👆
🎡 ተመልከት ሱብሀን አላህ ወጣ ብለህ ስትሄድ የምታየው ፈሳድ ፈሳድ አይደለም! ሌላውን ተወውና ሙስሊሞች ያሉበት ፈሳድ ፈሳድ አይደለም! በረመዳን ላይ እራሱ መስተካከል ያቃታቸው።
🎻 በረመዳን ቀን ቀን ላይ እራሱ መቆጠብ ያቃታቸው ከሀራም ነገር ራሱ መከልከል ያልቻሉ ዘፈንን እንኳን መስማት ማቆም ያቃታቸው ይቅርና ማታ ቀን እንኳን መቆጠብ ያልቻሉ።
🎻 እራሱን ይሸውዳል ያታልላ እሱ ዘንድ ዘፈን ብሎ ማለት እሱ ዘንድ አማርኛ ወይም እእንግሊዘኛ ነው።
🎧 ቀን ቀን አረብኛ ዘፈን ያዳምጣል ወይ ሱዳንኛ ዘፈን ያዳምጣል ማታ ካፍጥር ቡዃላ አማርኛ ዘፈን ያዳምጣል እንዲህ አይነቱን ምን ትለዋለህ?
⛺ ዲን አለው በረመዳን ጠንካራ ነው ምትለው ደሞ ቀኑን ሙሉ በመንዙማ ይሸኛል።
🔭ያሱብሀን አሏህ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘፈን ይቅርና ረመዳንን በመንዙማ ነበር ሚሸኙት?
📋 ዛሬ መንዙማ አውጪ እና ዘፈን አውጪ እኩል ሆነዋል በአመቱ ረመዳን ፖስቸራቸው አንድ ላይ ነው ሚለጥፍልህ ቲዲ~ምናምን አፍሮ~ምናምን ከመሀመድ አወል~ምናምን ከማል~ምናምን አንድ ላይ ይለጠፍልሀል አንተ በአረብኛ አናሺድ መንዙማ ትላለህ።
💸ያሱብሀን አሏህ ልንገርህ ንግድ ነው ንግድ ነው የተያያዙት።
💸በረመዳን ነው ሰው ገዝቶ ሚያዳምጠው ማውጣት ያለባቸው በረመዳን ነው ከዛ ውጪ አይገዛቸውም ቀን አይበላ አይጠጣ መስማት ያለበት በረመዳን ነው።
💰 መንዙማ አናሺድ ምናምን ያዋጣል ልንገርህ በጣም ከማዋጣቱ የተነሳ በጣምም ስለሚያዋጣ ሀታ ካፊሮች እራሱ አናሺድ ማውጣት ጀምረዋል ይቅርና ማይክል ጃክሰን እራሱ መንዙማ አውጥቶ የለ እንዴ?
