Postlar filtri


በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ
****************

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ይጫወታሉ፡፡

የዘሪሁን ሸንገታው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ18 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በጨዋታው ባለድል ከሆነ እስከ 9ኛ ደረጃ ድረስ መምጣት ይችላል፡፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ በዘንድሮው ዓመት እየተቸገሩ ካሉ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን፤ በደረጃ ሰንጠረዡም 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፤ ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ከዚህ በኋላ ባሉት ጨዋታዎች ውጤታማ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚካሄደው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሀዋሳ ከተማ እና መቻል ይገናኛሉ፡፡
https://web.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid0286MLBy2UkxkLoXKC4aZWEBQXhoHNn4aeTKpoBd2icdZb1vNUABB4SVkM1BK4m8PGl


ከአያት በተወረሰ ፍቅር ኢትዮጵያን የሚያገለግሉት ምሁር፦ አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር)
**********************

ታዋቂ የማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት እና ተመራማሪ ናቸው። በኢትዮጵያ እድገት፣ ባህላዊ ቅርሶች እና ማህበራዊ ሽግግር ላይ ባደረጓቸው ሰፊ ጥናቶች ዕውቅናን አትርፈዋል።

የመልሶ ማቋቋም፣ የምግብ ዋስትና፣ ማህበራዊ ጥበቃ፣ ሀገር በቀል ዕውቀት እንዲሁም ባህላዊ የግጭት አፈታትን ጨምሮ የተለያዩ መስኮችን በጥናቶቻቸው በስፋት ዳስሰዋል።

አሉላ ፓንክረስት(ዶ/ር) የተወለዱት በአውሮፓውያኑ 1962 በኢትዮጵያ ነው። አባታቸው ሪቻርድ ፓንክረስት ህይወታቸውን ሙሉ ለኢትዮጵያ የሰጡት የሲልቪያ ፓንክረስት ልጅ ናቸው። እንዲሁም በጣሊያን ወረራ ወቅት ለኢትዮጵያ በመወገን ጠንካራ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩት ዝነኛ ጋዜጠኛ እና የመብት ተሟጋቿ ሲልቪያ ፓንክረስት አያታቸው ናቸው። ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮጵያ ያላቸው ጥልቅ ፍቅር በትምህርታቸው ምርጫ ላይ ጭምር ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) ከተለያዩ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር በርካታ ጥናታዊ ሥራዎችን በማሳተም ለኢትዮጵያ ማኅበራዊ የምርምር ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በተለይም ፍልሰት በቤተሰብ እና በማኅበረሰብ ላይ የሚያሳድረውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ የሚያብራሩ ሥራዎችን አበርክተዋል።

የአሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፍቅር ከአያት የተወረሰ ነው፡፡ አያታቸው ሲልቪያ ፓንክረስት የጣሊያንን የግፍ ወረራ ለዓለም ማኅበረሰብ ያጋለጡ ብርቱ የኢትዮጵያ ጠበቃ ነበሩ፡፡

ሙሉ ፅሁፉን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-
https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=9570


እስራኤል 110 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ልትለቅ ነው
****

የእስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በሶስተኛው ዙር የእስረኞች ልወውጥ እስራኤል 110 የፍልስጤም እስረኞችን ልትለቅ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከ110 ፍልስጤማውያን ጋር በምትኩ 3 እስራኤላዊያን እና 5 የታይላንድ ዜጎችን በድምሩ 8 ምርኮኞች በሃማስ እና በሌሎች የፍልስጤም ወገኖችም እንደሚለቀቁ ተገልጿል።

ከእስር የሚለቀቁት ግለሰቦች በዌስት ባንክ ወደሚገኘው ራዳና አካባቢ ይደርሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በእስረኞቹ ዝርዝር ውስጥ ቢያንስ 30 ሕፃናት የተካተቱ ሲሆን ይህም የእስራኤልና የፍልስጤም ግጭት በወጣት ትውልዶች ላይ የሚያሳድረውን ቀጣይነት ያለው ተጽዕኖ የሚያሳይ ስለመሆኑም ነው የተገለጸው።

ከእስር ከሚለቀቁት እስረኞች መካከል በፍልስጤም የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ ታዋቂው ዘካርያ ዙቢዲ ይገኝበታል ተብሏል።

