EBSTV NEWS


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.
https://t.me/ebstvworldwide
Inbox - @EbswhatsnewBot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


🟢የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በሊባኖስ እና በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 456 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሱን ገልጿል።

🟢የሚንስቴሩ መረጃ እንደሚያመላክተው በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ የቀጠለ ሲሆን ፥ በሳምንቱ 157 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

🟢በዚህ ሳምንት ውስጥ ከሊባኖስ ወደ ሀገር የተመለሱት 157 ዜጎች 153 ሴቶች 4 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 18 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

🟢በተያያዘ በሳምንቱ 289 ወንዶች፣ 9 ሴቶች 1 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 299 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

🟢ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 90 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር  መረጃ ያመለክታል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ሉሲዎቹ ከኡጋንዳ እና ጅቡቲ ጋር ላለባቸው ጨዋታ ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል

⚽️የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ለአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ለ29 ተጫዋቾች ጥሪ አደርገዋል።

⚽️ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ (እሁድ ጥር 25) ከ8፡00 ጀምሮ አዲሱ ገበያ አካባቢ የሚገኘው " ጋራ ላይ ሆቴል " ሪፖርት አድርገው በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።

⚽️ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ከቀረበላቸው ተጫዋቾች መካከል በሀገረ አሜሪካ የምትገኘው ሎዛ አበራ እንዲሁም በታንዛኒያ ሊግ እየተጫወቱ የሚገኙት አረጋሽ ካልሳ እና አርአያት ኦዶንግ ተጠቃሽ ናቸው።

⚽️የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በወርሃ የካቲት  አራት ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች የሚያከናውኑ ሲሆን ከጅቡቲ አቻቸው ጋር በመጪው የካቲት 5 እና የካቲት 9 በአቋም መፈተሻ ጨዋታ የሚገናኙ ይሆናል።

⚽️በ2026 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ ከዩጋንዳ ጋር የካቲት 14 እና የካቲት 19 ካምፓላ እና አዲስ አበባ ላይ ቡሔራዊ ቡድኑ ጨዋታውን የሚያከናውን ይሆናል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


እንዴት አርፍዳችኃል ውድ የጣቢያችን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ተከታታዮች

🔸 በሳምንቱ የተከናወኑ አበይት አገራዊ እንዲሁም አለም አቀፋዊ ክንውኖችን መለስ አድርገን የምናስቃኝበት የአዲስ ነገር በሳምንቱ ፕሮግራማችን እንዳያመልጣችሁ ለማስታወስ እንወዳለን።

🔸 ይህ ሳምንታዊ ጥንቅር ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 8፡00 ሰዓት ለአየር የሚበቃ ሲሆን በተለይ ሳምንቱን በሥራ ብዛት ያሳለፋችሁ ባያመልጣችሁ መልካም ነው።

የቅዳሜ ቀጠሮዎን ከእኛ ጋር ቢያደርጉ ያተርፉበታል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#Shortcode_SMS_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የጥር 23 አበይት የ አለም  ዜናዎች !

🇺🇸  የብሪክስ ሀገራት የአሜሪካ ዶላርን ለመተካት የሚሰሩ ከሆነ በሀገራቱ ላይ 1መቶ ፐርሰንት ቀረጥ ሊጣልባቸው እንደሚችል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ አስጠነቀቁ ።

🇺🇸  የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዴሞክራቲክ  ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በሩዋንዳ መካከል ከሰሞኑ የተባባሰው ፍጥጫ አሳሳቢ ነው ሲሉ ተናገሩ ::

🇭🇺 የአውሮፓ ኅብረት  በሩሲያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ ሀንጋሪ ጠየቀች ።

🇮🇹 አውሮፓዊቷ ጣሊያን በአለም መነጋገሪያ በሆነው የቻይናው የሰው ሰራሽ አስተዋሎት መተግበሪያ ዲፕ ሲክ ላይ እገዳ ጣለች ::

🇨🇩 የ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገሬ ሉአላዊ ግዛት በሩዋንዳ  ተወሮብኛል ሲል ከሰሰ ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


❇️11ኛው አገር አቀፍ ኢግዚቢሽንና ባዛር ከመጪው ጥር 28 እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታውቋል።

