ሳሙኤል ተመስገን


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


ቤተክርስቲያን ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
እውነተኛ ሰላም ሕፃን መክሊት






ሥራህን ሥራ!

ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል፣ ያንን መሥራት የእሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው እሱን ማገድ የዲያቢሎስ ሥራ ነው፡፡ በእርግጥ ሥራውን እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሰይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡ የሐሜት ጐርፍ ያስወርድብሃል፡፡ ደራሲያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ጲላጦስ፣ ሄሮድስ፣ ሃናንያ፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ፡፡ ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሰላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል፡፡ ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዘብ አትችልምን?
ሥራህን ሥራ! አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፤ የሰይጣንን ውሻዎች ለመውገር አትቁም። ጥንቸሎችን ለማባረር ጊዜህን አታጥፋ። ሥራህን ሥራ!! ዋሾች ይዋሹ፣ ጠበኞች ይጣሉ፣ ማኅበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ። ሰይጣንም የፈለገውን ያድርግ፤ አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈጸም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ።
ሥራህን ሥራ!! ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክህም፤ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፤ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልነገረህም፤ ሰይጣንና አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅህም። እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሠራ አትችልም። ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለጌታ አልሠራህም፡፡
ሥራህን ሥራ ዓላማህ እንደ ኮከብ የጸና ይሁን፤ ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ፤ ይጨቃጨቅ። ጥቃት ይደርስብህ፣ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፣ ትቆስልና ትናቅ ይሆናል፡፡ ኃይለኛ ያጐሳቁልህ፣ ወዳጆች ይተውህ፣ ሰዎችም ይንቁህ ይሆናል፡፡ አንተ ግን በጸና ውሳኔ፣ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ጸንተህ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸምኩ፣ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ ለማለት እስክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

የዩቱብና የቴሌግራም ቻናሌ ቤተሰብ መሆን ለምትሹ

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq


ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው በወጥመድ እንዳይያዙ ነው። ሰዎችም የማሰቡ ኃይልን የተሰጣቸው ኃጢአትን እንዲያስወግዱ ነው። እንግዲህ እንዲህ የማሰብ ኃይል ተሰጥቶን ሳለ ይባስ ብለን ከምድር አራዊት በታች የማናስተውል ከኾንን ሊደረግልን የሚችል ምህረት ወይም ይቅርታ እንደምን ያለ ምሕረት እንደምንስ ያለ ይቅርታ ነው?

በወጥመድ ተይዛ የነበረች ወፍ ድንገት ከወጥመዱ ብታመልጥ፤ ወደ ወጥመድ ገብቶ የነበረ አጋዘን ወጥመዱን በጣጥሶ ቢሄድ ከእንግዲህ ወዲህ በተመሳሳይ ወጥመድ እነዚህን መያዝ ከባድ ነው። የሕይወት ተሞክሮ ለሁለቱም ጥንቃቄን አስተምሯቸዋልና። እኛ ግን ምንም እንኳ በተመሳሳይ ወጥመድ ብንያዝም ተመልሰን ወደዚያ ወጥመድ እንወድቃለን፣ ምንም እንኳን በለባዊነት የከበርን ብንኾንም አእምሮ እንደሌላቸው እንሰሳት እንኳን ቀድመን አናስብም፤ አንጠነቀቅም!

ሴትን በማየት እልፍ ጉዳቶችን ተቀብለን ወደ ቤታችን የተመለስነው፤ በዝሙት ተመኝተንም ስናበቃ ለአያሌ ቀናት ያዘንነው ስንቴ ነው? ነገር ግን ከዚያ በኋላም ቢሆን በዚሁ ጉዳይ ላይ ጠንቃቆች አልኾንም፤ አንዱን ቁስል ሳናገግም ወደዚያ ክፉ ጠባይ እንወድቃለን፣ በተመሳሳይ መንገድ እንያዛለን፤ እጅግ ጥቂት ለኾነች የደስታ ሽርፍራፊ ብለንም ረጅምና ተደጋጋሚ ሥቃይን እንቀበላለን።

