⚘አትዘን لا تحۡـــــزن⚘


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


❆لَا تَحْزَنْ إِنَّ اللَّهَ مَعَنَا ۖ ❆
⇘አትዘን:-

☞ ♡ዶ/ር ዓኢድ አል_ቀርኒ♡
https://t.me/joinchat/AAAAAELvlw_o9x05C8m61A ❥•••

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




የእናንተ ኢድ ዛሬ ነው
የእኛም ኢድ እንደዛው....
ጁምዓ + ዒድ = ውብ ቀን 💚💛❤️
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen


#አትዘን #ፈገግ #በል!
➲ የምትከስረው ነገር የለም ምክንያቱም
➲ አላህ አለ
➲ሪዝቅህ ተጽፎ
➲ዑምርህ ተውስኖ ያበቃ ነው
«ሁል ጊዜ በዙሪያህ ያለውን ውበት እንዲቆይ
ቆንጆ ሁን» 😊😄
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen


«ዩኑስ ዐ.ሰ ወደ ባህሩ በወረደ ግዜ የአሳ ነባሪው ሆድ ከመስመጥ ለሱ የተሻለ ነበር »
➲ አንዳንዴ አላህ ወደ ጭንቀት ሲያስገባህ ላንተ በማዘን ነው ከሚያጠፉህ ነገራቶች ሊጠብቅህ
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen


በዚህች ጠፊ ምድር ላይ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ ያውቃሉ???

መንገዳችንን ወደ ሀያሉ አላህ ብቻ እናድርገው!

የተዋበ ጁምዓ ይሁንላችሁ❤
ተረባረከ ዒድ ይሁንላችሁ 💛
መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ💚
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen


#ማሻአላህ #ውቦቼ❤️
በርቱልን 👏😍


የዘካ ግዴታዎን በጊዜው ይወጡ


◉ ዘካ መስጠት ውድና ዕንቁ የሆነ መንፈሳዊ ከንዝና ተግባር ነዉ. ዘካን በአግባቡ መስጠት ማህበራዊ ቀውስን ለመቅረፍና ድህነትን ለማንኮታኮት ታላቅ መፍትሔ ይሆናል።

_ዘካ ማውጣት ከእስልምና ማዕዘናት ሦስተኛው ማዕዘን ሲሆን ይህም የዘካን አስፈላጊነትና ግዴታነት ለማሳየት በቂ ነው፡፡ ለዚህም የሚከተለውን የአላህን (ሱ.ወ) ቁርኣናዊ አንቀፅ መጥቀሱ ማስረጃ ይሆናል፡፡

وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَارْكَعُوا مَعَ الرَّاكِعِينَ

ሶላትንም ደንቡን ጠብቃችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም (ግዴታ ምጽዋትን) ስጡ፡፡ (ለጌታችሁ) ከአጎንባሾች ጋርም አጎንብሱ፡፡


ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ኢስላም የተመሠረተባቸውን ማዕዘናት ሲያስረዱ እንደሚከተለው ብለዋል፡

" بني الإسلام على خمس: شهادة أن لا إله إلا الله وأن محمدا رسول الله وإقام الصلاة وإيتاء الزكاة" وحج البيت وصوم رمضان " متفق عليها


"ኢስላም በአምስት መሰረቶች ላይ ተገንብቷል። ከአላህ በስተቀር በእውነት ሊገዙት የሚገባው እውነተኛው አምላክ እንደሌለ እና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር ሰላትን አዘውትረው መስገድ፤ ዘካትን መስጠት፤ የረመዷንን ወር መም፤ ሐጅ ማድረግ የአላህን ቤት መጎብኘት/ ናቸው።

አላህ (ሱብሃነሁ.ወተዓላ) ዘካን ግዴታ ካደረገባቸው ምክንያቶች መካከል ጥቆቶቹ፡

► ዘካ የሚወጣበትን ሀብት ለማጥራትና ለማፋፋት፣

► ድሆችንና ሚስኪኖችን ለመርዳትና ለማገዝ፣
➢ ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ፣

► ንጹሕና ሠላማዊ የሆነና የተረጋጋ ማህበረሰብን ለመፍጠርና ወዘተ በመሳሰሉት ምክንያቶችና አላማዎች ሃብትና ንብረት ባላቸው ሰዎች ላይ ዘካ መስጠት ግዴታ ተደርጓል።

