ ገብተናል ብሏል።

ባለፈዉ ዓመት 800 የሚጠጉ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች ማስተላለፋቸውን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁን ገልጸው በያዝነዉ የበጀት ዓመት 400 ገደማ ተሸከርካሪዎችን ማስተላለፋቸውን ተናግሯል።

#ቢዝነስ


#መምህሩን በሃይማኖት የመሰለው አብሪ ኮከብ 

ቅዱሱ ታላቅ የሃይማኖት ጠበቃ ሲሆን የተወለደው ግብጽ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው፡፡ ሲሆን በምግባሩ፣ በትምሕርቱ ለምዕመናን ጥቅም ሆኗቸዋል፡፡ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ገና ልጅ ሳለ ምሥጢረ ክርስትናን ይማር ዘንድ ወደ ተፍጻሜተ_ሰማዕት ቅዱስ_ዼጥሮስ ሔዷል፡፡ ቅዱስ ዼጥሮስ የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክና ሊቅ ሲሆን በታሪክ የዘመነ ሰማዕታት መጨረሻ ተብሎ ይታወቃል፡፡ እርሱ ያስተማራቸው ብዙ አርድእት ቢኖሩም 3ቱ ግን ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ አኪላስ ውዳሴ ከንቱ ወዳጅ፣ ሆዱ ዘመዱ፣ አርዮስ ደግሞ ወልድ ፍጡር ያለ የቤተ ክርስቲያን ጠላት ሆኑ፡፡ አኪላስ ስለ ምንም የማይጨንቀው ሰው ነበር፡፡ ደጉ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በሃይማኖት በመመሰል በጾምና በጸሎት እየተጋ መምሕሩን ቅዱስ ዼጥሮስን ለመተካት ለመምሰል ይጥር ነበር::

ወቅቱ ዘመነ ሰማዕታት እንደ መሆኑ ቅዱሱ ከመምሕሩ ጋር ብዙ ነገሮችን አሳልፏል፡፡ አርዮስ ክዶ ቅዱስ ዼጥሮስ ካወገዘው በሁዋላ እንደ ባልንጀራ ገስጾ ሊመልሰውም ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን የአርዮስን ክፋት ከጌታ ዘንድ የተረዳው ቅዱስ ዼጥሮስ ደቀ መዝሙሩን እለእስክንድሮስን ጠርቶ መከረው፡፡ "እኔ ከሞትኩ በሁዋላ አኪላስ ይተካል:: ከአርዮስ ጋር ስለሚወዳጅ በ6 ወሩ ይቀሠፋል:: አንተ ግን ከአርዮስ መርዝ ተጠበቅ" አለው:: ይህንን ካለው በሁዋላ ወታደሮች የቅዱስ ዼጥሮስን አንገት ቆረጡ:: ይህ የተደረገውም እ.ኤ.አ በ311 ዓ/ም ነው:: ወዲያውም አኪላስ ተሾመ:: እንደ ተባለውም ከአርዮስ ጋር ስለተወዳጀ በ6 ወሩ ተቀሰፈ:: በዚያው ዓመትም ቅዱስ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ ወይም ግብጽ 19ኛ ፓትርያርክ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ::

ሊቁ ሲሾም መልካም አጋጣሚ የነበረው ያ የመከራ ዘመን ማለፉ ሲሆን በጣም ከባዱ ግን የአርዮስ ተከታዮች ከተገመተው በላይ መበብዛታቸው ነው፡፡ ቅዱሱ በዽዽስ መንበሩ ለ17 ዓመታት ሲቆይ ዕንቅልፍና ዕረፍትን ትቶ እየጾመ፣ እየጸለየ፣ ምዕመናንን ከአርዮስ የኑፋቄ መርዝ ለመታደግ በቃልም በደብዳቤም መሸ ነጋ ሳይል ሕዝቡን እያስተማረ ታግሏል፡፡ በመጨረሻም በ325 ዓ.ም በንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አዋጅ በተዘጋጀው የኒቂያ ጉባኤ ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ካሳለፉ ከ318 ሊቃውንት ጋር አውግዞታል ለይቶታል፡፡ በጉባኤው መጨረሻም ጸሎተ ሃይማኖትን ሠርተው፣ መጽሐፈ ቅዳሴ ደርሰው፣ 20 ቀኖናወችን አውጥተው፣ አሥራው መጻሕፍትን ወስነው፣ ቤተ ክርስቲያንን በዓለት ላይ አጽንተው ተለያይተዋል:: የዚህ ሁሉ መሪ ደግሞ ቅዱስ እለእስክንድሮስ ነው::

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወልድ ዋሕድ፣ አምላክ ወልደ አምላክ፣ የባሕርይአምላክ፣ መሆኑን መስክሮ ክብርን አግኝቷል፡፡ የእምነታችንም መሠረቱ ይሔው ነው፡፡ ክርስቶስን ከአባቱ ጋር በመለኮቱ የሚተካከል ብለው ካላመኑ እንኩዋን ድኅነት ክርስትናም አይኖርም፡፡ ከጉባኤ ኒቅያ በሁዋላ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመልካሙ ጐዳና ሲጋደል ምዕመናንንም ሲያጸና ኑሯል፡፡ ዘወትር ወንጌልን በፍቅር ያነብ ነበርና ሲጸልይ የብርሃን ምሰሶ ይወርድለት ነበር፡፡ ስለ ውለታውም ቤተ ክርስቲያን በግብጽ ካበሩ 5ቱ ከዋክብት ሊቃውንት እንደ አንዱ ታከብረዋለች፡፡ ቅዱሱ ሊቅ በ328 ዓ.ም ዐርፎ በክብር ተቀብሯል፡፡


ገዳማዊያን በዓለም ላለነው ለኛና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገራችንም ይጸልያሉ፡፡ ገዳማቸውን በመርዳት፣ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡ 


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ለJesus Winner Ministry ለተሰኘ እምነት ተቋም የሰጠው 20 ሚሊዮን ሽልግ በናይሮቢ ተቋሞ አስነሳ።


የኮሪደር ልማት መብራቶችን የሰረቀው ተከሳሽ በ5 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

#FastMereja I ወንጀሉ የተፈጸመው የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 8:00 ሠዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዋሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተከሳሽ ሄኖክ መኮንን በኮሪደር ልማት ላይ የተገጠሙ መብራቶችን ቆርጦና ነቅሎ በመውሰድ ሊያመልጥ ሲል በወቅቱ ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል።

ተከሳሽ ላይም ተገቢው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማደራጀት ምርመራ ተጣርቶበት በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፤

የተከሳሽን መዝገብ የተከታተለው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሄኖክ መኮንን ጥፋተኛ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ተከሳሽን ያርማል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስተምራል በማለት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

Via: ብስራት ሬዲዮ

#ችሎት


ተወዳጇ ድምጻዊት ትዕግስት አፈወርቅ በሞት ባጣነው ወንድሟ ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ስም 100 ሺህ ብር የለገሰች ሲሆን አንዲሁም በየአመቱ የድምጻዊውን ሙት አመት በማስመልከት 100 ሺህ ብር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 30 ሚሊዮን ብር አበረከተ።

አቶ አቤ እንዳሉት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች እና ማኔጅመንት አባላት የተሰበሰበ 18 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ባንኩ 12 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ በድምሩ 30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሁኑን ድጋፍ ሳይጨምር ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለማዕከሉ 205 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል።

Показано 20 последних публикаций.