ሐሽማል ቤተ-መዘክር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Books


👉Only for readers
👋መግቢያ👋
መግቢያ ለመግባቢያ
ገታ አርገነዋል የቃላትን ግልቢያ
እናም በዚህ ሀሳብ ከተስማማህበት
ያንኳኳኸዉን በር የገለፅከዉን ገፅ ፈቅደናል ግባበት
ምንጭ - ካልታወቀ ገጣሚ
Join the group
@amharicbooksforeadersgroup
አድሚኑን በ ቀጥታ ለማናገር ይህንን ቦት ተጠቀሙ @Digitallibraryofhashmal_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Books
Statistics
Posts filter


Stay Ahead in Ethiopian Business News

"Get real-time updates on Ethiopia’s economy, currency, and business trends! Dive into exclusive insights and stay informed on key issues impacting Ethiopia. Follow Addis Fortune for daily updates!"

👉 https://t.me/addisfortune


Forward from: Addis Fortune
Malaria, a persistent threat in rural areas, is resurging with alarming intensity in 2024, exposing deep-rooted systemic issues aggravated by climate change and inadequate health infrastructure. In the past three months alone, the Ministry of Health has reported nearly 2.9 million cases, a staggering 200pc increase compared to the same period in previous years.






















ለንባብ የበቁ አዳዲስ መጻሕፍት !






✅"በተቀመጥኩበት ደና አልነበርኩም ወይ ?"

በተቀመጥኩበት ወትወትህ ወትውትህ ፣ ከለመድኩህ በኃላ ፣ እቅዴ ውስጥ ከከተትኩ በኋላ ፣የኔ ነው ብዬ ካወጅኩ በኃላ ...

ድሮ ባገኘሁት ኖሮ ቁጭት ከወዘወዘኝ በኃላ ፣ ደስታ እሚያደርገኝን ካሳጣኝ በኃላ ፣ ጓደኛቼው ስለራሳቸው ሲያወሩኝ እኔም ብዬ ስላንተ ማውራት ከጀመርኩ በኃላ ....

ለናፍቆቴ ፊት ከሰጠሁት በኃላ ፣ መውደዴን ያለስስት ከወረወርኩ በኃላ ፣ ጓደኛዬም ካደረኩህ በኃላ ...

"የማያቁት አገር አይናፍቅም "

⭐መወደድን ከአየሁ በኃላ ፣ ናፍቆቴን ካስተናገድኩት በኃላ ፣ አለሁልሽ ካልከኝ በኃላ ፣ መኖርክን ከለመድኩ በኃላ ፣ ካመንኩህ በኃላ ...

ስትሄድ .....

እምነቴ ተናደ ፣ ናፍቆቴ ድብርት ወለደ ፣ ግርግሩ በአን'ዴ ጭር አለ ..!

ናፍቆት እና ማጣት አፈረሱኝ ...

ስጋቴን ቀስ ብለህ ሸርሽረህ ሸርሽረህ ከናድከው በኃላ.... !!

" ለአፍታ አላይክም ወይ አንዴ እንደገና ?"
✍ እንማር


እንኳን ደህና ቀሩ
[Red-8]

ዘጠና ዘጠኙን፡ አልጋዬ ስር ትቼ
አንዳንድ የምናፍቅ፡ ከጠፉት ሉኮቼ
ሥጭር ላቆሰሉኝ፡ ሙቼ ለፃፍኳቸው
አንድ ቀን አግኝቼ፡ ዳግም ላነባቸው፡
ወደ ወደቁበት ፡ ሀገርና ቅዬ
ያተጫነብኝን፡ ብዕሬን ፈንቅዬ፡
መጣለሁ ያልኩኝ፡ ከሞት ተነስቼ
እኔም ክርስቶስ ነኝ፡ ለጠፉት ግጥሞቼ።

ቢሆንም ቢሆንም፡

አዳማ ፍራንኮ፡ ከእርጎ ቤቱ በቀኝ
ይመጣል እያለች፡ የምትጠብቀኝ
ያቺ ወረቀት ግን ፡ ግጥም የፃፍኩባት
እንኳን ጠፍታኝ ቀረች፡ እንኳን ቀረሁባት።

ያቺ ኮብላይ ግጥሜ፡
መነሀሪያ አጠገብ፡ ቅጥቅጡ እስኪሞላ
ፍቅሩን በመጠበቅ፡ ለፈረሰ ገላ
ለማይረካ ናፍቆት፡ ለማይቆረጥ ጥም
ሻንጣዬን አዝዬ፡ በውሃ ጥም ዝዬ፡ የደረስኳት ግጥም
ሲበቃኝ ከኪሴ፡ አጥፌ ያኖርኳት
እንኳን የወደቀች፡ እንኳንም የጣልኳት።

አንዴ በፃፈው ልክ፡ እየተሰፈረ፡
ላንዴ ባፈለቀው፡ ጥቅስ እየታሰረ
ስንቱ ፈጣሪ ነው፡ ባለበት የቀረ?
ፍጡር ተነቦ ነው ፡ አምላኩ ሚከበር ፡
ፍጡር ተነቦ ነው፡ አምላኩ ሚቀበር
እንኳንም ወደቀች...
ብትኖር እሷን ብዬ፡ እዚያው እቀር ነበር።

አፈር ልሆን ሄድኩኝ፡ እሷን ከአፈር ጥዬ
በዝናብ ርሳ፡ በጣይ ተቃጥዬ
ያስተዋወቀንን፡ መልካችንን ትተን
ተላልፈን ይሆናል፡ ይሄኔ ተያይተን።

በተፃፃፍንበት፡ በነበር መች ቆየን?
በየደረስንበት፡ እንዳዲስ ተቃኘን
እሷ በሷ ሆዬ፡ እኔ በትዝታ
ከንግዲህ በኋላ፡ ባገኛትም እንኳ ፡ ከጣልኩበት ቦታ
አትሆነኝም ሎሌ ፡ አልሆናትም ጌታ።

እሷም ብቻ አይደለች፡ ያኮራችኝ ጠፍታ...

ከሶስት ቁጥር ቶታል ፡ በታቦት ማደሪያ
ለፀሀይ ዩኒፎርም ፡ ጋርደን ሰደርያ
ሲመሽ ከገብርኤል፡ እስከ አቦ ማዞሪያ
መንገዳችን እንጂ፡ ወሬያችን ሳይበቃን
መካኒሳን አልፈን ፡ ሳርቤት በቫቲካን
ለሚያረማምዱኝ፡ ለወክ አጣጮቼ
የታጠፈች ግጥሜን፡ ከኬሴ አውጥቼ
ቆም ሄድ እያልን፡ የመንገድ ባውዛው፡ በየደመቀበት
ያነበብኩላቸው ፡ የላመች ወረቀት...
ያቺ የዋህ ግጥም፡ «አንድም ሰው እንዳይሞት!» የሚል መዝጊያ ያላት
እንኳን የትም ጠፋች፡ እንኳን የትም ጣልኳት!

« አንድም ሰው እንዳይሞት? »
አረ ባክሽ?... እውነት?
የልጅነት ግጥሜ፡ ስሚኝ ተረት ተረት...

ዮኒፎርም አውልቀው፡ ከአብሮ አደግ ርቀው
በዓለም ስቃይ ልክ፡ ልብን አተልቀው
ከምኞት ደመና፡ በግፍ ወንጭፍ ወርደው
በወክ ካካለሉት ፡ካደጉበት ሰፈር፡ ተነቅለው ተሰደው
ተቃጥለው ከፃፉት ፡ በሀቅ በፍትሕ ጥም
«አንድም ሰው እንዳይተርፍ!» ይማፀናል ግጥም።

