🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ገና እንዘምራለን እንደ መላእክቱ
ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርሰቲያን አሰተምሮ ና ሰርአት የጠበቁ
✥👉መንፈሳዊ ትምህርቶች
✥👉መንፈሳዊ መዝሙሮች
✥👉መንፈሳዊ ንግሰ እናሳዉቃለን
✥👉መንፈሳዊ ምክር ነክ ፁሁፍ
✥👉መንፈሳዊ ታሪኮች

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
ሁሉም ክርስቲያን ፖስት ያድርገው አሁኑኑ 
እዚህ page ላይ የምትገቡ ሁሉ ይህንን ሳታዮ እንዳታልፉ!!

‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ በቲክቶክ ስሙ ሳላህ በትክክለኛው ስሙ ቶፊቅ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ቪዲዮ ላይ እንዳያችሁት ከሆነ በመጽሐፍ ነው ያለማስረጃ አናወራም የክርስትናን መጽሐፍ እኛ እናውቅላችዃለን በማለት መጽሐፍቶቻችንን እና አስተምህሮታችንን በመዘባበት  ፈጣሪያችንን በመሳደብ ለፈጣሪያችን የማይገባ ከአስተምህሮታችን ውጪ የሆነ አፀያፊ ቃልን በማድረግ ተማሪዎችን የሚያሰለጥኑ ኡስታዞች በፈለግ በመከተል እንግዲ በዚህ መልኩ ለኃልዎተ እግዚአብሔር በማይገባ በማይመጥን አማርኛ ቃል በመሰንጠቅ እና በማጣመም ሲሳለቅ ሲሳደብ የሚያሳይ አሳዛኝ ምስል ነው።

በጣም የማዝነው ከሚመለከታቸው አካላት ዝምታ ብቻ ሳይሆን ህዝቡ በፍቅር አክብሮ ወደ ዝና ማማ ያወጣቸው ግለሰቦች ናቸው።

የሚሰደበው ፈጣሪያችሁ አይደለምን ⁉️

ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ እድሜ ጤና ሰጥቶ የሰው ፍቅር እና መውደድን ጨምሮ ጨማምሮ በነገራችሁ ሁሉ ያልተለየ አምላካችሁ በአደባባይ መሳለቂ ሲሆን እያያችሁ እንዴትስ ልባችሁ እሺ አለ⁉️

እንዴትስ አእምሮቹ ፈቀደ⁉️

“ከጥፊው በላይ የወዳጄ ዝምታ ልቤን አደማው “ አለ ባለቅኔው።

😭😭😭😭😭😔😔😔😔😔
እፎይ እና ጰልድዮስ እውነት አላቸው

@Efoyewnetalew
@Efoyewnetalew

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በጣም አስደንጋጭ መረጃ አስቸኳይ መረጃ ‼️


ይድረስ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ይድረስ ለማህበረ ቅዱሳ ይድረስ ለሰንበት ትምህርት ቤት ማዳረጃ እና መምሪያ።

እስከመቼ ዝምታ ነገሩ ከእቅበት እምነት ሳይሆን በቤተክርስቲያናችን በሀገረ እና በዘር ላይ ያነጣጠረ ጭፍን ጥላቻ ሲሰበክ በአደባባይ እንዴት ዝም ይባላል?

አሁንም እንደዚህ አይነት ዘርን እና ሃይማኖትን ያነጣጠረ ጠብ እና አመጽ ቀስቃሽ አደገኛ የሆነ መልእክት እየተላለፈ አሁን ሁሉም የሚመለከት አካላት ይድረስልን ይህ በማሕበረሰባችን ያለውን ትስስር አደጋ ላይ የሚጥል ጸያፍ እና አስደንጋጭ የሆነ መልእክት ልትቃወሙት ይገባል። በሃይማኖት ሰበብ የጥላቻን እና የህዝብን ሉዐላዊነት አደጋ ላይ የሚጋርጥ መልእክት የምታዮት ሰዎች በሙሉ ይህ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በሀገራችነ‍እ ሉዓላዊነት ለዘመናት ተከባብረው ዜጎች የሚኖሩባት ሀገረን አደጋ ላይ የሚጥ አፀያፊ ጽንፈኛ አስተሳሰብነ‍እ ሁሉም የሃይማኖት አባቶች ሁሉም የእምነት ተቋማት እና የህግና የመንግስት አካላት ልታወግዙ እና ልታስቆሙ ይገባል ።

ስለዚህ ይህንን መልእክት የምታዩት ቢያንስ ለ20 ሰው ሼር በማረግ ለመንግስት እና የህግ አካላት ተጨማሪም ሀይማኖቶች ጉባኤ እንድታደርሱልን ስንል እንጠይቃለን !!!

