📌
የዝሙት አደገኛነት! ዝሙት : የአለምን ስርዓት የሚያናጋ ከመሆኑ ባሻገር ፣ ዘርን ከመጠበቅ ፣ ብልቶችን ከጥፋት ከመከላከል ፣ የአላህን ህግጋት ከማስከበር ፣ በሰዎች መካከል የሚከሰተውን ከፍተኛ ጠላትነት እና ጥላቻ ከመግታት አኳያ ደንቃራ የሆነ ጸያፍ ተግባር ነው።
ዝሙት ፡ የጓደኛውን ፣ የሴት ልጁን ፣ እህቱ፣ እናቱን ከማባለግ አኳያ የአለምን ስርዓት በጽኑ አዛብቶታል፡፡ የዝሙት ወንጀል በደረጃ ንጹህ ነፍስ ከመግደል ቀጥሎ የሚገኝ ነው፡፡ ለዚህ ነው አላህ በቁርዓኑ ፣ ረሱል ﷺ ደግሞ በሱናቸው ሁለቱን ወንጀሎች አቆራኝተው የተናገሩት፡፡
ኢማም አህመድ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል ፡ "لا أعلم بعد قتل النفس شيئا أعظم من الزنى" “ከነፍስ መግደል በኋላ ከዝሙት የከበደ (ወንጀል) አንድም አላውቅም” የዝሙትን ሀራምነት አላህ አጠናክሮ ነው የተናገረው ፡
"وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا
يُضَاعَفْ لَهُ الْعَذَابُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِ مُهَانًا
إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا"
"እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል፡፡ በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል፡፡ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡" (ፉርቃን ፡ 68-70)
ዝሙትን ፡ ከሽርክ እና ነፍስን ከመግደል ጋር አቆራኝቶታል፡፡
የዝሙት ቅጣት ባሪያው በተውበት ፣ በኢማን እና በመልካም ስራዎች ካልተማር በቀር በጀሀነም ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናገረ ፡
وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!" (ኢስራእ ፤32)
አሏህ የዝሙት ተግባር ጸያፍ እንደሆነ በተከበረው ቁርዓን ተናግሯል፡፡ የዚህን ተግባር ጸያፍነት ከሰው ልጆች አልፎ ከእንሰሳቶች በርካቶቹ የሚጸየፉት እንደሆነ ቡኻሪ በሶሂህ ኪታባቸው ዘግበዋል፡፡
ቡኻሪ በዘገቡት አምር ብን መይሙን አልአውድይ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
"رأيت في الجاهلية قردا زنى بقردة ، فاجتمع القرود عليهما فرجموهما حتى ماتا" “በጃሂልያ አንድ ዝንጀሮ ሌላዋን ዝንጀሮ ዝሙት ሲሰራት ተመለከትሁ፡፡ ከዚያም (ከተለያየ አቅጣጫ) ዝንጀሮዎች ተሰባሰቡ (ዝሙት በፈጸሙት) ሁለቱ ዝንጀሮዎች ላይ በዲንጋይ ቀጥቅጠው የሞት ቅጣት ብይን ፈጸሙባቸው፡፡” የዝሙት መንገድ የከፋ እንደሆነ አላህ በቁርዓኑ ተናግሯል፡፡ ዝሙት የጥፋት መንገድ ነው ፤ ዝሙት የቅጣት መንገድ ነው ፤ ዝሙት በአኼራ የቅጣት ፣ የውርደት እና የመቀጣጫ መንገድ ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርዓን የሚከተለውን ተናግሯል
وَلَا تَنكِحُوا مَا نَكَحَ آبَاؤُكُم مِّنَ النِّسَاءِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۚ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَمَقْتًا وَسَاءَ سَبِيلًا
"ከሴቶችም አባቶቻችሁ ያገቡዋቸውን አታግቡ፡፡ (ትቀጡበታላችሁ)፡፡ ያለፈው ሲቀር፡፡ እርሱ መጥፎና የተጠላ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!" (ኒሳእ ፡ 22)
አላህ የባሪያውን ከውርደት ከእሳት መዳን ብልቱን ከመጠበቅ ጋር አያይዞታል፡፡ ከእርሱ ውጭ የመዳኛ መንገድ የለም፡፡
"قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ وَالَّذِينَ هُمْ عَنِ اللَّغْوِ مُعْرِضُونَوَالَّذِينَ هُمْ لِلزَّكَاةِ فَاعِلُونَ وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ
إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ"
"ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡እነዚያም እነርሱ ዘካን ሰጭዎች፡፡እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው፡፡" (ሙእሚን ፡ 1-7)
ይህ የቁርዓን አንቀጽ ሶስት ነገሮችን አቅፏል፡
-ብልቱን ያልጠበቀ ከውርደትና ከቅጣት ነጻ አይወጣም
-ዝሙት የሚፈጽም ሰው ተወቃሽ ይሆናል
-ዝሙት የሚፈጽም ሰው ድንበር አላፊ ነው
በዚህ ምክንያት አላህ ፣ ምእመናን (ባእድ ሴቶችን ፣ ባእድ ወንዶችን) ሲመለከቱ አይናቸውን እንዲመልሱ ፣ ብልታቸውን እንዲጠብቁ አዟል፡፡
يَعْلَمُ خَائِنَةَ الْأَعْيُنِ وَمَا تُخْفِي الصُّدُورُ
"(አላህ) የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡"(ጋፊር ፡ 19)
የዝሙት በእይታ የሚጀምር በመሆኑ አይናቸውን (አጅነብይ ከሆኑ አካላት) እንዲመልሱ ምእመናንን አዘዘ፡፡ አላህ አይንን ባእድ አካላትን ከመመልከት መመለስን ፣ ብልትን ከመጠበቅ አስቀደመው፡፡ ከባድ የእሳት ቃጠሎ የሚጀምረው ከትናንሽ ቃንቄዎች ነው፡፡ የዝሙት መነሻውም እይታ ነው፡፡
መጀመሪያ ፡ እይታ ይቀድማል ፣ ልብ ያስባል ፣ ከዚያም ወደዝሙት ቦታ ይንቀሳቀሳል ፣ መጨረሻም ዋናውን ሐጢያት ይፈጸማል፡፡ በዚህ ምክንያት ፡ እነዚህን አራት ነገሮች የጠበቀ ዲኑን ጠበቀ ፡
-(ባእድ ሴቶችን) መመልከትን ፣
-በልቦና ትዝታን ፣
-(ከባእድ ሴቶች ጋር) ንግግርን ፣
-(ወደዝሙት) እንቅስቃሴ ማድረግን
እያንዳንዱ ባሪያ ከእነዚህ አራት በሮች የነፍሱ ዘበኛ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ሁሌ በእነዚህ በሮች መሽጎ ሊጠባበቅ ይገባል - ጠላት የሚገባው በእነዚህ አራት በሮች ነውና፡፡
الداء والدواء : العلامة ابن قيم الجوزية : ص\213- 214
https://t.me/alateriqilhaqكن على بصيرة