9. ኢብኑ ዐብዲል በር አልማሊኪ (463 ሂ.)፡-
“አላህ የት ነው?” የሚለውን ሐዲሥ አውስተው እንዲህ ብለዋል፡-
فَعَلَى ذَلِكَ جَمَاعَةُ أَهْلِ السُّنَّةِ وَهُمْ أَهْلُ الْحَدِيثِ وَرُوَاتُهُ الْمُتَفَقِّهُونَ فِيهِ وَسَائِرُ نَقَلَتِهِ كُلُّهُمْ يَقُولُ مَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابِهِ ﵟٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰﵞ وَأَنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ فِي السَّمَاءِ وَعِلْمَهُ فِي كُلِّ مَكَانٍ
“የአህለ ሱና ጀማዐ በዚህ ላይ ነው ያሉት። እነሱም የሐዲሥ ባለቤቶች፣ ዘጋቢዎቹ፣ በሱ ላይ አዋቂዎቹና ሌሎችም አቀባባዮቹ በሙሉ የላቀው አላህ በመፅሐፉ {አረሕማን ከዐርሽ በላይ ከፍ አለ} ያለውን ያስተጋባሉ። አሸናፊውና የላቀው አላህ በሰማይ እንደሆነና እውቀቱ በሁሉም ቦታ እንደሆነም እንዲሁ።” [አልኢስቲዝካር፡ 7/337]
وفيه دليلٌ على أنَّ اللهَ عزَّ وجلَّ في السَّماءِ على العَرْشِ، مِنْ فَوْقِ سَبْعِ سَمَاوَاتٍ، كما قالتِ الجماعةُ، وهوَ منْ حجَّتهم على المعتزلةِ، والجهميَّةِ، في قولهم: إنَّ الله عزَّ وجلَّ في كلِّ مكانٍ، وليسَ على العرشِ
“በዚህ ውስጥ አህሉ ሱና ወልጀማዐ እንዳሉት አላህ - ዐዘ ወጀል - ከሰባት ሰማያት በላይ ዐርሹ ላይ እንደሆነ ማስረጃ አለ። ይሄ አላህ - ዐዘ ወጀል - ‘ሁሉም ቦታ ነው፤ እንጂ ዐርሽ ላይ አይደለም’ በሚሉት ሙዕተዚላና ጀህሚያ ላይ ከሚጠቅሱ ማስረጃ ነው።” [አተምሂድ፡ 7/129]
10. ኢስማዒል ብኑ ሙሐመድ አተይሚይ (532 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
أهل السّنة يَعْتَقِدُونَ أَن الله ... عَلَى الْعَرْش كَمَا قَالَ تَعَالَى: {ٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ} وَأَنه ينزل كل لَيْلَة إِلَى السَّمَاء الدُّنْيَا كَمَا جَاءَ فِي الحَدِيث
“የሱና ሰዎች የላቀው አላህ {አረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ} እንዳለው በዐርሹ ላይ እንደሆነ በየሌሊቱም ወደ ቅርቢቷ ሰማይ እንደሚወርድ ያምናሉ። [አልሑጃ፣ ተይሚይ፡ 2/432]
11. የሕያ ብኑ አቢል ኸይር አልዐምራኒይ (558 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
عندَ أصحابِ الحديثِ والسُّنةِ أنَّ الله سبحانهُ بذاتهِ، بائنٌ عَنْ خَلْقِهِ، على العرشِ استوى فوقَ السَّمواتِ
“የሐዲሥና የሱና ተከታዮች ዘንድ የሚታመነው አላህ ጥራት ይገባውና በዛቱ ከፍጡራን ተነጥሎ ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነ ነው።” [አልኢንቲሷር፣ ዐምራኒይ፡ 2/607]
12. ኢብኑ ሩሽድ አልማሊኪይ (595 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
القولُ بالجهةِ: وأمَّا هذهِ الصِّفَةُ فلمْ يزل أهلُ الشَّريعةِ منْ أولِ الأمرِ يثبتونها لله سبحانه وتعالى، حتَّى نَفَتْها المعتزلةُ ثمَّ تبعهم على نفيِّها متأخرو الأشعريةِ، ... وظواهرُ الشَّرعِ كلُّها تقتضي إثباتَ الجهةِ
“በ(ላይ) አቅጣጫ ማመን፡ ይህቺ መገለጫ ከመጀመሪያው ዘመን ጀምሮ የሸሪዐ ባለቤቶች ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ከማፅደቅ ወደ ኋላ ብለው አያውቁም። ሙዕተዚላዎች እስከሚያስተባብሏትና የኋለኛው ዘመን አሽዐሪዮች በማስተባበል ላይ እስከሚከተሏቸው ድረስ ማለት ነው። … የሸሪዐ ግልፅ ማስረጃዎች እንዳለ የ(ላይ) አቅጣጫን ማፅደቅን ያመላክታሉ።” [መናሂጁል አዲላህ ፊ ዐቃኢዲል ሚላህ፣ ኢብኑ ሩሽድ፡ 176]
አላህ ከዐርሽ በላይ ነው ለሚለው አንዳች ማስረጃ ባይኖር እንኳን “... ከላይም፣ ከአለም ውጭም፣ ከአለም ተነጥሎም አይደለም” ብሎ ለማመን ወይ የቁርኣን ወይ የሐዲሥ ወይ ደግሞ የኢጅማዕ ማስረጃ ማቅረብ ግድ ነበር። ይህም ይቅር። ቢያንስ ከሶሐቦች፣ ከታቢዒዮችና ከአትባዑ ታቢዒን ይህን የሚያስረዳ ሀሳብ ማቅረብ ነበረባቸው። ይህንን የሚያሳይ ደግሞ ቅንጣት የላቸውም። ይልቁንም የቁርኣንም፣ የሐዲሥም፣ የኢጅማዕም ማስረጃዎች ያሉት ከነሱ ተቃራኒ ነው። እኛ እንደምናቀርበው ተፃራሪ ማስረጃ ቢያቀርቡ ሁለቱም ተፈትሾ፣ ተመዝኖ ሚዛን የሚደፋው ይታይ ይባል ነበር። እነሱ ግን ባዶ ኪሳቸውን እያፏጩ መጥተው የኡማውን ኢጅማዕ እንደ ዋዛ ሊንዱ ነው የሚገላገሉት። የጌታ ቃል፣ የመልእክተኛው ንግግር፣ የቀደምቶች ኢጅማዕ በአንድ ቃለ ያስተጋቡትን ሐቅ በ‘ተእዊል’ም ይሁን በሌላ ማመሀኛ ለማስተባበል መሞከር ድርቅና እንጂ ምን ሊባል ይችላል?!
እንግዲህ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ቁርኣኑም፣ ሐዲሡም፣ ኢጅማዑም አረጋገጠ። ከዚህ በኋላ ግራ ቀኝ ማማተር ከሙስሊም ይጠበቃል ወይ?! ዐብዱላህ ብኑ ዐዲይ አሷቡኒይ “ወይ ቁርኣን፣ ሱናና ኢጅማዕ ነው። ካልሆነ ግን (እንደ መነኩሴዎች) ዝናር መታጠቅ፣ ቢጫ መልበስና ጂዝያ መክፈል ነው የሚቀረው” ይላሉ። [ዘሙል ከላም፡ 1/27] አደገኛ ምርጫ! በነዚህ አካላት የተሸወድክ ወገኔ ሆይ! ግዴለህም ንቃ። መንቃትህ የሚጠቅመው አንተን ነው። አላህ ልብህን ለሐቅ ክፍት ያድርግልህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor