አል ኢህሳን ኢሥላሚክ ቻናል


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


በጎ ተግባርን እንያዝ እንማማር ♥♥♥♥ እንዋደድ ነገ በአርሽ ጥላ ስር እንዲያካለን አል ኢህሳን የሙስሊሞች ጀመዐ

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ATC NEWS dan repost
⚠️ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን እና መሰለ አደገኛ ሊንኮች ከማንም ቢላክላቹህ በፍፁም እንዳትነኳቸው


በስህተት ላለመንካት ከላኪው ብታጠፉት ይመከራል።


በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለ አደገኛ ሊንክ ሲሆን አካውንታችሁንና የግል መረጃዎቻችሁን ያሳጣቹሃል👹👹


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


AMU- Muslim Students Union dan repost
መልዕክቱ ይሰራጭ‼
===============

#ScamAlert



✍ ኧረ! ይሄን የጥንቃቄ መልዕክት በአስቸኳይ ሼር አድርጉት!

ብዙ ሰው እየተሸወደ ነው።

«የቴሌግራም ፕሪሚየም በነፃ ተቀብለዋል!» የሚል የአማርኛ ጽሑፍ ከስሩ ሊንክ ያለው እየተሰራጨ ነው።

ልብ በሉ! ሊንኩን ከተጫናችሁት አካውንታችሁ 100% ተጠልፏል።


በምታውቁት ሰው አካውንት ቢላክም፤ አውቆ ሳይሆን እርሱም ተበልቶ ነው።
ሊንኩን በፍፁም እንዳትከፍቱ።

ሳታውቁ በስህተት የከፈታችሁ ካላችሁ በአስቸኳይ ይህን አድርጉ።

✅ መጀመሪያ ፕሮፋይላችሁ ላይ ወዳለው Settings ላይ ግቡ Devices የሚለውን ንኩት። በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other Sessions የሚለውን ተጫኑና ከሁሉም አካውንታችሁ ሎግኢን ከተባለባቸው ዲቫይሶች ውጡ።  Ok በማለት 24 ሰአት ሳይቆይ አስወግዱት። 24 ሰዓት ከቆዬ ይህን ማድረግ ላትችሉ ትችላላችሁ። ምክንያቱም እነርሱ ይህን ስቴፕ ተከትለው እንደ ዋና ባለቤት ሆነው እናንተን ያባርሯችኋል። 

ብዙ ሰው እየተበላ ስለሆነ እባካችሁ በየቦታው ሼር አድርጉት። እንደው መቼ ነው የሚገባችሁ?

በስካመሮች ጉዳይ ስንት ጊዜ ልናገር? አሁን ማነው በነፃ ፕሪሚየም የሚሰጣችሁ?

ኧረ! ተው ጓዶች አትስገብገቡ! በአቋራጭ ለመበልፀግ አትጣደፉ።


||
© STEMwithMurad


ከሰለፎች ኮቴ dan repost
ሰላም ላንቺ እህቴ...

ቀኑን እየፆምሽ አድካሚ የሆነ ስራ ወይም ትምህርት ላይ የምትውይ፣

ተሯሩጠሽ ወደ ቤት ተመልሰሽ ደግሞ የማፍጠሪያ ምግቦችን የምትሰሪ፣

ማታ ደግሞ የመመገቢያ እቃዎችን አጥበሽ ቤት አስተካክለሽ ወደ ተራዊህ የምትሄጂ፣

ወገብሽ የመሸከም አቅሙን ቢያጣም ከተራዊህ መልስ የተወሰነ ቁርዐን ለመቅራት የምትጥሪ፣

ከሱሁር ሰዐት በፊትም ቀድመሽ ተነስተሽ አላህ ያገራልሽን አይነት ዒባዳ ፈፅመሽ ስትጨርሺ ማብሰል ያለብሽን አብስለሽ፤ የቀዘቀዙትንም ምግቦችን አሙቀሽ፣ የተኛውን ቀስቅሰሽ ልክ እንደ ኢፍጣር ሰዐቱ ለሱሁርም ቤተሰቦችሽን የምትኻድሚ፣

ከፈጅር ቡሀላ ደግሞ ቁርዐን ቀርተሽ ድጋሚ ወደ ስራ(ትምህርት) እስከምትሄጂ ባለው ሰዐት ሌሎች የቤት ስራዎችን የምትሰሪ፣

አንቺ ብርቱዋ እህቴ የአላህ ሰላም እና እዝነት ያካብሽ፣ ከሆንሽው በላይ ጠንካራ ያድርግሽ፣ ጀሊል ዱንያ አኺራሽን ያሳምረው፤ በእያንዳንዱ አድካሚ የዱንያ እንቅስቃሴሽ ሁሉ አላህን ለማውሳት ያልሰነፈ ምላስሽን አላህ ሸር ከመናገር ይጠብቅልሽ፣ የቤተሰቦችሽን ዱዐና ምርቃት አላህ ይቀበልልሽ