እፎይ እና ጰልድዮስ እውነት አላቸው።
ትክለኛ የቴሌግራም ቻናላቸው ነው ተቀላቀል አንተ ባለማህተብ ክርስቲያን የሆንክ
👇👇👇👇
@Efoyewnetalew
@Efoyewnetalew

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


ወንድማችን እፎይ የ63+ ሚሊዮን ኦርቶዶክሳዊያን አደራ ነው ይህ ይሰመርበት !!

ጌታ ኢየሱስ ይጠብቀው ጸልዩለት፣ ብዙኀናችን አብሮነታችንን እናሳየው !!


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


➖ይሁዳ ክርስቶስን አንድ ቀን ፫ ጊዜ ብቻ ካደው።➖

እኔ የዘመኑ ይሁዳ ግን ስንት ጊዜ ካድኩት ? ስንት ግዜ አሳልፌ ሰጠሁት ? ስንት ግዜ በንዋይ ቀየርኩት?

አላውቅህም ብዬ በሰው ፊት የምክድህ እኔ በደምምህ የዋጀኸኝ ብላቴና ነኝ።
ወደ ቤትህ መልሰኝ የደነደነህ ልቤን መልስልኝ፤ ይቅር በለኝ።

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


❓በዐብይ ጾም ፫ኛ ሳምንት ስያሜ ምን ይባላል❓
So‘rovnoma
  •   ደብረዘይት
  •   ምኩራብ
  •   ኒቆዲሞስ
  •   መፃጉ
1099 ta ovoz


☦️አቤት የዚያን ጊዜ☦️

አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ (፪)
ትንሹም ትልቁም (፫) መድረሻውን ሲያጣ


ከምስራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ (፪)
አየራት/መላእክት/ ሲላኩ (፫) መአትን ለማዝነብ፤
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሐዱ (፪)
የት ይሆን መድረሻው(፫) የት ይሆን መንገዱ
      አዝ= = = = =
ጻድቃን በቀኝ በኩል ኃጥአን በግራ (፪)
ሲነፋ መለከት (፫) ሲደለቅም ዕንዚራ
ምድር ቀውጢ ስትሆን አጽም ሲሰበሰብ (፪)
ሐፍረት ይይዘዋል (፫) ሰው ለፍርድ ሲቀርብ
     አዝ= = = = =
ጩኸት ሲበረታ የማይጠቅም ለቅሶ (፪)
እንደ ቍራ ጠቁሮ(፫) ጽልመትን ተላብሶ
ገነትን ሲያገኙ ጻድቃን በስራቸው (፪)
ኃጥአን ወደ ሲኦል(፫) ተፈረደባቸው።

            መዝሙር
   ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ


"አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳት በፊት ይቃጠላል"
             መዝ ፶፥፫


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


🗓የምጽዋት ብዛት

የምጽዋት ብዛት የሚመዘነው በሚሰ’ጠው ገንዘብ ቁጥር ሳይኾን ስጦታውን በሚሰጥ የልብ ስፋት ነው፡፡ አንዲት ድኻ ሴት ያላትን ጥቂት እንጀራ ምንም ከሌላት ከሌላ ሴት ጋር ተካፍላ የምትበላ ከኾነ፥ ወርቅን በሙዳዬ ምጽዋት ከሚጨምር ባለጸጋ ሰው እጅግ ትበልጣለች፡፡

ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ እውነት እንደ ኾነ ብዙ ክርስቲያኖች ቢያውቁም፥ ምስጋና የሚሰጡት ወርቅ ለሰጠው ነው፡፡

☦️☦️☦️☦️☦️☦️☦️
አንድ ባለጸጋ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ እጅግ ያመሰግኑታል፤ ካለው የሀብት ብዛት የተነሣ ያንን በመስጠቱ ምንም ባይጎድልበትም እንኳ፥ በሰዎች ዘንድ እጅግ ቸር እንደ ኾነ ተደርጎ ይንቆለጳጰሳል፡፡ ድኻው ጥቂት ገንዘብ ቢሰጥ ግን ሰዎች ስለ እርሱ ምንም ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምናልባት ያቺ የሰጣት ገንዘብ’ኮ በኋላ እርስዋን በማጣቱ ምክንያት ተርቦ እንዲያድር ልታደርገው የምትችል ትኾን ይኾናል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ የሚያመሰግነው አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም ሳይጎድልበት የሰጠውን ባለጸጋውን አመስግኖ ያለውን ኹሉ የሰጠውን ድኻ ሳያመሰግኑ ከሚቀሩ ከእነ ጭራሹ ምስጋና ባይኖር ይሻል ነበር፡፡

