👉 ለሞተ ሰው ሶደቃ ማድረግ
ለሞተ ሰው ሶደቃ ማድረግ የሚቻል ለመሆኑ በሙስሊሞች መካከል ኺላፍ የለም ። በተቃራኒው ደግሞ የሟች ቤተሰብ የሞተባቸው ቀን ሙስሊሞች ሰርተው ሊያበሉዋቸው ነው ሸሪዓችን ያዘዘው ። እንደዚሁ ሶስተኛ ቀን ፣ ሰባተኛ ቀን ፣ አርባኛ ቀን ብሎ ማረድ የተከለከለ ነው ። ወደ ሞተ ሰው ለመቃረብ ብሎ ማረድ ወይም ቀብር ጋር ወስዶ ማረድም አይፈቀድም ። እነዚህ ተግባራት በቀጥታ ሽርክ አሊያም ወደ ሽርክ መዳረሻ ይሆናሉ ። ከዚህ ውጪ በማንኛውም ቀን የሞተውን ሰው አላህ እንዲምረው ነይቶ አርዶ ቢያበላ ለሟቹም ሆነ ለሶደቃ አድራጊው የሚጠቅም ለመሆኑ ዑለሞች ያረጋገጡት ነው ። ይህን አስመልክቶ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ እንዲህ ይላሉ : –
سؤال : إن أنا تصدقت عن والدي، فهل يصيبني نفس الأجر، حيث أن والدي متوفى، وأرجو بيان الأوجه التي يمكن الإنفاق فيها عن الميت، وهل الدعاء أفضل من هذا كله
الجواب :
الصدقة عن الميت مشروعة ومفيدة ونافعة للميت، وقد ثبت في الصحيحين عن النبي ﷺ أنه سئل عن ذلك قال له رجل: «يا رسول الله! إن أمي ماتت أفلها أجر إن تصدقت عنها، قال: نعم فالصدقة تنفع الميت، ويرجى للمتصدق مثل الأجر الذي يحصل للميت؛ لأنه محسن متبرع، فيرجى له مثل ما بذل، كما قال عليه الصلاة والسلام: من دل على خير فله مثل أجر فاعله.
فالمؤمن إذا دعا إلى خير، أو فعل خيرًا في غيره يرجى له مثل أجره، فإذا تصدق عن أبيه، أو عن أمه، أو ما أشبه ذلك، فللمتصدق عنه أجر وللباذل أجر، وهكذا إذا حج عن أبيه أو عن أمه فله أجر ولأبيه وأمه أجر، ويرجى أن يكون مثلهم أو أكثر؛ لفعله الطيب وصلته الرحم وبره لوالديه، وهكذا أمثال ذلك فضل الله واسع.
وقاعدة الشرع في مثل هذا أن المحسن إلى غيره له أجر عظيم، وأنه إذا فعل معروفًا عن غيره يرجى له مثل الأجر الذي يحصل لمن فعل له ذلك المعروف، وقد قال عليه الصلاة والسلام: إذا مات ابن آدم انقطع عمله إلا من ثلاث: صدقة جارية، أو علم ينتفع به، أو ولد صالح يدعو له.
فأنت -يا عبد الله- في صدقتك عن والديك، وفي إحسانك إلى عباد الله بما تفعله من المعروف لك فيه أجر عظيم، ولمن أحسنت إليهم بأن علمتهم وقبلوا منك، وأرشدتهم وقبلوا منك، ودللتهم على الخير وقبلوا منك لهم أجر أيضًا ولك مثلهم. نعم.
نور على الدرب
በኡለሞች መካከል ኺላፍ ያለው አንድ ሰው ለሞተ ሰው ሶደቃ አድርጎ ሰዋቡን ለእገሌ ይሁን ማለት ይችላል ወይስ አይችልም በሚለው ነው ። ነገር ግን ጁሙሁሮቹ ዑለሞች እንደ ሐንበሊዮች ፣ ሐነፊዮች ፣ ማሊኪዮችና ከፊል ሻፊዒዮች ይቻላል ይላሉ ። ቀጥለን የተወሰኑትን የዑለሞች ንግግር እናያለን : –
قال الإمام أحمد :
" الميت يصل إليه كل شيء من الخير للنصوص الواردة فيه، ولأن المسلمين يجتمعون في كل مصر، ويقرءون، ويهدون لموتاهم من غير نكير، فكان إجماعاً، وكالدعاء والاستغفار".
المبدع في شرح المقنع (2/281)
وقال شيخ الإسلام ابن تيمية – رحمه الله تعالى – :
" وقد صح عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه أمر بالصدقة على الميت، وأمر أن يصام عنه الصوم، فالصدقة عن الموتى من الأعمال الصالحة، وكذلك ما جاءت به السنة في الصوم عنهم، وبهذا وغيره احتج من قال من العلماء،………… " انتهى من الفتاوى
وقال ابن قدامة رحمه الله :
" وَأَيُّ قُرْبَةٍ فَعَلَهَا , وَجَعَلَ ثَوَابَهَا لِلْمَيِّتِ الْمُسْلِمِ , نَفَعَهُ ذَلِكَ , إنْ شَاءَ اللَّهُ " انتهى
من المغني (2/226) .
ሰዋቡን ለእገሌ ማለት አይቻልም የሚሉ ዑለሞች ያሉ ሲሆን ከመረጃ አንፃር ተመዛኝ ነው ። ሀገራችን ላይ በተለይ በሰሜኑ ክፍል ሰው ሲሞት በሶደቃ ስም ከሽርክና ቢዳዓ ጋር የተገናኘ ተግባር በብዛት የሚፈፀም ሲሆን በሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች ከዚህ ጋር በተገናኘ ሙኻለፋዎች አሉ ። ይሁን እንጂ እነዚህን ሙኻለፋዎች ለይቶ ማውገዝና ማስተማር ሲገባ በጥቅሉ ለሞተ ሰው ሶደቃ የለም የሚሉ እንደውም የሱና ኡስታዞች ከሚባሉትም ጭምር መኖራቸውን እየሰማን ነው ። ከዚህም አልፎ ከላይ ከተጠቀሱት ሙኻለፋዎች በፀዳ መልኩ አርዶ በማብላት ሶደቃ ያደረገን ሰው ከሱና እስከማስወጣት ይደርሳሉ እየተባለ ነው ።‼ ለእነዚህና ለሌሎችም ወንድሞች ይጠቅም ዘንድ የዑለሞችን ንግግር መሰረት ባደረገ መልኩ ይህችን ማስታወሻ ጀባ ብያለሁ አላህ የምትጠቅም ያድርጋት ።
https://t.me/bahruteka