አላህም (ሱ.ወ) ይህንኑ አስመልክቶ እንደሚከተለው ተናግሯል፡፡

خُذْ مِنْ أَمْوَالِهِمْ صَدَقَةً تُطَهِّرُهُمْ وَتُزَكِّيهِم بِهَا وَصَلِّ عَلَيْهِمْ ۖ إِنَّ صَلَاتَكَ سَكَنٌ لَّهُمْ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

ከገንዘቦቻቸው ስትኾን በእርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነችን ምጽዋት ያዝ፡፡ ለነሱም ጸልይላቸው፡፡ ጸሎትህ ለእነሱ እርጋታ ነውና አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡



وَفِي أَمْوَالِهِمْ حَقٌّ لِّلسَّائِلِ وَالْمَحْرُومِ

በገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና (ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አልለ፡፡


◉ አላህ (ሱ.ወ) ሁሉን አዋቂ ነውና በህብረተሰቡ ውስጥ ችግረኛና ደካማ የሆኑ ሰዎች መኖራቸውን ያውቃል። የሰው ልጆች ሁሉ ደግሞ እኩል በሆነ ሁኔታና መልኩ ሃብትና ንብረት አይኖራቸውም፡፡ ስለዚህም ይህንን ክፍተት ለመሙላት፣ የድሆችን ችግር ለመቅረፍ፣ በሰዎች መካከል ሰላምና ፍቅርን ለማረጋገጥ በሃብታሞች ላይ ዘካ /ምፅዋት/ መስጠት በኢስላም ግዴታ ሆኖ ተደንግጓል።


○ሃብታሞች መደብ ፈጥረውና ተለይተው እራሳቸውን ከሌላው - ገድበው፣ ሃብታቸውን ቆልለው ለድሆች ምንም ነገር ሳይረዱና ሳይሰጡ ቢኖሩ አብዛኞቹ የህብረተሰብ ክፍሎች ይጎዱ ነበር፡፡ ማህበራዊ ቀውስም ይፈጠር ነበር፡፡ ሃብታሞቹም ቢሆኑ ሰላማቸው ይደፈርስ ነበር፡፡ ይህ እንዳይሆን ኢስላም የዘካን ሥርዓት ዘረጋ፡፡


◉ኢስላም በዘረጋው ሥርዓት መሠረት ዓለም ብትመራበት ኖሮ ይህ _ ሁሉ ዛሬ የሚስተዋለው ሰብአዊና መንፈሳዊ ቀውስ ባልተፈጠረ ነበር፡፡


_ አላህ /ሱ.ወ/ ለርስዎ ሃብትን በጥበቡ ለግልዎታል፡፡ እርስዎም ትዕዛዙን ለመፈፀም ቃል ኪዳን ፈፅመዋል፡፡ በመሆኑም ከሃብትዎ | ያልሰጡ ከሆነ አሁኑኑ በመስጠት ግዴታዎን ይወጡ! ጥቅሙም ለእርስዎ ነውና። እንዲሁም እርስዎ ውስጣዊ ሰላምንና ደስታን ለማግኝ ት ይፈልጋሉ፡፡ ነገ አላህ /ሱ.ወ/ ዘንድ ቀርበውም መልካም መስተንግዶውን ይመኛሉ፡፡ ታዲያ ይህ ይሳካ ዘንድ የዘካን ግዴታዎን በታማኝነትና በደስታ መስጠት ይጠበቅብዎታል፤ ጥቅሙም ለእርስዎ ነውና። (አላህ /ሱ.ወ/ ይፍቅዎት)

@La_Tehzen_Atzen
@La_Tehzen_Atzen


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ፆመኛውን ሙስሊም በአስለቃሽ መበተን ኢ-ፍትሃዊ ነው!!!!
https://t.me/theamazingquran
https://t.me/La_Tehzen_Atzen


በመላ ሀገሪቱ ሰላማዊ ዜጎች በየስፍራ ሲገደሉና ሲፈናቀሉ ያልተንቀሳቀሰ መሳሪያና የጸጥታ አካል ቴምር ብቻ ይዞ ለኢፍጣር የወጣ ንፁኻን ላይ ለመተኮስ ሲፈጥን ስታይ የዜጎችን ህይወት ከመታደግ ያንተን መብት መንጠቅ እንዴት እንደሚበልጥበት አይተሃል።ህዝበ ሙስሊም ሆይ! እኩልነታችንን በተግባር ለማረጋጋጥ ብዙ ትግል እንደሚጠበቅብን ተረድተሃል። ለአሁኑ ሁላችንም በሰላም ወደየቤታችን እናቅና።