ስለዚህ እውነተኛ ምጽዋት የሚባለው የባለጸጋውም ይኹን የድኻው በአግባቡና በሥርዓቱ ልናውቀው ይገባናል፡፡ ማመስገን የሚገባንም ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የምስጋናችን ስጦታም ሰዎች ከልባቸው ከሚሰጡት ገንዘብ ብዛት አንጻር ሊኾን ይገባል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


በጌቴ ሰማኔ

በጌቴ ሴማኔ በአታክልቱ ቦታ 2×
ለኛ ሲል ጌታችን (በአለም ተንገላታ 2×

አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት 2×
እኛም ነበረብን(የዘላለም ሞት 2×

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ(2×
ይገርፉት ነበረ (ሁሉም በየተራ(2×

ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ(2×
እያየች በመስቀል( ልጇ ሲንገላታ( 2×

በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው(2×
እንዲ ሲል ፀለየ (አባት ሆይ ማራቸው(2×

በረቂቅ ስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ
በረቂቅ ጥበቡ ሁሉን የፈጠረ
በሰው እጅ ተገሎ( ሞተ ተቀበረ(2×

ፍቅሩን የገለፀው ተወልዶ በስጋ(2×
ኢየሱስ ጌታ ነው (አልፋና ኦሜጋ(2×

በመስቀል ተሰቅሎ እንዲያ እየቃተተ(2×
አለምን ለማዳን (የማይሞተው ሞተ(2×

ከሞት ሊታደገን በመጣልን ፈጥኖ(2×
መስቀል አሸከሙት( ውለታው ይህ ሆኖ(2×

መከራውን ሳስብ ሳስታውስ ቀኑን(2×
ይቆስላል ይደማል (ልቤ በሀዘኔ(2×

መች ለራሱ ነበር ይህ ሁሉ መከራ(2×
መስቀል ተሸክሞ( የወጣ ተራራ(2×

ሲያጎሩሱት ሚናከስ ሰው ክፉ ነውና
እውሩን ቢያበራ ጎባጣን ቢያቀና
ጌታዬን ሰቀሉት (አይሁድ ጨከኑና(2×

ምነው አያሳዝን የአይሁድ ክፋት (2×
የዝናቡን ጌታ( ውሀ ሲነፍጉት(2×

በተንኮል በሀጢአት ቀሩ እንደሰከሩ(2×
ሙታን ከመቃብር( ተነስተው ሲያስተምሩ(2×

እናታችን ሔዋን ወየው በይ አልቅሺ
የአንቺን ህመም ታሞ ከሞት ሊያድንሺ
የህያዋን ጌታ (ተሰቀለልሽ(2×

አዬ ጉድ አዬ ጉድ አለም የኋላሽ(2×
መዳኒት ክርስቶስ (በግፍ ሞተብሽ(2×

በመስቀል ተሰቅሎ ስጋውን ሲቆርስ
በችንካር ተወግቶ ደሙንም ሲያፈስ
ዋለች በመከራ ድንግል ስታለቅስ
                    እናት ስታለቅስ

ሰውነትሽ ራደ ሀዘን ከበበሽ
ስቃይ ከመከራውም ዳግም ፀናብሽ
ተሰቅሎ ስታይው (አንድ አምላክ ልጅሽ (2×

ቢፈስም እንባዬ ሆኖ መንታ መንታ
መች ዋጋ ይሆናል ለአንዲቱ ጠብታ
ላለቀሽው ለቅሶ (ድንግል የዛ ለታ(2×

ባለቅስሽው ለቅሶ በልጅሽ ህመም (2×
ከሀጢያት ነፃሁኝ ዳንኩኝ ከገሃነም(2×

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

13k 1 225 122

✝️ጾም የተቀደሰ የእግዚአብሔር መንገድ መጀመሪያ ነው እና የመልካም ምግባራት አጋር ነው። ጾም በመንፈሳዊ ጦርነቱ መጀመሪያ ላይ በጎነትን ይመራል እና ንፅህናን ይጠብቃል። ጾም የጸሎት አባት፣ የመረጋጋት ምንጭ፣ የዝምታ አስተማሪ፣ የአዕምሮ ብርሃን ነው። የአንደበት ጾም ከአፍ ጾም ይሻላል፣ የልብም ጾም ከሁለቱም ይበልጣል። ከኃጢአትና ከምኞቱ ጋር የሚደረግ ትግል ሁሉ መጀመሪያ በጾም መጀመር አለበት። ልክ እንደ ጋለሞታ ስለ ንጽህና እንደምትናገር ወይም ሰውነታቸውን ሲወድ መንፈሳዊ ጉዳዮችን ሲፈልግ ነው።


[ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ]
መልካም የጾም ሳምንት ይኹንላችሁ!