❇️በኢግዚብሽኑ ከ350 በላይ አምራችና ሸማች የህብረት ስራ ማህበራትና ከ100 በላይ ልማታዊ ድርጅቶች ይሳተፉበታል ተብሏል።

❇️በተጨማሪም የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶች እንደሚቀርቡ የተገለፀ ሲሆን፣ከአዲስ አበባ ብቻ ከ120 በላይ የህብረት ስራ ማህበራት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።

❇️ከአዲስ አበባ ብቻ 110 የምርት አይነቶች ዝግጁ እንደተደርጉ የተነገረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለሸማች የሚቀርብ 20ሺ ኩንታል የግብርና ምርት ይገኝበታል ነው የተባለው።

❇️ከአዲስ አበባ በተጨማሪ የተለያዩ ክልሎች ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበት ቦታ በነፃ እንደተሰጣቸው የተገለፀ ሲሆን፣በመርሃግብሩም የፓናል ውይይት እንዲሁም በዘላቂነት የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚረዱ የልምድ ልውውጦች እንደሚደረጉ ተመልክቷል።

መረጃውን ያደረሰን ሪፓርተራችን ደስዬ ልባይ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


👯‍♀️🕺💃ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በመጪው እሁድ የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ተሳታፊዎች በነፃ የሚታደሙበት የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

👯‍♀️🕺💃ኮንሰርቱን አስመልክቶ ትላንት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲስ አበባ በሚገኘው የአደዋ መታሰቢያ ሙዚየም በሚካሄደው የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት ላይ እስከ 10ሺ ተሳታፊዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

👯‍♀️🕺💃ሆም ካሚንግ አዲስ በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የዳንስ ፊትነስ ኮንሰርት ላይ በተለይም ሃገራቸውን ለመጎብኘት ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ በርካታ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

👯‍♀️🕺💃‎በኮንሰርቱ ላይ የመታደም ፍላጎት ያላችሁ ዜጎችም በኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ዶት ኮም ላይ በነጻ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን በቪ አይ ፒና ቪቪ አይ ፒ ደረጃ መሳተፍ ለሚፈልጉ ታዳሚዎችም የተዘጋጀ ቲሸርት መኖሩን ሰምተናል፡፡  

👯‍♀️🕺💃ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በዳንስና ጭፈራ  እየተዋዙ የሚቀርቡበት የዳንስ ፊትነስ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃና ጭፈራዎች ለአለም ከማስተዋወቅ ባለፈ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን እንዲሁም የሰውነት ክብደት መጨመርን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽዎ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

👯‍♀️🕺💃እንደዚ አይነት በርካታ ህዝብ የሚሳተፍበት የጋራ ኮንሰርት መዘጋጀቱም አንድነትና መቻቻልን ለመፍጠር ሚናው የጎላ ነው ተብሏል፡፡

ዜናውን ያደረሰን ሪፖርተራችን ብሩክ አስቀናው ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም የምሽት 1፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና  ዜናዎች፡_

🇪🇹የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር የነበሩት ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው በመሾም በዛሬው እለት ቃለ መሃላ ፈጸሙ፡፡

❇️ለሶስት ቀናት የሚካሄደው የገዥው ብልፅግና ፓርቲ 2ተኛ መደበኛ ጉባዔ በዛሬው እለት  እየተካሄደ ይገኛል፡፡

🔽የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኦዲቶችን መርምሮ የሚያረጋግጥ አዲስ ክፍል ማደራጀቱን ገለጸ፡፡

🚝የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በግማሽ ዓመቱ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቶን ዕቃ በባሕር ላይ አጓጉዣለሁ አለ፡፡

👉ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በግማሽ ዓመቱ 454 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መሰብሰቡን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ አሳወቀ።

“ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"

ቆንጆ ቀን ተመኘንላችሁ!

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ጊዚያዊው የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ሆነው ከወርሃ ህዳር አንስቶ የሰሩት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።

እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በማህበራዊ ትሥሥር ገጹ ይፋ እንዳደረገው መሳይ ተፈት ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል እንዲቀጥሉ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ ላይ ደርሷል።

ከሶስት ወራት በላይ በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እየሰሩ የሚገኙት መሳይ ተፈሪ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች የሚያስመዘገቡትን ውጤት መሠረት ተደርጎ ሊታደስ በሚችል የአንድ ዓመት ውል ብሔራዊ ቡድኑን የሚመሩ ይሆናል።

አሰልጣኙ ቋሚ ኮንትራት የተሰጣቸው መሆኑን ተከትሎም አብረዋቸው የሚሰሩ የአሰልጣኝ ቡድን የማዋቀር ኃላፊነትም ተጥሎባቸዋል።

ከአፍሪካ ዋንጫ እና ከቻን ውድድር ውጭ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መጋቢት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከግብጽ እና ጅቡቲ አቻው ጋር የሚጫወት ሲሆን አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪም ብሔራዊ ቡድኑን ለእነዚህ ጨዋታዎች የሚያዘጋጁ ይሆናል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


❇️የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው  በመሾም  በዛሬው እለት ቃለመሐላ ፈጽመዋል።

❇️ባሳለፍነው ህዳር ወር ላይ የተሾሙት አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በዛሬው ዕለት ቃለመሐላ በመፈጸም ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤ እና የሥራ መመሪያ ተቀብለዋል።

❇️እስከ ቅርብ ቀናት ድረስ የሰላም ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት አቶ ብናልፍ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቅርቡ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

❇️ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከወራት በፊት ከአምባሳደርነታቸው ከተነሱ በኋላ ተተኪ ሆነው ሊሾሙ የታሰቡት አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ቢሆኑም አሜሪካ ዲፕሎማቱን እንደማትቀበል በመግለጿ ወደ ዋሽንግተን ሳይሄዱ መቅረታቸው ይታወሳል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


📺የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በነበሩና ያለደረሰኝ ሲገበያዩ ነበር ባላቸው ከ1ሺ 700 በላይ በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገለጸ፡፡

📺ከወጣቶቹ ጉዳይ በተጨማሪ ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ተሳታፊዎች ሊመለሱልን ይገባል ያሏቸውንም ጥያቄዎች አንስተው ነበር፡፡

ለመሆኑ ነዋሪዎቹ የጠየቁት ጥያቄ ምንድ ነው? ዝርዝሩን ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይመልከቱት
https://www.youtube.com/watch?v=3DBKEbu9Ngc


የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም የእኩለ ቀን 7፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፡_

🇱🇾በሊቢያ "ለባርነት ጨረታ" ቀርባ የነበረችው ኢትዮጵያዊት 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ቢቢሲ አማረኛ አስነበበ፡፡

🇪🇹የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ ሱዳን ፣ በህንድና አሜሪካ በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ፡፡

🔴በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሽሮሜዳ ታቦት ማደርያ አካባቢ የ13 ዓመት ታዳጊ ዋና ለመዋኘት ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳወቀ፡፡

❇️በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት 6 ወራት 125 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 111 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ፡፡

⚡️በመጪዎቹ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ጨምሮ 300 ሚሊዮን አፍሪካውያን የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ይሆናሉ ተባለ፡፡

❇️85ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ምስረታ በዓል በተለያዩ መርሐ ግብሮች በእንጅባራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

❇️የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት 74 አመራርና ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ አለ፡፡

“ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"

ቆንጆ ቀን ተመኘንላችሁ !

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews

Telegram (https://t.me/ebstvnews)


የጥር 23/2017 ዓ.ም የረፋድ ዓበይት የዓለም  ዜናዎች !

🇺🇸 በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ትናንት  ከወታደራዊ ሄሊኮፕተር ጋር የተጋጨው  አውሮፕላን ጥቁር ሳጥኖች መገኘታቸው ሲነገር በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ መቀጠሉ ተሰምቷል።

🇵🇸🇮🇱 የፍልስጤሙ የሀማስ ቡድን  ከ አንድ አመት በላይ አግቶ ይዟቸው የነበሩ 8 እስራኤላዊያን ታጋቶችን ዛሬ መልቀቁን አስታወቀ ። 

🇮🇱🇵🇱🇺🇦 እስራኤል በ አውሮፓዊቷ ፖላንድ በኩል ለዩክሬን የ ሚሳኤል የጦር መሣሪያ ድጋፍ ማድረጓ ተነገረ ።

🇨🇩 በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ  ክፍል የምትገኘውን የጎማ ከተማን የተቆጣጠረው የ ኤም 23 አማፂ ቡድን መሪ ጥቃታቸውን በመቀጠል ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ እናቀናለን ሲሉ ዛቱ ::

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN


▶️ከሽብር ወንጀል ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቁት ዱዱዞሌ ዙማ ሳምቡላ የደቡብ አፍሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መሆናቸውም ነው የተነገረው፡፡