ስፍር ቁጥር የለሽ የሙዚቃ ኮንሰርት የተካሄደበት ቦታ ላይ በ 1 ዓመት ውስጥ 1 ሰዓት የማይፈጅ የኢፍጧር ፕሮግራም ማዘጋጀት ዘላቂ ሰላም እና አብሮነትን ይበልጥ ያጠናክር ይሆናል እንጂ በመካከላችን መቃቃርን አይፈጥርም‼


ሁለተኛ ዜግነቱን አምኖ የተቀበለ ከአብዮት አደባባዩ የፈጥር ዝግጅት መቅረት መብቱ ነው።

#አህመዲን ጀበል


ለዛሬ ተዘጋጅቶ የነበረው የአብዮት አደባባይ ኢፍጣር ዝግጅትን መንግስት በቦታው አታድርጉ ማለቱን አዘጋጆቹ ከላይ በተያያዘው ደብዳቤ ገልጸዋል። እኩልነትህን ያልተቀበለ አካል ተሰምቶ መብትህ ሲከለከል በመለማመጥና በመንበርከክ እኩልነትህ እንደማይረጋገጥ ተረድተህ ለክብርህ በጋራ ቁም! «ብርሃናችሁ ይህን ከመሰለ ጨለማችሁ ምን ሊመስል እንደሚችል ተረድተናል» ብለህ በኢፍጣሩ የመሳተፍ ሃሳብ ያልነበረክ ጭምር ለኢፍጣር በቤትህ ያዘጋጀከውን ፈጥር አልያም ቴምርም ቢሆን ይዘህም ቢሆን ከስፍራው ተገኝተህ አፍጥር። ነገሩን አቃለው ለሚመለከቱት ካሉ ጉዳዩ የፈጥር ሳይሆን በእኩል የመታየት ጉዳይ እንደሆነ አስረዳቸው። ዳሩን ባለማስከበራችን መሃሉ ዳር ሆኖ መሪ ተቋም አልባ ወደመሆን እያመራንና መጅሊስን እያጣን እንደሆነ አስታውሳቸው። ሁለተኛ ዜግነቱን አምኖ የተቀበለ ከአብዮት አደባባዩ የፈጥር ዝግጅት መቅረት መብቱ ነው።
Ahmedin jebel


ሰበር ዜና ‼️

በግንቦት 01/2013 “ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” በሚል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ከአዘጋጅ አካላት የተሰጠ መግለጫ::
_______________________________________

ሃላል ፕሮሞሽን ከነጃሺ በጎ አድራጎት ደርጅት ጋር በመተባበር ዛሬ ግንቦት 01/2013 “ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” በሚል ስያሜ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማዘጋጀት ህጋዊ ፍቃድ ከሚመለከተው አካል አግኝቶ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።

እስከ አሁኑ ሰአት ድረስ ይህንን መልካም አላማ ያዘለ የሰላምና የአንድነት ተምሳሌት የጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማከናወን ቀን ከለሊት እየለፋንና ወጤታማ ለማድረግ ጥረት እያደረግን እንገኛለን።

ሆኖም ከመንግስት አካላት ዘንድ የዝግጅት ቦታውን እንድንቀይር የተጠየቅን ሲሆን ይህም ፍፁም ተገቢ አለመሆኑን ለሚመለከታቸው አካላት በማስረዳት እስካሁኗ ሰአት ድረስ ሰንነጋገር ቆይተናል።

ነገር ግን መንግስት በአቋሙ በመፅናቱ እኛም እንደተለዋጭ የተሰጠው ቦታ ላይ ፕሮግራሙን ማከናወን የማንችል መሆኑን
እናሳውቃለን።

ስለዚህም ጥሪ ያደረግንለት ማህበረሰብ በግንቦት 01/2013 በመስቀል አደባባይ የተሽከርካሪ ጎዳና ላይ ልናደርግ ያሰብነውን ፕሮግራም ለመሰረዝ የተገደድን መሆናችንን እንገልፃለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመንግስት በኩል አሁንም የዚህን ፕሮግራም ፍፁም መልካም አላማና ሰላማዊነት ተረድተው ውሳኔያቸውን ማስተካከል እንዳለባቸው እናምናለን።

ስለዚህም እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ ይህንን ለውጥ ተስፋ በማድረግ ዝግጅታችንን የምንቀጥል ይሆናል።

ከምስጋና ጋር

ለሚመለከተው አካል ሼር በማድረግ እናድር!!

