Postlar filtri


ወጣቶች በሰላም ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ ተጠየቀ

የምዕራብ ጎጃም ዞን ወጣቶች ሊግ ከወጣቶች ጋር የሰላም እና ልማት የንቅናቄ መድረክ በፍኖተ ሰላም ከተማ እያካሄደ ነው።

በድረኩ የተገኙት በምዕራብ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ የፓለቲካ ዘርፍ ኀላፊ አቶ ሙላት ጌታቸው የአንድ ሀገር እድገት መፋጠን የወጣቶች ሚና የጎላ መኾኑን ገልፀዋል ። ወጣቶች በልማት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ሁሉ በሰላም ግንባታ ላይም አተኩረው መስራት እንደሚያስፈልግ ነው የጠቆሙት ።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ወጣቶች ሊግ ሀላፊ አቶ በላቸው ፈጠነ የአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚረጋገጠው የሀገሪቱን ሀብት በተገቢው መንገድ መጠቀም ሲቻል ብቻ ነው ። በመሆኑም ሀብት ሊፈራ የሚችለው ሰላም ሲረጋገጥ ሲቻል በመኸኑ ወጣቶች የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።


በክልሉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ለሚሰጣቸው ተልዕኮ መዘጋጀታቸውን የአድማ መከላከል እና መደበኛ ምልምል ሰልጣኞች ተናገሩ፡፡

አማራ ፖሊስ፡- ጥር 29/2017 ዓ.ም
በብርሸለቆ የመሠረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ት/ቤት ስልጠናቸውን እተከታተሉ የሚገኙ የ33ኛ ዙር የአድማ መከላከል እና መደበኛ ፖሊሰ ሰልጣኞች የስልጠና እንቅስቃሴ የተገመገመ ሲሆን በጥሩ ወታደራዊ ስነ ምግባር የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በስኬት ማጠናቀቅ በሚቻልበት ቁመና ላይ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡

የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የሰልጠናው አሰተባባሪ የሆኑት ኮማንደር አብዩት ሽፈራው እየተሠጠ የሚገኘው ሰልጠና ሰልጣኞች ሰልጠናውን ሲያጠናቅቁ በክልሉን ህግና ሰርዓት በማሰከበር የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሂደት ውሰጥ ትልቅ ሀላፊነት የሚጠበቅባቸው በመሆኑ በፖሊሳዊ እወቀት፣ አመለካከት እና ሙያዊ ሰነ-ምግባር ማብቃት ላይ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በቁርጠኝነት እንዲሁም በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን አንሰተው የተሻለ የፖሊሰ ሠራዊት ለመገንባት ከዚህ የበለጠ ትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።


በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ታጥቀው በጫካ የነበሩ በሰላም እጃቸውን ተሰጥተዋል።

አማራ ፖሊስ፡ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም
በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ የሰላም አማራጩን የተቀበሉ የታጠቁ ሀይሎች ወደ ሰላማዊ አማራጭ መጣታቸውን የወረዳው ፖሊስ ገልጿል።
ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም የያዙት ትግል የተሳሳተ መሆኑን በመገንዘብ የሰላም አማራጩን ተቀብለው በሰላም ከህዝባቸው ጋር ለመቀላቀል ከ17 የታጣቂው አባላት 5 ከነትጥቃቸው እና 12 በጀሌ እጅ ሰጥተው ወደ ተሃድሶ በሰላም ገብተዋል ፡፡
ምንጭ ፡- የደ/ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ፖሊስ ኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ነው።


የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ በዞኑ አጠቃላይ የ2017 የሰላምና ፀጥታ ስራዎች ዙሪያ የስድስት ወራት የተግባራት አፈፃፀም ግምገማ ማካሄደ ጀመረ

አማራ ፖሊስ፦ጥር 28/2017 ዓ.ም

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ በዞኑ አጠቃላይ የ2017 የሰላምና ፀጥታ ስራዎች ዙሪያ የ6 ወራት የተግባራት አፈፃፀም ግምገማ በገንዳ ውሃ በዛሬው ዕለት ማካሄደ ጀመሯል።

ሰላምና ፀጥታ መምሪያው በዞኑ የሰላምና ፀጥታ ግምገማ መክፈቻው ላይ የምዕራብ ጎንደር ዞን ተወካይ አስተዳዳሪና የዞኑ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉአለም ታደሰ፣የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ምስጋናው ካሴን ጨምሮ ሌሎች የዞን፣የወረዳና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እዲኹም የሰላምና ፀጥታ አጋር አካላት ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ አጠቃላይ የዞኑን ሰላም በዘላቂነት ለማጽናት የሰላም ማስከበር ተግባራትን ለማጠናር የሚስችሉ ተግባርና ስራዎች በዞኑ ምኒሻ መምሪያ ተወካይ ኃላፊ በአቶ ባይመሽ ሰንደቄ ሪፖርቱ እየቀረበ ይገኛል።

በግምገማው በዞኑ የ2017 የሰላምና የፀጥታ ተግባር ዕቅድ ላይ በመወያየት ማጽደቅና ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተመልክቷል።