▶️የዙማ ልጅና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሏ ለፍርድ የሚቀርቡት በጎርጎርሳውያኑ 2021 የ350 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው አመጽ ጀርባ እጃቸው አለበት ተብሎ ነው፡፡

▶️በደቡብ አፍሪካ በወቅቱ አባታቸው ጃኮብ ዙማ እስር ቤት መግባታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ አመጽ ተከስቶ የነበረ ሲሆን ተከሳሽዋም በቀድሞ ትዊተር እና በአሁኑ ኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አመጽ ያስነሱት ሰዎች በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዲያደርሱ መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡

▶️በዚህም ምክንያት አመጹ እንዲቀሰቀስ እና የሰው ህይወት እንዲቀጠፍ በማነሳሳት በሚል የተከሰሱት ዱዱዞሌ ዙማ ሳምቡላ በራሳቸው እጃቸውን ለፖሊስ እንደሰጡም ነው የተገለጸው፡፡

መረጃው የአፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


📱የፌስ ቡክ ባለቤት የሆነው የሜታ ኩባንያ በተከሰሰበት የዶናልድ ትራምፕን የፌስቡክ ገፅ ላልተወሰነ ጊዜ ማገድ ክስ እንዲከፍል የተላለፈበትን የ22 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል መስማማቱ ተነገረ፡፡

📱ዶናልድ ትራምፕ ከአራት ዓመት በፊት በጃንዋሪ 6 አመጽ ወቅት ያስተላለፉትን ግጭት ቀስቃሽ መረጃ ተከትሎ ነው የሜታ ኩባንያ በወቅቱ የፌስ ቡክ ገፃቸውን አግዶ የነበረው፡፡

📱ታዲያ ትራምፕ የሜታ ኩባንያን በፍርድ ቤት ከሰው የነበረ ሲሆን ሜታም ይህን የተጣለበትን ቅጣት ለመክፈል ከሰምምነት ላይ የደርሷል። ይህ ገንዘቡም ትራምፕ ወደፊት ለሚያስገነቡት ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መፅሐፍት ድጋፍ ይውላል ተብሏል፡፡

📱ሜታ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከሌሎች መሰል ኩባንያዎች ጋር በመጣመር ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ለመመስረት በሚደረገው ጥረት እየተሳተፈ መሆኑን ተከትሎ እንዲሁም ከትራምፕ አስተዳደር ጋር አብሮ ለመስራት ያለመ ነው እየተባለ ይገኛል፡፡

መረጃው የኢውሮ ኒውስ ነው፡፡ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ኢትዮጵያ በአለማቀፍ ደረጃ 2ኛዋ ቡና ላኪ ሀገር ለመሆን እየሰራች እንደሆነና : ሶስተኛ የቡና አምራች ሀገር መሆን መቻሏን ጨምሮ : የኢትዮጵያን ቡና በብዛት የሚገዙት ሀገራት እነማናቸው ? የሚሉትን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበናል።

ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይከተሉ።
https://youtu.be/pQ-tv99FA2I


ኢትዮጵያ በአለማቀፍ ደረጃ 2ኛዋ ቡና ላኪ ሀገር ለመሆን እየሰራች እንደሆነ እና ሶስተኛ የቡና አምራች ሀገር መሆን መቻሏን ጨምሮ የኢትዮጵያን ቡና በብዛት የሚገዙት ሀገራት እነማናቸው ? የሚሉትን ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበናል።

ለመመልከት ተከታዩን ሊንክ ይከተሉ።
https://youtu.be/7EytuXgDL_Y


የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም የምሽት 1፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና  ዜናዎች፡_

🇺🇸አሜሪካ ለኤች አይ ቪ ቫይረስ ህክምና የምትሰጠውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ገለፀች፡፡

❇️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ በህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በነበሩና ያለደረሰኝ ሲገበያዩ ነበር ባላቸው ከ1ሺ 700 በላይ በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገለጸ፡፡

❇️በቋንቋ ጉዳይ ከህገመንግስቱ ጋር ይጋጫል የተባለው የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡

🇪🇹🛩ዘ አፍሪካ ሪፖርት ይዞት በወጣው መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2024 ከአፍሪካ ብቸኛው የቦይንግ ምርት በመግዛት ድርጅቱ ከደረሰበት ኪሳራ እየታደገው እንደሆነ ገለጸ፡፡

👨‍⚕️👩‍⚕️በሐኪሞች ላይ እየተፈጸሙ ናቸው የተባሉ ችግሮች ላይ የሚመክር ጉባኤ በመጭው ወር የካቲት ያካሄዳል ተባለ፡፡

👉በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ  ገለጸ፡፡

“ዜና አዲስ ነገር ነው! አዲስ ነገርም ዜና ነው!"