ዘውትር በወጥመዶች መካከል እንደምትኼድ በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ" የሚለውን ኃይለ ቃል ደጋግመን ለራሳችን ብንነግረው ግን ከእነዚህ ጉዳቶች ኹሉ እንጠበቃለን። (ሲራክ 9፥13)

የዩቱብና የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ

በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual




ክፋት ከአንተ_አርቃት
ሰይጣን ክርስቶስ በልብህ ውስጥ ያለ መሆን አለመሆኑን ያውቃል፡፡ ይኸውም ስትቆጣ ወይም ስትጮህ ወይም የማይረቡ ከንቱ ነገሮችን ስትናገር ሲያይህ ጠላት በአንተ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሌለ ያውቃል ያን ጊዜ በውስጥህም በውጭህም ያለውን ሳይቀር ይገዛል ፤ መዝጊያ እንደሌለው ቤት እንደ ክፉ ሌባ ይገባና ውስጥህን ይበረብረዋል፡፡
ቅዱስ ባስልዮስ
የቴሌግራምና ዩቱብ ቻናሌ ቤተሰብ መሆን የምትሹ

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq




+ ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 23 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

ፎቶ :- ኢያሪኮ "የዘኬዎስ ዛፍ" የነበረበት ሥፍራ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የዩቱብ እና የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq


"መላእክትን ማየት ትልቅ ተአምራት አይደለም፥ የራስን ስህተት መመልከት ግን ተአምር ነው።'

ቅዱስ አባ እንጦንስ


.ምክር_ዘቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

እስኪ ንገሩኝ! ከእናንተ መካከል ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ አንዲት ምዕራፍ ወይም ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥቂት [በቃልህ] ድገም ቢባል ይህን ማድረግ የሚችል ማን ነው? አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡
እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ግን ይኼ ብቻ አይደለም፡፡ ከመንፈሳዊ ነገሮች አንጻር እንደዚህ አእምሮ የጎደላችሁ ኾናችሁ ሳለ ዲያብሎሳዊ በኾኑ ነገሮች ላይ ግን እሳት የላሳችሁ ናችሁ፡፡ እንዲህም በመኾናችሁ አንድ ሰው መጥቶ ዲያብሎሳዊ ዘፈኖችንና የዝሙት ሙዚቃዎችን ንገሩኝ ቢላችሁ፥ ከእናንተ መካከል እነዚህን በትክክል የሚያውቁና ደስ ተሰኝተው የሚደግሙአቸው ብዙ ሰዎችን ያገኛል፡፡
ለምንድን ነው እንደዚህ የምትኾኑት? ከእናንተ መካከል “እኔ መነኰሴ አይደለሁም፡፡ ሚስት አለችኝ፡፡ ልጆች አሉኝ፡፡ የቤተሰብ መሪ ነኝ” የሚል ምክንያት የሚያቀርብ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ለምን እንደዚህ ትላላችሁ? ብዙዎችን ያጠፋው “ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ለመነኰሳት ብቻ ነው” የሚለው አመለካከታችሁ ነው፡፡ ከመነኰሳቱ ይልቅ ይበልጥ ማንበብ ያለባችሁ ግን እናንተ ናችሁ፡፡ ይበልጥ መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች በዓለም የሚኖሩና ዕለት ዕለትም ቁስል የሚያገኛቸው ሰዎች ናቸውና፡፡ ስለዚህ ካለማንበባችሁም በላይ “የእኛ ማንበብ ትርፍ ነገር ነው” ብላችሁ ማሰባችሁ በራሱ የዲያብሎስ አሳብ ነው፡፡ ወይስ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “ይህም ኹሉ እኛን ሊገሥጸን ተጻፈ” ያለውን አላደመጣችሁምን? (1ኛ ቆሮ.10፡11)፡፡
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! ወንጌልን በእጅህ ለመያዝ ብትፈልግ አስቀድመህ እጅህን ትታጠባለህ፡፡ ታዲያ በወንጌሉ ውስጥ ያለውን ቃለ እግዚአብሔር ከዚህ በላይ እጅግ አስፈላጊ እንደ ኾነ አታስብምን? ብዙ ነገሮች ምስቅልቅላቸው የወጣው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ጥቅሙ እንደ ምን የበዛ እንደ ኾነ ማወቅ የምትሻ ከኾነ መዝሙረ ዳዊትን ስትሰማና የአጋንንትን ዘፈን ስታደምጥ ምን እንደምትኾን፣ ቤተ ክርስቲያን ስትኾንና ቤተ ተውኔት ስትቀመጥ እንዴት እንደምታስብ ራስህን መርምር፡፡ ያን ጊዜ በነፍስህ ላይ የሚስተዋለው ልዩነት እንደ ምን ታላቅ እንደ ኾነ ትገነዘባለህ፡፡ ነፍስህ አንዲት ብትኾንም ቅሉ እዚያ ስትኾንና እዚህ ስትኾን በአኳኋንዋ እንዴት እንደምትለያይ ታስተውላለህ፡፡ ይኸውም የተወደደ ጳውሎስ፡- “ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” እንዳለው ማለት ነው (1ኛ ቆሮ.15፡33)፡፡ ስለዚህ ዘወትር ከመንፈስ ቅዱስ የኾኑ መዝሙራትን ልንሻ ይገባናል፡፡ ግዕዛን ከሌላቸው ፍጥረታት ያለን ብልጫ ይህ ነውና፡፡

ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሼር አድርጉት

የቴሌግራምና ዩቱብ ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq






አህያና ግርዛት

አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::

ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::

በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20

በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::

ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ"

"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"
(የአህያን ስም በአሳማ በአይጥ በውሻ ወዘተ እየቀየሩ ዐረፍተ ነገር ይሥሩ:: ሃሳቡ ያው ነው) ግዝረትም የማይበሉ ምግቦችም ከ613 የአይሁድ ሕግጋት (The 613 Mitzvot) ውስጥ ናቸው::

እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::

ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ቄራ (የበሬ)

"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" ኤፌሶን 4:29

የዩቱብ እና የቴሌግራም ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@1tewahdo

የቴሌግ
https://t.me/tsidq




ብዙ ሰው ብዙ ጊዜ ቃለ እግዚአብሔር ብማርም በተማርኩት ፍሬ ማፍራት አቅቶኛል ወደ ቤተ እግዚአብሔር መመላለስ እንጂ መመለስ አቅቶኛል መለወጥ ካልቻልኩ መማሩ ቢቀርብኝስ ሲሉ ይስተዋላል

ለእንዲህ አይነት ሰዎች አፈ በረከት ቅዱስ ዮሐንስም እንዲ በማለት ይመክራል
አንተ ሰው

"ቃለ እግዚአብሔርን ተማር! "
ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር፤
ኹልጊዜ ተማር ፤
ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር!
ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ ።
ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም ፡፡
ስለዚህ ተማር ! ስትማር ቢያንስ ኃጢአት እንኳን ስትሠራ ራስህን
እየወቀስክ ትሠራለህ ፡፡
ይህች የንስሐ በር ትኾንልሃለች ፡፡ አንድ ቀን ወደ ንስሐ ትመራሃለች ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉት
ዩቱብና ቴሌግራም ቻናሌም ቤተሰብ መሆን ለምትሹ

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@1tewahdo
ቴሌግራም
https://t.me/tsidq




"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

የዩቱብና እና የቴሌግራም ቻናሌ ቤተሰብ መሆን የምትሹ

ዩቱብ
https://www.youtube.com/@1tewahdo

ቴሌግራም
https://t.me/tsidq




ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይፀልያሉ አንደኛው ፀሎቱ ተመለሰለት አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ፀሎቱ ያልተመለሰለት ሰው "ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ፀልየን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ ከለከልኝ ለምንድ ነው?" አለው። እግዚዘብሔርም "ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ደግሞ ትጠፋለህ" አለው ይባላል።

እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሳቱም ሁለቱም በፍቅር ነውና በልመናችን በፀሎታችን የአንተ ፈቃድ ይሁንልን ማለት ተገቢ ነው። ስለሁሉም የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን። አሜን!!

ዩቱብ ቻናሌ ቤተሰብ መሆን ለምትሹ

https://www.youtube.com/@1tewahdo

https://t.me/tsidq

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.