ኒቃብ ያደረገች ሴት ከሌሎች ሴቶች ግድ ልትለይባቸው የሚገቡ ጉዳዮች
📌 አደብ( ስርኣት) ሊኖራት ይገባል
📌ንግግሯ የተስተካከለ መሆን አለበት
📌አካሄዷ በእርጋታ የተሞላ መሆን አለበት
📌ከሀሜት ልትርቅ ይገባል
📌ወሬ ምታበዛ መሆን የለባትም
📌አለባበሷን የማይመጥን ቦታ መገኘት የለባትም ወዘተ…
👉 አንዳንድ ኒቃብ ለባሾች ግን ለምን እንደለበሱት ሁላ የሚያውቁ አይመስሉም።
አሳፋሪ ይሆኑብሃል❗️ታክሲ ውስጥ በል መንገድ ላይ …ሀረካት በሀረካት እንዴ? ተረጋጉ እንጂ ❗️ሰከን በሉ❗️
👉ሲጀመር ለሌላ አላማ የተለበሰ በሚመስልክ መልኩ እንዲህ መንቀልቀል ተገቢ አይደለም❗️
ሴት ልጅ ባጠቃለይ ረጋ ስትል ያምርባታል 👉ኒቃብ ያደረች ከሆነ ደግሞ በተለየ መልኩ ሀያት(እፍረት) እንዲሁም እርጋታ ያስፈጋታል። ካልሆነማ የኒቃሙ ጥቅም ምኑ ጋር ነው ❓
እራስሽን ከሃራም ካልደበቅሽበት ሰዎችንም ከፈተና ካልጠበቅሽበት ትርጉም አልባ ነው ሚሆነው እንደውም ሌሎች ይህን የተከበረ ልብስ ሊለብሱ አስበው እንደአንቺ አይነቷን ሲያዩ እስልምናን ከማሰድብ ብለው ይተውታል በርግጥ ልክ አይደሉም ዑዝርም አይሆናቸውም አላህ ዘንድ ከመጠየቅም አያድናቸውም።
🫵 አንቺ ግን ሰዎችን ከመልካም ነገር አባራሪ ንፁህ የዲን ሴቶችን አሰዳቢ ነሽ።
እውነት እውነቱ ይወራ ከተባለ በጣም ጋጠወጥ ሴቶች አሉ ምንም እፍረት የሌላቸው ቅብዥብዥ ያሉ ።
📌 እናም አንዳንዱ ዋልጌ እንደዚህች አይነቷን ስርኣት አልበኛ አይቶ ሁሉም ኒቃም ለባሽ ዝርክርክ ይመስለዋል ሊተናኮል ሊያናግርም ይቃጣዋል።
እንዲህ አይነት ሰው በየታክሲው ሌላም ቦታ ሲያጋጥማችሁ ጠንካራ የሚያስደነግጥ መልስ መልሱ
ፀጥ ብላችሁ ወሬውን አታዳምጡ❗️
አሏህ ሷሊሆችን ይጠብቅልን🤲
ለሁሉም ነገር ወሳኙ ተቅዋ ነው።❗️አላህም እንዲህ ይላል፦
وَلِبَاسُ ٱلتَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ
አላህን የመፍራትም ልብስ የተሻለ ነው።
وَلِبَاسُ ٱلتَّقْوَىٰ
አላህን የመፍራት ልብስ ሲባል ሙፈሲሮች የተለያየ ገለፃን አስቀምጠዋል እሱም፦
ኢማን ፣
እፍረት፣
አላህን መፍራት ወዘተ…
📌ከምንም በላይ አስፈላጊው ጉዳይ አላህን መፍራት
ተቅዋ ነው። ተቅዋ የሌላት እንስት መጀመሪያ ያሉባትን መጥፎ ባህሪያቶች፣ መጥፎ ጓደኞቿን ርቃ ጥሩ ሁኔታ ላይ ስትሆን ጊዜ ኒቃሟን ብትለብስ ጥሩ ይመስለኛል ካልሆነ ግን ከሷ አልፎ ሌሎችን በሚያስተች ሁኔታ ላይ ሆኗ መልበሷ ካልተቀየረችበት መጥፎ ባህሪዋን ለሌሎች ታጋባለች።
ውስጧ የተበላሽለ ቀልቧ የደረቀባት ሴት ቶሎ ብላ ወደ አላህ ካልተመለሰች አደጋው ከባድ ነው። በዱንያ ጭንቀት በአኼራ ደግሞ ውርደትን ትከናነባለች።
👉 አንድ ጊዜ ከመድረሳ ወጥቼ እየሄድኩኝ ሳለ አንዲት ኒቃብ ያደረገች ሴት ድምፇን ከፍ አድርጋ ታወራለች የምታወራው ነገር ወላሂ ልቤት ትርክክ ነው ያደረገው አላመንኩም ጮክ ብላ ማንቼ እንዴት ሆነ ተሸነፈ አሸነፈ ትላለች لاإله إلا الله ድርቅና ወላሂ አሁን እንዲህ አይነቷ ምን ትባላለች❓
📌አንቺ ሙተነቂብ እህቴ ሆይ አስተውዬ ይህ ልብስ ተራ ልብስ አይደለም ይህ ልብስ ለውበት ፣ለአይነናስ፣ ለትዳር ማምጫ ተብሎ በተበላሸ ኒያ የሚለበስ ነገር አይደለም። ይህ ልብስ የነብዩ ባልተቤቶች ይለብሱት የነበረ የክብር የጥቡቅነት መገለጫ ነው። ግዴታም ጭምር ነው።
ዛሬ የምንሰማቸው ነገራቶች ግን ወላሂ ልብ ይሰብራሉ❗️ በጥቂት ሰዎች ምክንያት የነዛ ድምፃቸው እንኳ የማይሰማ ጥቡቅ እንስቶች ስም አንድ ላይ ሲነሳ ልብ ያደማል ❗️
ቆይ ግን ምን ማለት ነው ኒቃብ አድርጋ ለወንድ ፎቶ መላክ ❓
ኒቃም ስትለብሺ እኔ ጥቡቅ ነኝ እያልሽ እኮ ነው አልገባሽም እንዴ ❓ሲጀመር እንኳን ፎቶ መላክ ይቅርና ማውራት ራሱ መች ተፈቅዶልሽ
ብልሽትሽ የጀመረው ፎቶ የተነሳሽ ቀን ነው። በጣም ነውር ወላሂ በጣም አሳፋሪ ድርጊት ነው።
ነገ አላህ ዘንድ እርቃንሽን የምትቆሚበት ቀን ይመጣል
በአፈር የተከበበውን ጨለማውን የቀብር ቤትሽንም አትዘንጊው 📌
ስህተት የቅፅበት ነች ፀፀት ግን የእድሜ ልክ ነው። 📌
ወደ መጥፎ ሊገፋሽ የሚችልን ነገር በሙሉ ራቂ በተለይ ስልክና መጥፎ ጓደኛን❗️ እኔ ይህን ብያለው እናንተ ብዙ ልታውቁ ትችላላቹ አላህ ደግሞ ሁሉምን አዋቂ ከሱ የሚደበቅ ነገር ፈፅሞ የለም❗️
አንዳንዴ ላለመታመም ለራሴ የምላት ነገር አለች ካፊሮች ይሆናሉ አውቀው ወንጀልን ለማለማመድ ልብሱን ለማጠልሽት ሲሉ ግን… ምኞት ነው።
اللهم استرنا اللهم أصلح شبابنا وشباب المسلمين 🤲
👉
https://t.me/AbuEkrima