ያማረ ምሽት ተመኘንላችሁ !

ትክክለኛውን የኢቢኤስ አዲስ ነገር የቴሌግራም ገፅ ለመወዳጀት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ👉
https://t.me/ebstvnews

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🇺🇸 ዛሬ በአሜሪካዋ መዲና ዋሽንግተን ዲሲ 60 ሰዎችን የ ጫነ አንድ አውሮፕንላን ከ አሜሪካ የጦር ሄሊኮፕተር ከመጋጨቱ ጋር በተያያዘ 60 ዎቹ  ተሳፋሪዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ   ተሰምቷል ::

🇮🇱 የፍልስጤሙ የ ሀማስ ቡድን  ከ አንድ አመት በላይ አግቶ ይዟቸው ከነበሩ 8 እስራኤላዊያን ታጋቶች ውስጥ የመጀመሪያው ታጋችን ለቀቀ::

🇮🇱 እስራኤል በፍልስጤሟ ዌስት ባንክ ዛሬ ባካሄደችው የአየር ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት ተናገሩ።

🇨🇩 የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ቲሺሰከዲ የኤም 23 ታጣቂ ቡድን በምስራቃዊ ኮንጎ  ከያዛቸው አካባቢዎች ለማስለቀቅ  ውጊያው ይቀጥላል ሲሉ ተናገሩ ።

🇺🇬 የኡጋንዳ መንግስት በመዲናዋ ካምፓላ የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱን እና አንድ ሰው በበሽታው መሞቱን አስታወቀ ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🇺🇦🇺🇸ለዩክሬን በመዋጋት ላይ እያሉ የሚሞቱ አሜሪካዊያን ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተከትሎ የወታደሮችን አስክሬን ወደ አሜሪካ መመለሱ አስቸጋሪ ሥራ እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ፡፡

🇺🇦🇺🇸ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ለዩክሬን ለመዋጋት ወደ ዩክሬን ካቀኑት አሜሪካውያን መካከል ከ20 በላይ የሚሆኑት በጦር ግንባር ደብዛቸው መጥፋቱ ተነግሯል፡፡

🇺🇦🇺🇸ዩክሬን ያጋጠማትን የሰው ኃይል እጥረት ለመሙላት በፍላጎታቸው ፈርመው ወደ ዩክሬን ካቀኑት አሜሪካውያን መካከል ህይወታቸውን የሚያጡት ቁጥር ባለፉት 6 ወራት እያሻቀበ መሆኑን በምርመራ ዘገባዬ አረጋግጫለው ያለው ሲ.ኤን.ኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🇺🇸 በአሜሪካ መዲና  ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ አየር ማረፊያ አቅራቢያ 60 ሰዎችን የጫነው አውሮፕላን ከአንድ የጦር ሄሊኮፖተር ጋር መጋጨቱን ተከትሎ በአደጋዉ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 18 ሲደርስ ከአደጋው የተረፉ ሰዎችን የማፈላለግ ስራው አሁን ድረስ እየተካሄደ መሆኑን ተነግሯል ::

🇺🇸 የአሜሪካ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ጨምሮ 3ዐዐ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋው በደረሰበት የ ፖቶማክ  ወንዝ ላይ ተሰማርተው የነፍስ አድን ተግባር ስራውን በተጠናከረ መንገድ እያካሄዱ ነው ተብሏል።

🇺🇸 ከአደጋው ጋር በተያያዘ በአሜሪካዋ ርዕሰ ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሚካሄዱ ከ 1መቶ በላይ በረራዎች ሲሰረዙ የመዲናዋ አየር ማረፊያ ተዘግቷል መባሉንም የአሜሪካ ባለስልጣናት ተናግረዋል ።

🇺🇸 የአሜሪካ የ ፌዴራል አቪየሽን ባለስልጣን እና የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር በተናጥል በ አደጋው ምክንያት ዙሪያ ልዩ ምርመራ መጀመራቸው ሲነገር ከአደጋው ጋር በተገናኘ  አሸባሪዎች ይሳተፉ አይሳተፉ ይሄ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ስፑቲክ አፍሪካ ዘግቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.