እንኳን ጠፋታ ቀረች፡ ግጥሜ እንደልጅነት
ዓለሙን ሳታውቀው ፡ የተፃፈች ጀነት
በምኞት ቡርሿ፡ ሲዖል ለማቆንጀት
ስትጣጣር ያኔ፡ እንኳን ነቃሁባት፡
እንኳን የትም ጣልኳት፡ ይቺ ተረት ተረት...
የወተት ግጥሞቼ፡ እየተነቀሉ፡ ሲበቅል የስጋው
ለነከሰኝ ሁሉ፡ ሰው ብዬ ስጠጋው
እንኳንስ ልታገል፡ ስለት እንዳይወጋው...
ሞት አንሷል ብዬ ነው፡ አሁን የምሰጋው።

ምን ያቺ ብቻ...?

እየደረሳቸው፡ የመሰወር እጣ
ከሀይስኩል መድረክ፡ ፑሽኪን እስክመጣ
ከአዳማ ክበብ፡ ከግቢ እስክወጣ
ከጦቢያ በጃዝ ፡ከፒክኒክ በረንዳ
ጆሮ እየጠመድኩኝ፡ በስንኝ ልነዳ
ከኪሴ እየሳብኩኝ፡ መመለስ ዘንግቼ
የትም የጣልኳቸው ፡ ባይተዋር ግጥሞቼ

ያጡትን ለማግኘት፡ ጠፍቶ ከመመኘት
ተነፋፍቆ ኖሮ፡ ተጣባብቆ መቅረት
ከሚባል መንትያ ፡ቀንበር ነፃ ይውጡ
ከእንግዲህ ግጥሞቼ ፡ ወደኔ እንዳይመጡ...

'ጠፍተን ያልተገኘን፡ ልጆችም ነን' ቢሉ
እንድውጣጣባቸው፡ ለተደለደሉ
ሆኜ ለተውኳቸው፡ ሆኜ ላለፍኳቸው፡ አልቀው ለተጣሉ
ላለፉት እኔዎች፡ መቃብሮች ናቸው፡ የፃፍኳቸው ሁሉ።


😍ፍቅር- ፈራን:ጠላን😍

"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን

ሌሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

✍✍✍


እፈራለሁ
[ ]

ቆይ፥
መንፈስ ብትሆኚስ?
ለእኔ ብቻ የሚታይ ፥ ከህልም የተሰራ፥
'ዴልዩዥን' ብትሆኚስ?
የምኞት መዶሻ ፥ ጠራርቦ ያቆመሽ ፥ የልቤ ፈጠራ፤

ከጨዋታ መሐል ፥ ድንገት ብትጠፊብኝ፤
'የታለች?' ስላቸው፥
'ማን ናት ደሞ?' ብለው ፥ ሰዎች ቢስቁብኝ፤

ህልም ብትሆኚስ?
ስነቃ ብትቀሪስ?
ቆይ አሁን፥
ጭራሹን ባትኖሪስ?

ሞልተሽኝ በእቅፌ፥
እጆቼን ቀንፌ፥
ደስታዬ እንደድመት ፥ ልቤን እየላሰው፥
ሳቅ ሆዴን ሲያምሰው፥
ባዶዬን ቢሆንስ፥
ብቻዬን እንደእብድ ፥ የምታየው ለሰው?
እንደንፋስ ነክቶኝ ፥ ሲያልፍ ሰቀቀኔ፥
ከተዳከምሁበት ፥ ከውብ ሰመመኔ፥
'ቢሆንስ?' እያልሁኝ፥
ድንገት እየባነንሁ ፥ እፈራለሁ እኔ፥

መቼም፥
ነፍሱን መርጦ አጥቦ ፥ ውድ አካል ቢያለብሰው፥
ምን ያህል ቢወደድ ፥ ፍቅር ቢያንተርሰው፥
እንዲህ ሁሉ አምሮለት
በስጋና በደም ፥ አይገለጥም ሰው።

©ሚካኤል ሚናስ

@wegochi



20 last posts shown.