አንቺ መልካም ሴት ዱንያ እንዳንቺ አይነት ምግባሩም መልኩም ያማረ ነገርን አብዝታ አልያዘችም፣ አንቺ ልዩ ነሽ ፣ አላህ ለኸይር የመረጠሽ ጠንካራ ባሪያው ነሽ፥ በርቺልኝ የኔ ውዷ እህት You got this👑

moon


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ለባለሃብቱ!
~
ለገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የምትከፍለውን ግብር እያሰብክ ከዘካ እንዳትዘናጋ። ዘካ ለደካሞች የሚሰጥ ሐቅ እንጂ ለሹማምንት የሚሰጥ ግብር ወይም ጉቦ አይደለም። አኺል ከሪም! ገንዘቡን የሰጠህ አላህ ነው። እንጂ ካንተ የበለጠ የሚለፉ ድሃዎች በዙሪያህ አሉኮ። በእውቀቴ አገኘሁት እንዳትል ካንተ የበለጠ የተማሩ ድሃዎች ሞልተዋልኮ። ጥለኸው ለምትሄደው ገንዘብ ብለህ በራስህ ላይ አትሳሳ። እውነተኛው ያንተ ገንዘብ ማለት ለአኺራህ ያሻገርከው ነው። ዐብዱላህ ብኑ ሺኺር - ረዲየሏሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
أتَيْتُ النَّبيَّ صلى الله عليه وسلم، وَهُوَ يَقْرَأُ: {أَلْهَاكُمُ التَّكَاثُرُ} قَالَ: ((يَقُولُ ابْنُ آدَمَ: مَالِي، مالي، وَهَلْ لَكَ يَا ابْنَ آدَمَ مِنْ مَالِكَ إلا مَا أكَلْتَ فَأفْنَيْتَ، أَو لَبِسْتَ فَأَبْلَيْتَ، أَوْ تَصَدَّقْتَ فَأَمْضَيْتَ؟)
"ነብያችን ﷺ ዘንድ መጣሁኝ። {በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ} የሚለውን እየቀሩ ነው። ቀጥለው እንዲህ አሉ፦
'የአደም ልጅ 'ገንዘቤ ገንዘቤ!' ይላል። የአደም ልጅ ሆይ! በልተህ ከጨረስከው፣ ለብሰህ ካሳለቅከው፣ ሶደቃ ሰጥተህ አጅሩን ካሻገርከው ውጭ ገንዘብ አለህ'ንዴ?' " [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2958]
እወቅ! የምታወጣው ካጠቃላይ ገንዘብህ 2.5 ከመቶ ብቻ ነው። መቶ ብር ያለው ሰው ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም ቢያወጣ ብዙ ነው ወይ? ምስሉ ላይ በጣት የተጠቆመችዋን ተመልከት። ካጠቃላይ ሃብትህ ይቺን ታክል ለዘመዶችህ፣ ለጎረቤቶችህ፣ ለምታውቃቸው ምስኪኖች ብታወጣ ብዙ ነውን? በአኺራ እጥፍ ድርብ ምንዳ እንደሚጠብቅህ የቂን የለህም ወይ?
ደግሞም እወቅ! ወላሂ ሶደቃ ሃብትን አይቀንስም። ይልቁንም ይበልጥ በረካ እንዲኖረው ነው የሚያደርግልህ። አላህ ትእዛዙን ለመፈፀም ያግራልህ።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor


ኢብኑ ተይሚያ የተውሂድ የሱና ቻናል dan repost
የኢሻ ሶላት አምልጦህ ተራዊህ እየተሰገደ መስጂድ ከደረስክ ለብቻህ ከኋላ አትቁም። አብረሀቸው በኢሻ ንያ ስገድ። እነሱ ሲያሰላምቱ ተነስተህ የጎደለህን ሙላና የቀረውን የተራዊህ ሶላት አብረህ ስገድ።


አልሃምዱሊላህ..!!

ነገ የረመዷን የመጀመርያው ቀን ይጀምራል።

አላህ የምንጠቀምበት ወር ያርግልን


Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①∅

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ


Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑨

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ


Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑧

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ


Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑦

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ


Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑥

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ


Mizan Tv - ሚዛን ቲቪ 🇪🇹 dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑤

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ


አንድ የአላህ ባሪያ ለሶላት የቆመ ጊዜ ሁሉም ወንጀሎቹ ከራሱ እና ጫንቃው ላይ ይደረጋሉ። ከዚያ ባጎነበሰ እና ሱጁድ ባደረገ ልክ ወንጀሉ እየተንጠባጠበ ይረግፋል።

Copied


إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ صَلُّوا۟ عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


የሰው ልጅ እግሩ እዚህ አለም ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ ወደ መጪው አለም (አኼራ) መንገደኛ ነው፡፡ የጉዞ ቆይታው እድሜው ነው፣ ቀንና ሌሊት ማረፊያው ናቸው፡፡ ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ

Copied


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
Allah yzenln Allah ywefken yhnn niema Amin


አላህዬ…!!

ማየት ለሚችሉት አይኖቻችን
መስማት ለሚችሉት ጆሮዎቻችን
ዓፊያን ለተላበሰው ሰውነታችን
ባጠቃላይ ቆጥረን ለማንዘልቃቸው
በኛ ላይ ላዋልክብን ፀጋዎችህ ሁሉ
ምስጋና ይገባህ ።
الحمد لله


Copied


Abuki Tech በነፃ‼️ dan repost
የጥንቃቄ መልዕክት!

የኢ.ን.ባ ባደረገው የደህንነት ፍተሻ ፋርማ ፕላስ (Pharma+)/ሲቢኢ ቫካንሲ (CBE Vacancy) የተሰኙ አንድሮይድ ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች እንደ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ ባሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ። እነዚህን መተግበሪያዎች ስልክዎት ላይ ከተጫኑ ከእርሶ እውቅና ውጪ የገንዘብ ዝውውር ሊፈፅሙ ስለሚችሉ፣ከዚህ መሰል ጥቃት እራስዎን ለመከላከል መተግበሪያዎችን ከቴሌግራም/ዋትስአፕ አውርደው አይጠቀሙ። አጠራጣሪ ነገሮች ሲመለከቱ ወዲያውኑ 951 በመደወል ያሳውቁ።

~~

ከላይ ያለዉ አይነት አፕ ነዉ ተጠንቀቁ ለማለት ያክል ነዉ‼️

https://t.me/abukiweb
https://t.me/abukiweb

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.