📷 West Gondar zone Communication


የክልሉን ሰላም በዘላቂነት ለመፍታት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ የቋሚ ኮሚቴ አባላት አሳሰቡ።

አማራ ፖሊስ: ጥር 27/2017 ዓ.ም

የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።

ቋሚ ኮሚቴው የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማቱን የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል።

የቋሚ ኮሚቴ አባላትም የጸጥታ ተቋሙ የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ እየከፈለው ያለው መስዋዕትነት ክብር የሚያሰጠው መኾኑን ገልጸዋል። በራስ አቅም የአካባቢን ሰላም ለማረጋገጥ እየተሠራ ያለው ሥራም የሚበረታታ ነው ብለዋል።

መስዋዕትነት እየከፈለ በሠራው ሥራ በክልሉ አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣ አድርጓል ነው ያሉት። የጸጥታ ኀይሉ ለሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት በጀግንነት እየታገለ ነው፣ ለዚህ ክብር ልንሰጠው ይገባል ብለዋል።

የጸጥታ ችግሩን ሕግ በማስከበር ብቻ ሳይኾን በእርቅ እና በይቅርታ ለመፍታት እየተሄደ ያለው ርቀትም የሚበረታታ ነው ብለዋል።

የጸጥታ ተቋሙ የክልሉን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመመለስ መስዋዕትነት ከመክፈል ባሻገር ውይይትን እንደ አማራጭ መጠቀም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ነው ያሉት።

ከሕዝብ ጋር ጥብቅ ቁርኝት መፍጠር እንደሚጠበቅበትም አንስተዋል። የክልሉን ግጭት በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ በመቋጨት ሕዝቡን ከተራዘመ ጦርነት መውጣት ይጠበቃል ነው ያሉት።

የሰላም እና የጸጥታ ተቋማት የሕዝብን መታገት፣ መገደል እና መጎዳት ማስተካከል እንደሚገባቸውም ገልጸዋል። የጸጥታ ኀይሉን መፈተሽ እና ታማኝነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።

ለሕዝብ የሚሠሩ እንዳሉ ሁሉ መረጃ የሚያወጡ ከመንግሥት በተቃራኒ የሚሠሩ የጸጥታ ኀይሎች አሉ ነው ያሉት።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/share/p/19qZHk8Zts/


በወረታ ከተማ በተደረገ ኦፕሬሽን ውጤታማ ተግባር መከናወኑን የወረታ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አስታወቀ።

በወረታ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኘው ቋሃር ሚካኤል በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ በዛሬው ዕለት ማለትም ጥር 27/2017 ዓ.ም እረፋድ ላይ በነበረው የሰላም ማስከበር ኦኘሬሽን በፅንፈኛው ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን መደረጉን የወረታ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች በወሰዱት የጸጥታ ማስከበር ኦኘሬሽን እርምጃ ላይ 5 የፅንፈኛ ቡድን መደምሰሱንና 8 የጠላት ቡድን ደግሞ መቁሰሉን እንዲሁም 1 ብሬንና 4 ክላሽ የጦር መሣሪያዎች መማረካቸውን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

በተደረገው ኦኘሬሽን ላይ ከመንግስት ጸጥታ አስከባሪና ታጣቂ ኃይሎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱንና ይህም ድል የተገኘው በተደራጀና በተቀናጀ የመረጃ መዋቅር ፣በወረታ ከተማ አስተዳደር ጸጥታ አስከባሪ ኃይሎችና አድማ ብተና እንዲሁም በፎገራ ወረዳ አጋዥ አድማ ብተናና የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት መሆኑን በጽ/ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።

መረጃው፦የወረታ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬን ነው።


"ለፍትህ ስርዓቱ ውጤታማነት በትብብር መስራት ይገባል"
ምክትል ኮሚሽነርና የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኀላፊ ረ/ኮሚሽነር ውበቱ አለ
አማራ ፖሊስ፡ጥር/2017 ዓ.ም

የአማራ ክልል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሰድስት ወራት አፈፃፀምን በገመገመበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ውበቱ አለ በዘንድሮው ግማሽ ዓመት በተፈለገው አግባብ ተንቀሳቅሶ ለመስራት እንቅፋቶች ቢኖሩም በብዙ ችግሮች ውስጥ ሆኖ በግማሽ ዓመቱ ከቀረቡ 5453 መዝገቦች 4725ቱ ተጣርተው ለዐቃቤ ህግ ተልከዋል። ይህም የምርመራ የማጣራት ዐቅምን 86.9 በመቶ ያደርሰዋል ብለዋል።
ምንም እንኳን ወቅቱ ፈታኝ ቢሆንም በተፋጠነ የፍትህ ስርዓት መታዬት ከነበረባቸው 1108 መዝገቦች 956ቱን በማቅረብ 86.4 በመቶ መፈፀምም ተችሏል።

በወንጀል ምርመራ ዘርፍ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ም/ዘርፍ ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ በበኩላቸው የነበሩንን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለዬት ድክመቶቻችንን አርመን የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይኖርብናል ብለዋል።


የሕዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ወታደራዊ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውን የፍኖተ ሰላም ተመራቂ ሚሊሻዎች ተናገሩ።

አማራ ፖሊስ: ጥር 26/2017 ዓ.ም

በፍኖተ ሰላም ማዕከል ሥልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ የፍኖተ ሰላም ቀጣና የ2ኛ ዙር የሰላም አስከባሪ እና የሚሊሻ አባላት የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

ተመራቂዎቹ የአካባቢያቸውን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል አካላዊ እና ወታደራዊ ሥልጠናዎችን በሚገባ ስለመውሰዳቸው በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ሠራዊት የሰላም ማስከበር ማዕከል ኀላፊ ሜጀር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴን ጨምሮ የዞን እና የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር መሪዎች ተገኝተዋል።


‘’የጸጥታ መዋቅሩን እና የኅብረተሰቡን አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም ዘላቂ ሰላም የማፅናት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል’’ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር

አማራ ፖሊስ፦ ጥር 26/2017 ዓ/ም
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ሕግ የማስከበር ሥራ አፈፃፀም እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ገምግሟል። ከሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው ግምገማው የተካሄደው።

በግምገማ መድረኩ የተገኙት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክትል አሥተዳዳሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ኀላፊ አይተነው ታዴ እንደ ክልል የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማስከተሉን ተናግረዋል።

የጸጥታ መዋቅሩ በጠንካራ ሕዝባዊ ድጋፍ ታጅቦ በከፈለው መስዋዕትነት የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው መመለሳቸውንም ምክትል አሥተዳዳሪው ገልጸዋል።

የፀጥታ መዋቅሩን እና የኅብረተሰቡን አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም የብሔረሰብ አሥተዳደሩን ዘላቂ ሰላም የማፅናት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ምክትል አሥተዳዳሪው አንስተዋል።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ጌታቸው ቢሻው የሕይዎት እና የአካል መስዋዕትነት ተከፍሎበት የተገኘው ሰላም እንዳይቀለበስ ዘላቂ ሰላምን የማስፈን ሥራ ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

በብሔረሰብ አሥተዳዳሩ አሁን እየመጣ ላለው ሰላም የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የኅብረተሰቡ ሚና የጎላ እንደኾነም ኀላፊው አንስተዋል።

የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት በሠሩት ሥራ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከ240 በላይ የታጠቁ ኀይሎች የመንግሥት እና ሕዝብ የሰላም ጥሪን ተቀብለው ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቅለዋልም ነው ያሉት።

የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር እሱባለው መኮንን በበኩላቸው ለሕገ መንግሥቱ እና ለሕዝብ ዘብ የቆመ የጸጥታ መዋቅር በመገንባት ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።


በፀጥታው ችግር ምክንያት ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የሴቶችን የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ገለፀ።

የምዕራብ ጎጃም ሴቶች ፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶች የተደራጀ እና ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት ግንባታ በሚል መሪ ቃል ከሴት የመንግስት ሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ በፍኖተ ሰላም ከተማ አካሂዷል።

መድረኩ ላይ የተገኙ በምዕራብ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፓለቲካ ዘርፍ ኀላፊ አቶ ሙላት ጌታቸው በክልሉ የገጠመውን የሰላም እጦት በኢኮኖሚ ፣ በፓለቲካ እና ማህበራዊ ዘርፎች በርካታ ቀውሶች እያደረሰ መኾኑን ተናግረዋል።

ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የመጀመሪያ ተጠቂዎች ሴቶች መኾናቸውን ገልፀው ለሰላም ግንባታ የሴቶች ሚና የጎላ በመኾኑ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ሴቶች በማህበራዊ ፣ በፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ሰላምን ለመጠበቅ እና ለማሳደግ አይነተኛ አበርክቶ አለው ።

በፀጥታው ችግር ምክንያት ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የሴቶች ማህበራትን በማስተባበር የመደገፍ ስራ እየተሰራ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ሴቶች ፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ስለእናት ዘሪሁን ተናግረዋል ።

በተለይም የሴት አደረጃጀቶችን በማጠናከር ሴቶች ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ፤ ታጥቀው ወደ ጫካ የገቡ ኃይሎችም ፊታቸውን ወደ ሰላም እንዲያዞሩ ነው ወ/ሮ ስለእናት የጠየቁት።

ሴቶች በማህበራዊ ፣ ፓለቲካ እና ኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ሁሉ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የሰላም ግንባታ ሂደት ላይ ተሳትፏቸውን የማጠናከር ስራ እየተከናወነ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን ሴቶች ሊግ ኀላፊ ወ/ሮ አክሊለ ዞማነህ ገልፀዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉ ሴት የመንግስት ሰራተኞችም የፀጥታ ችግሩ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ቅድሚያ በመስጠት እና ከዚህ የከፋ ችግር ሳይከሰት ሁሉም አካላት ለውይይት እና ለድርድር ዝግጁ መሆን አለባቸው ለዚህ ደግሞ ሁሉም ማህበረሰብ ሊረባረብ ይገባል ነው ያሉት።



11 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.