📮 ለምን~አወጣ? ማን~ሊገዛው? ማን~ሊያዳምጠው? ማን~ሊያዳምጠው? ማን? ማን? ሙስሊሞች።
🎧 ማሻአላህ ረመዳን መጣ አናሺድ ያሱብሀን አሏህ የኡለማዎችን ንግግር አዳምጥ ኢማሙ ሻፍኢ ረሂመሁሏህ አናሺድ መንዙማ ሚባለው ኢራቅ ውስጥ ተፈጥሮ ወደ ሌላ ሀገር ሲሰራጭ ስለ አናሺድ ጠየቁት እኛ ኢባዳ አድርገን የያዝነው መንዙማ
ኢማሙ ሻፍኢ እንዲህ አለ:- ዘናዲቃዎች የፈጠሩት ነው ይላል በእስልምና ላይ አዲስ ሙናፊቆች የፈጠሩት ፈጠራ ነገር ነው ይላል።
💊 ኡላማኧል ኢስላም ኢብኑ~ባዝ ኢብኑ~ኡሰይሚን ማሁመድ~ናሲርዲን~አልባኒ አብድል~ሙህሲን~አባዲል~በድሪ ሌሎችም ብዙ ኡለማዎች አናሺድ መንዙማ:- ስሜታቸውን የሚያረኩበት የሱፍዮች ዘፈን ነው ብለዋል።
📛 ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ያልተገኘ ከሰሀቦች ያልተገኘ ከማንም ያልተገኘ መረጃ የሌለው ዘፈን ስሜታቸውን የሚያረኩበት ዘፈን አያዳምጥም አይጨፍርም በዛ ምትክ ግን ድቤ እየተመታ ኢኢ ይለዋል ናአም ይጨፍራል።
🚨 ከዚህም የሚበልጠው መስጂድ ውስጥ ጭፈራ መሆኑ ከዚህም ይበልጥ ወንጀሉ ውጪ ብቻ አለመሆኑ መስጂድ ውስጥ ጭፈራ መግባቱ ለዚህም ተብሎ ሰላት ለጭፈራ ተብሎ መቋረጡ ሀዛ ሁወ።
♨ ሰውን ገደሉት አመቱን ሙሉ ዘፈን ላይ ተዘፍቆዋል ረመዳን ሲመጣ ከዘፈን አይወጣም ከና~ወደ~ሌላ መንዙማ ይከቱታል ከዘፈን~ወደ~መንዙማ ተመልሶ~ወደዘፈን ከዘፈን~ወደ~መንዙማ ተመልሶ~ወደ~ዘፈን
📖 መች ነዉ~ቁርአን ሚቀራው? መች ነው~የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሀዲስ ሚቀራው? መች ነዉ~ሚሰራበት? መች ነዉ~የአሏህ ባርያ ሚሆነው? መች ነዉ~አሏህን ሚገዛው? መች ነዉ ሰው~ሚሆነው? መች ነው~ሰው ሚሆነው? መች ነዉ~እራሱን ሚቆጣጠረው?
💭 ጫወታ ጫወታ ጫወታ ረመዳን ይመጣል መሸወድ ይመጣል መዝፈን ይመጣል መንዙማ ይመጣል መጨፈር መቃም መጫስ ምናምን ሀዛ ሁወ።
📮 እስከ መች ድረስ~እንደ እንስሳ ተሆኖ ይኖራል? እስከመች ድረስ~እራስህን መቆጣጠር ያቅትሀል? እስከመች ድረስ~በዚህ ሁኔታህ ትሞታለህ? በዚህ ሁኔታህ~ልጆችህ ይዩህ? ምንግዜም ለቤተሰቦችህ~ሰው ተብለህ ምትቆጠረው በዚህ ሁኔታህ ነው? ልጆችህ የሚያድጉት~ኢሄን ምሳሌ እያዩ ነው? አንተም~ሰው ነኝ ብለህ ምትኖረው በዚ ሁኔታህ ነው? ሀላስ በቃ~ከዚ የተሻለ የለም? የአሏህ ቁርአን~ሚሰራበት ጠፋ? የነብዩ ሀዲስ~ጠፋ? ሚሰራበት~ጠፋ? ዘፈን ጭፈራ~በቃ መንዙማ? ላሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢሏህ።