⇩Join us⇩
https://t.me/theamazingquran


የረመዳን 27ተኛ ለሊት
★★★★★★★★★★★
በለይለተል-ቀድር የሚሰራ ዒባዳ ከ83 ዓመት ዒባዳ የሚበልጥ ሲሆን ከነቢዩ ሰሀባዎች ውስጥ፥ ዑመር፣ ኢብኑ ዐባስ፣ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዊያ፣ ሁዘይፋና ሌሎችም ለይለተል-ቀድር የረመዳን 27ተኛ ለሊት ላይ ናት ይሉ ነበር!

ይህች ለሊትም ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ላይ ናትና እንበራታ!


#ረመዷን 26
✆ ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አያችሁን?
እናንተ ከደመናው አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?

ብንሻ ኖሮ መርጋጋ ባደረግነው ነበር፡፡ አታመሰግኑምን?
Surah 56:68-70
አትዘን ለማመስገን ያለን ከበቂ በላይ ነው
እስኪ አልሐምዱሊላህ እበል😞
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen


ማስታወሻ

የዛሬዋ ምሽት የለይለተል ጁምዓ እና የረመዳን 25ተኛ ለሊት ነው:: አንዳንድ ፉቅሃዎች የሁለቱ ቀናት መገጣጠም ለሊቱ የለይለቱል ቀድር ለሊት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል

ኢብኑ ረጀብ ላቲፍ አል ማሩፍ ውስጥ ከኢብኑ ሁባይራህ የሚከተለውን ዘገባ አስፍረዋል:-

* የጁምዓ ምሽት ከረመዳን የመጨረሻዎቹ የዊተር ቀናቶች ጋር የሚገጥም ከሆነ ከሌሎቹ የበለጠ ለሊቱ ለይለቱል ቀድር ሊሆን ይችላል" ይላሉ

* ኢብኑ ተይሚያህም እንዲህ ይላሉ:-

"የአርብ ምሽት በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ከአንድ የዊትር ሌሊቶች ጋር የሚገጥም ከሆነ ያኔ የበለጠ ለሊቱ የለይለቱል ቀድር ሊሆን ይችላል"

* የአለማቱ ጌታችን አላህ ሆይ የለይለቱል ቀድርን ደርሰን ከተቀበሉት እና ከተጠቀሙት መካከል አድርገን
ዶ / ር ሰይፍ አል ሱዋይዲ
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen


"ልክ እንደ አባቶቹ ታሪክ የሚሰራ ትውልድ እንጂ፤በግብረሰዶምና መሰል የወረዱ ባህሎች የሚዘፈቅ ትውልድን አናፈራም።"
ኤርዶጋን
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen


إِنَّ مَعَ اُلْعُسْرِ يُسْرًا ☆
ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ♡
( አል_ኢሻራሕ )♡አልህምዱሊላህ

አልሀምዱሊሏህ


ወዳጄ አሁን አንተ እያነበብክ ባለህበት ቅፅበት ብዙዎች ሞት አፋፍ ላይ ደርሰው መልካም ስራን ባስቀደምኩ፣ ረመዷንን ሳልዘናጋ በተጠቀምኩ ኖሮ በማለት ይመኛሉ።አሁን አንተ እዚህ ቁጭ ብለህ ይህን በምታነብበት ቅፅበት ብዙዎች ኦክስጅን(አየር) አጥተው ፊታቸው ጠቁሮ ሞት አፋፍ ላይ ደርሰዋል።አንድ ሰዓት ኦክስጅን(አየር) ለመሳብ ብቻ 40,000 ብር ተጠይቀው የሚከፍሉት አጥተው ገርገራ(የሞት ስካር) ላይ ናቸው።ወዳጄ ሆይ! አላህ 1 ሰዓት ስተነፍስ 40,000 ብር ያስከፍልሃልን!??? ቢያስከፍህ ኖሮስ ከፍለህ ትዘልቀው ነበርን? ወዳጄ ሆይ ሁሉንም ነገር እንደ ቀልድ መመልከትህን አቁም ተነስ ወቅቱ ረመዷን ነው።ትንሽ እንኳን ብትዘራ ብዙ የምታጭድበት!ሱና ሰላት ብሰግድ በፈርድ የሚቆጠርበት!በዚህወር በለይለተል ቀድር ቀን እስንፋሳችን የሆነው ቁርዓን ወደ ሰማአ ዱንያ የወረደበት ወር ነው።ወይስ ነፍሳችንን ጎሮሯችን ካልደረሰች አንነቃም?!
ረመዷንን መጠቀም ፍቃድህ ብቻ ሳይሆን ግዴታህም እንደሆነ ልብ በል።ረመዷንን አግኝቶ ሳይጠቀምበት ያለፈው አላህ ከእዝነቱ ያርቀው ጂብሪል(ዐ.ሰ) ይህን ሲል አሽረፈል ኸልቅ (ሰ.ዐ.ወ) አሚን አሉ።