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


በአብይ ፆም የመጀመሪያው ሳምንት እስከ ስንት ሰዓት መጾም ይጠበቅብናል❓(ኢትዮጲያ አቆጣጠር)
So‘rovnoma
  •   ሀ. እስከ ፱ ሰአት
  •   ለ. እስከ ፲፪ ሰአት
  •   ሐ. እስከ ፲፩ ሰአት
  •   መ. እስከ ፩ ሰአት
1847 ta ovoz


✝️​​ተመከር ሰው ሆይ

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር(፪)


መላ ሰውነትህን አስገዛ ለእግዚአብሔር



ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)


እጅና እግርህ ታስሮ ሳትወርድ ወደ መቃብር

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)


ተሰብከዋል እና በዓለም ቅዱሳት መጻህፍት ለአንተ ለመመስከር

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር 
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር (፪)


የእግዚአብሔር ሕጉን በአንዱ ጆሮ ሰምተህ በአንዱ ማፍሰስ ይቅር

ተመከር ሰው ሆይ ተመከር
እባክህ ተመከር (፪)
የዛሬ አበባ የነገው አፈር(፪)


                 መዝሙር
                ቀሲስ አበበ


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

          


አትቁረጡ_ተስፋ 

አትቁረጡ ተስፋ የእግዚአብሔር ልጆቹ/2
ከናንተ አይለዩም የፍቅር አይኖቹ/2/
ምድርና መላዋ ናት እና የእግዚአብሔር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር

በጥልቁ እንኳን ቢሆን ከናንተ ጋራ ነው
ወገኖቼ አትስጉ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው
ጌታ አይረሳም እና የእጆቹን ስራ
ይኸው በልጆቹ አይተናል ሲስራ

አዝ✝️✝️✝️✝️

እንደ ጠላት ቢሆን እንደሱ ጉልበት
ማነበር የሚኖር ዛሬ በሂወት
የሚያኖር ጌታ ነው የሚገልም ጌታ
ብርቱ እሱ ብቻ ነው በሀይል የበረታ

አዝ✝️✝️✝️✝️

በምስጋና ትጉ ፅኑ በፀሎት
በስሙ ታመኑ ቁሙ በእምነት
ለናንተ የምትሆን እግዚአብሔር ቀን አለው
አትቁረጡ ተስፋ ሁሉም አላፊ ነው

አዝ✝️✝️✝️✝️

ብትሆኑም ከ ጉርጓድ እሱ የያቹዃል
በማዳኑ ጥላ ይጎበኛቹዃል
ገና ያበዛቹዃል ከዚህም በላይ
ሁሉ ይቻለዋል ነውና አዶናይ

    ሊቀ-መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


የዓብይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ምን ይባላል⁉️
So‘rovnoma
  •   ሀ. ቅድስት
  •   ለ. ዘወረደ
  •   ሐ. ደብረዘይት
  •   መ. ገብርኄር
1917 ta ovoz


🗓☦️​​ዘወረደ

የመጀመሪያ የዐቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ «ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3-13

እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”ገላ 4፥4 እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ ፡ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ።

ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው፡፡


ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው። እኛም በዚህ በዐብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀር እንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ።

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


🗓የዕለቱን ወንጌል እናንብብ!
የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የማቴዎስ ወንጌል ም 21 ቁ 1 - 6
መልካም ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት !


#የዕለቱ_ወንጌል

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


🗓ማኅበራዊ ሚድያን እንደ ቋሚ ዕውቀት መጠቀም ብዙ በሽታዎችን ወደ ውስጣችን ማስተጋባት ነው።
ለአእምሯችን እድገት ሊሆኑ የሚችሉ መጻሕፍትን በማንበብ ግን ከደዌው መላቀቅ ይቻላል።