📌 ከየት አመጣኸው? ከየት መጣልህ? ከየት? ከየት? ሱፍዮች የፈጠሩት ነው ነብዩ በተራዊ መሀል ይዘፍኑ ነበር? ድቤ ይዘው ይጨፍሩ ነበር? ከየት መጣ? ኧረ ነቃ በሉ ኧረ ነቃ በሉ ኧረ ዲናቹሁን እወቁ አሏህን ተገዙ ማንም አይጫወትባቹሁ የማንም መጫወቻ አትሁኑ እስከመች ድረስ ሰው እየተጫወተብህ ትናራለህ? ረመዳን ሲመጣ ትመጣለህ ወሏሂ ከረመዳን ውጭ የምትመጣ ሰው ብትሆን ኖሮ ሌላ ሰው ነበር ዛሬ የሚመጣው ዛሬ ግን አንተ ስለመጣህ ሌላ ሰው መምጣት አልቻለም ምክንያቱም እስከ ዛሬ ዘግተህ ይዘኸው ነበር ሰብር አጣን? አሏህን ለመገዛት ሰብር አጣን? አሏህን ለመገዛት ሰብር የለም? አሏህ የከለከለንን ለመከልከል ሰብር የለም? ላሀወለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢሏህ።
📖 አሏሁ ሱብሀነሁ ወተአላ ሰብር አድርጉ እያላቸው የነብያቶች ተከታይ ያሁሉ ስቃይ እየደረሰባቸው ሰብር እያደረጉ የአሏህ ደጋግ ባሮች ሰብር እያደረጉ አሏህ በቁርአን ዘጠና ምናምን ቦታ ስለ ሰብር እየተናገረ ነብዩ صلى الله عليه وسلم ስለ ሰብር እየተናገሩ ሰሀቦች በሰብር እያሳለፉ ስለ
ሰብር እየተናገሩ ታቢኢዮች በሰብር እያሳለፉ ስለ ሰብር እየተናገሩ ኡለሞች መልካም ሰዎች ሁሉ ስለሰብር እየተናገሩ በሰብር እቺን ዱንያ እያሳለፉ።
⌚ የተወሰነ ሰአት ሰብር አድርገን ለመማር ጊዜ የለንም? የተወሰነ ሰአት ጊዜ ሰጥተን አሏህን ለመገዛት ጊዜ የለንም? ረመዳን ወር እንኳን ከጫት መላቀቅ አልቻልንም? ረመዳን ወር ከሲጋራና ከዘፈን መላቀቅ ፂም ለማሳደግ ሰው ለመሆን አልቻልንም? ከአመት ሰላሳ ቀን? እድሜ ልክህ ነበር እንደዛ የታዘዝከው በረመዳን ሰላሳ ቀን ግን አቃተህ ረመዳን ላይ ምንም ማድረግ ካልቻልክ ከረመዳን ውጪ ሰው እንደማትሆን እወቀው ምክንያቱም አሏህ ረመዳንን ያመጣው ለምንድነው? ፆምን ያመጣው ለምንድነው? አሏህን ልትፈሩ ይከጀልላቹዋል ነው።
🌄 በዚህ ወር አሏህን ካልፈራህ እንዴት ልትፈራው ነው? ሸይጣን ታስሮ ተለቆ ሸይጣን ታስሮ አሏህን ያልተከዛህ ሸፍጣን ተፈቶ እንዴት ልትሆን ነው? ሸይጧን ታስሮ የሏህ ባርያ ያልሆንክ ሸይጧን ሲፈታ እንዴት ልትሆን ነው?
💫 አይሆንም አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ሀልህን እሚቀይርልህ አንተ እራስህ ሀልህን ስትቀይረው ነው አላህም እንዲህ ይላል:-
📖 { ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتّٰى يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ٍۗ } [ سورة الرعد : 11 ]
📖 አላህ በሶዎች ላይ ሀላቸውን አይቀይርባቸው በራሳቸው ላይ ያለውን ሀል እስኪቀይሩ ድረስ።
💫 ከመጥፎም ይሁን ወደ መልካም ከመልካምም ይሁን ወደ መጥፎ ያው ነው በራስህ ላይ ያለውን ሀል እስካልቀየርክ ድረስ።...
🎙️ "ሶብረን ዱንያ ጠፊ ናት" በሚል ርዕስ ኡስታዝ አቡ ዐብዱረህማን አብራር. ካደረገው ሙሀደራ ተቀንጭቦ ወደ ፁሁፍ የተቀየረ።
💻 አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱድዮ
የሰለፍዮች ልሳን!!
📎 https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio
✍️ https://t.me/Ibnu_Akil_Media