ብልጥ ሁን ወዳጄ!!

#ቆይ አላህን በየትኛው ፀጋው ታስተባብለዋለህ?ንፁህ አየር ስለሰጠህ ወይስ ንፁህ ውሃ ስላጠጣህ ወይስ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ስለመገበህ?ወይስ ይህን ታላቅ ወር ስላደረሰህ? አረ በየትኛው እስኪ ንገረኝ?! አላህም ይህን ጥያቄ በሱረቱል ረህማን 31 ጊዜ ደጋግሞ አስፍሮልሃል።

فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

(ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?78፥13


ወይስ አንተ ጥርጣሬ ውስጥ ነህ?

فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ

ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?53፥55

#አማኝ ልብ ያለን እንደሆነ ይህን ረመዷን ሳንጠቀምበት አይለፈን።ከረመዷን አዲስ የህይወት ካርታ ይዘን መውጣት አለብን።አዲስ ማንነት ያስፈልገናል ረመዷን የመጣው ተቅዋን(የአላህን ፍራቻ) ልንማር ዘንድ ነውና ከረመዷን በኋላ ተቂይ(አላህን ፈሪ) ልብ ማግኘታችን ይከጀላል።ካለዚያ ምናልባት ከዝንጉዎቹ እንዳንገባ ያሰጋል።

በመጨረሻም ምመክርህ ለውጥ ትፈልጋለህ? ስለዚህ ተለወጣ ከለውጥ የሚያግድህ ነገር አለን? ኡማው ያለበት ሁኔታ አሳሰበህ? አማኞች ላይ የሚደርሰው ግፍ እንቅልፍ ነስቶሃላ።
ብሰራቱን ልንገርህ ነገሮችን ሁሉ በአላህ ፈቃድ መለወጥ ትችላለህ።
ከዚህ ሁሉ በፊት ግን አንተ እራስህ መለወጥ አለብህ።አላህም ጥበብ በተሞላው ንግግሩ እንዲህ ብሏል፦

....إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ....

....አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡....13፥11

#ሰዎች አላህን ከማምለክ እሱን ወደማመፅ ሲዞሩ እሱም ፀጋውን ያነሳባቸውና በቅጣት ይቀይረዋል።እኛም አላህን ከማመፅና ወንጀል ከመስራት ከተቆጠብን አላህ ደግሞ በላኡን አንስቶ በፀጋ ይመልስልናል።ውርደትን አንስቶ የበላይነትን ያጎናፅፈናል።ስለዚህ ጣቶቻችንን ወደሌሎች ከመቀሰራችን በፊት እራሳችን እንመልከት የገዛ እራሳችንን እንለወጥ

ቤተሰብ ይሁኑን

@theamazingquran
@theamazingquran


#ረመዷን 16 መዓል #ቁርአን 🌙
____________
ﺃَﻓَﻤَﻦ ﻛَﺎﻥَ ﻣُﺆْﻣِﻨًﺎ ﻛَﻤَﻦ ﻛَﺎﻥَ ﻓَﺎﺳِﻘًﺎ ۚ
❀ አማኝ የሆነ ሰው አመጸኛ እንደ ሆነ ሰው ነውን?

ﻻَّ ﻳَﺴْﺘَﻮُﻭﻥَ
አይስተካከሉም፡፡

💐== Surah ሰጅዳ 32:18 ==💐
Te→:¨·.·¨:
 `·. ⚘t.me/La_Tehzen_Atzen

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

28 189

obunachilar
Kanal statistikasi