እስረኞች መለቀቃቸውን ተከትሎ የተኩስ አቁም ስምምነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነፃ የወጡትን የፍልስጤማውያን እስረኞች ቁጥር እንደሚጨምርም ተነግሯል፡፡

በቅርብ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከ10 ሺህ የሚበልጡ ፍልስጤማውያን በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡

በሜሮን ንብረት


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በአሜሪካ አውሮፕላን እና ሄሊኮፕተር የተጋጩበት ክስተት #planecrash #jetcollides #USA #US #america #trump


የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
***************

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ከየካቲት 1 አስከ 2 2017 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ እ.ኤ.አ በ2019 የተቋሙ ኃላፊ ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ዋና ዳይሬክተሯ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ቅድሚያ በሚሳጣቸው ፖሊሲዎች እና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በኢትዮጵያ ስላለው የንግድ ሁኔታ እና በኢኮኖሚ እድሎች ዙሪያ ውይይት እንደሚያካሂዱም ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሀገሪቱ በማህበራዊ ልማት የተሰሩ ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል፡፡


አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ
**************

አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡

ምክር ቤቱ ባካሄደው ስብሰባ አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሹሟል።

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙት አቶ ብርሃኑ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ምክር ቤቱ ውይይት ሲደረግበት የነበረውን አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በህይወት አበበ


ሀገራዊ ለውጡ የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ያረጋገጠ ነው፦ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ
*****************

ሀገራዊ ለውጡ የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና አካታችነት ያረጋገጠ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ ፈዲላ ቢያ ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊዋ የብልፅግና ፓርቲ ምስረታና የፖለቲካ ለውጡ ትሩፋትን በተመለከተ በዛሬው የኢቲቪ አዲስ ቀን "የሀገር ጉዳይ" መሰናዶ ላይ ሀሳባቸውን አጋርተዋል፡፡

ከለውጡ በፊት ለዘመናት ሲንከባለል በመጣ የፖለቲካ ስብራት የዴሞክራሲ እና የእኩልነት ጥያቄ ሳይመለስ መቆየቱን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

ሁሉም ህዝብ በሀገር ጉዳይ እኩል መወሰን የሚችሉበትን እድል የፈጠረ የፖለቲካ አውድ መፈጠሩን አንስተዋል።

በዚህም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ እኩል ተሰሚና ውሳኔ ሰጭ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል ያሉት ኃላፊዋ፤ብልጽግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ለውጦችን አስመዝግቧል ሲሉ አክለዋል፡፡https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid028Bhhwu1SFPasuJtiHEVfdvQcYLzScgasiqr6V8WEn1if5iHezPynigNDaxk4sRfNl


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ማስታወቂያ
********

ቀላልና ምቹ የሆነውን የሲንቄ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ይጠቀሙ፡፡

Siinqee Mobile Banking


Tajaajila Moobaayil baankiingii Baankii Siinqee salphaa fi mijataa ta’e fayyadamaa.

Download use url https://bit.ly/SiinqeeMB and
activate, log in via USSD (*871#) and select option 12.

#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER


የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ሲጎበኙ በምስል፡-


የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ
***************

85ኛውን የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በዓል አስመልክቶ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ከአዊ ብሄረስብ አስተዳደር ጋር በመተባባር ያዘጋጀው ሲምፖዚየም መካሄድ ጀምሯል።

በሲምፖዚየሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዊ ብሄረስብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አይተነው ታዴ፤ እንኳን ለ85ኛው ታሪካዊውና አንጋፋው የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

ክብረ በዓሉን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አቶ አይተነው ገልፀዋል።

የአገው ፈረሰኞች ማህበር ለረጅም አመታት ሲጠይቅ የነበረው በእንጅባራ ከተማ ለገቢ ማስገኛ ቦታ 2 ሺህ 860 ካሬ ሜትር ቦታ መፈቀዱንም መናገራቸውን ከአስተዳደሩ ከሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
*****************

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ የ16ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔን ያጸደቀ ሲሆን አሁን ላይ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ላይ የቀረበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ እያዳመጠ ይገኛል፡፡

የረቂቅ አዋጁን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ በምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር ) ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እያቀረቡ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክር ቤቱ በቀጣይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

11 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.