ፍጡራዊ ሰው ሙሉ የሚሆነው  በትምህርት እና በንባብ ነው።
ከትምህርት እና ከንባብ የተገታ ሰው ግን የወሬ ጋን ነው የሚሆነው።
ማህበራዊ ሚድያ ሀሳብን ለመሸጥ መረጃን ለማየት ነው እንጂ ቋሚ የዕውቀት ቦታ አይደለም።
በረጂም አንቀጽ የተጻፉትን ለማየት ዓይኑን የሚያመው አፉን የሚያዛጋው ሰው በወሬ ሱስ የተሞላ ስለሆነ ነው።
ይሄ ደዌ  ደግሞ በደንብ ተንፍሶ መፈወስ የሚችለው በመጻሕፍት ምርመራ ነው።

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤 dan repost
🗓ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝️

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-

‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)
 
ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !
እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣

አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን።

እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤ በዚህ ሁሉ ተግባራችን  እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤ በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . .ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤ ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት


በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ  ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን፤
   “እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!
                አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ
     ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
                ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
                  አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


(EOTC Broadcasting Service Agency)

✨✨✨✨✨✨
✝️#ድምፀ_ተዋህዶ✝️
✨✨✨✨✨✨


✝️የእናታችን_የአማላጃችን_የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ከፅንሰት እስከ ትንሣኤዋ ያሉት እውነታዎች:- ✝️
-  ነሐሴ ፯ ተፀነሰች ።
-  ግንቦት ፩ ተወለደች ።
-  ታህሣስ ፫ ወደ ቤተመቅደስ ገባች።
-  መጋቢት ፳፱ ቀን አምላክን በድንግልና ፀነሰች ።
-  ታህሣስ ፳፱ ቀን አምላክን በድንግልና ወለደች ።
-  የካቲት ፲፮ ቀን ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከአምላካችን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምህረት ቃል ኪዳን ተቀበለች (ኪዳነ - ምህረት)
-  ጥር ፳፩ ቀን በክብር አረፈች ።
-  ነሐሴ ፲፬ ቀን በክብር ተቀበረች ።
-  ነሐሴ ፲፮ ቀን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ ተነስታ በክብር አረገች ።

ክብር ምስጋና ለቅድስት ድንግል ማርያም

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


🗓 #ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
      #ቀን:- ጥር ፳፩ ፳፻፲፯(21/5/17) ዓ.ም
በቅድስት ቤተክርስቲያናችን

እመቤታችን በዓለ ረፍት✅
ነቢዩ ኢዩኤል፣ አቡነበትረ ማርያም፣ ቅድስት ሔራኒ፣ ጻድቁ ቆጵርያኖስ


አክብረን እና አስበን እንውላለን:

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )


✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨


✝️የኔ መሃሪ ✝️

የኔ መሀሪ ሁሉን መርሻዬ
ሁሉን መርሻዬ
እንደ ህልም አልፏል ትናንትናዬ
ባንተ ጌታዬ...(2)

አዝ.....
      አዳፋው ልብሴ ከነፃ
      ከእዳ ከፈታኝ በነፃ
      የፅድቁ ባሪያው ሆኛለው
      ሳገለግለው ኖራለው።
                የእንባ ዘለላን ያቀፈው
                አይኔም እልልታ ተረፈው
                ደልዳዩ መዳፍ ደርሶሎኝ
                ተራራው ሜዳ ሆነልኝ።
አዝ.....
     አይኖቼን ከጉድ ጋርዶልኝ
     ክንዶቼን በእጁ ይዞልኝ
     ከእግሬ በታች ነው ወጀቡ
     አሁን ታይቶኛል ወደቡ።
                   ሰላም ይነፍሳል ዙሪያዬ
                   እረፍት ሆኖልኝ ጌታዬ
                   የባረከኝን ባርኬ
                   ተለወጠልኝ ታሪኬ።
አዝ.....
   ብርሃንህ ገፏል ድቅድቁን
   በልቤ ተክሏል ሰንደቁን
   ተቆጣጥሮኛል መውደዱ
   መንገዴ ሆኗል መንገዱ።
                    ያበቃው ነገር ቀጥሏል
                   ጭንቄ በሞቱ ተሰቅሏል
                    የእየሱስ ሆኜ ምን አጣሁ
                    ሁሉን በስሙ ተወጣሁ።
አዝ.....
       እንደኔ ማንን ታግሷል
       ይቅርታ ፍቅሩን አልብሷል
      ማይገባኝን አድርጎ
       ያሳለፈልኝ ሸሽጎ።
               መልካም ነው ለኔስ መልካም
               ፀጋው ያገዘኝ ስደክም
               ሞትኩኝ ስል ምህረት ደርቦ
               አቆመኝ በህይወት አስዉቦ።

✝️ለባለ ማህተቦች✝️ሼር ያድርጉ↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

15k 1 191 157
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.